ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቲዩብ / orthodox tewahdo tube

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቲዩብ / orthodox tewahdo tube ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቲዩብ

https://youtu.be/l0wQk9OOu3o?si=KwiKbKchqnaHQwK1
22/01/2024

https://youtu.be/l0wQk9OOu3o?si=KwiKbKchqnaHQwK1

የጥምቀት በዓል አከባበር በጀርመን 2024 እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ እያልንይህንን የዩቱይብ ገፅ ለሰዎች እንዲደርስ ሼር ኮፒ ሊንክ በማድረግ ገፁን እናሳድግ እናመ....

Always
12/02/2023

Always

06/02/2023
06/02/2023
12  enkan adresachu
21/11/2022

12 enkan adresachu

 ?....._ _ _ _ _ _  #ሚስጢሩ _ _ _ _ _ _ _ _በቤተክርስቲያናችን  ስርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔርከታሰራችሁበት ኃጥያት ማሰሪያ ይፍታቹ ሲሉ 12 ጊዜእግዚኦ መሐረነ ክር...
15/09/2022

?.....

_ _ _ _ _ _ #ሚስጢሩ _ _ _ _ _ _ _ _

በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር
ከታሰራችሁበት ኃጥያት ማሰሪያ ይፍታቹ ሲሉ 12 ጊዜ
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና 12 ጋዜ ደግሞ በእንተ እግዝትነ
ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላሉ። ካህናትና ምእመናን
በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህኑን 12 ጊዜ እንላለን።

እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት አቤቱ ክርስቶስ ማረን
ሲሆን በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ
ስለእመቤታችን ማርያም ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን ማለት ነው።

አስራ ሁለት ጊዜ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12ሰዓት በእንተ
እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ለሊቱን 12ሰዓት ሲሆን
በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሰራነው ኃጥያት በሃያ አራቱ 24ቱ
ሰዓት ምሕረት እናገኝ ዘንድ ነው።

_ ሌላው አስራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት፦
_ 1 ኛው በስመ ሥላሴ ነው በእያንዳንዱ ፊደል
_ አ ብ ወ ል ድ መ ን ፈ ስ ቅ ዱ ስ
_ ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪

_ 2 ኛው የድህነታችን ምክንያት በሆነች በእመቤታችን ስም
ፊደል ነው።
* ቅ ድ ስ ት ድ ን ግ ል ማ ር ያ ም
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪

_ _ _ _ _ _ _ _ እግዚኦ __ _ _ _ _ _ _ _ _ _

_ አቆጣጠረም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራ ጣት
እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ፣ ቀጥሎ በመሐል ጣት
ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደታች ተደርጎ በማርያም
ጣት /በትንሿ /ጣት ወደ ላይ ነው።

_ ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ~ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ
እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር
መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን።

_መሐል ጣት ወደ ላይ ~ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን
በቀለበት ጣት ወደ ታች ስንቆጥር ወደዚች አለም ለፍርድ
መምጣቱን፤ በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ስንወጣ ደግሞ
በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው።

_ _ _ _ _ _ _በእንተ _ _ _ _ _ _ _

_ በእንተ እግዝትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ ከትንሿ ጣት
ወደ ታች ይጀመርና በጠቋሚ ጣት ወደ ላይ ይፈጸማል
ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና
ከፍ ማለቷን የሚያሳይ ምሥጢር ነው።

_ብእንት ሲባል በትንሿ ጣት ወደ ታች የሚጀመር ራሷን ዝቅ
አድርጋ የትህትናዋ ምሳሌ ስለሆነ ነው ከላይ ወደ ታች
ሚጀምረው።

_ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም
የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል - የማት ወን 23:12

_ ደግሞ የበእንት ፍጻሜ ወደላይ የሚያልቀው ሚስጢሩ
እመቤታችን በመቃብር አልቆየችም ወደ ላይ አረገች ማለት ነው።

አቤቱ ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥አንተና የመቅደስህ ታቦት

_ መዝ 132:8

ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተክርስቲያን ማንኛውንም ነገር
ያለ ትርጉም አታደርግም።

እንኳን ለደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል በሰላም  አደረሳችሁ።
18/08/2022

እንኳን ለደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ  ባሕርን ተናገረው እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራትሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበርእ...
17/08/2022

እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው

እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት

ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር

እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር"

ልብ አድርጉ :-

ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል
ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል

ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው::

ይህንንም እናስታውስ

ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው::

ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :-

"ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 23 2013 ዓ ም
Translated from Mighty arrows publications
ሥዕል:- ቤተ አብ ዓለሙ

19 yamet sew yeblen
26/07/2022

19 yamet sew yeblen

Address

Bucharest

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቲዩብ / orthodox tewahdo tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category