Tilahun's View

Tilahun's View Lawyer

ለክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ አቀባበል ተደረገላቸው። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ለተመደቡት ክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በኮሚሽኑ የማኔጅመንት አባላት እና መኮንኖች...
05/04/2025

ለክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ አቀባበል ተደረገላቸው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ለተመደቡት ክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በኮሚሽኑ የማኔጅመንት አባላት እና መኮንኖች የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የሰው ኃብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ የተቋሙን አመራሮች እና አባላትን በመወከል አዲስ የተመደቡትን ክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴን እንኳን ደህና መጡ ብለዉ በከፍተኛ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ለህብረተሰቡ ሰላም በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

ክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በበኩላቸው ፖሊሳዊ ብቃት እና ስብዕናን የተላበሰ የተሰጠውን ተልዕኮ የሚወጣ ዘመናዊ ፖሊስ እና አደረጃጀት በመፍጠር የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በጋራ እና በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል።

አንድ ድሃ ልጅ ከሀብታሞች መንደር ከሚገኝ ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ላይ ሆኖ የተራረፈ ምግብ ይፈልግ ነበር።ከመንደሩ የሚወጣ ከድሃው ልጅ ጋር በእድሜ ተቀራራቢ የሆነ የሀብታም ልጅ ወደ ገንዳ...
21/03/2025

አንድ ድሃ ልጅ ከሀብታሞች መንደር ከሚገኝ ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ላይ ሆኖ የተራረፈ ምግብ ይፈልግ ነበር።

ከመንደሩ የሚወጣ ከድሃው ልጅ ጋር በእድሜ ተቀራራቢ የሆነ የሀብታም ልጅ ወደ ገንዳው ጠጋ ብሎ ድሃውን ልጅ እንዲህ አለው።

" እዚህ ገንዳ ውስጥ ያለው ምግብ ጀርም እና ባክቴርያ አለው ምግቡን ከበላህ ትታመምና ትሞታለህ"

ድሃውም ልጅ " ምግብ ካልበላው በረሃብ እሞታለው ልክ እንደ በሽታ ረሃብም ይገድላል" አለው።
የሀብታሙ ልጅም "ቤተሰቦችህስ? በማለት ጠየቀው።

" አባቴን አላውቀውም እናቴ ግን ምግብ ስትፈልግ ጎርፍ ወሰዷት ሞተች" በማለት መለሰለት።

የሀብታሙ ልጅ በጣም ልብ አዘነና ጠብቀኝ ብሎት ከቤታቸው ትኩስ ሾርባ፣ዳቦ፣ ወተት ሌሎች የታሸጉ ምግቦችን ይዞ በመምጣት ለድሃው ልጅ ሰጠው።

ድሃው ልጅ በጣም ተገረመና ተደነቀ እንደዚህ አይነት ምግብ በህይወቱ በልቶ አያውቅም ህልም መሰለው የሀብታሙን ልጅ ለማመስገን ቀና ሲል ልጁ እየሮጠ ርቆ ሄዶል።

በሚቀጥለው ቀን ይህ የሃብታም ልጅ የጥርስ ብሩሽ፣ ሳሙና መጫወቻ እና ምግብ ይዞለት መጣና ሰጠው።

ድሃው ልጅ ጭንቅላቱን ወደ ታች በመድፋት አለቀሰ እንደዚህ አይነት ነገሮች ይኖረኛል ብሎ አንድ ቀን እንኳን አስቦ አያውቅም ነበረ ልጁንም አመሰገነው።

በሌላ ቀን ይህ የሀብታም ልጅ ሱሪ፣ጫማ፣ካልሲና ብርድ ልብስ ለድሃው ልጅ ይዞለት መጣ።
አንድ ቀን ወደ ሃብታሞቹ መንደር በመሄድ ልጁን ሊያየው አልቻለም፤ ትንሽ ጠብቆ ሲያጣው ከቤተሰቦቹ ጋር የሆነ ቦታ ሄዶ ይሆናል ብሎ አሰበና ቢጠብቀው ስላልመጣ ምን ሆኖ ነው ብሎ አሰበና ተጨነቀ።

ድሃው ልጅ ተስፋ ሳይቆርጥ በሌላ ቀንም ልጁን ብዙ ሰዓት ጠብቆት ሊሄድ ሲል አንድ ሰው ወደ እሱ በመኪና መጣና በባግ ብዙ ምግቦችን ከመኪና ውስጥ አወጣና"ይህን ትንሹ ልጄ ነው የሰጠህ" በማለት ሲሰጠው ሰውየው የልጁ አባት እንደሆነ አወቀ።

ድሃው ልጅ የልጁን አባት "ልጅህ የትነው?" ብሎ ጠየቀው

አባቱም "ወድቆ በጣም ታሞ ሆስፒታል ተኝቷል" አለው።

ድሃውም ልጅ ሆስፒታል ሄዶ ደጉን የሃብታም ልጅ ጠየቀው።

ሆስፒታል የተኛው ልጅ ገና ልጁን እንዳየው "የላኩት ምግብ ደረሰህ? ዶክተሮቹም ስለ እኔ ጥሩ ነገር አያወሩም እኔም በጣም አሞኞል!" አለው።

ድሃው ልጅ እንባው በአይኑ እየሞላ "እንዲ አሞህ አልጋ ላይ ተኝተህ እንኳን ደግ ነህ"አለው።

የሃብታሙ ልጅም በደከመ ድምፅ "በድጋሚ ካልተያየን እና ካልተገናኘን ስለእኔ ምን ታስታውሳለህ?"በማለት ድሃውን ልጅ ጠየቀው።
ድሃውም ልጅ እንድህ አለው።

"ያንን ዘመናዊ ፣ትልቁ ቪላ ቤታችሁንና ውድ መኪኖቻችሁን አላስታውስም! ሃብታችሁንና የቅንጦት ኑሮቹሁን ፈፅሞ ትዝ አይለኝም! ደግነትህ ፣ቸርነትህና ለእኔ ያደረክልኝን ነገር ሁሌም አስታውሳለሁ፤ ከትንሹ ልቤ ተፅፎ ይኖራል።

ያደረክልኝን በጎና ጥሩ ነገር በህይወት እስካለሁ ድረስ ለዘላለም በአይምሮዬ ተስሎ ይኖራል!"አለው።

የሀብታሙ ልጅም ፈገግ በማለት ህይወቱ አለፈች።

18/09/2024

እግ/ር ይመስገን

18/09/2024

የክብር ሽኝት እና ሥርዓተ ቀብር 💔

| የጋራድ ሀንሳር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ፣ ሐሙስ - መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት በብርሐናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር እንደሚፈጸም በድጋሚ አሳውቀዋል።

በተያያዘ ዜና
በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ነገ፣ ሐሙስ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ የለቅሶ እና ሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል።

መላው የዞኑ ነዋሪ ሕዝብ በተገለፀው ሰዓት እና ቦታ በመገኘት በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሀዘን እንዲገልጽ ጥሪ ቀርቧል።

ነፍስ ይማር !

😭 ቤተሰቦቻቸው 💔

20/07/2024

ሰማዩም ምድርም የእኛ ነው።ግን ሰማይ የእኛ ነው።

20/07/2024

ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ቢጠፋ ጥሩ ነው?

20/07/2024

ሰበር ዜና

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በመጪው ኅዳር ወር ከሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ራሳቸውን ለማግለል ተስማምተዋል!

13/09/2023

አድሱ ዓመት የሠላምና የስኬት እንዲሁም መገፋፋት የለለበት የመቻቻል ዓመት ይሁንልን!!
መልካም አድስ ዓመት 2016

የርዕሰ መስተዳድር ዋና መቀመጫ የሆነችው ውቢቷ ወላይታ ሶዶ ከተማ በነገው ዕለት እንግዶቿን ትቀበላለች ወላይታ ሶዶ፤ ነሓሴ 22/2015 ዓ/ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሥራ ...
29/08/2023

የርዕሰ መስተዳድር ዋና መቀመጫ የሆነችው ውቢቷ ወላይታ ሶዶ ከተማ በነገው ዕለት እንግዶቿን ትቀበላለች

ወላይታ ሶዶ፤ ነሓሴ 22/2015 ዓ/ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሥራ ማስጀመሪያ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ-ግብር በርዕሰ መስተዳድሩ ዋና መቀመጫ ከተማ በሆነችው ዉቢቷ ወላይታ ሶዶ በነገው ዕለት ይካሄዳል።

የርዕሰ መስተዳድር ዋና መቀመጫ ከተማ የሆነችው ወላይታ ሶዶም በነገው ዕለት እንግዶቿን ለመቀበል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቅቃ ሽር-ጉድ እያለችም ነው።

በእንግዳ አቀባበል የዳበረና ቱባ ባህል ያለው የወላይታ ህዝብ ወደ ዉቢቷ ወላይታ ሶዶ ከተማ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል በደስታ እየተጠባበቀም ይገኛል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአስተዳደርና የፖለቲካ ማዕከል ሆና መመረጧ የሚታወስ ነው። ለዚህም ዞኑ አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት በማጠናቀቅ እንግዶችን በነገው ዕለት በደማቅ ሁኔታ ይቀበላል።

ከእንግዶች አቀባበል በተጨማሪ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሥራ ማስጀመሪያ ብስረታ መርሃ-ግብርም እንደሚካሄድ ታውቋል።

በዚህም ከፌደራል፣ ከክልል እና ከተለያዩ ዞኖች የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ነጋዴዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

17/11/2021

The law is what ever a court says the law is.

Address

S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tilahun's View posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tilahun's View:

Share

Category