Mesfin Tadesse Lawyer

Mesfin Tadesse Lawyer በፌዴራልና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማናቸውም ፍርድ ቤቶች የጥብቅና እና ማማከር አገልግሎት እንሰጣለን።

01/02/2026
‎ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ:- እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!
07/01/2026

‎ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ:-
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

06/10/2024

Big shout out to my newest top fans! Kalkidan Workineh, Teshale Ayele

17/09/2024

በዝምታ የሚናገሩት የሥነ-ሕይወቱ ሊቅ፤
ፖለቲከኛው ታጋይ፣ ባለውለታችን ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ።
***
(ሄኖክ ስዩም - ለድሬ ቲዩብ)

ቤተሰቦቻቸው ለኢትዮጵያ የጠቀሙ ኢትዮጵያውያንን አበርክተዋል። የጴጥሮስ ልጆች የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው። ለኢትዮጵያ የኖሩ፣ ባለውለታዎቻችን።

ዝምተኛው ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በፀጥታቸው የሚጮሁ፣ በዝምታቸው የሚደመጡ፤ ሹመት ሳይኾን እምነት በቦታቸው ያፀናቸው። ላመኑበት የኖሩ ድንቅ ሰው።

ለሃድያ ህዝብ ክብር አለኝ። በተለይ በተደጋጋሚ የሚደርስበትን ጫና ተቋቁሞ እንደ ሀገር የመታገል ምሳሌ ጭምር የሚባሉትን ፕሮፌሰር በየነ ይወክሉኛል ብሎ መርጦ ሌላ መወከል በሚያስፈራበት ሰዓት ካከበርነው ፓለቲከኛ ጋር አስተዋውቀውናል።
ሰውዬው በፓለቲካው መድረክ አደባባይ ወጥተው ሲታዩ ላብራቶሪው ውስጥ የሙያቸውን አበርክተው ነበር። የ Tropical Diseases ተመራማሪው በየነ ወደ ፓለቲካል ኢኮኖሚው አደባባይ ሲመጡ ኤችአይቪ/ኤድስ እና ሳምባ ነቀርሳ ላይ የሚያደርጉትን ጥናት ሜዳ ሳይበትኑ ነበር። እንደ ፌዴራሊዝሙ የወባ በሽታን ያጠኑ፣ ለሰው ብቻ ሳይሆን ለሰው ህዋስ ጭምር ቅርብ የነበሩ የሳይንስ ሰው።

ፓርላማ ገብተው ለሀገራቸው ይበጃል ያሉትን የሚናገሩት እና የሚፅፉት ፕሮፌሰር በየነ የተማርንበትን Introductory to Basic Biology አዘጋጅተው ለህትመት ያበቁ መምህር ናቸው።

ስራቸውን አክባሪ፤ ተማሪዎቻቸው ጥንቅቅ ብለው የሚመጡ በሚል ከዝግጅታቸው የተነሳ የሚያደንቋቸው መምህር፣ ቀዳሚው የሥነ ሕይወት ትምህርት ክፍል ባልደረባ፣ ረዥም ዘመን በትምህርት ክፍሉ የጀርባ አጥንት የነበሩ ባለውለታ።

የዛሬ 75 ዓመት በገራዶቹ ምድር ሾኔ ጉያ ባለችው ገጠር የተወለዱት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሥነ ሕይወት ሰው ናቸው። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በባዮሎጂ ከወሰዱ በኋላ በሳይንሱ ተወስደው ቀጠሉ። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አሜሪካን ሀገር ከሚገኘው ዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲም የወሰዱት ሁለተኛ ዲግሪ በዚሁ የጥናት መስክ ነበር። ከዚያም በህዝብ ጤና አጠባበቅ እና በተላላፊ በሽታዎች የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በሀገረ አሜሪካ ከቱለን ዩኒቨርሲቲ ተቀበሉ፡፡

በፓለቲካው መድረክ ያለ ድካም የምናያቸው ፕሮፌሰር በየነ አርባ አምስት ዓመታት ለሚጠጋ ዕድሜ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባዮሎጂ መምህር ኾነው ያለ መጉደል በመኖር ነው።

የፓለቲካ ሰዎች የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት ሲሉ ይገልጿቸዋል። ያነሱት የላብራቶሪ መሳሪያ ነው። ከዚያ ሌላ ደግሞ ለሀገሬ ይበጃል ያሉትን ሀሳብ።

ዝምታቸው የሚናገር ድፍረታቸው የሚያስገርም ትጋታቸው የሚያስቀናው ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ሀገር ካስተማረቻቸው ሙያ ለሀገር በሚል ሳይነጠሉ ማስተማር ከመብት ትግል ሳይጣላባቸው ኖረዋል። ፓለቲካ ጠብ በኾነበት ባህላችን ሀሳብ እንጂ ጠላትነት መርሃቸው ሳይኾን ሰክነው አስክነዋል።

ከብዙ ጠንካራ ተመራማሪዎች ጀርባ የእሳቸው አብሮነት አለ። ጥናትና ምርምሮችን በመምራት እና በማስተባበር ለውጤት ያበቋቸው ምርምሮች ብዙ ናቸው። በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ጆርናሎች የሥነ ህይወት ሳይንስ ዘርፍ ላይ ላወጧቸው የምርምር ህትመቶችና የማስተማር አበርክቷቸው። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷቸዋል።
በእርግጥም ሀገራቸውን ይወዱ ነበር። ለሀገራቸውም ኖረዋል። በሙያቸው ሀገር አኑረዋል። ለተበደለ ድምፅ ሆነዋል።

የሚበድል ሥርዓትን በሰለጠነ ፓለቲካ ታግለዋል። ሞኝ ወይም ፈሪ አልነበሩም፤ ፍርሃትን አሽቀንጥረው የአደባባይ ፓለቲከኛ፣ የክፍል ውስጥ መምህር፣ የላብራቶሪ ሳይንቲስት በመሆን ለአመኑበት ኖረዋል። በኢትዮጵያ ጉዳይ ተስፋ የማይቆርጡት ምሁር ስለ ኢትዮጵያ ደክመው አሁን ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ለቤተሰቦቻቸው፣ ለተማሪዎቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው፣ ለሀገራቸው መጽናናት ይሁን።

እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2017 ዓ/ም በሠላም እና በጤና አደረሰን። አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ዓመት ይሁንልን።
11/09/2024

እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2017 ዓ/ም በሠላም እና በጤና አደረሰን። አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ዓመት ይሁንልን።

✍️የፍርድ_ተቃውሞ_ክስ_(Opposition)_የፍ/ሥ/ሥ/ህ ቁ 358=================================ወደ ክርክር መግባት ያለበት አካል በክርክሩ ተሳታፊ ሳይሆን የተወሰነው ...
10/09/2024

✍️የፍርድ_ተቃውሞ_ክስ_(Opposition)_የፍ/ሥ/ሥ/ህ ቁ 358
=================================
ወደ ክርክር መግባት ያለበት አካል በክርክሩ ተሳታፊ ሳይሆን የተወሰነው ውሣኔ መብቱን የሚነካ ሆኖ ሲገኝ ውሣኔው ከመፈፀሙ በፊት ውሣኔው እንዲነሳና ክርክሩ እርሱ ባለበት እንዲቀጥል መጠየቅ ይችላል።
የፍርድ ተቃውሞ ክስ የሚቀርበው በግራ ቀኙ መካከል በነበረው ዋናው ክርክር በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 41 መሠረት ጣልቃ ገብቶ መከራከር የነበረበት ነገር ግን በግራ ቀኙ መካከል ክርክር ስደረግ በማያውቅ ሰው ነው።

ምን አይነት ፋራ አጭበርባሪ ነው? እባካችሁ ጥንቃቄ እናድርግ።
27/07/2024

ምን አይነት ፋራ አጭበርባሪ ነው?
እባካችሁ ጥንቃቄ እናድርግ።

👉 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክረምቱ የዳኞች እረፍት ወቅት(ከነሐሴ 01 እስከ መስከረም 30 ድረስ) በተረኛ ችሎቶች የሚታዩ ጉዳዮችን ለሥር የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ከዚህ...
21/07/2024

👉 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክረምቱ የዳኞች እረፍት ወቅት(ከነሐሴ 01 እስከ መስከረም 30 ድረስ) በተረኛ ችሎቶች የሚታዩ ጉዳዮችን ለሥር የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ከዚህ በታች በተለጠፈው ደብደቤ አሳውቋል።

18/07/2024

ሰ/መ/ቁ.180389፡-የፌደራል መንግስት አስፈፀሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀፅ 13(1)(ሸ) የሀይማኖት ድርጅቶችን የመመዝገብ ስልጣን የፌደራል መንግስት አካል ለሆነው የፌደራል የሰላም ሚኒስቴር የተሠጠ ስለመሆኑ ተደንግጓል። በዚህም መሰረት የሀይማኖት ተቋማትን የመመዝገብ ስልጣን ለፌደራል መንግስቱ አስተዳደር አካላት የተሰጠ ስልጣን ከሆነ እነዚህ ተቋማት ተከራካሪ የሆኑበትን ክርክር የመዳኘት ስልጣን የፌደራል መንግሰቱ ስልጣን ይሆናል ማለት ነው።
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 133667 እና 179740 በፌደራል መንግሰቱ አካላት ተመዝጋቢ የሆኑ ተቋሟት ተከራካሪ የሆኑበትን ክርክር የመዳኘት የፌደራል ፍርድ ቤቶች በመሆኑና በክልል ፍርድ ቤቶች የሚታይ ከሆነም የመጀመሪያ ደረጃ የመዳኘት ስልጣን የተሰጠው ለክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ነው ሲል ወስኗል።
በመሆኑም የፌደራል መንግስት አካሉ የመዘገባቸው የሀይማኖት ተቋማት ተሣታፊ የሆኑበትን የይዞታ የሁከት ይወገድልኝ ክርክር የክልል ወረዳ ፍርድ ቤቶች የመዳኘት ስልጣንን የላቸዉም። መስከረም 25 ቀን 2013ዓ/ም

#ማስታወሻ ነገር ግን ትርጉሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን አይጨምርም

ሰ/መ/ቁ.184533/186720፡-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህጋዊ ሰውነት የሚመነጨው ከ1952ቱ የፍትሐ ብሔር ህግ አንቀፅ 398 እንጂ የፌደራል መንግስቱ ተመዝጋቢ አካል አይደለችም። እናም ቤተክርስቲያንዋ ተካፋይ የሆነችበት ክርክር የፌደራል ጉዳይ የሚባል ሳይሆን እንደክርክሩ ዓይነት፣ መጠን እና ቦታ ጉዳዩ በቀረበበት ክልል የሚታይ ይሆናል።

መጋቢት 30/2013 ዓ.ም የተወሰነ በእንዳለ መኮንን

Address

Hossana

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251936212247

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mesfin Tadesse Lawyer posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mesfin Tadesse Lawyer:

Share