Chelot - Free Legal Advice and Knowledge ችሎት ነፃ የሕግ ምክር እና ዕውቀት

Chelot - Free Legal Advice and Knowledge  ችሎት ነፃ የሕግ ምክር እና ዕውቀት በማንኛውም የህግ ጉዳዮች ላይ የሕግ ምክርና የጥብቅና አገልግሎት

፨ ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ:  መዝገብ ቁጥር 236212በቀን ጥር 25 ቀን2018 ዓ.ም፨ አንድ ሰዉ መብቱን የሚነካ ዉሳኔ የተፈጸመ እንደሆነ አዲ...
02/04/2026

፨ ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 236212በቀን ጥር 25 ቀን2018 ዓ.ም

፨ አንድ ሰዉ መብቱን የሚነካ ዉሳኔ የተፈጸመ እንደሆነ አዲስ ክስ በማቅረብ መብቱን ማስከበር የሚችለዉ፣ ከአቅም በላይ ወይም በቂ በሆነ ምክንያት ዉሳኔዉ ከመፈጸሙ በፊት መብቱን የሚነካ ዉሳኔ ስለመኖሩ ማወቅ ባለመቻሉ ወይም በተመሳሳይ ምክንያት መቃወሚያ ማቅረብ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው” ተብሎ ተሻሽሎ ተተርጉሟል።

፨ ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁጥር 50835 “በአንድ መዝገብ ላይ የተሠጠ ውሳኔ ከተፈፀመ በኋላም ቢሆን በውሳኔው መብቱ የተነካበት 3ኛ ወገን በሌላ መዝገብ ላይ ክስ አቅርቦ መብቱን ማስከበር ይችላል “ በሚል እንዲሁም በሰ/መ/ ቁጥር 67127 “በፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መብቴን ይነካል የሚል ሰው በዚያው መዝገብ ላይ የመቃወም አቤቱታ አቅርቦ መብቱን ማስከበር ከሚችል በቀር ዉሳኔዉ በአፈጻጸሙ ከተቋጨ በኋላ በሌላ መዝገብ ላይ አዲስ ክስ ማቅረብ አይችልም፤ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የቀረበ ክስ ተቀብሎ ውሳኔ መስጠትም መሠረታዊ የሕግ ስህተት ነው” በሚል የተሰጡት አስገዳጅ ውሳኔዎች ተሻሽሏል፡፡

♧ ሰ/መ/ቁ.235844 (ጥቅምት 06 ቀን 2016 ዓ.ም)♧ የቤቱ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በባልና በሚስት ስም በጋራ የተመዘገበ ቢሆንም፣ በንብረት ክፍፍል ወቅት ቤቱ ለአንደኛው ተጋቢ ብቻ ሊ...
01/12/2026

♧ ሰ/መ/ቁ.235844 (ጥቅምት 06 ቀን 2016 ዓ.ም)

♧ የቤቱ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በባልና በሚስት ስም በጋራ የተመዘገበ ቢሆንም፣ በንብረት ክፍፍል ወቅት ቤቱ ለአንደኛው ተጋቢ ብቻ ሊወሰን ይችላል።

♧ ቤቱን የጋራ ለማድረግ የተደረገ የጋብቻ ውል በሌለበት ሁኔታ፣ ቤቱ የተገነባው (የተፈራው) ከጋብቻ በፊት መሆኑ ከተረጋገጠ፣ የይዞታ ማረጋገጫው ላይ የሁለቱም ስም መኖሩ ብቻ ንብረቱን የጋራ አያደርገውም። በመሆኑም ቤቱ የአንደኛው ተጋቢ የግል ሀብት ተብሎ ሊወሰን ይገባል።

♧ ሰ.መ.ቁ. 212950  [ቅፅ 27]♧ ተከሳሽ ይከላከል ከተባለ በኋላ በመከላከያ ማስረጃው ማስረዳት የሚጠበቅበት  በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ነው ወይስ ጥርጣሬ መፍጠር ????♧ በወንጀ...
01/09/2026

♧ ሰ.መ.ቁ. 212950 [ቅፅ 27]

♧ ተከሳሽ ይከላከል ከተባለ በኋላ በመከላከያ ማስረጃው ማስረዳት የሚጠበቅበት በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ነው ወይስ ጥርጣሬ መፍጠር ????

♧ በወንጀል የተከሰሰ ሰው መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ የሚታዘዘው በዓቃቤ ህግ ማስረጃ የተረጋገጠበትን ክስ እና ማስረጃን እንዲያስተባብል ሲሆን ማስተባበል ማለት ደግሞ የተከሳሹን የወንጀል ድርጊት እና ጥፋተኝነት አረጋግጠዋል በተባሉት ማስረጃዎች ላይ በእንድም ይሁን በሌላ መንገድ ጥርጣሬ እንዲፈጠር በማድረግ በማስረጃዎቹ የማስረዳት አቅም ላይ መተማመን እንዳይኖር ማድረግ በመሆኑ ከተከሰሰው ሰው የሚጠበቀው በመከላከያ ማስረጃው በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረዳት ሳይሆን የዐቃቤ ህግ ማስረጃን አስመልክቶ ቀድሞ በተያዘው አቋም ላይ ጥርጣሬን መፍጠር ብቻ ስለመሆኑ::

Better Call Lawayer Amin: 091 089 5414

12/06/2025

፨ ሰ.መ.ቁ. 220986

፨ ከሳሽ (ቼክ አምጭዉ) ቼኩ በምን አግባብ በእጁ እንደገባ (ለቼኩ መሰጠት ) ምክንያት የሆነዉን ግንኙነት የማስረዳት ግዴታ የሌለበት ስለመሆኑ

ተከሳሽ ክስ የቀረበበትን ቼክ ለከሳሽ መስጠቱን ሳይክድ ይልቁንም ቼኩን መስጠቱን በግልጽ አምኖ ቼኩን የሰጠሁት ለመተማመኛ ነዉ በማለት ከተከራከረ ተከሳሽ በቼኩ (ሰነደ) ህጋዊነት ላይ /real defense/ መከራከሪያ ያላቀረበ መሆኑን ይልቁንም ለቼኩ መዉጣት ምክንያት ነዉ የሚለዉን የግል ግንኙነትን መሰረት በማዴረግ ክፍያ እንደማይገደድ የተከራከረ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ ቼኩ ክፍያ የማይፈጸምበትን ህጋዊ ምክንያት ስለመኖሩ በቀዳሚነት የማስረዳት ሸክም (ግዴታ) የተከሳሽ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ። ከዚህ አኳያ በእጃቸው ሊገባ የቻለው በግራ ቀኙ መካከል በነበረ የብድር ውል ስምምነት ለብድሩ ገንዘብ መክፈያነት ስለመሆኑ በማስረጃ አረጋግጠው የማቅረብ ግዳታቸውን ያልተወጡ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ቼኩን ያላአግባብ ነው የያዙት በሚል ክሱን ውድቅ ማድረጉ አግባብነት የለውም ።
ሲጠቃለል ለዚህ አቤቱታ መሰረት የሆነዉ የቼክ ክስ ተከሳሽ እንዲከላከል ፍርድ ቤቱ ከፈቀደለበት በኋላ ተከሳሽ እንደ ክርክሩ አቀራረብ ማስረዳት አለማስረዳቱን ሳያረጋገጥ ከሳሽ የሆነዉ ወገን ቼኩን ያገኘበትን ዉል አላስረዳም በማለት ክሱን ዉድቅ ማድረጉ በቀዳሚነት የማስረዳት ሸክም የማነዉ የሚለዉን ባለመለየት የማስረዳት ሸክም ያለአግባብ ወደ ከሳሽ በማዞር ክርክሩን የመራበት አግባብ ስህተት የተፈፀመበት ስለመሆኑ::

https://t.me/LawyerAminT
https://t.me/LawyerAminT

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

📲+251910895414
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

፨ ሰ.መ.ቁ.153258፨ የባልና ሚስት ፍቺ ተፈጽሞ የንብረት ክፍፍል እስከሚደረግ ድረስ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረትም ሆነ ከዚህ ንብረት የሚገኝ ገቢ የጋራ ሆኖ የሚቆይ ስለመሆኑ።
11/08/2025

፨ ሰ.መ.ቁ.153258

፨ የባልና ሚስት ፍቺ ተፈጽሞ የንብረት ክፍፍል እስከሚደረግ ድረስ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረትም ሆነ ከዚህ ንብረት የሚገኝ ገቢ የጋራ ሆኖ የሚቆይ ስለመሆኑ።

፨ ሰ.መ.ቁ. 282248 [ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም] ፨ ተከሳሽ ሕጻናት ልጆች ካሉት ቅጣት መገደብ ግደታ ነው።፨ ተከሳሽ ጥፋተኛ የተባለበት ድንጋጌ ቅጣት እንዲገደብ በህጉ  ክልከላ ካ...
10/27/2025

፨ ሰ.መ.ቁ. 282248 [ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም]
፨ ተከሳሽ ሕጻናት ልጆች ካሉት ቅጣት መገደብ ግደታ ነው።

፨ ተከሳሽ ጥፋተኛ የተባለበት ድንጋጌ ቅጣት እንዲገደብ በህጉ ክልከላ ካልተደረገበት በስተቀር ተከሳሽ ህጻናት ልጆች የሚያስተዳድር መሆኑን ገልጾ ባቀረበበት ፍ/ቤት በህጻናቱ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ቁሳዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ለማስቀረት ሲባል ቅጣቱ ያለመገደብ መሠረታዊ የህግ ስህተት ስለመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መ/ቁ 282248 በቀን 06/02/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል።
https://t.me/LawyerAminT
https://t.me/LawyerAminT

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

📲+251910895414
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

10/17/2025

፨ አሰሪና ሰራተኛ ህግ: የይርጋ ህግ (Statute of Limitations) ዋና ዋና ነጥቦች!

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳዮች ላይ የይርጋ ጊዜን (ክስ የሚቀርብበት የጊዜ ገደብ) በተመለከተ የሰጣቸውን ወሳኝ የሕግ ትርጓሜዎችና መርሆዎች እናጋራችሁ። መብታችሁ በጊዜ ገደብ እንዳይታገድ እነዚህን ነጥቦች ይወቁ!
1. መደበኛ የይርጋ ጊዜ ገደቦች:
የተለያዩ የክርክር ዓይነቶች የሚቀርቡበት የይርጋ ጊዜ ገደብ የሚከተለው ነው፦
• ወደ ሥራ ለመመለስ የሚቀርብ ጥያቄ: 3 ወራት ነው (ሰ/መ/ቁ. 238017, 229714)።
• ከሥራ መቋረጥ ጋር የተያያዙ ክፍያዎች (ካሳ፣ ስንብት፣ ወዘተ): 6 ወራት ነው (ሰ/መ/ቁ. 238017, 205966)።
• ከሥራ መቋረጥ ጋር ያልተያያዙ ክፍያዎች (ትርፍ ሰዓት፣ ደመወዝ ጭማሪ): 6 ወራት ነው (ሰ/መ/ቁ. 79476, 197437)።
• አሰሪ በሠራተኛ ጥፋት ውል ለማቋረጥ (ከጥፋቱ እውቀት ጀምሮ): 30 የሥራ ቀናት ነው (ሰ/መ/ቁ. 230388)።
• ከቅጥር ግንኙነት የሚመነጩ አጠቃላይ ክሶች: 1 ዓመት ነው (ሰ/መ/ቁ. 229247)።
2. የይርጋ ጊዜ መቆጠር መቼ ይጀምራል? 🗓
የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው መብቱን ለመጠቀም ክስ ማቅረብ ከተቻለበት ቀን ጀምሮ ነው።
• ግልጽ የውል መቋረጥ: ውሉ ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ ነው (ሰ/መ/ቁ. 238017)።
• አሻሚ የውል መቋረጥ: የሥራ ውሉ መቋረጡ ግልጽ ካልሆነ፣ የይርጋው ጊዜ የሚጀምረው ሠራተኛው ስለ ውሉ መቋረጥ አውቆ ክስ ማቅረብ ከቻለበት ቀን አንስቶ ነው (ሰ/መ/ቁ. 237493, 236453, 221212, 218049)።
• የማይቀይሩ ሁኔታዎች: ከወንጀል ክስ በነጻ መውጣት ወይም አሠሪው ወደ ሥራ የመመለስ ጥያቄን ውድቅ ማድረጉ የይርጋውን መነሻ ጊዜ አይቀይረውም (ሰ/መ/ቁ. 238017)።
3. የይርጋ ጊዜን የሚያቋርጡ/የሚያቆሙ ልዩ ሁኔታዎች! ⏸️
መብቱን ለማስከበር የሚጥር ወገን መብቱ በይርጋ እንዳይታገድ እነዚህ ምክንያቶች ይርጋን ሊያቆሙ ይችላሉ፦
• ከአቅም በላይ የሆኑ ሁኔታዎች (Force Majeure):
o ከባድ ሕመም ክሱን በወቅቱ ማቅረብ ካላስቻለ (ሰ/መ/ቁ. 234501)።
o የመንግሥት ዕገዳ ወይም የሥራ ውሉ በመንግሥት ዕገዳ ምክንያት ከቆመ (ሰ/መ/ቁ. 237497)።
o የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለክፍያ ጥያቄዎች (ለ3 ወር የሥራ መመለስ ጥያቄ ግን አያቆምም) (ሰ/መ/ቁ. 233253)።
• ስልጣን በሌለው ፍርድ ቤት ክስ መመስረት: ሰራተኛው በስልጣን በሌለው ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ መከራከሩ ይርጋን ያቋርጣል (ሰ/መ/ቁ. 216200)።
• የአሠሪው ዕውቅና: አሠሪው የክፍያ መብቱን በጽሑፍ ሲያምንለት ወይም በከፊል ሲፈጽምለት (ሰ/መ/ቁ. 197437)።
4. የይርጋ ጊዜን የማያቋርጡ ምክንያቶች 🚫
• የወንጀል ክስ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ መጠበቅ ወይም ከክስ በነጻ መለቀቅ (ሰ/መ/ቁ. 238017, 229714)።
• በእስር ላይ መሆን (ሰ/መ/ቁ. 229714)።
• ክስ መስርቶ በፍርድ ቤት ፈቃድ መተው (ሰ/መ/ቁ. 205966)።

የሰበር ሰሚ ችሎት ዋና መልዕክት:
የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች የይርጋ ደንብ ዓላማ መብቱን ለማስከበር የማይተጋን ወገን ለመገደብ እንጂ ትጋት ያለውን መብቱን እንዳይጠቀም ማድረግ እንዳልሆነ ያጎላሉ። ፍርድ ቤቶችም በራሳቸው ተነሳሽነት የይርጋ መቃወሚያ ማንሳት እንደማይችሉ አስቀምጧል (ሰ/መ/ቁ. 230388)። ©ኣብርሃም_ዮሃንስ

Big shout out to my newest top fans! 💎 Maru Gebre, Yoel MayawDrop a comment to welcome them to our community,  fans
08/08/2025

Big shout out to my newest top fans! 💎 Maru Gebre, Yoel Mayaw

Drop a comment to welcome them to our community, fans

02/10/2025

፨ ሰ.መ.ቁ. 182136 [ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም]

፨ በተከራካሪው የተወከለው ጠበቃ ሌላ ችሎት ስለተደረበበት ክርክሩ በሚሰማበት ቀን መቅረብ ባለመቻሉ መዝገቡ ከተዘጋ እንደነገሩ ሁኔታ በቂ ምክንያት በመሆኑ የተዘጋው መዝገብ ሊከፈት ይገባል።

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.74 [2] ደንጋጌ መሰረት “በቂ ሆኖ የሚገመት እክል” ምን እንደሆነ የተመለከተ ባይሆንም አመልካች ቀጠሮ ለመቅረት የቻለዉ በምን ምክንያት እንደሆነ አጠቃላይ ሁኔታዉን መመርመር የሚያስፈልግ ሆኖ፣ አመልካች በራሱ ጉድለት ወይም ቸልተኛነት ቀጠሮዉን ሳይከታተል ቀርቶ ካልሆነ በስተቀር፣ ፍትሕ የማግኘትና የመከራከር መብት ከግምት በማስገባት አመልካችን የገጠመዉ እክል እንደበቂ ምክንያት በመውሰድ ለተጠሪ [መዝገቡ የተዘጋው በክልል ሰበር ችሎት በነበረው ክርክር ነው] ተገቢ ኪሳራና ወጪ በማስከፈል፣ የተዘጋዉ መዝገብ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲሰማ መድረጉ አግባብ ነዉ። በመሆኑም አመልካች ክርክሩን በጠበቃ ለማካሄድ ወስኖ በሕጉ አግባብ ተገቢዉን ዉክልና ሰጥቶ እያለ ጠበቃዉ ችሎት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ ተገኝቶ አመልካችን ወክሎ ተገቢዉን ክርክር የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል። ነገር ግን ጠበቃ የተለያዩ ደንበኞች ሊኖሩት ስለሚችል ፍ/ቤት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ በተቻለ መጠን ለደንበኞቹ ተገቢዉን የጥብቅና አገልግሎት መስጠት በሚያስችለዉ አግባብ አጀንዳዉን አስማምቶ ቀጠሮ እንዲያዝለት ለፍ/ቤቱ ማመልከት ይጠበቅበታል። ይህም ሆኖ ቀጠሮ ተደራርቦበት በአንድ ጊዜ በተለያዩ ችሎቶች የሚቀርበበትን እድል በማዛባቱ ምክንያት የባለጉዳዩ መዝገብ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ የህጉ ድንጋጌ መሰረት ተዘግቶ እንደሆነ፣ አጠቃላይ የነገሩን ሁኔታ በመመርመር፣ የአመልካች የመከራከርና ፍትሕ የማግኘት መብት ታሳቢ በማድረግ መዝገቡ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲሰማ ማድረጉ ተገቢ ነዉ።
https://t.me/LawyerAminT
https://t.me/LawyerAminT

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

📲+251910895414
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

02/08/2025

፨ ሰ.መ.ቁ. 222277
፨ የነበረን ቤት ባለበትም ሆነ አፍርሶም ማደስ ከፍ/ሕ/ቁ 1179 ድንጋጌ አንፃር

አንድ ሰው በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ባለይዞታው ሳይቃወም ቤት ቢሰራ የተሰራው ቤት ባለቤት እንደሚሆን ከተደነገገው ጋር የሚገናኝ አይደለም።ስለዚህ ቤቱን አፍርሶ ስለሰራ ወይም አድሶ ስለሰራ ባለይዞታ ሳይቃወም አፍርሼ የሰራሁት ወይም ያደስኩት ቤት በመሆኑ የቤቱ ባለቤት ነኝ ለማለት አይቻልም።ሲል የፌ/ሰ/ሰ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 222277 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
https://t.me/LawyerAminT
https://t.me/LawyerAminT
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

📲+251910895414
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

02/07/2025

፨ ሰ.መ.ቁ. 220042 [ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም]

፨ ካርታ ይምከንልኝ የሚል ዳኝነት ጥያቄ ጉዳይ በቀጥታ ለፍ/ቤት ሊቀርብ ይችላል?

አመልካች በስር ፍርድ ቤት የጠየቁት ዳኝነት ከይዞታቸዉ ላይ ተቀንሶ አለአግባብ 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ የሰጠዉ ካርታ ይምከን የሚል ነዉ። ካርታ የመስጠትም ሆነ የማምከን ሰልጣን ያለዉ ካርታዉን የሰጠዉ አካል ነዉ፡፡ በተያዘዉ ጉዳይ ካርታ የመስጠት ሰልጣን የ2ኛ ተጠሪ ስለ መሆኑ አላከራከረም። ይህ ማለት የአስተዳደር ዉሳኔ ሰለመሆኑ ያሳያል፡፡ በአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ 1183/2013 አንቀጽ 2(3) መሰረት አስተዳዳር ዉሳኔ አስተዳዳር መስርያ ቤቶች በዕለት ዕለት ስራቸዉ መሰረት የሚሰሩት ስራ ነዉ። ከአስተዳደራዊ ዉሳኔዎች ዉስጥም ካርታ ማምከን አስተዳደራዊ ዉሳኔ ተደርጎ የሚወሰድ ነዉ፡፡አስተዳደራዊ ዉሳኔዎች ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 44 መሰረት ለተቋቋመ የአስተዳደር ተቋም የቅሬታ ማስተናገጃ አካል በአንቀጽ 43 ቅሬታ የሚቀርብበትና ይህ ቅሬታ ሰሚ አካል በአንቀጽ 46 መሰረት የተቋሙን መጨረሻ ዉሳኔ ሲሰጥ በአንቀጽ 49(1)አግባብ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክለሳ አቤቱታ የሚቀርብበት ነዉ፡፡በአመልካች በኩል የቀረበዉ ክስም በአዋጁ በተዘረጋዉ ስርዓት መሰረት ያሉትን ሂደቶች ተከትለዉ ያንን ከጨረሱ (exhaustion of local remedies) በኋላ መምጣት ሲገባቸዉ ቀጥታ ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ አዋጁን ያገናዘበ ሆኖ አላገኘንም፡፡ ተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የፌ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥር 220582 (ያልታተመ) ገዥ ዉሳኔ ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለዉ ችሉት ሰጥተል። ጉዳዩ መጀመሪያ የቀረለበት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የቀረበለት ጉዳይ ካርታ ይምከን ዳኝነት ጥያቄ ሆኖ ይህን ጉዳይ ለማየት ስልጣን ያለዉ መሆን አለመሆኑን በመጀመሪያ ማየት ሲገባዉ ዋናዉ ጉዳይ ላይ ዉሳኔ መስጠቱ ይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንን ማረም ሲገባዉ ሳያርም በትዕዛዝ መዝገብ መዝጋቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ዉሳኔ ነዉ በማለት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።

https://t.me/LawyerAminT
https://t.me/LawyerAminT
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

📲+251910895414
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

02/06/2025

፨ ሰ.መ.ቁ. 253740
፨ ቅጣትን መፍራት ተፈጥሯዊ ነው።

ከወንጀሉ ክብድትና ቅጣት አንፃር ተከሳሹ ዋስትና መብቱ ቢጠበቅ ቅጣቱን በመፍራት ቀጠሮውን አክብሮ ይመጣል የሚል ግምት ችሎቱ የለውም በማለት በወ/ሰ/ሰ/ህ/ቁ 67(ሀ) መሰረት የዋስትና ግዴታውን አያከብርም በሚል ጥያቄ ላይ ሰበር በቂና ምክንያታዊ ህጋዊ ማስረጃ ሳይቀርብ እና ተጨባጭ መንደርደሪያ ሣይናረው ከወንጀሉ ክብደት ብቻ በመነሳት ቅጣትን መፍራትን ብቻ ምክንያት በማድረግ ዋስትናን መከልከል ተገቢነት የለውም በማለት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል።

https://t.me/LawyerAminT
https://t.me/LawyerAminT

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

📲+251910895414
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

Address

Minneapolis, MN

Opening Hours

Monday 9am - 5pm
Tuesday 9am - 5pm
Wednesday 9am - 5pm
Thursday 9am - 5pm
Friday 9am - 5pm
Saturday 9am - 5pm

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Chelot - Free Legal Advice and Knowledge ችሎት ነፃ የሕግ ምክር እና ዕውቀት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Chelot - Free Legal Advice and Knowledge ችሎት ነፃ የሕግ ምክር እና ዕውቀት:

Share