Wodiidi Sidaami Zoone Aliidi Yoo MIne/ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት/

Wodiidi Sidaami Zoone Aliidi Yoo MIne/ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት/ Everyone is equal before the law...!

Qoqqowu Amaale Mine shiqqine Xaphoomu Yoo Minira, Aliidi Yoo Minnaranna Umi Dirimi Yoo Minnara Yooaanchimmate Mootoo'mit...
02/27/2025

Qoqqowu Amaale Mine shiqqine Xaphoomu Yoo Minira, Aliidi Yoo Minnaranna Umi Dirimi Yoo Minnara Yooaanchimmate Mootoo'mitinoonni ayirradda Yooaano hawalle hagiidhitioonni.
Dancha loosu yanna ikkito'ne....!!!

ክስ ቀርቦብኝ ከዚህ ቀደም ጉዳዩ በእርቅ ስምምነት መዝገቡ ተዘግቶ ነበር የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በፍሬ ነገር ክርክር ላይ በእርቅ ስምምነት መዝገቡ ስለመዘጋ...
02/26/2025

ክስ ቀርቦብኝ ከዚህ ቀደም ጉዳዩ በእርቅ ስምምነት መዝገቡ ተዘግቶ ነበር የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በፍሬ ነገር ክርክር ላይ በእርቅ ስምምነት መዝገቡ ስለመዘጋቱ መከራከሪያ እስከተነሳ ድረስ ፍ/ቤቱ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ወስዶ በቅድሚያ እልባት ሊሰጠው የሚገባ እና ፍ/ቤቱ እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አስቀድሞ ሊመለከተው የሚገባ ስለመሆኑ የፌደራል ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 222041 ጥቅምት 15 ቀን 2015 የተሰጠ አስገዳጅ ትርጉም::

Wodiidi sidaamu zoone Aliidi yoo miniti cinaancho yooaanote gashshoo songo babbaxitino hajo aana hassaabbe gumulo sayiss...
01/24/2025

Wodiidi sidaamu zoone Aliidi yoo miniti cinaancho yooaanote gashshoo songo babbaxitino hajo aana hassaabbe gumulo sayissinoha ikkanna goofimarchohono Ayirrado yooaancho kalaa Yedili Beqqeleha cinaancho yooaanote gashshooti B/mini sooreessa assite motoonsiteenna barru hasaawa jeefinsoonni.

01/24/2025

በፍትሐብሔር ጉዳይ ሕግ ወደ ኋላ ሄዶ ይሰራልን ?

እንደሚታወቀው በወንጀል ጉዳይ አንድ የወንጀል ድርጊት በኢፌድሪ የወንጀል ህግ መሠረት ወንጀል ሆኖ በተሻረው የወንጀል ሕግ ግን እንደወንጀል ካልተቆጠረና የተፈፀመው ይህ ሕግ ከመፅናቱ በፊት ከሆነ ሊያስቀጣ እደማይችል በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 5(2) ላይ የወንጀል ህግ ወደኃላ ተመልሶ የማይሰራ መሆኑን ይደነግጋል፡፡የኢፌድሪ ህገ-መንግስትም በአንቀፅ 22(1) ላይ ማንኛውም ሰው የወንጀል ክስ ሲቀርብበት የተከሰሰበት ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈፀሙ ወይም አለመፈፀሙ ወንጀል መሆኑ በህግ የተደነገገ ካልሆነ በስተቀር ሊቀጣ አይችልም፡፡ሲል ይደነግጋል፡፡ይህ የወንጀል መርህ ለፍትሐብሔር ተፈፃሚነት ይኖረዋልን ?ይህን አከራካሪ ጭብጥ የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 229940 (ባልታተመ) ውሳኔው ላይ ህግ ወደኃላ ተመልሶ አይሰራም በሚል የሚታወቀው መርህ መሰረት ሀሳቡ አንድ ህግ በሥራ ላይ መዋል ያለበት ሕጉ ከፀና በኃላ በተፈጠረ መብትና ግዴታ ወይም ፍሬ ነገር ላይ ተፈፃሚ መሆን እንዳለበት እና ዜጎች በሚያውቁት ህግ መተዳደር አለባቸው የሚለውን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡እንዲሁም አንድ ህግ የሚፀናበትን ጊዜ አስመልክቶ በህግ አውጪው ከተደነገገበት ቀን በፊት ለተፈጠሩት ክስተቶች ወይም መብትና ግዴታዎች ተፈፃሚነት አይኖረውም የሚል ሀሳብ ያለው ነው፡፡የዚህ መርህ ተግባራዊነት የህግ የበላይነት ከሚረጋገጥባቸው መገለጫዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ስለሆነም በተለይም አንድ መሠረታዊ ህግ(substantive law) ወደ ኃላ ተመልሶ እንዲሰራ ህግ አውጪው በህጉ ላይ በልዩ ሁኔታ ካላመለከተ በስተቀር ፍርድ ቤት ወይም ሌላ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል ለያዘው ጉዳይ ተፈፃሚነት ያለውን መሠረታዊ ህግ ሲመርጥ መሠረት ሊያደርግ የሚገባው ወይም መሠረት እንዲያደርግ የሚጠበቅበት ለክርከሩ መነሻ የሆነው ጉዳይ በተፈጠረበት ጊዜ ተፈፃሚ ሲሆን የነበረውን ህግ ሊሆን ይገባል፡፡ሲል በፍትሐብሔር ጉዳይ አንድ ህግ ወደኃላ ሄዶ የሚሰራው በህጉ ላይ በልዩ ሁኔታ ካመላከተ ብቻ ነው ካልሆነ አንድ ህግ ወደኃላ ሄዶ አይሰራም ማለት ነው፡፡

01/24/2025

የትራምፕ አንደኛው ትፅዛዝ በፍርድ ቤት ታገደ !!!
____________________________________

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ ሀገር ውስጥ ገብቶ በመወለድ የሚገኝ ዜግነት አይኖርም ብለው በነጩ ቤተመንግስት የፈረሙትን ህግና ትዕዛዝን " " በማለት ጉዳዩ ሌላ ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልገዋል በማለት የፌደራሉ ፍርድ ቤት የፕሬዝደንቱን ውሳኔ አግዶታል ።

በጣም የገረመኝ ለካስ የህግ የበላይነት በሰፈነበት ሀገር የመሪው ትዕዛዝ እንኳ ሕዝብን ይጎዳል ተብሎ ከታስበና ከዋናው ህገ መንግስት ጋር ከተቃረነ በፍርድ ቤት ውድቅ ይደረጋል ።

ለማንኛውም በዛ ሀገር በስዴት እየኖራችሁ ልጆች ያፈራችሁ ወገኖቻችን እንኳን ደስ ያላችሁ ፤ ስትፀልዩ የስደተኞች አሜሪካን ለቀው ይውጡ አዋጅም ሊቀየር ይችላል ።

በ_Eyasu Regassa የተፃፌ

የዋስትና መብት ከወንጀል ድርጊት አፈፃፀሙ  እና ክብደት አንጻር ሊያስከለክል እንደማይችል በክርክር ሂደት ወደፊት የሚረጋገጥ ከመሆኑ  አንፃር ከጥፋተኝነት በፊት  ንፁህ  ሆኖ የመገመትን መብ...
01/02/2025

የዋስትና መብት ከወንጀል ድርጊት አፈፃፀሙ እና ክብደት አንጻር ሊያስከለክል እንደማይችል በክርክር ሂደት ወደፊት የሚረጋገጥ ከመሆኑ አንፃር ከጥፋተኝነት በፊት ንፁህ ሆኖ የመገመትን መብት የሚጥስ በመሆኑ የዋስትና መብት አያስከለክልም ሲል አዲስ የሰበር ውሳኔን አስተላልፏል ።

የፍርድ መፈፀም እና የፍርድ አፈጻጸም ስርአት --በሰበር ችሎት⚖️ፍርድ ተፈጸመ የሚባለው መቼ ነው?የፍርድ መፈፀም 1. እንደ ፍርዱ ይዘት መፈጸም፣ የፍርዱ ወደ ተግባር ወይም ውጤት መለወጥ፣ ...
12/23/2024

የፍርድ መፈፀም እና የፍርድ አፈጻጸም ስርአት
--በሰበር ችሎት
⚖️

ፍርድ ተፈጸመ የሚባለው መቼ ነው?

የፍርድ መፈፀም
1. እንደ ፍርዱ ይዘት መፈጸም፣ የፍርዱ ወደ ተግባር ወይም ውጤት መለወጥ፣ የአፈጻጸም አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ ተቋጭቶ መዝገቡ መዘጋት
2. ስለፍርድ አፈጻጸም የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በመከተል ፍርድን በተግባር መተርጎም
ሰ/መ/ቁ. 84446 ቅጽ 15፣ ሰ/መ/ቁ. 91622 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 5፣ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች አዋጅ ቁ. 199/92 አንቀጽ 24/3/

ፍርድ ተፈጸመ የሚባለው መቼ ነው? የሚለው ጥያቄ ለክርክሩ መነሻ እንደሆነው ንብረት ልዩ ባህርይ ታይቶ ሊመለስ የሚችል ነው፡፡ የፍርድ ባለመብት ፍርዱ ተፈጽሞለታል የሚባለው ጥሬ ገንዘብ ከሆነ ገንዘቡ ሙሉ በሙሉ ሲመለስለት፣ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ ደግሞ ንብረቶቹን ተረክቦ በይዞታው ላይ ሲያደርግ ነው፡፡
በገጠር የእርሻ መሬት ላይ በተሰጠ ፍርድ የፍርድ መቃወሚያ ሲቀርብ ፍርዱ ተፈጽሟል ሊባል የሚችለው የፍርድ ባለመብቱ በይዞታው ላይ ሕጋዊ ማረጋገጫ ሲያገኝ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 101079 ቅጽ 17፣ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 33፣ 39-41፣ 358፣ የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር አዋጅ ቁ. 456/1997፣ የተሻሻለው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር መወሰኛ አዋጅ ቁ. 133/1998፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ስርዓት ማስፈጸሚያ ክልል መስተዳድር ም/ቤት ደንብ ቁ. 51/1999

በሕግ አግባብ ታይቶ የተሰጠ ፍርድ እንደ ፍርዱ መፈጸም ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ያሳያሉ፡፡ በእነዚህ ድንጋጌዎች በተዘረጋው ስርአት አግባብ በመመራት ካልሆነ በስተቀር በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሣኔ ሕጋዊ ባልሆነ እና ውሳኔውን ውጤት አልባ በሚያደርግ መልኩ ውድቅ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ አይኖርም፡፡ አፈጻጸሙን የያዘው ፍርድ ቤት አፈፃፀሙን ምቹ ሁኔታዎች ሁሉ ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ በተቻለ መጠን ፍርዱ ተግባራዊ የሚሆንበትን መንገድ ሊከተል ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 91622 ቅጽ 16፣ ፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 378፣ 392፣ ፍ/ብ/ህ/ቁ. 998፣ 1195 እና 1196፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 40/1/ እና /2/

ፍርድ የሚፈፀመው በፍርድ ውስጥ በተገለፀው ውሳኔ መሰረት መሆኑን የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 378 ንዑስ አንቀጽ 1 ደንግጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የፍርድ ባለመብት ፍርዱን እንዲፈፀምለት ሲጠይቅ፣ የፍርድ ባለዕዳው፣ የፍርድ ባለመብቱ ተነጻጻሪ የሆነ ግዴታውን እንዲወጣ ትዕዛዝ ይስጥልኝ በማለት ጥያቄ ለማቅረብ የሚችለው በአንድ ፍርድ ውስጥ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች የፍርድ ባለመብት መሆናቸው ተረጋግጦ ውሳኔ ተሰጥቶበት እንደሆነ መሆኑን ከፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 398 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡
የፍርድ ባለመብት ሊፈፅምልኝ የሚገባው ግዴታ አለ በማለት የፍርድ ባለዕዳው በአፈፃፀም መከራከሪያ አድርጎ የሚያቀርባቸው ነጥቦች በዋናው ጉዳይ መከራከሪያ ሆነው ቀርበው ፍርድ ካልተሰጠባቸው የፍርድ ባለዕዳው ከባለመብቱ የሚጠይቀው መብት ካለ፣ በሕግ አግባብ ክስ አቅርቦ በፍርድ ተረጋግጦ እንዲንወስንለት ከሚጠይቅ በስተቀር፣ ፍርድ ያላረፈበትን ቅድመ ሁኔታ በአፈፃፀም ክርክር በመደርደር ፍርዱን የመፈፀም ግዴታ የለብኝም በማለት የሚቀርበው መቃወሚያ የሕግ መሠረት ያለው አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 99743 ቅጽ 17፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 37

የገጠር መሬት ባለይዞታ መሬቱ ወደ ከተማ ፕላን ክልል የገባ ቢሆንም ቤት ለማደስ ወይም ለመስራት ካርታ እና ፕላን ስለሌላቸው የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም ( ህንፃ ሹም )ማው...
12/17/2024

የገጠር መሬት ባለይዞታ መሬቱ ወደ ከተማ ፕላን ክልል የገባ ቢሆንም ቤት ለማደስ ወይም ለመስራት ካርታ እና ፕላን ስለሌላቸው የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም ( ህንፃ ሹም )ማውጣት የማይገደዱ ሰለሆነ አስገዳጅ የሰበር ትርጉም ተሰጥቷል።

06/09/2024

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከታች በተጠቀሰው መዝገብ ቁጥር የሚከተሉትን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል::
ፍርድ ቤት እስከ 15 ቀን ድረስ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 109/1 መሰረት የሰጠዉ ጊዜ ከአለቀ በኋላ በተጠርጣሪዉ ላይ ክስ ሳይመሰርት ተጠርጣሪዉን በእስር ላይ ማቆየት በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17/2 እና በተባበሩት መንግሥታት የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን አንቀጽ 9/1 የተከለከለዉን በሕግ ከተደነገገዉ ሥርዓት ዉጭ በዘፈቀደ አስሮ እንደማቆየት የሚቆጠር እንደሆነ አንስቷል፡፡
ይህም ተጠርጣሪው የዋስትና መብት እንዲጠበቅለት ጥያቄ አቅርቦ ጥያቄዉ ውድቅ ከሆነ በኋላ የዋስትና ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ ሲፈጠር ይህንኑ አዲስ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ለዚያዉ ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ ሥነ ሥርዓታዊ መብት የአለዉ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡
ይህም ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት የተሰጠዉ የ15 ቀን ጊዜ ክስ ሳይመሰርት ያለቀ ከሆነ ተጠርጣሪው በድጋሚ ዋስትና ለመጠየቅ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ የተፈጠረ በመሆኑና በድጋሚ የሚያቀርበዉ የዋስትና ጥያቄ አግባብነት ካለዉ ሕግ አንጻር ሳይመረመር በደፈናዉ ጥያቄዉ በድጋሚ የቀረበ ነው በሚል የተያዘዉ ሰዉ ክስ ሳይመሰረትበት ላልተወሰነ ጊዜ ታስሮ እንዲቆይ የሚያደርግ ትእዛዝ/ዉሳኔ መስጠት ስነስርዓታዊ አለመሆኑን አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል:: ያልታተመ ሠ.መ.ቁ 252231

Address

A/Wondo/Sidama/Ethiopia
New York, NY

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wodiidi Sidaami Zoone Aliidi Yoo MIne/ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Featured

Share

Category