21/12/2023
'' ሆመቾን በጋራ እናልማ ''!! ይላል በሶስት ሰው ጣምራ ፊርማ የሚንቀሳቀስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ስያሜው።
የበለፀገ ሀሳብ ሀገርን ይገነባል።የምንኖራት ሀገር የምትለማውም የምትጎሳቀለውም በኛ ሀሳብ ነው። የሚጠበቅን ልትለግስ ስትጀምር ከመልካም ሀሳብ ጀምር።ምክንያቱም ጥሩ ሀሳብ ከምትሰጠው ንዋይ እጅጉን ይበልጣል።
እናንተ ደጋግ የሀሳብ ባለቤቶች ሆይ ተባረኩ። ምክንያቱም ሆመቾን እንድታድግ ከኔ ይጀምር ማለታችሁን በተግባር አሳይታችሁዋልና።ከጥቂት ቀን በፊት የሆመቾን የውጭ ማብራት በውዛ ለማስገባት አካውንት ከፍተን እንመለሳለን ባልኩት መሠረት እነሆ በሶስት የአከባቢው ተወላጆች አማካይነት ተከፍቷል።
አካውንቱ በስማቸው ያስከፈትነው ባለ ራዕዮች ስራው ከኛ ይጀምር በሚል:-
1ኛ. እረሽ ሀዱሞ የሁለት በውዛ ዋጋ 5600 ብር ገቢ አድርጓል።
2ኛ. ታገሰ ጋታ የሁለት በውዛ ዋጋ 5600 ብር ገቢ አድርጓል።
3ኛ. መስፍን ላጲሶ የአንድ በውዛ ዋጋ 2800 ብር ገቢ አድርጓል።
4ኛ. ደምበሎ ቢካጎ የአንድ በውዛ ዋጋ 2800 ብር ገቢ አድርጓል።
5ኛ. ጌታብቻ ደጀኔ የአንድ በውዛ ዋጋ 2800 ብር ገቢ አድርጓል።
6ኛ. ሰለሞን ታምሬ የአንድ በውዛ ዋጋ 2800 ብር ገቢ አድርጓል።
ይህ ገቢ በሺዎች በሚቆጠሩ በአከባቢያችን ቀና አሳቢዎች ይቀጥለል።ካለኛ ለኛ አከባቢ የሚያስብ የለምና በዚህ መልካም ተግባር ለመሳተፍ ለጠየቃችሁን አካውንት ቁጥሩን ከዚህ በታች መለጠፋችንን እያሳወቅን ላላችሁ ቀና ሀሳብ ከወዲሁ ልናመሰግናችሁ እንወዳል።
ደቡብ አፍሪካ ያላችሁ ውድ ወንድሞቻችን ለከተማችሁ ለከተማችን ያላችሁን ተቆርቃሪነት እያመሠገንን ከዚህ በፊት በተነጋገርነው መሠረት ተሳትፎዋችሁን እንድትጀምሩ እየነገርናችሁ ያደረጋችሁን አስተዋጽኦ ህዝቡ እንዲያመሰግናችሁ በዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ስማችሁን ከመለጠፍም በላይ ሙሉ መረጃችሁን ወስደን በአከባቢያችን ባሉ ልማት ናፋቂ ሽማግሌዎች እንደምናስመርቃችሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።
ሀገር ውስጥ ያላችሁ ወንድም እህቶቼ ከዚህ በፊት ለሠጣችሁ ልባዊ ሀሳብ ከልብ ለማመስገን እንወዳለን። ሆመቾን ለማልማት ያላችሁን ሀሳብ አምጡ።ምክንያቱም የእድገት ቁንጮ ሀሳብ ነው።ያለኛለዚህች ከተማ የሚንቀሳቀስ የለም እያልኩ በአካውንቱ በልባችሁ የመጣውን ማስገባት እንደምትችሉ እየገለጽን ያስገባችሁትን የባንክ አስሊፕ ወይም በሞባይል ባንክንግ ከሆነ ስክሪን ሹት በማድረግ በውስጥ መስመር እንድትልኩልን እናሳስባለን።
ሆመቾን በቅርብ ጊዜያት እንደምናለማት አልጠራጠርም።
==== ተባረኩ ====