JAZI- About law

JAZI- About law This page provides detailed information about Ethiopian law and international law issues and practices.

19/08/2022

"... No one break law but break himself against the law"

The Stranger from Albert Camus's novel "The Stranger" ("L'Étranger")

ስለ ዉርስ ይርጋ  በ ሳሙኤል ግርማ 👇✍️!
09/07/2022

ስለ ዉርስ ይርጋ በ ሳሙኤል ግርማ 👇✍️!

የውርስ ጉዳይን የተመለከቱ የይርጋ ገደቦች ከተመረጡ የሰበር ውሳኔዎች ጋር በማጠቃስ የቀረበ!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

1) ኑዛዜን ለመቃወም የተቀመጠ ጊዜ ገደብ

ኑዛዜ ፈራሽ ነው የሚል ክስ የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በቁጥር 973 ላይ የተመለከተው ተፈጻሚ ሚሆነው ኑዛዜ ፈራሽ ነው የሚለውን ክስ ኑዛዜው ሲነገር በነበሩ ሰዎች የቀረበ እንደሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973/1/ ላይ እንደተገለጸው “ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ወይም የተወከሉ ሰዎች ኑዛዜው አይጸናም ወይም አንዱ በኑዛዜው የተነገረው ቃል አይጸናም በማለት ክስ ለማቅረብ ያላቸውን ሀሳብ መግለጫ ወይም ስለ ክፍያው በሂሳብ አጣሪው የቀረበውን የድልድል አመዳደብ ሀሳብ ለመቃወም ኑዛዜው ከተነበበት አንስቶ በሚቆጠር የአስራ አምስት ቀን ጊዜ አላቸው”፡፡

በሌላ መልኩ ደግሞ ኑዛዜው ሲነበብ ያልነበሩ ሰዎች መቃወሚያቸውን መቼ ሊቀርቡ ይችላሉ ለሚለው በፍ/ሕ/ቁ 974/1/ እና 2 ላይ የተገለጸ ሲሆን በዚህም መሰረት “ በኑዛዜ ንባብ ሥነ-ሥርዓት ላልነበሩ ወይም በኑዛዜው ንባብ ሥነ-ሥርዓት በወኪልነት ላልሰሙ ሰዎች እንዲሁም ኑዛዜው በሌሉበት የተነበበ እንደሆነ ከዚህ በላይ የተገለጸው የጊዜ ገደብ ለመቁጠር መነሻ የሚሆነው ሥለ ክፍያው ድልድልና አመዳደብ ሀሳቡን ከተነገራቸው ቀን አንስቶ ነው”፡፡

በፍ/በ/ህ/ቁ 973/2/ ላይ በተገለጸው መሰረት ኑዛዜ ከፈሰሰበት ጊዜ ከአምስት ዓመት በኋላ ወይም ኑዛዜ የሌለ እንደሆነ ሟች ከሞተ ከአምስት ዓመት በኋላ ስለ ኑዛዜው መጽናትና ስለክፍያው አመዳደብ አጣሪው ያቀረበውን የድልድል ሀሳብ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን መቃወሚያ ሊቀርብበት አይችልም፡፡

ከዚህ በላይ ከተገለጹት የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በተያያዘ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 82585 በቅጽ 15 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ የሰጠ ሲሆን በትርጓሜውም “በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ድንጋጌዎች አቤቱታ አቅርቢው ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ ወይም የተወከለ የመሆን አለመሆን መስፈርት መሰረት በማድረግ ይርጋው መቁጠር የሚጀምርበትን ጊዜ እና ፍጹም የሆነ የይርጋ ጊዜ በቁጥር 974/2/ ከመደንገጋቸው በስተቀር ሁለቱም ድንጋጌዎች ኑዛዜው ፈራሽ ነው የሚል ክስ የሚቀርብበትን ስርዓት የሚደነግጉ በመሆቸው ተያያዥነት አላቸው በማለት ኑዛዜ መኖሩን ማወቅ እና የኑዛዜውን ሙሉ ይዘት ማወቅ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው ሲል በፍ/ብ/ህ/ቁ 973/1/ የተመለከተው የ15 ቀን ጊዜ ገደብ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ ሳይሆን የመግለጫ ማቅረቢያ ጊዜ ነው፡፡ በመሆኑም ስለ ኑዛዜ መኖር እንጂ ስለድልድሉ የማያውቅ ወራሽ መግለጫ የማቅረብ ግዴታ ስለማይኖርበት ጊዜው መቁጠር የሚጀምረው በኑዛዜው የተደረገውን ድልድል ካወቁበት ቀን ጀምሮ ነው” በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በሟች የተደረገ ኑዛዜ ከውርስ የነቀለኝ በመሆኑ ሊፍርስ ይገባል በማለት ኑዛዜው ሲነበብ በነበረ አመልካች የሚቀርብ የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 መሰረት በተገለጠው የጊዜ ገደብ ነው ወይስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ነው? የሚለው አከራካሪ ጉዳይ በመሆኑ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 152134 በቅጽ 23 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ በውሳኔውም መሰረት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 ስለ ኑዛዜ መነበብ እንዲሁም ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ሰዎች ኑዛዜው እንዲፈርስ አቤቱታ የሚያቀርቡበትን ሥርዓትና ጊዜውን በሚመለከት የሚደነግግ ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል /ነቅሎናል/ በማለት ኑዛዜው እንዲፈርስ የሚቀርብን ወይም የቀረበ አቤቱታን የሚመለከት አይይለም፡፡ በመሆኑም ኑዛዜው ከውርስ የመንቀል ውጤት ያለው በመሆኑ እንዲፈርስ በሚል የሚቀርብ የዳኝነት ጥያቄ ሊታይ የሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት ነውእንጂ በአንቀጽ 973 መሰረት አይደለም በማለት አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የሕግ ትርጓሜ መሰረት ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ አመልካች ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል በማለት የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ህ/ቁ 973 መሰረት ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ አንድ ኑዛዜ ፈራሽ ነው በሚል ስለሚቀርብ መግለጫ እና እንዲሁም መግለጫው እና ክሱ ሊቀርብ ስለሚገባው የጊዜ ገደብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 ተፈጻሚነት የሚኖረው ኑዛዜ ሲነበብ በነበሩ ወይም በተወከሉ ሰዎች ጉዳይ ሲሆን በአንቀጽ 974 ድንጋጌ ደግሞ ተፈጻሚነቱ በኑዛዜ ሥነ-ሥርዓት ባልነበሩ ወይም ባልተወከሉ ሰዎች ጉዳይ ነው፡፡ ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ አመልካች ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል በማለት የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ህ/ቁ 973 መሰረት ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት ነው፡፡

2) የወራሽነት ጥያቄ ለማቅረብ የተቀመጠ ጊዜ ገደብ

የወራሽነት ጥያቄን ለማቅረብ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የሚመለከቱ የሕግ ድንጋጌዎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000 ላይ የተመለከተ ሲሆን ወደዚህ ነጥብ ከመግባቴ በፊት ወራሽነት ጥያቄ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን እደሚከተለው ለመዳሰስ እሞክራለሁ÷
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 996(1) ላይ በተገለጸው መሰረት ወራሽ የሆነ ሰው የሟቹ ወራሽ መሆኑንና ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ የሚያመለክት የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል በማለት የተገለጸ ሲሆን ይህ ማለት ፍ/ቤቱ የወራሽነት ምስክር እንዲሰጠው ወራሹ ሲፈልግ የሚጠይቀው እንጂ ሟችን ለመውረስ የግድ ከፍ/ቤቱ የወራሽነት ማስረጃ ማምጣት እንዳለበት የሚያስገድድ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በተግባር እንደሚስተዋለው ስመ ንብረቱ ለማዛወር እና ከሌሎች የሟች መብቶች ለመጠቀምና ለመስራት በፍ/ቤቱ የተረጋገጠ የወራሽነት የምስክር ወረቀት መጠየቁ የተለመደ አሰራር ሆኗል፡፡

ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን መሰረት በማድረግ አንድ ሰው ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው ውርሱን ወይም ከውርሱ አንዱን ክፍል በእጁ ያደረገ እንደሆነ እውነተኛው ወራሽ ወራሽነቱን እንዲታወቅለትና የተወሰዱበት የውርስ ንብረቶች እንዲመለሱለት በዚህ ሰው ላይ የወራሽነት ጥያቄ ክስ ሊያቀብበት ይችላል በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 999 ላይ ተደንግጓል፡፡ ስለዚህ ይህን መሰል የክስ አቤቱታ አቤቱታ መቼ ሊቀርብ ይገናል ለሚለው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ ላይ የጊዜ ገደብ ተቀምጧል፡፡

በዚሁ መሰረት ከሳሽ መብቱንና የውርሱን ንብረት በተከሳሽ መያዛቸውን ካወቅ ሶስት ዓመት ካለፈ በኋላ ስለ ወራሽነት ጥያቄ የሚቀርበው ክስ ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም፡፡ በሌላ መልኩ በአንቀጽ 1000(2) ላይ እንደተገለጸው “ሟቹ ከሞተበት ወይም ከሳሹ በመብቱ ለመስራት ከቻለበት ቀን አንስቶ አስራ አምስት አመት ካለፈ በኋላ ከዘር የወረደ ርስት ካልሆነ በቀር የውርስ ጥያቄ ክስ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን ተቀባይነት አያገኝም የሚለው ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ከዚህ በላይ በአንቀጽ 1000(1) እና (2) ላይ የተመለከቱት የጊዜ ገደቦች ከሌሎች የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች በተለይም 1ኛ) አንድ ወራሽ የሟች ኑዛዜ ተጠቃሚ መሆን የሚችለው ኑዛዜ በእጁ እንደሚገኝ ለውርስ አጣሪው አቅርቦ ውርስ አጣሪው ኑዛዜውን በሚነበብበት ሰዓት ራሱ ወይም ወኪሉ ካልነበረ ወራሹ ኑዛዜው ከፈሰሰበት ቀን አንስቶ በአስራ አምስት አመታት ውስጥ መቃወሚያ ካላቀረበ ከዚያ በኋላ ሊቀርብ እንደማይችል በፍ/ሕ/ቁ 974(2) የተመለከተው በፍ/ሕ/ቁ 1000(1) ካለው የጊዜ ገደብ ጋር እንዴት ተጣጥሞ ተግባራዊ ይሆናሉ ከሚለው ጋር ጥያቄ የሚያስነሳ ሲሆን በሌላ መልኩ በፍ/ሕ/ቁ 1000(1) እና (2) አተረጓጎምና አፈጻጸም እንዴት መሆን አለበት በሚል አልፎ አልፎ ጥያቄ ሲያስነሳ ይስተዋላል፡፡ ስለዚህ በእነዚህ የሕግ ማዕቀፎች ላይ የተጠቀሱት የጊዜ ገደቦች በተመለከተ መከተል የሚገባንን የሕግ ትርጓሜ እንደሚከተው ለማብራራት ተሞክሯል÷ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 974/2/ ተፈጻሚ የሚሆነው የሟች ውርስ የሚያጣራ ፤በሕግ በኑዛዜ ወይም በፍርድ ቤት የተሾመ የውርስ አጣሪ ፤ሟች አድርጎታል የተባለው ኑዛዜ አግኝቶ የኑዛዜውን ፎርምን የኑዛዜውን ዋጋ መኖር ፤የሟች ያለኑዛዜ ወራሾች ወይም አራት አካለመጠን ያደረሱ ሰዎች ባሉበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 968 በተመረመረበት ሁኔታ ነው፡፡ ሆኖም ግን ኑዛዜ ያለ መሆኑን ለውርስ አጣሪው ሳያሳውቅ ቀጥታ የኑዛዜ ወራሽ መሆኑ እንዲታወቅለት ለፍ/ቤት አመልክቶ የወራሽነት የምስክር ወረቀት በመውሰድ የሟች ንብረት በእጁ ያደረገ ሰው ወይም በሀሰት የሟች ያለኑዛዜ ወራሽ ነኝ ብሎ የሟችን ንብረት ከወሰደው ሰው ለማስመለስ አግባብ የሆነው የይርጋ ገደብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 968 የተጠቀሰው ሳይሆን በፍብ/ሕ/ቁ 1000/1/ የተመለከተው ተፈጻሚነት ሊኖረው ይገባል፡፡

በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ እና 1000/2/ አስመልክቶ የተለያዩ አተረጓገሞች የሚስተዋሉ ሲሆን ለዚህ ጽሁፍ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 30158 ፤26422 እና 34011 በቅጽ 7/6/6/ እንዲሁም በቅጽ 11 በሰ/መ/ቁ 52407 የሰጠውን አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ለመዳሰስ ሞክሬያለው፡፡ በዚሁ አግባብ በፍ/ሕ/ቁ 1000/2/ ላይ ሟች ከሞተ አስራ አምስት አመት በላይ ወይም ተከሳሹ በመብቱ ሊሰራበት ከቻለበት ቀን አንስቶ አስራ አምስት ዓመት ውስጥ ክስ ካልቀረበ አስራ አምስት ዓመት ካለፈው በኋላ ክስ ሊያቀርብ የሚቻለው ከዘር የወረደ ርስት በሆነ ንብረት ላይ ነው፡፡

ርስት የሚለው ቃል በፍ/ሕ/ቁ 1130 እና ስለ ንብረቶች በሚናገረው የፍ/ብሔር የህጉ ክፍል መሬት የሚያመለክት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በኢትዮጲያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል የተዘጋጀው የአማርኛ መዝገበ ቃላት ርዕስት የሚለው መሬትን የሚመለከት መሆኑን ጠቅሶ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ በዚሁ አግባብ ከዘር የወረደ ርዕስት የሚለው ቤትን አያጠቃልልም የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ በርዕስት የሚተላለፍ መሬት ብቻ ማለት ሰለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/2/ መሰረት ለተወላጆች የሚተላለፍ መሬት ብቻ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
በኢፌድሪ ህገ መንግስት መሰረት መሬት የመንግስትና የህዝብ ሀብት በመሆኑ ከዘር የወረደ ርዕስት ካልሆነ በስተቀር በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/2/ ላይ የተገለጸው የተሻረ እና ተፈጻሚነት የሌለው ነው በማለት አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ አፈጻጸምን በተመለከተ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 32407 በቅጽ 11 ላይ ትርጓሜ የሰጠ ሲሆን በዚህም መሰረት በወራሾች መካከል የሚነሳ የውርስ ንብረት ክርክር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ በተደነገገው አግባብ በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ሲሆን ወራሽ በሆነ እና ወራሽ ባልሆነ ተከራካሪ ወገን መካከል የሚቀርበው የውርስ ንብረት ይገባኛል ጥያቄ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1677 እና 1845 መሰረት በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ መብቱ በይርጋ የሚታገድ ይሆናል፡፡

3) የክፍፍል ጥያቄ በይርጋ የማይታገድ ስለመሆኑ

ወራሾች ተለይተው የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየ የውርስ ሀብት ያለ እንደሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1062 በተገለጸው መሰረት እያንዳንዱ የጋራ ወራሾች ውርሱን እንከፋፈል በማለት በማንኛውም ጊዜ ለመጠየቅ የሚችሉ በመሆኑ የክፍፍል ጥያቄ በይርጋ የማይታገድ ይሆናል፡፡

⭕️ በቴሌግራም ያገኛሉ 👇

👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw

🇪🇹⚖🇪🇹⚖
🇪🇹⚖🇪🇹⚖🇪🇹⚖🇪🇹⚖🇪🇹⚖🇪🇹⚖🇪🇹⚖🇪🇹⚖🇪🇹⚖🇪🇹

(By Muluken Seid Hassen)

ከ ክፍል 1- የቀጠለለዝህም አንፃራዊ ምክንያት :የ ሟች ቤተሰብ /በ ሟች የምጦሩ /: በሱ ሞት ምክንያት የምያጡት የ ኤኮኖሚ ድጋፍ ለመካስ ነው ::👉✍️ዎራሽ ለመሆን የምያስፈልጉ ዋና :ቅድ...
11/06/2022

ከ ክፍል 1- የቀጠለ
ለዝህም አንፃራዊ ምክንያት :የ ሟች ቤተሰብ /በ ሟች የምጦሩ /: በሱ ሞት ምክንያት የምያጡት የ ኤኮኖሚ ድጋፍ ለመካስ ነው ::
👉✍️ዎራሽ ለመሆን የምያስፈልጉ ዋና :ቅድመ ሁኔታዎች 👇
በ መሰረቱ :ልዩ ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ :የ ኢትዮጵያ ዉርስ ህግ የምከተለዉን ሁኔታዎችን እንዴ ቅድመ -ሁኔታ አስቀምጧል :-
ሀ )ሟችን ለመዉረስ በ ሕዎት ስለመኖር (Theory of Survivorship ) ነው አንቀፅ -832:: በዝህም አንቀፅ መሰረት ምትክ ሆኖ መዉረስ እንደተጠበቀ ሆኖ /succession by representation ):አንድ አዉራሽ በ ሕዎት እያለ የሞተ ዎራሽ : የ አዉራሽ ዉርስ ሲከፈት ከ ዉርስ ዉጭ: ይሆናል ማለት ነው :: ነገር ግን ለ ዎራሹ ልጆች ካሉ /ተክቶ የሞተ እንደሆነ /የ አያታቸውን ዉርስ ሀብት ከ አጎታቸዉ ዎይም አክስታቸዉ ጋር ይካፌላሉ ማለት ነው ::
ለ )ለመዉረስ ያልተገባ ስለ አለመሆን (Being Free From Unworthiness) ቁጥር -838
👉አንቀፅ -838(1 ):-ወንጀሎች ዎይም ቅጣቶች
ሀ ) "ሟችን ዎይም የ ሟችን ዎደ ታች የምቆጠር ተዎላጅ /descendants /: ለምሳሌ የ ሟች ልጆች ዎይም የ ገዳይ ዎንድም :እህት ዎይም ዎደ ላይ የምቆጠር ዎላጅ : ለምሳሌ አባት :እናት :አያት /ascendants /ዎይም የ አዉራሽ ባል ዎይም ምስት አስቦ /intentional crime only / በ መግደል የተፈረደበት እንድሆነ ልዝህ ሰው ዉርስ አይገባም ማለት ነው :: ታዲያ ከዝህ ቁጥር በ ጥንቃቄ ማየት ያለብን እንዝህ ከላይ የተቀሱ ሰዎችን በመግደል : ብቻ ገዳይን ከ ዉርስ እንደማይነቅል ነው ::ስለዝህም ገዳይን ያልተገባ ለማለት ዎንጀል ፍ /ቤት ቀርቦ :ገዳይ :በ መግደል ጥፋተኛ መሰኘት አለበት ::
ለ ) ቁጥር -838(ለ ):- ከላይ በ ንኡስ -1 ከተጠሰዉ ሰዎች አንዱን :ለመግደል በ መሞከር የተቀጣ :: በዝህም መሰረት ሙከራ ዎንጀል ሁሉ ጊዜ ሆን ተብሎ የምፈፀም እንድሆነ ከ 1996 ኢ. ፈ. ዴ. ሪ. ወንጀል ህግ አንቀፅ -27 መገንዘብ ይቻላል ::በተጨማሪም የመግደል ሙከራ ወንጀል : ስልጣን ባለው ፍ /ቤት :ዎራሹ መቀጣት አለበት ::
ሐ) ቁጥር 838(ሐ ) አህንም እላይ በ ንኡስ-1 ላይ ቤተጠቀሱ ሰዎች ላይ በ ሐሰት በ መዎንጀል :ዎይም ሐሰት ምስክር በመሆን 'በዝህም ምክንያት :ከ እንዝህ ሰዎች አንዱ የ ሞት ፍርድ ዎይም ከ 10 ዓመት የበለጠ :ፅኑ እስራት እድቀጣ ያደረገ ዎራሽ :ለ ዉርስ ያልተገባ ይሆናል ማለት ነው 🙏🙏🙏
ስጠቃለል : ለመዉረስ : በ መርህ ደረጃ ሟች ስሞት በ ሕዎት ያሌ መሆን (surviving deceased ) እና ለመውረስ የተገባ (Being worthy ) አስፈላጊ እና ዎሳኝ ቅድመ ሁኔታ ናቸው ✍️
👉👉 ክፍል 2 ይቀጥላል :ስላነበባችሁ አመሰግናለሁ 🙏
ታዲያ :አስተያየት መስጠት :ማጋራት :መጠየቅ እንዳትረሱ 🙏🙏

ክፍል አንድየ "ዉርስ "ፅንስ ሃሳብ በ ኢትዮጵያ ህግ :በ ዎፍ በረር እይታThe theory succession under Ethioipia law, through berds eye view!በ መሰረቱ ...
11/06/2022

ክፍል አንድ
የ "ዉርስ "ፅንስ ሃሳብ በ ኢትዮጵያ ህግ :በ ዎፍ በረር እይታ
The theory succession under Ethioipia law, through berds eye view!
በ መሰረቱ አንድ ግለሰብ በ ሕዎት እያለ ብዙ ግዙፍ (tangible ) እና ግዙፍ ያልሆነ (intangible ) መብት ሊኖረው ይችላል :: መብትን ከ ዉርስ ህግ ጋር ስናገናዝብ :በ ሁለት ልከፈል ይቻላል :: አንደኛ :-ከ ሟች ልዎረስ የምቻል :መብት (patrimonial Right )እና ሁለተኛዉ :-ከ ሟች ዎደ ዎራሽ ልተላለፍ የምይችል (extra-patrimonial Right )ናቸው Art-826(2) of civil code :: ለምሳሌ :አሁን በዝህ ዘመናዊ ዓለም አንድ ሟች ከመሞቱ በፊት የ አንድ ሀገር መሪ (ጠቅላይ ሚንስቴር ): ብሆን : ልጆቹ ዎይም ሕጋዊ ዎራሾች :ይህንን ኃላፊነት (መብት ) ልዎርሱት አይችሉም :የ ስርው መንግስት (dynasty system ) እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው ::ይህም extrapatrmonial Right ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ::በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ግለሰብ ከመሞቱ በፊት ሙዝቀኛ ብሆን እና የተለያዩ ሙዝቃ ስራዎች ብኖሩለት :ዎራሾች :የ ሟች: ቂጂ መብት /copy Right /ይዎርሳሉ ማለት ነው ::ይህም patrimonial rightተብሎ ልጠቀስ ይቻላል ::
👉 በ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተለያዩ ሕጎች ህንን ዉርስ መብት ለማስከበር እና ለማስጠበቅ በ ተለያዩ ጊዜ ተደንግጉአል ::የ መጀመሪያዉ የ ኢ. ፈ. ዴ. ሪ. ህገ መንግስት ሲሆን :ይህም በ አንቀፅ -40 ስለ ንብረት በምያትተው ክፍል :የ አንድ ንብረት ባለቤት የ ማዉረስ መብት መሰረታዊ ከሆኑ ንብረት መብት አንዱ እንደሆነ በ ንዑስ ቁጥር 1እና 7 በ ግልፅ አስቀምጧል ::
👉 ሌላኛው የ 1952 ፍትሐ ብሔር ህግ ነው ::በዝህም ሕግ ዉስጥ አንቀፅ -5/Title Five / ስለ ዉርስ (አዎራረስ )በ ጠቅላላ ያዎራል ::ቁ-826 "አንድ ግለሰብ በ ሞተ ጊዜ ዉርስ በዛች ጊዜ እና ስፍራ እደምከፈት ነው ::የዝህ አንቀፅ ንኡስ ቁ -2 ከላይ ያነሳነውን ሃሳብ patrimonial እና extrapatrmonial Right ያዎራል ::
👉 እዝህጋ የ አንድ ሟች የ ዉርስ አካል ያልሆኑ /የማይዎረሱ /ንብረት መመልከት ተገቢነት አለው :: አንቀፅ 827 እና 828 የ ዉርስ አካል ያልሆኑ ንብረቶችን ያስቀምጣል ::በዝህም መሰረት :ሟች በ ሕዎት እያለ የ ሕዎት መድን /life insurance /: ተጠቃሚዎቹን ለይቶ የገባ እንድሆነ :የዝህ መድን ገንዘብ የ ዉርስ አካል አይሆንም ማለት ነው ::🖋️ ሌላው ደግሞ የ ጡረታ እና ካሳ ገንዘብ ናቸው(ቁ -828): በዝህም አንቀፅ መሰረት አንድ የ መንግስት ዎይም የ ግል ድርጅት ሰራተኛ የ ጡረታ መብቱን አስከብሮ ብሞት :በ መሞቱ ምክንያት የምከፍለው የ ጡረታ /ዳረጎት /:የ ዉርስ ሀብት አካል አይደለም ::ለዝህም ምክንያት ብሎ ብዙ የ ሕግ ምሁራን የምያስቀምጡት :ጡረታ ሟች በ ጥረት ሰርቶ ያገኘ ሀብት ሳይሆን :መንግስት ዎይም አንድ ግል የ ንግድ ድርጅት :ሰራተኛዉ ጉልበት ባለ ጊዜ :አገልግሎት ሰጥተሄኛል:ስልሆኔም:በሸመገልክ ጊዜ (ጡረታ =ጡሩ -ተኛ ) በ ማለት የምከፍለው አይነት ክፍያ ስልሆነ ነው ::
👉ሌላኛው ደግሞ አንድ ሟች በመሞቱ ምክንያት ለ በተዘመዶቹ የምከፍል ካሳ (indemnity )ነው (ቁርጥ -828)
በመሰረቱ አንድ ግለሰብ በ ሰው ሰራሽ አደጋ ምክንያት ብሞት ለሞቱ ኃላፊነት የምቀበል አካል በ ኢትዮጵያ ከ ዉል ዉጭህ ህግ (Etra-Contractual law) መሰረት :ይጠይቃል :ካሳም ይከፍላል ማለት ነው ::... ይቀጥላል 👉

በ ገጠር መሬት ባለ ይዞታ ለሆነው ሰው ያለዉ መብት በ ኢ.ፈ.ዴ.ሪ ህገ-መንግስት እና በ ገጠር መሬት አዋጆች ::🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️በ መሰረቱ የ ሰው ልጅ በ ሕዎት ዘመኑ ብዙ ንብ...
04/06/2022

በ ገጠር መሬት ባለ ይዞታ ለሆነው ሰው ያለዉ መብት በ ኢ.ፈ.ዴ.ሪ ህገ-መንግስት እና በ ገጠር መሬት አዋጆች ::🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️
በ መሰረቱ የ ሰው ልጅ በ ሕዎት ዘመኑ ብዙ ንብረት መብት ልያፈራ ይቻላል ::ገጠር መሬት ይዞታ መብት አንድ ግለሰብ ካለው ንብረቶች መብት አንደኛዉ ነው :: መብት አለ ካለን ደግሞ በ ህግ ጥበቃ መሰጠቱ ግዴታ ይሆናል ማለት ነው ::የነ Thomas Hobs እና John Lock "Social Contract Theory " እና የነ Jermy Bentham "Utilitarian Theory " ስለ ንብረት አመጣጥ እንደምሉት :- ማህበረሰብ ለራሳቸው ያላችውን :መብት :መንግስት ወክል ሆኖ እንድጠብቅላቸው ዉል ሰጥቱዋል ይላሉ ::
ይህንን:አስተሳሰብ (theory ) መሰረት ስናደርግ :ኢትዮጵያ የ ንብረት መብት ለማስጠበቅ ከ ደነገጋችሁ ሕጎች መካከል ኢ.ፈ.ደ.ሪ ህገ መንግስት እና ሌሎች የ ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጆች ይገኙበታል ::
ከ ህገ መንግስት ስንነሳ :አንቀፅ -40 ስለ ንብረት መብት በ ጠቅላላ ያዎራል ::ከዝህ የምንረዳው :- የ ገጠር መሬት ባለበትነት መብት የ ኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት እንደሆነ ነው (አንቀፅ 40(3)):: በተጨማሪም :መሬት የማይሸጥ :የማይለዉጥ:የ ኢትዮጵያ ብሔር :በሔርሰቦች እና ህዝቦች የ ጋራ ሀብት እንዴሆነ ነው :: ይህ ግን ማለት አንድ ግለሰብ በ ገጠር መሬት ላይ ምንም አይነት መብት የለዉም ማለት አይደለም :: ይልቁንስ የ ይዞታ መብት (possession Right )እንደተጠቀ ነው :: የ ይዞታ መብት ስቶሮጎማ : እንዴ አብዛኛው ምሁራን አስተያየት :-"በ ንብረት ላይ ያለ ሁሉንም መብት:ግን ባልቤትነት መብት ሳይጨምር... "(All right on property less ownership ) but this definition make it the same with "usufract" ) ይሉታል :: ከዚህም ረገድ በ ንብረት ህግ ታውቂ ፀሐፊ እና ተመራማሪ : ዶ/ሪ ሙራድ አብዱ :የምከተለዉን ትርጉም ሰጥቱዋል :- "የ መሬት ይዞታ መብት ማለት ሁሉንም በ መሬት ማድረግ የምችለውን ሁሉ ማድረግ : ሆኖ ግን በ ሽያጭ መብት ማጣትም ሆነ ማግኘት እና ለ ቤተሰብ አባል ላልሆነ በ ስጦታ ማስተላለፍ አይጨምርም" ይላል
ይህንን አገላለፅ የምደግፍ አዋጆች በ ፌደራልም ሆነ በ ክልል ደረጃ ዎጥተው እየተሰራ ይገኛል ::
ከ እንዛም :አዋጅ ቁ-456/1997:አንዱ ስሆን : በ ትርጉሙ ክፍል :አንቀፅ :2(4) ላይ "የ ይዞታ መብት ማለት : ማንኛውም አርሶአደር ዎይም አርብቶአደር በ ግብርና :ማልማት :ጥቅም ላይ ማዋል :ማከራየት :ለ ቤተሰብ እና በ ህግ መብት ለተሰጣቸው :ለማስዎረስ :እና ንብረት የ ማፍራት መብት ያጠቃልላል "ይላል ::
በተመሳሳይ አገላለፅ የ ደቡብ ብሔር :ብሔርሰቦች እና ህዝቦች ክልል መንግስት ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁ-110/1999 አንቀፅ -2(6) እላይ የተባለውን ያስቀምጣል ::
የ ቤተሰብ አባል እኔማናቸው ለምለዉ ጥያቄ :ሁለቱም አዋጅ በ አንቀፅ 2(5) እና 2(7) እንዴ ቅደም ተከተላቸው "የ ቤተሰብ አባል ማለት የ ይዞታ ባለ መብቱን መተዳዴርያ ገቢ በ መጋራት : በ ቁዋምነት አብሮ የምኖር ማናቸውም ሰው ማለት ነው"
ታድያ ከዚህ ፅሁፍ የምከተለዉን ማጠቃለያ ነጥብ ማዉጣት እንችላለን ማለት ነው ::
🖋️ በ ኢትዮጵያ ሕግ መሰረት የ መሬት ባልቤትነት መብት የ ህዝብ እና መንግስት ጋራ ነው :
🖋️የ ኢትዮጵያ አርሶ አደር እና አርብቶ አደር ገጠር መሬት የ ይዞታ መብት ብቻ አላቸው :
🖋️በተለይም ገጠር መሬትን መሸጥ :መለዎጥ :በ ህግ የተከለከለ ነው :
🖋️የ ገጠር መሬት ይዞታን በ ስጦታ ብሆን ማስተላለፍ የምቻለው ለ ቤተሰብ አባል ብቻ ነው :
🖋️በ ገጠር መሬት ይዞታ ላይ የተደረገው ሽያጭ ዉል ዋጋ የለውም :በ ማናቸውም ጊዜ በ ፍርድ ቤት ልፈርስ ይችላል (ሰበር መ /ቁ -43226)
🖋️የ ገጠር መሬትን ከ ቤተሰብ አባል /በ ህግ መውረስ ከምገባቸው ሰው ዉጭ በ ስጦታ ዉል ማስተላለፍ በ ህግ ፊት አይፀናም ::
👍በ አጠቃላይ :የ መሬት ይዞታ ጉዳይ :በ ኢትዮጵያ ዉስጥ ትልቅ የ ሕግ ዉጤት ስለምያስከትል :ጥንቃቀ ይሻል!!
ስላነበባችሁ አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏
Don't forget like, share and comment Page
ቀጣይ በ ሌላ ጉዳይ እስክንገናኝ ቸር ሰንብቱ 🤝

👇✍️
03/06/2022

👇✍️

በይርጋ የማይታገዱ የፍትሐብሔር ጉዳዮች
===============
የይርጋ መሰረታዊ ዓላማ ማንኛውም በህግ በግልፅ የተደነገገ መብትና ግዴታ በህጉ በተወሰነው ወይም በተገደበው ጊዜ ውስጥ ስልጣን ላለው አካል እንዲቀርቡ ግዴታን በማስቀመጥ መብቴ ተጣሰብኝ የሚል ወገን ዳተኛ ሳይሆን በትጋት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል መሆኑ ይታወቃል።

ነገር ግን አንዳንድ ጉዳዬች ከንብረቶቹ ልዩ ባህሪና የመንግስት ፖሊሲ አንፃር ህግ አውጪው በይርጋ እንዳይታገዱ አድርጎ ያስቀመጣቸው የፍትሀብሄር ጉዳዬች አሉ። ከእነዚህ መካከል፦

#የመፋለም ክስ ( petitory action)
~~~~~~××××××~~~~~

ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከል ንብረቱ ያለ እርሱ ፈቃድ ከህግ ውጪ በሌላ ሰው ወይም ሀይል ከተወሰደ ንብረቱን ካለበት ድረስ በመከታተል የማስመለስ ወይም የመፋለም መብት አንዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 ድንጋጌ ያስረዳል፡፡

ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን” በሚል ርዕስ ስር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1192 የተመለከተው በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት በአስር ዓመት የጊዜ ወሰን /ይርጋ/ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ያመላከተ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ግን አያሳይም፡፡

ድንጋጌው የሚንቀሳቀስ ንብረትን የባለሀብትነት ጥያቄ የጊዜ ገደብ ካስቀመጠ በኋላ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ቀሪ መሆን በዝምታ ያለፈው ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት በሌለው በፍ/ብ/ህግ አንቀፅ 1845 ስር የተመለከተው ተመሳሳይ የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ እንደሆን ተፈልጎ ካለመሆኑ በላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሚንቀሳቀስ ንብረት በተለየ ሁኔታ የዘላቂነት ባህሪ ያለው እና ከትውልው ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በመሆኑ የባለሀብትነቱ መብት ቀሪ የሚሆነው በይርጋ ሳይሆን በሌሎች ሁኔታዎች( አንቀፅ 1168....) ይሆን ዘንድ ተፈልጎ የተቀመጠ ድንጋጌ መሆኑን እንገነዘባለን።

በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም ክስ (petitory action) በይርጋ ቀሪ አይሆንም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/መዝ/ቁ 43600)

N.B= ይህ ሲባል ግን ከውርስ፣ ከሽያጭ፣ ከስጦታና ከሌሎች ውሎች በመነጨ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ክርክር ይርጋ የለውም ማለት የሚቻል ሳይሆን ለጉዳዩ አግባብነት ባላቸው ህጎች በተቀመጡ የይርጋ ጊዜዎች የሚስተናገዱ ይሆናል።

#ህገ ወጥ ውል (unlawful contrat)
~~~~~~~×××××~~~~~~

እንድ ውል የፀና ውል ለመሆን መሟላት ከሚገባው አንዱ ነጥብ ውሉ ህጋዊ በሆነ ጉዳይ ላይ የተመሰረተ መሆን የሚገባው እንደሆነ የፍ/ብ/ህግ 1678 ይደነግጋል። አንድ ውል ህገ ወጥ ውል ነው የሚባለው ደግሞ ተዋዋዬቹ የተዋዋሉበት መሰረታዊ ጉዳይ ዓላማ በመሰረታዊና ሞራላዊ ይዘቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት በማድረግ መብትና ግዴታ እንዲፈጥሩበት በህግ ያልተፈቀደ ወይም በህግ ክልከላ የተደረገበት ሆኖ ሲገኝ ነው።

አንድ ውል የተመሰረተበት መሰረታዊ ጉዳይ (object of contract) በህግ ክልከላ የተደረረበት በሆነ ጊዜ ውሉ በህግ ፊት እንደሌለና ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት የማያስከትል (null and void contrat) እንዲሁም ችግሩን በማስተካከል ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ የማይቻል ነው። ለምሳሌ፦ የመሬት ሽያጭ ውል፣ በሰው ለመነገድ የተደረግ ውል፣ ወንጀል ለመፈፀም የተደረገ ውል......
ህገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ ደግሞ በህጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊቀርብ የማይችልና ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በይርጋ የሚታገዱ አይደሉም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 43226)

N.B= ይህ ሲባል ግን የህጉን መስፈርት ያላሟሉ ውሎች (illegal contract) ከህገ ወጥ ውል በተለየ ሁኔታ ታይተው የይርጋ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆንባቸው መሆኑን መረዳት ይገባል።

#የመንግስትን መሬት የማስመለስ ክስ
~~~~~××××××~~~~~~

ግለሰቦች በፌደራሉ እና በክልሉ መንግስት በወጡ የገጠር መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር አዋጅ በሚደነግጉት መሰረት በህጋዊ መንገድ ሳይሰጣቸው ከህግ ውጪ የወል ወይም የመንግስትን መሬት ይዘው መቆየታቸው እና የመሬቱ ባለይዞታ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማግኘታቸው የመሬቱ ህጋዊ ባለይዞታ ሊያደርጋቸው አይችልም። በወረራ የተያዘ የመንግስት መሬትም ይርጋ የሌለው መሆኑን የአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 በግልፅ ያስቀምጣል።

በመሆኑም ከህግ ውጭ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን መኖራቸውን ሲረዳ መሬት አስተዳደርም ሆነ የመንግስት ወኪል የሆነ አካል መሬቶቹን ለማስመለስ የሚያቀርበው ክስ በይርጋ የሚታገድ አይደለም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 93013 እና 96203 ያልታተሙ)

#በህገ ወጥ መንገድ የተያዘ የግለሰብ ይዞ መሬት
~~~~~~××××××~~~~~~

ከላይ እንደተመለከትነው ህገ ወጥ ውልን መሰረት አድርጎ የግለሰብን መሬት በያዘ ሰው ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የሌለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 መሰረት ህጉ በማይፈቅድበት መንገድ በሀይልም ሆነ በህገ ወጥ አግባብ የገጠር መሬትን ይዞ የተገኘ ግለሰብ ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የለውም።

N.B= በህገ ወጥ መንገድ የሚለው ሀሳብ በህግ ተቀባይነት በሌለው አኳኋን የያዘን በሚመለከት እንጂ የህጉን መስፈርት ባላሟላ ውል ወይም ተግባር (illegal contrat) አማካኝነት የተያዘን መሬት የሚመለከት አይደለም። ምክንያቱም መሬቱን የያዘው በህጉ በተፈቀደ የውል ተግባር ሆኖ የሚፈለገውን ፎርማሊቲ ወይም መስፈርት አለማለቱ ብቻ አያያዙ ህገ ወጥ ነው የሚያስብል ስላልሆነ ነው።

#የአደራ ውል
~~~×××~~

አደራ ተቀባይ በአደራ የሚጠብቀውን ዕቃ የሚመልስበት የጊዜ ገደብ በውል ተመልክቶ ከሆነ ይህ ጊዜ ሲያበቃ ዕቃውን መመለስ ያለበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2781(1) የተመለከተ ሲሆን በውል ላይ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ ከሌለ ግን አደራ ሰጪው እንደጠየቀ ወዲያውኑ እንደሚመለስ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2989(1) ስር ተመላክቷል።

ከእነዚህ ድንጋጌዎች ለመረዳት የሚቻለው አደራ ተቀባይ ዕቃውን የሚመልስበት የጊዜ ገደብ ከሌለ በቀር አደራ ሰጪው በአደራ እንዲቀመጥ የሰጠው ዕቃ ያለምንም የጊዜ ገደብ በማንኛውም ጊዜ እንዲመለስለት መጠየቅ የሚችል መሆኑን ነው።

#የውርስ ሀብት ክፍፍል
~~~~××××~~~~

ወራሾች ተለይተው እና የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ነገር ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየን የውርስ ሀብት በማናቸውም ጊዜ መጠየቅ እንደሚችልና በይርጋ የሚታገድ እንዳልሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1060 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።

እንዲሁም ከውርስ ሀብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የውርስ ሀብቱን በእጁ አድርጎ በመገልገል ላይ ያለ ተከራካሪ የሆነ ወራሽ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የውርስ ንብረት በጋራ ይዞ ከቆየ ሰው ላይ የውርስ ድርሻዬን ልወቅ ወይም ይለይልኝ ጥያቄ በይርጋ ይታገዳል የሚባልበት አግባብ የለም።

#የድምፅ ብክለት
~~~×××~~~~

የድምፅ ብክለት ክልከላ ባለቤቱ ስራውን የሚፈፅመው በራሱ ንብረት ወይም ቤት ውስጥ ቢሆንም ድርጊቱ ሌላውን ጎረቤት እንዳይረብሽ፣ እንዳያውክ፣ ወይም ችግር እንዳያስከትል በማድረግ መብቱን ይጠቀም ዘንድ ህጉ ያበጀው የባለቤትነት መብት አጠቃቀምን አድማስ የሚወስን ስርዓት መሆኑን ከአንቀፅ 1226 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።

ይህን ችግር ለማስወገድ የሚቀርበው አቤቱታ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1149 ስር ከተመለከተው በይዞታ ላይ ሁከት መፍጠር ተግባር የሚለይ ሲሆን አንዴ የተፈጠረ የድምፅ ብክለት እንዲቀጥል የሚደረግበት አግባብ ስለሌለ በይርጋ የሚታገድ አይደለም።
Source:- The Voice of Justice page

ክፍል 2የ ክፍል አንድ ማጠቃለያ.. ስናጠቃልል ከ ቁጥር -49 የምንረዳው ነገር :-ግልፅ የሆነ ሌላ ድንጋገ ከለለ በቀር :አንድ ፖሊስ በ አንቀፅ 50 እና 51 ከተመለከቱ ሁኔታዎች  ውጪ ያ...
31/05/2022

ክፍል 2
የ ክፍል አንድ ማጠቃለያ.. ስናጠቃልል ከ ቁጥር -49 የምንረዳው ነገር :-
ግልፅ የሆነ ሌላ ድንጋገ ከለለ በቀር :አንድ ፖሊስ በ አንቀፅ 50 እና 51 ከተመለከቱ ሁኔታዎች ውጪ ያለ ፍ /ቤት መያዝ ትእዛዝ አንድን ተጠርጣርይ መያዝ አይችልም ማለት ነው :: ነገር ግን እንደዝ ስንል በ ሌላ ሕጎች ዉስጥ ያሉ ልዩ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ይሆናል ማለት ነው :: ለምሳሌ :- የ ሙስና ወንጀል ስረ - ነገር እና ስነ-ስርዓት በ ልዩ አዋጅ ቁ -881 እና 882 እንደምመራ ማለት ነው ::
ታድያስ እዚህ ጋ ልሰመር የሚገባው ነጥብ :አንድ ፖሊስ ያለ ፍ/ቤት ትእዛዝ ተጠርጣሪን አይዝም ስባል ያ ፖሊስ ያ ግለሰብን በራሱ መጥርያ(summon) ጠርቶ ሊያመጣ አይችልም ማለት አይደለም :: ምክንያቱም በ አንቀፅ 25 መሰረት :ፖሊስ አንድ ግለሰብ ወንጀል ሰርቷል ብሎ ለማመን ምክንያት ባለ ጊዜ ሁሉ (... Reason to believe commission of crimes ) የተባለውን ግለሰብ በ መጥርያ ልጠራ ይችላል ::
Thank you for your Reading 🙏🙏
ታዲያ:ያላችሁን አስተያየት :ሃሳብ : ፃፉ :አጋሩ : ጠይቁ ::
በ ክፍል 3 በ ሌላ ርዕስ እና አጀንዳ እስክንገናኝ ቸር ሰንብቱ .... 🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️

1954 ወ/መ /ሥ /ሥ /ህ መሰረት መጥርያ (summon) እና መያዝ ( arrest ) አንድነት እና ልዩነት🖋️🖋️🖋️**********************************************...
29/05/2022

1954 ወ/መ /ሥ /ሥ /ህ መሰረት መጥርያ (summon) እና መያዝ ( arrest ) አንድነት እና ልዩነት🖋️🖋️🖋️**********
*************************************
ክፍል 1
ከላይ በተጠቀሰው ሕግ ቁጥር :25 ስለ መጥርያ ምንነት ያስቀምጣል ::በዝህም መሰረት ፖሊስ ለ አንድ ተጠርጣሪ መጥርያ በ መላክ እንድመጣ ሊያደርግ ይችላል :: በ መሰረቱ መጥርያ (summon )ማለት አንድ ሰው በ ፍቃደኝነት ዎደ ፖሊስ ጣቢያ እንድመጣ የምይደርግ የ ፅሁፍ ደብዳቤ ማለት ነው ::ታድያስ በ መጥርያ የተጠራ ግለሰብ በ ፍቃደኝነት ልመጣም ዎይም ልቀርም ይችላል ::ደግሞም በ መጥርያ ጠርቶ ያመጣ ፖሊስ ተጠርጣሪዉን በ ዋስ ልለቅም ዎይም ሊያስር ይችላል :እንዴ ወንጀሉ ክብደትና ቅሌት ማለት ነው ::
=- መያዝ (Arrest ) ማለት ሁለተኛ መጥርያ (secondary summon )ይባላል :: ይህም የተባለበት ምክንያት :አንድ ተጠርጣሪ በ ፖሊስ ተገዶ በመያዝ ወደ ህግ ጥላ ስር እንድመጣ የምደረግበት ሕደት ስለሆነ ነው :: መያዝ (arrest) በ ወ መ /ሥ /ሥ ህ /ቁ 26 መሰረት አስገዳጅ መጥርያ ነው :: ማለትም በ መጥርያ እንድቀርብ የታዘዘ ግለሰብ ባለመቅረቡ ፖሊስ ዎይም ፍ/ቤት ያ ግለሰብ ተገዶ እንድቀርብ የምሰጠው ትእዛዝ ስልሆነ ነው ::
በ አንቀፅ 49 እና ተከታዮች 'ድንጋጌ መሰረት መያዝ በ ሁለት ይከፈላል :: 1ኛ በ ፍ /ቤት ትእዛዝ የምደርግ መያዝ (Arrest with court warrant ) እና 2ኛው ያለ ፍ /ቤት ትእዛዝ የምፈፀም መያዝ (arrest with out court warrant ) ናቸው ::
ሀ ) ያለ ፍ /ቤት ትእዛዝ የምደረግ መያዝ!
(አንቀፅ 49:50 እና 51)
የመጀርያው እጅከፍጅ ወንጀል (ቁ-50)
ከዝህም ህግ ድንጋጌ የምንረዳው ነገር :-በ ወ/መ /ሥ /ሥ /ህ /ቁ -19-20 መሰረት አንድ ተጠርጣሪ: አንድ ወንጀል ሲፈፅም እጅ ከፍንጅ (flagrant ኦፍፈንቸስ or ) ከተያዘ እና አደርጌ ተብሎ የተጠረጠረ ዉ ወንጀል አድራጊዉ ብቀጣ ከ 3ወር ቀላል እስራት የምያስቀጣ ከ ሆነ ነው ::
ታድያስ እዝህ ጋ ልነሳ የምችል ጥያቄ :-አንድ ወንጀል ከ 3 ወር በታች ዎይም በላይ ስለ ማስቀጣቱ ፖሊስ በ ምን እርግጠኛ ልሆን ይችላል? ምክንያቱም በ ኢትዮጵያ ወንጀል ህጎች ወንጀል ተብሎ የተደነገጉ እና በ ቀላል እስራት የምያስቀጡ ወንጀል ቁጡር እጅግ ብዙ ናቸው ::
በሌላ በኩል ደግሞ አንቀፅ 51(1)/ሀ /መልክት አበጠርጥሮ ማየት ተገብነት አለው :: በዝህም መሰረት ፖሊስ በ አንድ ሰው ከ አንድ ዓመት በ ማያንስ እስራት የምያስቀጣ ወንጀል ለመስራት ዝግጁ የሆነዉን ዎይም ሰርቷል ተብሎ "በምገባ የተጠረጠረ "(... Reasonable suspction ) ያለ ፍ /ቤት ትእዛዝ መያዝ ይችላል ማለት ነው :: ታዲያ እዝህ ጋ ልነሳ የምችለው ጥያቄ =- ከ አንድ ዓመት የማያንስ እስራት ስባል "ቀላል " ነው ዎይስ "ፅኑ "? በርግጥ ፅኑ እስራት በ ወንጀል ሕግ መሰረት ከ አንድ ዓመት እና ከዛ በልይ ስሆን ቀላል እስራት ደግም ከ 10 ቀን እስከ 3 ዓመት ሆኖ በ ልዩ ሁኔታ (exceptional circumstances ) እስከ 5ዓመት ልሆን እንደምችል ነው :: ከዝህም አንፃር የ አንቀፅ 51/1/ሀ / እስራቱ "ፅኑ "በሚል ቢተካ አስማሚ ነው ::
ሌላኛው ጥያቄ "... በምገባ የተጠረጠረ "የምለው ሐረግ :ፅንሰ ሃሳብ ነው ::
ይህም ሐረግ ከ ምን አንፃር መቶርጎም እንዳለበት በ ምሁራኖች ዘንድ ሁለት አይነት ክርክር አለ :-1 objective standard (ገሃዳው ዎይም አንፃራ አገላለፅ ) ሲሆን :ዋና ሃሳቡም :ማንኛውም ወንጀል መከላከል ሳይንስ የተማረ ፖሊስ ሊያደገው የምችለው ተግባር ዎይም ምክንያታዊ ፖሊስ (reasonable police )ደረጃ ስታይ ልደርግ የምችል ተግባር ማድረግ ነው ::
ሌላኛው ደግሞ የ አንድ ፖሊስ ግላዊ አስተያየት (subjective standard ) የምንለው ሲሆን :-ከዚህ ፅንሰ ያሳብ አንፃር አንድ ፖሊስ በ ዉስጣዊ ስሜት ዎይም ዉሳኔ ተመርኩዞ የምያደርገው ተግባር ማለት ነው ::
ታድያስ ከዝህ ሁለቱ ሃሳብ ክፍል የ አንቀፅ 51(1)/ሀ / ሃሳብ ስተሮጎማ ከ መጀመሪያዉ ዎይስ ሁለተኛዉ ነው የምለው አከራካር ብሆንም : አብዘኛዉ ምሁር የምስማማዉ በ መጀመሪያዉ ፅንሰ ሃሳብ ሲሆን : ለዚህም ምክንያት :አንድ ፖሊስ በ ዉስጣዊ ስሜት እና ግምት ብቻ ተነስቶ አንድን ግለሰብ እንድይዝ የ ሕጉ አላማ አይደልምና ::
ክፍል 2...ይቀጥላል. 🙏🙏

የ 1954 ወ /መ /ሥ /ሥ/ህ ቁ -42(1ሀ ),44(1) እና 150 ፅንስ ሃሳብ እና በ ፍትህ ተቁዋማት ያሌ አሁናዊ ተግባር!!🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️በ ዋናነት የ ውንጀል ክ...
18/05/2022

የ 1954 ወ /መ /ሥ /ሥ/ህ ቁ -42(1ሀ ),44(1) እና 150 ፅንስ ሃሳብ እና በ ፍትህ ተቁዋማት ያሌ አሁናዊ ተግባር!!
🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️🖋️
በ ዋናነት የ ውንጀል ክስ አቀራረብ በ 2 መንገድ ይከፈላል :: 1ኛው በ ውንጀል ክስ አቅራብነት የምያስቀጣ ውንጀል ( Crimes up on accusations ) 2ኛው በ ግል አቤቱታ የምቀርብ የ ውንጀል አይነት(crimes up on compliant )ነው ::
የ 1954 ወ /መ /ሥ /ሥ /ህ ምዕራፍ -3 ስለ ክስ አቀራረብ በተለያዩ ድንጋጌዎች ያ ስቀምጣል ::ከ እንዝህም መካከል ቁ -42 ክስ የማይቀርባቸዉን ሁኔታዎች በ 3 ዋና ዋና ምክንያቶች ከፋፍሎ ያትታል ::አንደኛው 42(1ሀ ) መሰረት ተጠርጣሪን ጥፋተኛ ለማድረግ በቂ መረጃ :ስላለመኖ ነው ::
ታድያስ እዝህጋ ላነሳ የፈለኩት ነጥብ ብኖር አንድ የ ፖሊስ ምርመራ መዝገብ ዓ /ህግ በ 42(1ሀ ) መሰረት የዘጋ መዝገብ ዳግም በ ግል ተበዳይ የ ውንጀል ክስ ለተገብዉ ፍ /ቤት ልቀርብ እንደምችል ነው ::ነገር ግን ይህ እዉነታ በ አሁናው ፍትህ ተቁዋማት ያልተለመድ ተግባር መሆኑን ለማስገነዘብ ነው ::
በ መሰረቱ የ ግል ዎንጀል ክስ (private prosecution ) በ ሕጉ በ ግልጽ የተቀመጠ ይሁን እንጂ እኔ እስቀማዉቀው ድረስ (... As to my knowledge is concerned ) በ ኢትዮጵያ ፍ /ቤቶች አንድ ግለሰብ የ ውንጀል ክስ በራሱ ስም ከፍቶ ለ ፍ /ቤት ማቅረብ የተለመደ አይደለም ::
ነገር ግን የ ወ /መ /ሥ /ሥ /ህ /ቁ -150እና ተከታዮች መሰረት አንድ ግል ተበዳይ ከ ፍ /ቤት ፈቃድ በ ማግኘት በራሱ ስም ውንጀል ክስ መክፈት እንደምችል ነው ::
እላይ ከጠቀስኩዋቸው ሁለት ዓይንት ክስ አቀራርብ ዘዴ :በ ግል ውንጀል ክስ መክፈት የምቻለው : በ1996 ዓ. ም የዎጣው ኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሳዊ :ረፓብልክ ውንጀል ህግ መሰረት በ ግል አቤቱታ አቅራብነት ብቻ የምያስቀጣ ዎንጀል ሲሆን ነው ::
ወደ ያዝነው ጥያቄ ስንመለ በ ወ /መ /ሥ /ሥ /ህ /ቁ -44(1):መሰረት ዓ /ሕግ ዉሳኔ ሲሰጥ : የ ውንጀል አይኔ crimes up on complaint መሆን አለበት ::በዚህም መልኩ ዓ /ሕጉ ዉሳኔ የሰጠ እንደህነ:በ ቁ - 47 ለተመለከተው ተገቢ ለሆነው ሰው የ ግል ክስ ማቅረብ ትችላለህ የምል የ ፍቃድ ደብዳቤ መስጠት አለበት :: ይህም መፍቀጃ ዉሳኔ ግልባጭ ክስን ለመስማት ስልጣን ላለው ፍ /ቤት መላክ አለበት ማለት ነው ::🖋️
ታድያስ ከዝህ ፅሁፍ የምንረዳው ነገር እና ወሳኝ ነጥቦች የምሆነው :-
- የ ውንጀል ክስን በ ግል ከሳሽነት ማቅረብ ያልተለመድ መሆኑን : ነገር ግን ሕጉ በ ግልፅ ያስቀመጠ ስለመሆኑ :
-በ ግል ክስ አቅራብነት የምቀርብ የ ውንጀል ጉዳይ በ 42(1ሀ ) መሰረት ዓ /ሕጉ ለመክሰስ በቂ መረጃ የለኝም በ ማለት የዘጋ ኡንደሆነ : ይህ የ መደምደምያ ዕድል እንዳልሆነ እና በ ወ/መ /ሥ /ሥ / ህ /ቁ -47&150 ላይ የተመለከተ ግል ተበዳይ የ ግል ውንጀል ክስ ማቅረብ እንድምፈቅድለት ነው ::
የ ዛረዉን በዝህ አበቃን : ስላነበባችሁ አመሰግናለው 🙏🙏

ታድያስ Don't forget like, share and comment this page🙏🙏

በ መሰረቱ ህግ ፍርድ ቤትን በ ደንብ ያምናል :: ማለትም አንድ  ዳኛ ፍርድ ሲሰጥ ዎይም ችሎት ሲያስችል በጣም ታማኝ እንደሆነ ህግ ይገምታል :: በርግጥም ታማኝነት ከ ሙያዊ ግዴታዎች አንዱ...
14/05/2022

በ መሰረቱ ህግ ፍርድ ቤትን በ ደንብ ያምናል :: ማለትም አንድ ዳኛ ፍርድ ሲሰጥ ዎይም ችሎት ሲያስችል በጣም ታማኝ እንደሆነ ህግ ይገምታል :: በርግጥም ታማኝነት ከ ሙያዊ ግዴታዎች አንዱ ነዉና :: ኢትዮጵያ ካሉዋት ህግ አሁን የያዝነው ጉዳይ በተመለከተ 1960ዎቹ ፍትሐብሔርም ሆነ ወንጀል ስነ- ስርዓት ህጎች ዳኛ መታመን እንደምገባ ቤ ግልፅ ያስቀምጣሉ :: ነገር ግን ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ልነሳ የምችለው ጥያቄ :አንድ ዳኝ በተ ለይም የ ማስረጃው ቃል ስቀበል ማስረጃዎች ከሰጡት ቃል ትንሽ አንሻፈው ብቀበል ::ማለትም የ ማስረጃ ቃል ቤ ፍርድ መዝገብ ላይ ስፅፍ መሰረታዊ ለዉጥ ሳይኖር ነገር ግን ምስክር ከሰጠው ቃል ትንሽ እያዛብ ብቀበል ምን ይደረጋል የሚለዉ ቤ ኢትዮጵያ ህግ ዉስጥ ግልፅ የሆነ መልስ በ ፍትሐብርም ሆነ በ ውንጀል ህግ ዉስጥ የለም 🖋️🖋️::
ታድያስ በዝህ አይነት የ ምስክር ቃል ተውሶዶ በተሰጠዉ ፍርድ ላይ እንዴት ይግባኝ ማለት ይቻላል? ማለትም ምን አይነት የ ይግባኝ ምክንያቶች ልቀመጡ ይችላሉ? ዳኛው ቃል ሲቀበል ምስክሮች ከሰጡት ሌላ ቃል ነው የ ፃፈው ተብሎ ነው?
እንድህ አይነት ጥያቄን በተመለከተ የ ኢትዮጵያ ህግ ፍቱን የሆነ መልስ አላስቀምጥ!!
🙏🙏🙏
ለ ዛሬ ንባባችሁ አመሰግናለሁ 🙏 በ ቀጣይ ቆይታችን ለ ያዝነው ጉዳይ አግባባው መልስ የምለውን ይዥኤ እስክመጣ ዴና ቆዩ
ፔጁን like እና share ማድረጋቹን አትርሱ!!🙏

Address

S**o

Telephone

+251923050584

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when JAZI- About law posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to JAZI- About law:

Share

Category