Jawaarummaa-Jawaariizimii -ጀዋሪነት

Jawaarummaa-Jawaariizimii -ጀዋሪነት Know Law for your betterment and Survival

07/08/2025
26/05/2024

Shingaa?

20/10/2022

lies within this

20/09/2022

የጀዋርን ሩብ አትሆኑም!
-----
ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ማውራት እጅ እጅ ብሎናል። ነገር ግን በቆሎ-ጆሌ ንግድ የከሰሩ አቅል አልባዎች እየነካኩ ያናግሩናል።
-----
ጀዋር ሙሐመድ የሰው ልጅ ነው። የሰው ልጅ በሚሰራው ስራ ሊሳሳት ይችላል። በመሆኑም ጀዋር ሲሳሳት "ተሳሳትክ" ማለት ያለ ነገር ነው። እኛም ስሕተት መስሎ የተሰማንን ሁሉ ስንነግረው ነበር።

ጀዋር ከእስር ተፈትቶ "ኡቡንቱ" ከተባለ የዩቲዩብ ሚዲያ ጋር ቃለ-ምልልስ ካደረገ ጀምሮ በእርሱ ላይ የሚካሄደው ዘመቻ ግን ስህተትን መጠቆም እና ትችትን መግለጽ ሳይሆን በጥላቻ ዘመቻ ህዝቡን አደናግሮ ልጁን ከህዝብ ጋር የማራራቅ ተንኮል ነው።
-----
አንድ ነገር ልንገራችሁ!!

ይህ ዘመን በቲፎዞ ብዛት ህዝብን እያምታቱ ደጋፊን የሚያበራክቱበት ነው። ብቃት እና ችሎታ የሌለው ሙስኬቶ ሁላ ጀግና መስሎ የሚንጎማለለው በአብዛኛው በሰራው ስራ ሳይሆን በቲፎዞ ወከባ ነው። ዛሬ በሚዲያ እየቀረቡ ጀግና መስለው ከሚደነፉብን የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችና ተንታኞች ነን ባዮች መካከል 90% የሚሆኑት populism በሚባለው የሆሊጋኖች ማምታቻ ዘዴ እየተስፈነጠሩ ወደ ላይ የወጡ ናቸው።

ጀዋር ሙሐመድ ግን ከእነርሱ ይለያል። አንደኛ፣ ተጨባጭና ውጤታማ የሆነ ስራ ሰርቷል። በኢትዮጵያ ታሪክ የእርሱን ያህል ተጽእኖ መፍጠር የቻሉ ግለሰቦች የታዩት በጥቂት ወቅቶች ነው። ጀዋር አንድ ግለሰብ ሆኖ በአራት ዓመት ውስጥ ብቻ በርካታ ድርጅቶች ያልሰሩትን ነገር ሰርቷል። በተለይ ግን ምድረ ኮልኮሌውን ሁሉ እርሱ በሚጠራበት ስም "activist" እያሉ መጥራት ያሳፍራል።

ሁለተኛ፣ ጀዋር ለመሪነት፣ ለፖለቲከኛነትም ሆነ ለተንታኝነት ብቁ ነው። ለጸሐፊነትም ብቁ ነው። በሶስት ቋንቋዎች ፍሱሕ ሆኖ መናገር ይችላል። እውቀቱ በጣም ሰፊ ነው። ስለፖለቲካ ሳይንስ ብቻ ሳይሆን ስለሌሎች ፊልዶችም ብዙ አንብቧል። ከበርካታ የታሪክ አውራዎቻችን ጋር እየተገናኘ የአንደኛ ደረጃ መረጃዎችን ሰብስቧል።

እርግጥ ጀዋር በአሁኑ ጊዜ ባላወቅነው ምክንያት ዝም ብሏል። ቢሆንም ዝም ማለት መብቱ ነው። ስለዚህ ተናገር ብለን አንጎተጉተውም። ያለፈውን ገድሉን እያስታወስን ዛሬም እናከብረዋለን። ዛሬም እናሞግሰዋለን።
-----
ጀዋርን የሚዘልፉት!

ስለእነርሱ ለመናገር እና ለመጻፍ አፍራለሁ። ነገር ግን በፖለቲካው ረገድ ሁላቸውም ቢደመሩ የጀዋርን የሩብ ሩብ አይሆኑም።

ዛሬ ጀዋርን ለማንጓጠጥና ለመዝለፍ አፋቸውን ያሞጠሞጡት ዋልጌዎች እና ምንደኞች ሚዛን የማይደፉ አሜኬላዎች መሆናቸው የተጋለጠው ጀዋር ታስሮ በቆየበት ወቅት ነው። በዚያ ወቅት ምን የሰሩት ነገር አለ? የወያኔ ኮርቻ መሆናቸውን ከማሳየት ውጪ አንድም ቁም ነገር አልሰሩም።
-----
አፈንዲ እና ጀዋር

እዚህ ኢንተርኔት ላይ ከሚወዛገበው ጀማ በፊት ነው ጀዋርን የማውቀው። ከሁልሽም በፊት ነው የምናውቀው። እኔ የተወለድኩበት ገለምሶ (ሀረርጌ) እና እርሱ የተወለደባት ዱሙጋ (አርሲ) 65 ኪሎሜትር ብቻ ነው የሚራራቁት። በዕድሜ እኔ በስድስት ዓመት ያህል ብበልጠውም የአንድ ዘመን ሰዎች ነን።

ብዙዎች እንደሚያስቡት ታዲያ እኔ እና ጀዋር በአመለካከታችን 100% ተመሳሳይ አይደለንም። በመካከላችን ብዙ ልዩነቶች አሉ (እኔ "ኤርትራዊ" መሆኔንም አስታውሱ)። ነገር ግን የሚያቀራርበን ነገር ይበልጣል። ልዩነት ማለት ደግሞ ጠላትነት አይደለም። ደግሞ ሳትደርስብህ የሚደርስብህና ስምህን እያጠፋ ነገር የሚፈልግህ ሰው ጠላት ብቻ ሳይሆን "ጭቶ ሚልኪ" ነው።
-----
አፈንዲ ሙተቂ
መስከረም 9/2015

Address

Shashamene, Awasho, 01
Shashemene

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jawaarummaa-Jawaariizimii -ጀዋሪነት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Jawaarummaa-Jawaariizimii -ጀዋሪነት:

Share

Category