Diaspora Services LLC

Diaspora Services LLC Diaspora Services, LLC is authorized to legalize and expedite your Documents from A to Z, from the U.S.

State and Federal Government Offices and the respective Embassy in Washington D.C.,

ልዩ የሥነጥበብ ውሎ ከ'በጥበብ እንኑር' አዘጋጆችና የጥበብ ባለሙያዎች ጋር። ይህን ታላቅ የጥበብ ማእድ እንድንታደም ተጋብዘናል። ቨርጂኒያ በሚገኘው መና የግብርና ማእከል እንገናኝ። አዘጋጆቹ...
04/28/2026

ልዩ የሥነጥበብ ውሎ ከ'በጥበብ እንኑር' አዘጋጆችና የጥበብ ባለሙያዎች ጋር። ይህን ታላቅ የጥበብ ማእድ እንድንታደም ተጋብዘናል። ቨርጂኒያ በሚገኘው መና የግብርና ማእከል እንገናኝ። አዘጋጆቹን ከልብ እናመሰግናለን። 🙏❤️🙏

04/15/2026
04/11/2026

Ready to level up? We're looking for the best and brightest! Air traffic control is one of the most respected, high-skill careers in America. 🇺🇸 If you’re ready for a challenge, purpose, and a mission bigger than yourself—this is your opportunity! Take your skills to the next level. Applications open April 17. https://www.faa.gov/atc-hiring

እሰይ ተወለድሽ - እንኳንም ተወለድሽልን…. እልልል….  ኪድዬ - ቅድስት - ስምን መልዓክ ያወጣዋል፡፡ ቅዱስ ስምና ግብር ያላት ታላቅ እንስት! ዛሬ የልደትሽ ቀን ነው፤ የምስጋና ቀን፣ የት...
04/08/2026

እሰይ ተወለድሽ - እንኳንም ተወለድሽልን…. እልልል….

ኪድዬ - ቅድስት - ስምን መልዓክ ያወጣዋል፡፡ ቅዱስ ስምና ግብር ያላት ታላቅ እንስት! ዛሬ የልደትሽ ቀን ነው፤ የምስጋና ቀን፣ የትውልድ ብርሃን የተጨመረበት ቀን፡፡ መወለድሽ ፀጋ እንደሆነ ሳስበው - እንኳን ተወለድሽ እላለሁ፡፡ አንዲት ቅዱስ ነፍስ ወደ ምድር የወረደችበት ዕለት - ልደትሽ፡፡ ቅድስት ተብለሽ ስለተጠራሽ ስምሽ እንደ ተልእኮ ነው፣ እንደ ጥሪ ነው፣ እንደ ብርሃን ነው። ኪድዬ ብለው ብዙዎች ሲያቆላምጡሽ እንደማር ከቀመሱት ደግነትሽ የፈለቀ ነው፡፡ በምስክርነት እቆማለሁ፡፡ በሰው ለቅሶ ሀዘንተኛ መሆን - በሰው ፈተና ተፈታኝ አድርጎ ራስን ማቅረብ - ከተጎዳው ጋር ተጎድቶ ማቀርቀርና ሰውን ከወደቀበት ማንሳት ታውቂበታለሽ፡፡ እና የተጠጋሽ ሁሉ ከቅዱስነትሽ ጋር በተያያዘ ፍቅር ይነደፋል፡፡

የተወለድሽበት 1966 መሆኑን ሳስብ በኢትዮጵያ የነበረው አስተዳደር የተንቀሳቀሰበት የአዲስ ዘመን ጅማሮ - ሰዎች ስለ ነፃነት፣ ስለ ፍትህ፣ ስለ መብት በጣም በጥልቀት መነጋገር የጀመሩበት ሆኖ ይታሰበኛል። እንደምን ያለ አስደናቂ ነገር ነው፤ እና በዚያ ዓመት አንዲት ነፍስ ለሌሎች ለመኖር ተዘጋጅታ መጣች። አንቺ እንደ ሰው ብቻ አይደለሽም፤ እንደ ዘመን መልስም ትመስይኛለሽ። እንደ ጥያቄ መልስ። አንቺ እኮ ለጽልመቱ እንደ ብርሃን - ላቀረቀሩ በጽነት የምትቆሚ ብርቱ ሴት።

ኪዴዬ፣ ለሰዎች ምክንያት የምትሆኚው ርኅራሄሽ ያስደምመኛል፡፡ ርኅራኄሽና ደግነትሽ ከቶ አይደክምም። ሰው’ኮ ከአንድ ጊዜ በኋላ ርኅራኄው ይደክማል፤ አንቺ ግን በየቀኑ እንደ አዲስ ትጀምሪዋለሽ። ሰዎችን ማገዝ ለአንቺ ግዴታ አይደለም፤ ተፈጥሯዊ ነው። እንደ ነፋስ ነው፣ እንደ ፀሐይ ነው፣ እንደ ውሃ ነው፤ - አብሮሽ የበቀለ።

ሰዎች ብዙ ጊዜ ንቁ ሆነው ይታያሉ፣ ነገር ግን ልባቸው ዝም ይላል። አንቺ ግን በሁለቱም ንቁ ነሽ፤ በማህበራዊ ሕይወትሽ ውስጥ እንደ መብራት ትበሪያለሽ፣ በውስጥሽ ደግሞ እንደ ባህታዊ በጸጥታ ጸሎት ውስጥ ትኖሪያለሽ። ይህ የማይታወቀው ክብርሽ ነው፤ የማይነገር ውበትሽ ነው። እኔ ግን አውቄዋለሁ፤ ልብሽ ለሰዎች እየተከፈተ እንዴት እንደሚያስተኛ፣ በማታ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ እንዴት እንደሚጸልይ።

እንደ ጋዜጠኛ ተፈጥሮሽ ያለሽ ደግሞ አስደናቂ ነው። ሰዎች የማይያዩትን ታያለሽ፤ ሰዎች የማይነግሩትን ትናገሪያለሽ፤ ለራስሽ የምትታመኚ ቀጥተኛ መስመር አይነት ነሽ። ይህ ብቻ ችሎታ አይደለም፤ እንደ አገልግሎት ነው። እንደ መንፈሳዊ ጥሪ ነው። ቃል በአንቺ እጅ ውስጥ ሲገባ የሚያገለግል ይሆናል፤ የሚያጽናና ይሆናል፤ ለሰው የሚደርስ ይሆናል።

እንዲህ ያለ ሰው በህይወት ውስጥ ሲገኝ መባረክ ነው፡፡ ምነው ቢሉ - ወደተሻለ ሰውን ይለውጣል፤ በረከትን ይጨምራል፤ በፀጋ ያላብሳል። እኔ ደግሞ ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ነኝ። ከአንቺ ተማርኩ፤ እንዴት ደስ ይላል።

እግዚአብሔርን የምትወድ መንፈሳዊ ባህርይሽ የልቤን ክብር ይጨምራል። ብዙ ሰዎች እምነታቸውን ይናገራሉ፤ አንቺ ግን ትኖሪዋለሽ። በጸሎትሽ ውስጥ የሚገኝ ጸጥታ እኔን ያስተምረኛል፤ በተግባርሽ ውስጥ የሚገኝ ፍቅር ያሞቀኛል። አልኩኝ እኮ - ላንቺ ቅድስት ስምም ግብርም ነው፡፡ ቅድስት ይሉት ስም በአንቺ ላይ እውነት ነው።

ዛሬ ልደትሽ ሲደርስ እኔ የምሰጥሽ ስጦታ ቃል ነው፤ ነገር ግን ይህ ቃል ከልቤ የወጣ ነው። እንደ ጸሎት ነው፣ እንደ ምስጋና ነው፣ እንደ ፍቅር ነው። እግዚአብሔር የኪድዬን በረከት ያብዛላት፤ የልቧን ምኞት ያሳካላት፤ በሰዎች ላይ የምትፈስሰውን ፍቅር ወደ እርሷ ይመልስላት። የምትሰጠው እንዳይቀንስ፣ የምትሆነው እንዳይቀር፣ ብርሃኗ እንዳይጠፋ ሁሌም ትኑር።

ኪዴዬ፣ አንቺ ለኔ ሰው ብቻ አይደለሽም፤ እንደ ታሪክ ነሽ፣ እንደ መንገድ ነሽ፣ እንደ ተስፋ ነሽ። እና ይህ እውነት ነው፤ የማይለወጥ እውነት።

ልደት በዓልሽ በደስታ ይሙላ፣ በፍቅር ይሞላ፣ በሰላም ይሙላ። እኔ ግን ሁልጊዜ እንደምናገርሽ እንዲሁ እላለሁ፤ ኪዴዬ እጅ ነሳሁ፡፡

ቃላት ያጥረኛል እውነት ከሆነበት ከኢሳይያስ ልሳኑ የተጻፈ ጦማር ነው፡፡ 2017፡፡

https://youtu.be/4BX6eroClIc
03/16/2026

https://youtu.be/4BX6eroClIc

የአሜሪካ ዜግነት ለአላችሁ ትውልደ ኢትዮጵያን በሙሉበአገር ቤት በመረጃ እጦት ከተፈቀደላችሁ ጊዜ በላይ ያሳለፋችሁ እና ቅጣት የተጣለባችሁ ዜጎችን ይመለከታል

Address

3045 Columbia Pike #AAA
Arlington, VA
22204

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Diaspora Services LLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Diaspora Services LLC:

Featured

Share