Gezahegn Jafaro Desta

Gezahegn Jafaro Desta በሾሻል ሚድያ በቀለጠፈ መልኩ በመጠቀም በዘመነ መንገድ የህዝባችን መሰረታዊ የልማት ጥያቄ እንመልሳለን ሾሻል ሚድያ ፖልትካ ለማራመድ ሳይሆን በቀለጠፈ መልኩ የህዝባችን ጥያቄ ለማመለስ ነው ፡፡

05/08/2026
04/08/2026
የአንድነት እና የደግነት ጥሪ! "እጅ ለእጅ ተያይዘን ለአቶ ሆስሶ ሐሻለ የቤት ጥላ እንሁንለት ወገን !​ወገናችን [ ሆስሶ ሀሻለ] በአሁኑ ወቅት አስቸጋሪ በሚባል ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣...
04/08/2026

የአንድነት እና የደግነት ጥሪ! "እጅ ለእጅ ተያይዘን ለአቶ ሆስሶ ሐሻለ የቤት ጥላ እንሁንለት ወገን !
​ወገናችን [ ሆስሶ ሀሻለ] በአሁኑ ወቅት አስቸጋሪ በሚባል ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ የለበሱት መጠለያ ከዝናብና ከብርድ የሚከላከል አይደለም።
​እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን የምንረዳዳ ወገኖች ነንና፣ ለእነሱ የተሻለና አስተማማኝ የመኖሪያ ቤት ለመሥራት ተነስተናል። ይህን መልካም ዓላማ ከዳር ለማድረስ የእያንዳንዳችን ትንሽ ድጋፍ ትልቅ ለውጥ ያመጣል!
​የምንፈልገው ድጋፍ፦ የገንዘብ፣ የቁሳቁስ (የቆርቆሮ፣ የሲሚንቶ፣ እንጨት...) ወይም የጉልበት ድጋፍ።
​የባንክ ቁጥር፦ 1000784525922
​ለበለጠ መረጃ፦ [0995520921/ 091 419 3974 095 060 6198/091 968 8226 ]​"የሰጡት አይጎድልም፤ ያደረጉት መልካም ነገር ደግሞ ለዘላለም ይኖራል።"
እባክዎ ይህንን መልእክት ለሌሎችም በማጋራት (Share) የወገናችን የቤት ጥላ ይሁኑ!
1000784525922

04/08/2026
16/07/2026
16/07/2026

እንኳን በሰላም ተገላገልሽ!

"ምንም እንኳን የመውለጃዬ ቀን ቢቃረብም “ሀገሬ ጠርታኝ አልቀርም” በማለት ከጋምቤላ ክልል ወደ አዲስ አበባ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመጣችው ወጣት ክርኑዶ ኡጁሉ፣ በጉባኤው ሂደት ላይ እያለች በዘውዲቱ ሆስፒታል ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች።

የሀገር ፍቅር እና የእኔነት ስሜት ሲኖር የማይቻል ነገር አለመኖሩን ማሳያ የሆነችውን ይህችን ጀግና እናት፤ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ ጋር በመሆን ባረፈችበት ቤት በመገኘት እንኳን ደስ አለሽ ብለናታል።
ይህችው ጀግና እናት፤ የተለመደውን ስም የማውጣት ባህል በመተው፣ የልጇን ስም ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ እንዲያወጣላት በጠየቀችው መሰረት የህፃኑን ስም "ምክክር" ብላዋለች።

ዛሬም በሄድንበት ወቅት፣ ወጣቷ የመጣችበትን ታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት ከጥቂት ቀናት እረፍት በኋላ ወደ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በልበ ሙሉነት እንደምትመለስ አረጋግጣልናለች። እኛም ጉባኤውን አጠናቃ ወደ መጣችበት እስክትመለስ ድረስ ለእሷና ለልጇ የሚያስፈልገውን ድጋፍ እናደርግላታለን።

እህታችን ወንድ ልጇን በሰላም ተገላግላ በደስታ እንደተሞላች ሁሉ፤ ኢትዮጵያ ሀገራችንም ከገጠማት አንዳንድ ችግሮች በምክክር እና በንግግር ተገላግላ፣ ትልቅ እና ወሳኝ የሽግግር ምዕራፍ እንደሚሆንላት ፅኑ እምነታችን ነው።

ህፃን ምክክርም፤ እደግ ተመንደግልን! አንተ እና መሰል የኢትዮጵያ ህፃናት ሁሉ ቦርቃችሁ እና ተደስታችሁ የምታድጉባት፣ እንዲሁም የምትረከባት ሀገር ሰላሟ ሙሉ የሆነች፣ የህዝቦች ፍቅር ያበበበት እና የበለፀገች ኢትዮጵያ እንድትሆን ከልብ እንመኛለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

16/07/2026
16/07/2026

አራተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ተጨማሪ ግርማሞገስ የሆነበት ይህች የትከተማ ናት?

16/07/2026

የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ከመቸውም በላይ እጅግ በፍጥነት እየተቀያየረ ሲሆን ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ጠረፍ ተዋሳኝ አገር ለመሆን የምታደርገው የኅልውና ጥረት በመልካም ጉዳና ውስጥ ይገኛል።

የአሰብ ወደብን ጨምሮ ደቡባዊ ቀይ ባህር ለሐቀኛ ባለቤቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይመለሳል !!

[ The Jerusalem Post በዛሬው እለት ያወጣውን ሰፊ ሐተታ አስተያየት መስጫው ስር ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ያንብቡ 👁️]

Address

Hawassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gezahegn Jafaro Desta posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category