ተመረሮት የበጎ አድራጎት ማህበር Temererot Charity Association

  • Home
  • Ethiopia
  • Kibet
  • ተመረሮት የበጎ አድራጎት ማህበር Temererot Charity Association

ተመረሮት የበጎ አድራጎት ማህበር Temererot Charity Association Charity association

 #ማስታወቂያ #ኢትዮ- #ላይት  #የሶፍትዌር  #ኩባንያኢትዮ ላይት የሶፍትዌር ኩባንያ የርስዎን የሶፍትዌር ፍላጎት ችግሮን በመፍታት ስራዎን ሊያቀልሎት እና ዘመናዊነትን ሊያገንፅፍዎ በውቢቷና...
21/04/2026

#ማስታወቂያ
#ኢትዮ- #ላይት #የሶፍትዌር #ኩባንያ

ኢትዮ ላይት የሶፍትዌር ኩባንያ የርስዎን የሶፍትዌር ፍላጎት ችግሮን በመፍታት ስራዎን ሊያቀልሎት እና ዘመናዊነትን ሊያገንፅፍዎ በውቢቷና በሰላም ሰገነቷ ወራቤ የብዙ ዓመት ልምድ ባካበቱ የሶፍትዌር ኢንጂነሮች ስራ መጀመሩን ሲገልፅ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል።

ኢትዮ ላይት እንደስሙ ብርሃንን ይዞ ለተለያዩ ተቋማት እና የድርጅት ባለቤቶች ዘመኑን የዋጁና ዘመኑ የደረሰበትን የመጨረሻው ቴክኖሎጂ በመጠቀም ስራ ለማቅለል የሶፍትዌር ባለቤት በማድረግ የቴክኖሎጂ ብርሃንን ይዞ ከተፍ ብሏል።

ስለዚህ ከርስዎ የሚጠበቀው ከታች በምናስቀምጥልዎ ስልክ መደወልና ማዘዝ አሊያም ወደ ቢሯችን በመምጣት ለድርጅትዎ የሚፈልጉትን ሶፍትዌር ኪስ በማይጎዳ በተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝና ኑሮዎን ማቅለል ነው።

ኢትዮ-ላይት ምን አገልግሎቶችን ይሰጣል ?

👉ሶፍትዌር ማበልፀግ
① የክሊኒክና፣ ፋርማሲ እና መድኃኒት የጅምላ ሽያጭ ሲስተም
② ድህረገፅ ማበልፀግ
③ዴስክቶፕ አፕልኬሽን ማበልፀግ
④ሞባይል አፕልኬሽን ማበልፀግ
⑤ኢ-ለርኒንግ ስርኣት ማበልፀግ
👉ለማንኛውም ድርጅት ሶፍትዌር ማበልፀግ
👉ሶፍትዌር መጫንና ጥገና
👉የኔትወርክ ዝርጋታ
👉የደህንነት ካሜራ ዝርጋታ
👉የቴክኖሎጂ ስራዎችን ማማከር
👉ሎጎ ዲዛይን
👉አጫጭር ስልጠናዎች
① ኮዲንግ
② መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠናዎች

👌ማሳሰቢያ: ክሊነክ እና ፋርማሲ ያላችሁ እጃችን ላይ የተዘጋጀ የክሊኒክ እና የፋሰርማሲ ሲስተም ስላለን ለጊዜው በዲስካውንት እየሸጥን ስለሆነ ፈጥነው ይደውሉ እድሉን ይጠቀሙ

👉 ከላይ ያያዝናቸው ፎቶዎች ከዚህ በፊት ሶፍትዌር ያበለፀግንላቸው ተቋማት ከብዙዎቹ ለ Sample ያክል የወሰድናቸው ናቸው

🌏 አድራሻ፡- ወራቤ ዱና ሀያው መንገድ ላይ ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ መታጠፊያ

☎️ስልክ፡- 0912 28 11 74/ 0919 21 08 67/ 0926 07 22 37/ 0913252582
ኢትዮ-ላይት የሶፍትዌር ኩባንያ

ተመረሮት በጎ አድራጎት ማህበር ለ63 አቅመደካሞች የረመዷን አስቤዛ አከፋፈለ።ተመረሮት ኮሚኒኬሽን የካቲት 09/2018አሰላሙዐለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህእንኳን 1447 ዓ/ሂ የረመዷን ፆም...
19/02/2026

ተመረሮት በጎ አድራጎት ማህበር ለ63 አቅመደካሞች የረመዷን አስቤዛ አከፋፈለ።

ተመረሮት ኮሚኒኬሽን
የካቲት 09/2018

አሰላሙዐለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ

እንኳን 1447 ዓ/ሂ የረመዷን ፆም በሰላም አደረሳችሁ

ረመዷን ሙባረክ

ተመረሮት በጎ አድራጎት ማህበር ዛሬ እለተ ሰኞ የካቲት 09/2018 ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ካሉ ከአካባቢው ወጣቶችና የማህበሩ አባላት ጋር በመተባበር ከመቶ ሺ ብር በላይ የሚገመት ብር ወጪ በማድረግ ለ63 (ስልሳ ሶስት) አቅመደካሞች የረመዷን አስቤዛ አከፋፈለ።

ተመረሮት በጎ አድራጎት ማህበር ለአቅመደካሞች በየአመቱ አቅመደካሞች የረመዷን ድጋፍ እንደሚያደርግ ይታወቃል። ዘንድሮም በ 2018 ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ካሉ ከአካባቢው ወጣቶችና የማህበሩ አባላት ጋር በመተባበር ለ63 አቅመደካሞች ማከፋፈል ተችሏል።

በዚህም መርሓግብር ለአንድ ቤተሰብ 8 ኪሎ ቅንጬ እና አንድ ሊትር ዘይት ማከፋፈል ተችሏል።

ይህ ድጋፍ የተከናወነው የተመረሮት በጎ አድራጎት ማህበር አባላት እና የማህበሩ ደጋፊዎች ከሰበሰቡት ድጋፍ ነው። የማህበሩ አባላት በየወሩ ቋሚ መዋጮ የሚያደርጉ ሲሆን ማህበሩ ድጋፎችን የሚያደርገው ከዚህ መዋጮ፣ለረመዷን እና ለተለያዩ በዓላት ከሚሰበሰበስ ገንዘብና ማህበሩን ከሚደግፉ ደጋግ ግለሰቦች ጋር በመተባበር ነው።

የበጎ አድራጎት ማህበሩ ከዚህም ቀደም ብሎ ዘርፈ ብዙ የበጎና የልማት ተግባራት ላይ ሲሳተፍ ቆይቷል። ከዚህ በፊት ከተከናወኑ የበጎና የልማት ስራዎች መካከል መንገድ የማስተካከል፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር፣ በሴቶችና ህፃናት ላይ ፆታዊ ትንኮሳ እንዳይደርስ ሰላም የማስከበር፣ በረመዳን ማፍጠሪያ ለሌላቸው ድጋፍ፣ በኢድ ማክበሪያ ለሌላቸው ድጋፍ፣ መታከሚያ ለሌላቸው የመታከሚያ ድጋፍ፣ ቤት ለሌላቸው ቤት መገንባት፣ ደብተርና እስክሪብቶ ማሟላት ለማችይችሉ ተማሪዎች ድጋፍ እና የመሳሰሉት ድጋፎች ከብዙ በጥቂቱ ለአብነት ያክል መጥቀስ ይቻላል።

ማህበሩ ለወደፊት ከዚህም በላይ ለመስራት ራዕይ ያለው ሲሆን መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ማህበሩ ያለመው ዓላማና ራዕይ ያሳካ ዘንድ ከጎኑ ይሆኑ ዘንድ በዚሁ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን።

በዚሁ አጋጣሚ ለዚህ መሳካት ትብብር ያደረጋችሁ ሁሉ በተለይም የማህበሩ አባላት፣ ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያላችሁ የማህበሩ ደጋፊዎች በማህበሩና በአባላቱ ስም ለማመስገን እንወዳለን። አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁ!! ጀዛኩሙላሁ ኸይረን ወባረከላሁ ፊኩም !!!

የማህበሩ አባል ለመሆን የሚከተለውን ሊንክ ጆይን ያድርጉ
1. Telegram: t.me/temerarot
2. Tiktok: temererot.charity

ማህበሩን ለመደገፍ ከፈለጉ በማህበሩ ስም በተከፈተ የንግድ ባንክ ቁጥር

የማህበሩ አካውንት ቁጥር/ንግድ ባንክ👇👇

1000504873416
የትመረሮት በጎ አድራጎት ማህበር
ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ

// አቅመደካሞችን በጋራ እንታደግ//
ተመረሮት በጎ አድራጎት ማህበር

ተመረሮት በጎ አድራጎት ማህበር 15,000ብር ለአባታችን ሳሎ ባርጊቾ ህክምና በቲክታክ Live ኒያ አድርጓልማሻ አላህ ማሻ አላህአላሁ አክበር አላሁ አክበር
13/02/2026

ተመረሮት በጎ አድራጎት ማህበር 15,000ብር ለአባታችን ሳሎ ባርጊቾ ህክምና በቲክታክ Live ኒያ አድርጓል

ማሻ አላህ ማሻ አላህ

አላሁ አክበር አላሁ አክበር

27/01/2026

ለአቶ ሳሎ ባርጊቾ ገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌግራም ግሩፕ
Join አድርጉ

27/01/2026



አቶ ሳሎ ባርጊቾ ነዋሪነቱ ስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር አጎዴ ቀበሌ ሲሆን ለብዙ ዘመናት የቀበሌ አመራር ሆኖ ህብረተሰቡን እያገለገለ የነበረ ሲሆን እንዲሁም እንዲሁም ህመሙ እስኪጥለው ድረስ ቅበት ከተማ አስተዳደር አጎዴ ቀበሌ ምክትል ሊቀመንበር በመሆን እያገለገለ ቆይቷል።

በዚህ ሁኔታ ባለበት ነው እንግዲህ ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከአገልግሎት ውጪ የሆኑት(fail ያደረጉት)

ዛሬ በኩላሊት ህመም እየተሰቃየ የሚገኘው አባታችን አቶ ሳሎ ባርጊቾ የዛሬ አያድርገውና ከመታመሙ በፊት ደግ፣ ቅን እንዲሁም ለሰው አዛኝ እና ሩህሩህ ከመሆኑ የተነሳ የአካባቢው ማህበረሰብ "የደነብ ሼክ" በሚል መጠሪያ ስም ሲጠራው ቆይቷል።

አቶ ሳሎ ባርጊቾ በደረሰበት የኩላሊት ህመም ሁለቱም ኩላሊቶች ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ከ2015 ዓል ጀምሮ ከወራቤ ኮ/ስ/ሆ ሪፈር ተፅፎለት አዲስ አበባ ሲ.ኤም.ሲ አጠቃላይ ሆስፒታልከዚያም ወደ ኢትዮ ጠቢብ አጠቃላይ ሆስፒታል ተዛውሮ ለብዙ ወራት ፅኑ ህሙማን ክፍል ተኝቶ የታከመ ሲሆን ከታመመበት ግዜ ጀምሮ ትንሽ ሲያገግም ወደቤተሰብ እየተመለሰ ህመሙ ሲብስበት አአ የጠቀስናቸው ሆስፒታሎች ላይ እየተመላለሰ ቆይቶ ወራቤ ሂስፒታል የኩላሊት እጥበት/dialesis ሲጀምር ወደ ወራቤ በመዛወር ህክምናውን በመከታተል ላይ ይገኛል።

አባታችን አቶ ሳሎ ባርጊቾ ወደ ወራቤ ሆስፒታል በመመላለስ በሳምንት ሶስት ግዜ ለአንድ እጥበት ብቻ 5000/አምስት ሺህ ብር እንዲሁም ለመድሃኒት ብቻ 6000/ስድስት ሺህ ብር በመክፈል የኩላሊት እጥበት/dialesis በማድረግ ያለውን ገንዘብና ንብረት ጨርሶ የወገን ደራሽ ወገን ነውና እጁን ወደናንተ ደጋግ ወንድሞችና አህቶች እጁን ዘርግቷል።

ስለሆነም ውድና የተከበራችሁ ወንድምና እህቶች “አንዲትን ነፍስ ያዳነ ሰዎችን ባጠቃላይ እንደማዳን“ ነውና አቶ ሳሎ ባርጊቾ ነፍስ ለማዳን ከፊታችን ቅዳሜ (23/05/2018) ጀምር ለተከታታይ ሰባት ቀናት አጎዴ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ስለተያዘ ሁላችሁም በቀጠሮው ቀን መኖሪያ ቤቱ ላይ በመገኘት አቅማችሁ የፈቀደውን ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ በአላህ ስም እንማፀናችኋለን።

በአካል ለመገኘት የማትችሉ በወንድሞቹ (ሸረፋ ባርጊቾ፣ አብዶ ባርጊቾ እና ኢስማኢል ባሙድ) በጣምራ በተከፈተው የንግድ ባንክ ቁጥር
1000742285247
ገቢ ማድረግ ትችላለችሁ።

ለምታደርጉልኝ ድጋፍ ከወዲሁ አመሰግናለሁ፣ ጀዛኩሙላሁ ኸይረን ይላችኋል።
አባታችን አቶ ሳሎ ባርጊቾ!!
አላህ ከእንደዚህ አይነት አደጋ ይጠብቃችሁ!! አሚን!!

አድራሻ፦ ቅበት ከተማ አስተዳደር አጎዴ ቀበሌ መንደር 1 ከጥቁር አስፓልት ገባ ብሎ ወደ ሀረ-ሸይጣን ሀይቅ መሄጃ መንገድ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር
0920 97 34 51
0912 91 34 21
ይደውሉ

Address

Kibet

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ተመረሮት የበጎ አድራጎት ማህበር Temererot Charity Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category