Israel Tibebu

Directions

Israel Tibebu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Israel Tibebu, Legal, Tepi.

ሰበር 💪💪ከባዛር እና ከባዛር ጋር ተያያዥ ከሆኑ ገቢወች ብቻ 19,000,000 ደርሰናል 🙏🙏🙏ቴፒ አስፓልት ሆና ማየት ህልሜ ነው ያለ ሁሉ ሕልሙን እዉን ለማድረግ በጥረት ላይ ነው ::ይህ የ...
06/02/2026

ሰበር 💪💪ከባዛር እና ከባዛር ጋር ተያያዥ ከሆኑ ገቢወች ብቻ 19,000,000 ደርሰናል 🙏🙏🙏ቴፒ አስፓልት ሆና ማየት ህልሜ ነው ያለ ሁሉ ሕልሙን እዉን ለማድረግ በጥረት ላይ ነው ::ይህ የሁላችንም ጉጉት ነው ::የናፈቅነው ጊዜ እየመጣ ይመስላል :ህዝባችን እንዴት ደሥሥሥ...ይላል ሁሉንም ነገሮች ተጋፍጦ ለትዉልድ የሚሻገር አሻራዉን ለማኖር ሌት ተቀን ይታትራል ፈጣሪ ከክፉ ይጠብቅልን 🤲🤲በህብረት ጉዞ ወደ አስፓልት 🙏🙏ደስ ብሎኛል 👏👏👏

የልማት አርበኞች ትብብር ጀምሯል!​አቶ ነስረዲን አባፎጊ አባገሮ ለቴፒ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት ግንባታ በነጋዴዎች ላይ የተጣለባቸውን የልማት ኮታ ቀድመው በመክፈል የ50,000 ብር ግ...
23/01/2026

የልማት አርበኞች ትብብር ጀምሯል!

​አቶ ነስረዲን አባፎጊ አባገሮ ለቴፒ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት ግንባታ በነጋዴዎች ላይ የተጣለባቸውን የልማት ኮታ ቀድመው በመክፈል የ50,000 ብር ግዙፍ ድጋፍ አድርገዋል።ይህ ተግባር እውነተኛ የልማት
አርበኝነትና ለከተማችን ያለን ተቆርቋሪነት ማሳያ ነው።
​የቴፒን ብሩህ ተስፋ እውን ለማድረግ ከገንዘብ ባሻገር በጉልበት፣ በእውቀትና በተለያዩ አማራጮች ተሳትፎ ማድረግ ያስፈልጋል።

የቴፒ ነጋዴዎችና የልማት ወዳጆች የወንድማችሁን ፈለግ ተከትለን የተጣለብንን ኮታ ቀድመን በመክፈልና ባለን አቅም ሁሉ በመሳተፍ ለከተማችን ታላቅነት አሻራችንን እናሳርፍ !

​የቴፒ እድገት በሁላችንም ትብብር ይረጋገጣል!
​

ደስ ብሎናል እጅግ መሳጭ ዉይይት :--አቶ ሸሎ አዴሎ የቴፒ ከተማ የመንግስት ተጠሪ እና ሀገር ወዳድ የቴፒ ከተማ ነጋዴወች ወስነዋለን አስፓልቱ ያለጥርጥር ይሰራል ብለዋል 🙏🙏🙏"በህብረት እን...
23/01/2026

ደስ ብሎናል እጅግ መሳጭ ዉይይት :--አቶ ሸሎ አዴሎ የቴፒ ከተማ የመንግስት ተጠሪ እና ሀገር ወዳድ የቴፒ ከተማ ነጋዴወች ወስነዋለን አስፓልቱ ያለጥርጥር ይሰራል ብለዋል 🙏🙏🙏"በህብረት እንችላለን "ጊዜው አሁን ነው 🙏ለቴፒ የምንሰስተው የለም 💪💪💪💪

ተገኝቷል
15/01/2026

ተገኝቷል

አስቸኳይ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ​የነጃሽ አባመጫ ልጅ 4 አመትልጅ ዛሬ ስምንት ሰዓት ላይ ከቤት እንደወጣ እስካሁን አልተመለሰም። ካያችሁ ወይም ያለበትንየምታውቁ በስልክ ቁጥርፈላጊ አባት ነጃሽ...
15/01/2026

አስቸኳይ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ
​የነጃሽ አባመጫ ልጅ
4 አመትልጅ ዛሬ ስምንት ሰዓት ላይ ከቤት እንደወጣ እስካሁን አልተመለሰም። ካያችሁ ወይም ያለበትንየምታውቁ በስልክ ቁጥር
ፈላጊ አባት ነጃሽ አባ መጫ
+251911111066 ደውላችሁ ብታሳውቁን ወረታ ከፋይ ነን ይላሉ ፈላጊ አባት ነጃሽ አባመጫ
።
​እባክዎ ለሌሎች በማጋራት (Share በማድረግ) ይተባበሩን።

‎    ‎ይህ ለቴፒ ከተማ የትንሳኤ አዋጅ ነው ።‎ለከተማችን የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ የሚውል ገቢ ለማሰባሰብ የተዘጋጀ ታላቅ የልማት ንቅናቄ ከተጀመረ ሰነባብቷል።በመሆኑም የ...
13/01/2026

‎
‎ይህ ለቴፒ ከተማ የትንሳኤ አዋጅ ነው ።
‎ለከተማችን የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ የሚውል ገቢ ለማሰባሰብ የተዘጋጀ ታላቅ የልማት ንቅናቄ ከተጀመረ ሰነባብቷል።በመሆኑም የንግድ ትርዒትና ባዛሩ በቀን 15/05/2018 ዓ ም በይፋ ይጀመራል!

‎በከተማችን ​ጭቃና አቧራ ያበቃለታል ።ልጆቿ ቀፎው እንደተነካ ንብ ለልማት የሚነሱበት ጊዜው አሁን ነው ።

‎​ይህ የንግድ ትርኢትና ባዛር ብቻ ሳይሆን የቴፒን ታሪክ የመቀየር ታሪካዊ ዘመቻ ነው።
‎​ሁሉም አይኖች ወደ አስፓልት ስራው አተኩሯል።ነገ ልጆቻችን በሚያምር አስፓልትእና ውብና ማራኪ በሆነች ከተማ እንዲኖሩ በታሪካዊው የንግድ ትርዕትና ባዛር ላይ ተገኝታችሁ ህብረታችንን እናሳይ።

‎ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ።
‎
‎ቦታ፦ቴፒ ከተማ ትልቁ አዳራሽ ግቢ
‎በህብረት ሁሉንም እንችላለን !

በህብረት እንችላለን የሚለው የልማት ድምፅ ከተማችን ማሰማት ከጀመረች ጀምሮ ሁሉም ተወላጅ፣ ወዳጅና መላው ኢትዮጵያዊ ከያለበት ለጥሪዋ ምላሽ መስጠት ጀምሯል በዚህም ለልማቱ የሚያስፈልገው ጥሪ...
05/01/2026

በህብረት እንችላለን የሚለው የልማት ድምፅ ከተማችን ማሰማት ከጀመረች ጀምሮ ሁሉም ተወላጅ፣ ወዳጅና መላው ኢትዮጵያዊ ከያለበት ለጥሪዋ ምላሽ መስጠት ጀምሯል በዚህም ለልማቱ የሚያስፈልገው ጥሪት ለመሰብሰብና ለማከማቸት የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ደግፏል።

ከተማችንን ወደ ቀድሞ ገናናነቷ ለመመለስና የመንገድ መሰረተ ልማቷን በራስ አቅም ለመሙላት በተለያየ መንገድ የገቢ ማሰባሰቢያ በመቀየስ ከተማ አስተዳደሩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ማሳካት ተችሏል።

ተያይዞም ከጥር አጋማሽ ጀምሮ በከተማችን ለሚካሄደው ባዛርና የንግድ ትርዒት ቅድመ ዝግጅትን የማጠናቀቅና ይህንንም ፕሮግራም ከማስኬድ ጎን ለጎን በከተማ ውስጥ በሚደረጉ የአገልግሎትና የንግድ ልውውጦች ማለትም በመጠጥ፣ በሉካንዳና ጫት ላይ ለፕሮጀክቱ የሚገባ የታሪፍ ማሻሻያ በማድረግ በአጭር ቀናት ውስጥ ከ3ሚሊዮን 1መቶ 20ሺህ ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።

በቀጣይም ይህን የገቢ አቅም በተለያየ መንገድ በማስፋትና በማጠናከር የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱን እውን የሚሆንበትና የከተማችን ብልፅግናና ቀደምት የስልጣኔ መናገሻ መሆኗ በታሪክ ብቻ ሳይሆን እራሷ አድጋ መሰረቷ ልማቷን በራስ አቅም አሟልታ ለሀገር ኢኮኖሚ መከታ መሆኗን ምታስመሰክርበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም።

አዎ! በህብረት ሁሉን እንችላለን💪💪

በህብረት እንችላለን !ወንድማችን  ዘላለም ብርቁ  በቴፒ ከተማ  አስተዳደር  በህብረተሰብ ተሳትፎ ለሚገነባው  የውሰሰጥ ለውስጥ አስፓልት  መንገድ ስራ  አምስት ሺ ( #5000.0)ብር ድጋፍ...
02/01/2026

በህብረት እንችላለን !
ወንድማችን ዘላለም ብርቁ በቴፒ ከተማ አስተዳደር በህብረተሰብ ተሳትፎ ለሚገነባው የውሰሰጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ስራ አምስት ሺ ( #5000.0)ብር ድጋፍ አድርጓል።

እናመሰግናለን !
ይቀጥላል ...

በህብረት እንችላለን!!!

300ሺህ ብር ተጨማሪ ከቴፒ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም መምህራንና ባለሙያዎች ለከተማችን🙏የቴፒ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ማዕከል በበላፈው ቃል የገቡት 700ሺህ እንዳለ ሁኖ በውይይት ...
30/12/2025

300ሺህ ብር ተጨማሪ ከቴፒ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም መምህራንና ባለሙያዎች ለከተማችን🙏

የቴፒ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ማዕከል በበላፈው ቃል የገቡት 700ሺህ እንዳለ ሁኖ በውይይት የፕሮጀክቱን ለከተማዋ አስፈላጊነትና የእነርሱ ተሳትፎ እስከምን በሚለው ጉዳይ ላይ ከመግባባት በመድረስ በተጨማሪ 300ሺህ ብር ለውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ ለመስጠት ወስነዋል።

በቀጣይም ከተማዋን ዘመናዊና ስሉጥ እንዲሁም ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተቋሙ ትውልድ ከመቅረፅ አንስቶ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ተግባራዊ የሚደረግ የምርምር ውጤትን በመስራትና በሌሎች አከባቢ የምንመለከታቸውን ፈጠራዎች ወደአከባቢያችን በማምጣት፣ በመስራት የበኩል ሚና እንደሚጫወት ገልጿል።

በህብረት እንችላለን!!!

በህብረት ሁሉን እንችላለን!     በህብረት ሁሉን እንችላለን በማለት እድሜ ጠገቧን ቴፒ ከተማን ተመራጭ ከተማ ለማድረግ ለተነሳነው  #ቻሌንጅ የቀድሞ የሸካ ዞን ፖሊስ አዛዥ  አሁን የክልል ...
29/12/2025

በህብረት ሁሉን እንችላለን!

በህብረት ሁሉን እንችላለን በማለት እድሜ ጠገቧን ቴፒ ከተማን ተመራጭ ከተማ ለማድረግ ለተነሳነው #ቻሌንጅ የቀድሞ የሸካ ዞን ፖሊስ አዛዥ አሁን የክልል ፖሊስ ሰልጠና ክፍል ሀላፊ ረ/ኮሚሸነር ፋሩቅ በድሩ ለሚወዳት ቴፒ ከተማ ለሚሰራው የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ከደሞዙ በተጨማሪ የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ 3,000ብር ለግሷል። ወንድማችን በወጣው ይተካ 👨‍🍳👨‍🍳👨‍🍳👨‍🍳👨‍🍳👨‍🍳

ይቀጥላል ..

በህብረት እንችላለን!!!

Address

Tepi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Israel Tibebu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category