MAALE PRESS

MAALE PRESS Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from MAALE PRESS, Legal, ማሌካ. . . ሌሞ-ጌንቶ, Ma'ale Adummim.

እንደዚህ ያምርብናል!!👏👏ተያይዘን ወደፊት እንሂድ!!
25/01/2026

እንደዚህ ያምርብናል!!👏👏

ተያይዘን ወደፊት እንሂድ!!

መልካም አዲስ ዓመት!
09/01/2026

መልካም አዲስ ዓመት!

እናመሰግናለን🙏 ወንድም ደቡብ ኣሪ ወረዳ🙏
09/01/2026

እናመሰግናለን🙏 ወንድም ደቡብ ኣሪ ወረዳ🙏

የደቡብ ኣሪ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ሀገሬ ጥላሁን የማሌ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የሆነውን "ዶኦማ" በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።
ታህሳስ 30/4/2018ዓ,ም
ጋዘር
የማሌ ብሔረሰብ የአድስ ዘመን መለወጫ በዓል የሆነውን "ዶኦማ" በዓል" ብስራት ለአንድነትና ለዕድገት” በሚል መሪ ቃል ለ12ኛ ጊዜ በአደባባይ በድምቀት መከበሩ ይታወቃል በመሆኑም መላውን የማሌ ብሔረሰብ በ2018 ዓ.ም ለሚከበረው አድስ የዘመን መለወጫ በዓል ለሆነው “ለዶኦማ” በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ስሉ ክብርት ወ/ሮ ሀገሬ ጥላሁን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

ይህ በዓል የማሌ ብሄረሰብ ዘመን መገለጫ፤ ሀገራዊ አንድነትን ይሰፍካሉ ከምንላቸው እሴቶች አንዱ ከመሆኑም ባሻገር ከ“ዶኦሞ” በዓል መገለጫዎች መካከል በተለይም ደግሞ "ሄሌሞ" የራሱ ያልሆነን ነገር የማይሻ፣ ስርቆትን የሚፀየፍ፣ ልዩነቶችን በሰከነ መንገድ ተወያይቶ የመፍታት ልምድ ያለው፣ የሐቀኝነት ማሳያ እና የዴሞክራሲ መገለጫነቱ ለአብነት ተጠቃሽ ነው።

"ዶኦማ" የመላው ማሌ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ማስጀመሪያ አሮጌው ዓመት ደግሞ የምሸኝበት እንዲሁም በአሮገው ዓመት በተለያዩ ሁኔታዎች ተጣልተው የነበሩ በመታረቅና ይቅር በመባባል አንድ የሚሆኑበት ፣ ለመጪዉ ትዉልድ ባህላዊ ትውፊቱን ፣ ተፈጥሯዊና ታርካዊ ቅርሶችን የሚያስተዋውቁበት ትልቅ በዓል ነው በተጨማሪም የብሔረሰቡን ማህበራዊ ፣ ባህላዊ ፣ ኢኮኖሚያአዊ ፣ አካላዊና መንፈሳዊ እሴቶችን ከፍ በማድረግና አጉልቶ በማሳየት የሚከበር በዓል ነዉ ብለዋል ክብርት ሀገሬ ጥላሁን።

በመጨረሻም በዓሉ የአንድነት ፣ የአብሮነት ፣ የደስታ ፣ የሠላምና የፍቅር በዓል እንዲሆን እመኛለሁ በማለት አፌ ጉባኤዋ የመልካም ምኞት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።

ዘገባው የደ/አ/ወ/መ/ኮ ነው።

09/01/2026
እንኳን አብሮ አደረሰን!
09/01/2026

እንኳን አብሮ አደረሰን!

የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ የማሌ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ "ዶኦሞ" በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፦

ታህሳስ፦ 30/2018 ዓ.ም (ኣዞመኮአ)

"የዶኦሞ ብስራት ለአንድነትና ለዕድገት!” በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለ12ኛ ዙር በድምቀት ለሚከበረው የማሌ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ “ዶኦሞ” ክብረ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ!

በዓሉ የአንድነት፣ የሰላም፤ የአብሮነት፤ የመተሳሰብ እና የወንድማማችነት ተምሳሌት በዓል በመሆኑ ሌሎች ወንድም እህት ህዝቦች ጋር በአብሮነትና በአንድነት፤ የእርስ በእርስ ትስስርን በሚያጠናክር እና የወንድማማችነት እሴቶችን በሚያጎለብት መልኩ የሚከበር በዓል ነዉ።

በዓሉን በአብሮነትና በአንድነት፤ የእርስ በእርስ ትስስርን በሚያጠናክር እና የወንድማማችነት እሴቶችን በሚያጎለብት መልኩ የሚከበር በመሆኑ ሁላችንም ናፍቀን የምናከብረው ታላቅ በዓላችን ነው።

"ዶኦሞ" የማሌ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት ማስጀመሪያ የአሮጌው መሸኛ፣ የመጪዉ ትዉልድ ባህላዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ ታርካዊ ቅርሶችን ማስተዋወቂያ እና የማሌ ብሔረሰብን ማህበራዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያአዊ፣ አካላዊና መንፈሳዊ እሴቶችን ከፍ ለማድረግ የሚከበር በዓል ነዉ ።

''ዶኦሞ'' መጪው ዘመን ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን በምድር ለሚዘራው ዘር፣ ለዕፅዋትና ለእንስሳት ሁሉ የተመቸና የተባረከ እንዲሆን "ካኣቲ" (የማህበረሰቡ ንጉስ) ምርቃትና ቡራኬ ይሰጣል፤ የዓመቱ የምርት ወቅት መጀመርንም ያበስራል።

ይህ በዓል የማሌ ብሄረሰብ መገለጫ፤ ሀገር በቀል ከምንላቸው እሴቶች አንዱ ከመሆኑም በላይ ከ“ዶኦሞ” በዓል መገለጫዎች መካከል በተለይም ደግሞ "ሄሌሞ" የራሱ ያልሆነን ነገር የማይሻ፣ ስርቆትን የሚፀየፍ፣ ልዩነቶችን በሰከነ መንገድ ተወያይቶ የመፍታት ልምድ ያለው፣ የሐቀኝነት ማሳያ እና የዴሞክራሲ መገለጫነቱ ለአብነት ተጠቃሽ ነው።

በዚህ በዓል ተገኝቶ መታደም ትልቅ እድል ነው!

ይሁን እንጅ ባለፉት 11 ዓመታት በዓደባባይ ይከበር የነበረው ይህ ድንቅ በዓል "ዶኦሞ" ዘንድሮ በአካባባቢው የተከሰተውን የማርበርግ በሽታ ወረርሽኝ መከላከልን ከግምት በማስገባት በዓሉ በፓናል ውይይቶች እና ባህላዊ ዝግጅቶች በድምቀት እንደሚከበር በወረዳው አስተዳደር ቀድሞ ተገልጿል።

ይህ የሆነው የሚገጥመንን ማንኛውም ፈተና በፅናትና በትብብር እንደምናልፍ ሁሉ በዓሉን ስናከብር ወቅታዊና አላፊ ከሆነው " የማርበርግ ቫይረስ በሽታ" ራሳችንንና ወገኖቻችንን ለመጠበቅ ቅድሚያ ተሰጥቶ ስለሆነ ፤ በዓሉን በየትኛውም መንገድ ስናከብር የግልና የጋራ ጥንቃቄ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ እኔም መልዕክቴን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ።

በድጋሚ ውድ የማሌ ህዝብ እንኳን ለ2018 "ዶኦሞ" የዘመን መለወጫ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን! አደረሳችሁ ማለት እወዳለሁ!!!

ዘመኑ የሰላም የጤናና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ! እንዲሆንልንም እመኛለሁ !

‎ መልካም አዲስ አመት "ዶኦሞ"
‎ አቶ ማዕከል ማሊኮ
‎ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

እንኳን አብሮ አደረሰን! ዶኦሞ
09/01/2026

እንኳን አብሮ አደረሰን!
ዶኦሞ

እንኳን አብሮ አደረሰን! ክቡርነትዎ🙏
09/01/2026

እንኳን አብሮ አደረሰን!
ክቡርነትዎ🙏

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለማሌ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ "ዶኦሞ" በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ማዳ ኮሽ ሄልሰኔ!
ፂሎ ማሌ ኮሽ ሄልሰኔ!

እንኳን ለ"ዶኦሞ" የማሌ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ!

"ዶኦሞ" ከክልላችን ብዝኃ ህዝቦች መካከል አንዱ የሆነው የማሌ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የዘመን መለወጫ በዓል፤ በወርሃ ጥር መጀመሪያ በአደባባይ በጋራ የሚያከብሩት የአብሮነት በዓል ነው፡፡

ባህላዊ ሥርዓቱንና ትውፊቱን ጠብቆ የሚከበረው በዓሉ፤ አዲሱ ዓመት የሰላም፤ የጤና፤ የጥጋብ፤ የአንድነትና የፍቅር ይሆን ዘንድ ለፈጣሪ "ኦፃ" (ፀሎት) በማድረስ የሚከበር ደማቅ በዓል ነው፡፡

ዶኦሞ የማህበረሰቡ ባህላዊ መሪ 'ካኣቲ' ህዝቡ ተግቶ እንዲሰራ፤ ሀብት እንዲያፈራና ለበልግ እርሻ እንዲዘጋጅ የምርት ወቅት መጀመርን የማብሰሪያ አዋጅ የሚያውጅበት፤ ማህበረሰቡ ጥሮ ግሮ አካባቢውን በመቀየር ከድህነት እንዲወጣ የሚያነሳሳ እና ጠንካራ የሥራ ባህልን የሚያሰርጽ ድንቅ እሴት ያለው በዓል ነው፡፡

የማሌ ህዝብ የማንነት መገለጫ የሆኑ የሰላም፤ የአብሮነት እና የመደጋገፍ እሴቶች ያሉት ዶኦሞን፤ ከአጎራባች ህዝቦች ጋር የእርስ በርስ ትስስርንና ትብብርን በሚያጠናክር እና ወንድማማችነትን በሚያጎለብት መልኩ በጋራ ያከብራሉ።

የዘንድሮውን በዓል በአካባቢው ከተከሰተው የማርበርግ በሽታ ምክንያት በርከት ያለ ሰዉ መገኘት አልቻልንም።
ስለዚህ በበዓሉ ዝግጅት የምትሳተፉ የበሽታው ስርጭት ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር በመደረግ ላይ ያሉ ጥረቶችን በሚያግዝ መልኩ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የፕሮግራሙ ተሳታፊ እንድትሆኑ አደራ ለማለት እፈልጋለሁ።

በዓሉ የሰላም፤ የፍቅር፤ የአንድነትና የአብሮነት እንዲሆንልን እመኛለሁ!!

ፈጣሪ ሀገራችንንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ባለሀብት አብዱልናስርን ከልብ እናመሰግናለን🙏
06/01/2026

ባለሀብት አብዱልናስርን ከልብ እናመሰግናለን🙏

05/01/2026

Address

ማሌካ. . . ሌሞ-ጌንቶ
Ma'ale Adummim

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MAALE PRESS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category