Teklemichael Ab Sahlemariam

Teklemichael Ab Sahlemariam Toronto-based Ethiopian Canadian Lawyer

በዚህ ሳምንት 49 ዓመት ሞላኝ። በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ 50 እገባለሁ። መጽሀፈ መክብብን ባነበብኩ ቁጥር እንደ ሰሎሞን ልቤ ይጠይቃል፤ “ዘመኖቻችንን እንዴት እንደምንቆጥር አስተምረን፤ ጥበበ...
07/21/2026

በዚህ ሳምንት 49 ዓመት ሞላኝ። በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ 50 እገባለሁ። መጽሀፈ መክብብን ባነበብኩ ቁጥር እንደ ሰሎሞን ልቤ ይጠይቃል፤ “ዘመኖቻችንን እንዴት እንደምንቆጥር አስተምረን፤ ጥበበኛ ልብ እንድናገኝ” ይላል።

ዛሬ: ከ25 ዓመት በፊት በናይሮቢና በካኩማ ስደተኞች መጠለያ: ኬንያ ነበርኩ። ወጣት: የነብር ጣት: ያኔ 25 ዓመት ለእኛ ዘላለም ይመስለን ነበር። እግራችን አይደክምም፣ ሕልማችን አያልቅም፣ ነገም በጣም ሩቅ ይመስለን ነበር። ግን ዘመን እንደ ወንዝ አለፈ። በየቀኑ ፍጥነቱን አላሳየም፤ 25 ዓመታት ግን በአንድ ትንፋሽ አለፉ። ዛሬ ወደ ኋላ ስመለስ፣ ያለፈው ሕይወት እንደ ሕልም ይታየኛል፤ የደስታው፣ የሐዘኑ፣ የድሉ፣ የሽንፈቱ፣ የጓድኝነቱና የመለያየቱ ድምፅ እንደ ሩቅ አያስተጋባ ይሰማኛል። አሁን አንድ ጥያቄ ብቻ ከልቤ አይወጣም። ቀጣዩን 25 ዓመት እንዴት ልኑረው?

መጽሐፍ እንደሚለው፣ የሰው ልጅ ዘመን ሰባ፣ ቢበዛ ሰማኒያ ዓመት ነው። ከዚያ በላይ ጸጋ ነው። ግን ድካምም ነው። ይህን ሳስብ፣ ድንገት ብኖር: የሚቀጥለው ሩብ ምዕተ ዓመት አጭርም ይመስለኛል፣ ከባድም ይሆንብኛል። አሁን ባለው መልኩ ኖሬ ጡረታ ልውጣ? ልነግድ? ልጻፍ? ልጓዝ? ቤት ልስራ? ልፖትልክ? ወይስ በየቀኑ ፈጣሪ የሚሰጠኝን ጊዜ በእንዴት አይነት መልኩ ልኑርበት? ዛሬ የሚያስጨንቀኝ: ጊዜ ነው። አጭርም ረጅም የሚመስል ጊዜ ነው: ቀጣዩ 25 አመት።

ገንዘብ ቢጠፋ ሊመለስ ይችላል፤ ጤናም ቢዳከም ሊሻሻል ይችላል። ያለፈ ጊዜ ግን ፈጽሞ አይመለስም። የሚመጣውስ ጊዜ እንዴት ይሰላል: ይሳላል: ይመተራል: ይኖራል?

ዕድሜ ሲገፋ ሰው አዲስ ነገር ከመጨመር ይልቅ አላስፈላጊውን መቀነስ ይማራል። ጓደኞቹ ይመረጣሉ፤ ሕልሞቹ ይጠራሉ፤ ፍላጎቶቹ ይጠበባሉ። በመጨረሻም ሁለት ጥያቄዎች ብቻ ይቀራሉ: “እኔ ማን ሆኜ ነበር?” "ቀጣዮቹን አመታትስ ማን ልሁን?"

ከሁሉ በላይ የሚያስፈራኝ ሞት አይደለም። ኑሮ እንጂ። ቀጣዩን 25 አመት እንዴት ልኑረው?

ሰዎች የሚሞቱት በመቃብር ብቻ አይደለም፤ ሕልማቸውን ሲተዉ፣ ተስፋቸውን ሲያጡ፣ እውነታቸውን ሲሸሹም ይሞታሉ። ፈጣሪ ቢፈቅድ ከ25 ዓመት በኋላ ይህንን ጽሑፍ እንደገና አነበዋለሁ። ልክ የዛሬ 25 አመት ኬንያ ሆኜ: ይሄን ዘመን እንዳላሰብኩት: በዚያ ቀን የዛሬን እኔን እንዴት አየዋለሁ?

“ምነው ጊዜን በተሻለ መንገድ ተጠቅሜበት በነበር!” ወይስ…“ፈጣሪ የሰጠኝን ዘመን በተገቢው ኖሬዋለሁ።” ስለዚህ: የቀረኝን ዘመን ትርጉም የሚሰጠው ምንድን ነው? ትሬጉሜ ብትንትን አለ። እንዴት ልተልመው? እንዴትስ ልሳለው? ምክንያቱም መጪው 25: ልክ እንዳለፈው 25 ዓመት በድንገት ያልፋል። እንደ ትላንት ይሆናል። ከዚያም ዛሬን ወደ ኋላ እያየን እንነጋገራለን።

ስለዚህ … እስኪ፣ ከልብ ምከሩኝ። ማለትም: ሀሳብ ስጡኝ: መጪውን 25 አመት እንዴት ልኑረው? "አግባ: ውለድ: ባታገባም ውለድ" አትበሉኝ። እስኪ 25 አመቱን ተመኙልኝ። ተቀኙልኝ። ተንብዩልኝ። ተርጉሙልኝ። ምክንያቱም ሰው ሕይወቱን በዓመታት አይለካውም። በትርጉሙ ነው የሚለካው። እስኪ መጪውን 25 አመታት የምኖርበት ሀሳብ አዋጡ። ተርጉሙልኝ። መልካም ልደት ለኔ። wow 49 አመት።

Obbo Dereje Dadi የዛሬ 24 አመት: Nairobi ያነሳው photo ነው።

Selam ጎበዝ። ከ Elias Aweke ጋር የምናደርገውን የመጻሕፍት ዳሰሳ: እንደወደዳችሁት (አንዳንዶችም እንዳልተመቻችሁ) በመስማታችን ተደስተናል። እንግዲያውስ: እስኪ ይሄንን መድረክ su...
06/10/2026

Selam ጎበዝ። ከ Elias Aweke ጋር የምናደርገውን የመጻሕፍት ዳሰሳ: እንደወደዳችሁት (አንዳንዶችም እንዳልተመቻችሁ) በመስማታችን ተደስተናል። እንግዲያውስ: እስኪ ይሄንን መድረክ subscribe አድርጉልን።

አናካብድ Take it easy

🚨✨ DON’T MISS: U: BY DESIGN WORKSHOP ✨🚨Parents & guardians — this is a FREE, high-impact opportunity for high school you...
05/27/2026

🚨✨ DON’T MISS: U: BY DESIGN WORKSHOP ✨🚨

Parents & guardians — this is a FREE, high-impact opportunity for high school youth (ages 14–17) to design their future with confidence.

P2P in partnership with Decanthropy invites your youth to a hands-on design thinking experience.

📍 DETAILS

🗓 May 30 | 10:30 AM – 2:30 PM
📍 180 Main St, Toronto
💰 FREE | 👥 Only 35 spots

💡 WHAT THEY’LL GET

* Build & prototype real ideas
* Learn design thinking from industry pros
* Meet mentors from Interior Designers of Canada
* Lunch, snacks & prizes included 🎁

⚡ WHY IT MATTERS

A fun, interactive space where youth build leadership, creativity, and a clear vision for their future.

📌 Register now — spots are limited:
Sign Up👉🏽https://forms.cloud.microsoft/pages/responsepage.aspx?id=LrIqTJ4RVEK-rE3UDTlM5zT4YRTBi79AkXqtYh1TzDNUQ0pRWEs2RzdDT0w2MUpKSFZJQ0VDRUZKNi4u&fbclid=IwdGRjcASESUlleHRuA2FlbQIxMQBzcnRjBmFwcF9pZAo2NjI4NTY4Mzc5AAEeqYTIOEIEz6xamTkEyNvyI6S5eOLPL6n7YnlYWBIxaGlr7fspH6StUpeYLSM_aem_s0u4DXhJN25rDZOeo8d3MA&route=shorturl

05/27/2026
Petros Dejene, good job.
05/27/2026

Petros Dejene, good job.

“ብሆን እስትንፋስሽ” is a song about silent love — the kind that lives ent...

Greetings to you all, ሰላም ሰላም:I would like to ask for your support by signing and sharing this petition to the Canadian ...
05/15/2026

Greetings to you all, ሰላም ሰላም:

I would like to ask for your support by signing and sharing this petition to the Canadian Parliament.

እባካችሁ ይህንን ለካናዳ Parliament የቀረበ ጥሪ/ማመልከቻ ይፈርሙልን። ሌሎችም እንዲፈርሙ በማድረግ ድምፃችን እንዲሰማ ያግዙን።

This petition calls for fair and equitable processing of the long-delayed resettlement and sponsorship applications of African refugees. Many African refugee families have been waiting for years, separated from loved ones and left in uncertainty, while applications from other regions are processed much faster.

የአፍሪካ ስደተኞች የካናዳ ማመልከቻዎች ከሌሎች አገሮችና አህጉራት ጋር ሲነጻጸሩ በጣም ይጓተታሉ። ይህ petition ይህ ፍትሃዊ ያልሆነ መጓተት እንዲያበቃ ይጠይቃል።

Please take a moment to sign and share:

Petition e-7435 https://www.ourcommons.ca/petitions/en/Petition/Details?Petition=e-7435

Address

526 Richmond Street East, 2nd Floor, Toronro
Toronto, ON
M5A1R3

Opening Hours

Monday 9am - 5pm
Tuesday 9am - 5pm
Wednesday 9am - 5pm
Thursday 9am - 5pm
Friday 9am - 5pm

Telephone

+16477225328

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Teklemichael Ab Sahlemariam posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Teklemichael Ab Sahlemariam:

Shortcuts

Featured

Share

Category