BLOOD GROUP 0 Negative

BLOOD GROUP 0 Negative Public service

22/08/2026
ሰሞኑን ሰው ለማስታመም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተገኘሁ ። የሚታየው ነገር ሁሉ ህመም ላይ ይጥላል ። የኤምአርአይ ፣ ሲቲስካን ፣ ኤክስሬይ ፣ አልትራሳውንድ ፣ የኩላሊት እጥበት ፣ የጨረር ...
22/08/2026

ሰሞኑን ሰው ለማስታመም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተገኘሁ ። የሚታየው ነገር ሁሉ ህመም ላይ ይጥላል ።
የኤምአርአይ ፣ ሲቲስካን ፣ ኤክስሬይ ፣ አልትራሳውንድ ፣ የኩላሊት እጥበት ፣ የጨረር ህክምና መስጫ መሳሪያዎች በአንድ ጊዜ ብዙ ሺ ታካሚዎችን ስለሚያስተናግዱ በተለያየ ጊዜ ይበላሻሉ ።

በፅኑ ህሙማን ክፍል ተኝተው የሚታከሙ ታካሚዎች እነዚህን ምርመራዎች ለማድረግ ለሰአታት ወረፋ ይጠብቃሉ።

በመኝታ ክፍል ህንፃ ፡ ታካሚዎች ፣ ሀኪሞች ፣ አስታማሚዎች እንዲመላለሱበት ከተሰሩት ሊፍቶች ውስጥ የሚሰራው አንድ ብቻ ነው። እርሱም ለሊፍት አንቀሳቃሹ ሰው ከውስጥ በቀዳዳ የፎቅ ቁጥር በጩኸት እየተነገረው ነው የሚቆመው።

ለህክምና አገልግሎት አሰጣጥ አያመችም ። ከፅኑ ታካሚዎች ጋር አብረው የሚንቀሳቀሱ የመተንፈሻ መሳሪዎችንና የመሳሰሉትን ለመጫን ያዳግታል ። ቢበላሽ በሰከንዶች መዘግየት ምክንያት ህይወት ሊጠፋ ይችላል።

ዊልቸር ለማግኘት ከፎቅ ፎቅ መመላለስና ሌላ ታማሚ እስኪለቅ ለደቂቃዎች መጠበቅ ግድ ይላል ።

መድኃኒት ከቤቱ መድኃኒት ቤት ማግኘት ሱሚ ነው ፣ በብዙ ሺ ብሮች ከአስታማሚ ኪስ እየወጣ የሚገዛው ከውጪ ነው ። የእጅና የፊት መሸፈኛ ጭንብሎችን ጨምሮ ከፕላስተር አቅም ሆስፒታሉ አያቀርብም ፤ ለመግዛት ወደ ውጪ ሩጫ ነው ።

የሚታዘዙ መድኃኒቶችን ለመግዛት አንድ አስታማሚ ብቻ ያለው ሰው ገንዘቡ ቢኖረው እንኳን ውጪ ሄዶ እስኪመለስ ታካሚው አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል ።

ገንዘብ የሌለው ሰው ከሌሎች አስታማሚዎች በሚገኝ የገንዘብ እርዳታና ለእነርሱ ታማሚ በተገዛ ትርፍ መድኃኒት ያዘግማል ። ቅሪታቸውን አሟጠው መኖሪያቸውን ሸጠው የሚያሳክሙም አልጠፉም ። አለፉ ሲልም ጥለው የሚጠፉ አስታማሚዎች አሉ።

ሆስፒታሉ የማይሰጣቸው የደም ምርመራ እና የማሽን ህክምናዎችም አሉ ።

ጤና መድህን ለሌለው ሰው የአልጋ እና የቀዶ ጥገና አገልግሎት ክፍያ እንኳን ከአስርና መቶብሮች ወደ ብዙ ሺ ብሮች ተመንድጓል ።

በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ግን የህክምና ባለሙያዎቹ ወገናቸውን ለማገልገል የሚያደርጉት ጥረት የሚመሰገን ነው ።

ይህንን ችግር እያሰብኩ መስኮት ዳር ቆሜ መቆዘም ያዝኩ ። ካለሁበት ጥቂት ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኘው ግዮን ሆቴል ውስጥ ብዙ ቢሊዮን ብሮች ወጥቶበት የተሰራው ሰው ሰራሽ የውሃ ፏፏቴ ሽቅብ እየተምዘገዘገ ቁልቁል እየወረደ በሙዚቃ ስልት በቀለማት አሸብርቆ ይደንሳል ።

ከዚህ ሀሳብ ሽንቴ ቀሰቀሰኝና ወደ መፀዳጃ ቤት አመራሁ ። ለመፀዳጃ ቤቱ
የተቀመጠው በርሜል ውሃ የለውም ። ከቧንቧ ውሃ ማግኘት የማይታሰብ ነው ።ግዴታ ለመጠቀም እሽግ ውሃ ይዤ መመለስ ነበረብኝ ።

03/08/2026
የህሊና ወ*ንጀል ነው። ይኼ ምግብ ሳይሆን የሕይወት አድን መድሐኒት ነው። ሰዎች ሳያዉቁ ገዝተው ሊመገቡ ይችላሉ። አንዳንዴም ቤተሰብ ለታመመችዋ ልጅ የታዘዘውን ሸጠው ለቤተሰብ ቀለብ የሚገዙ ...
03/08/2026

የህሊና ወ*ንጀል ነው።

ይኼ ምግብ ሳይሆን የሕይወት አድን መድሐኒት ነው። ሰዎች ሳያዉቁ ገዝተው ሊመገቡ ይችላሉ። አንዳንዴም ቤተሰብ ለታመመችዋ ልጅ የታዘዘውን ሸጠው ለቤተሰብ ቀለብ የሚገዙ አሉ። በሞ*ት አፋፍ ላይ ካለ ህፃን ነጥቆ እንደመብላት ነው።

በተለይ ክብደት ለመጨመር እየተባለ ለቅንጦት ከተራበች ነፍስ እየቀሙ እንደሆነ ይወቁ። ለጤናማ ሰው ምናልባትም ለጤና አ*ደገኛ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም ምግብ ሳይሆን የምግብ እጥረት መድሐኒት ስለሆነ ነው። አይግዙ፤ አይሽጡ። ለታመሙት ብቻ እናውለው።

ከልብ እናመሰግናለን ❤🙏
30/07/2026

ከልብ እናመሰግናለን ❤🙏

Address

S**o
S**o
0916ADMAS

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BLOOD GROUP 0 Negative posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to BLOOD GROUP 0 Negative:

Shortcuts

Share

Category