28/06/2026
⚖️ ስም ማጥፋት (Defamation) በሕግ ፊት ምን ማለት ነው? ውጤቱስ?
📌 በፍትሐብሔር ሕጋችን መሠረት፦
ስም ማጥፋት ከውል ውጪ (Extra-contractual) ከሚፈጸሙ የጥፋት ዓይነቶች አንዱ ሲሆን፤ የአንድን ሰው ክብር፣ መልካም ስም ወይም ዝና ያላግባብ የሚያሳንስ፣ የሚያጎድፍ ወይም በኅብረተሰቡ ዘንድ ጥርጣሬ ላይ የሚጥል ድርጊት ነው።
📱 ማሳሰቢያ፦ ድርጊቱ በጽሑፍ፣ በንግግር፣ በምልክት ወይም በማንኛውም የሶሻል ሚዲያ መገናኛ ዘዴ ሊፈጸም ይችላል።
🔍 ሊሟሉ የሚገቡ 3 መሠረታዊ መስፈርቶች (ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2109)
ለሶስተኛ ወገን መድረስ (Publication)፦ ወሬው ከከሳሽና ከተከሳሽ ውጭ ለሌላ ሰው መድረስ አለበት።
ሐሰተኝነት (Falsity)፦ የተባለው ነገር ፍጹም ሐሰት መሆኑ መረጋገጥ አለበት።
ከእነዚህ 5 ነጥቦች አንዱ መሆን አለበት፦
❌ ሳይሠራ "ወንጀለኛ ነው" ማለት
❌ በሥራው "ችሎታ ወይም ታማኝነት የለውም" ማለት
❌ ነጋዴን "ዕዳ መክፈል አይችልም" ብሎ ማጠልሸት
❌ "ተላላፊ በሽታ አለበት" ብሎ ማስወራት
❌ "አስነዋሪ ባሕርይ አለው" ብሎ ስም ማጥፋት
💰 ውጤቱ፦ የካሳ ኃላፊነት
📉 የቁስ (የገንዘብ) ካሳ፦ በስም ማጥፋቱ ምክንያት በቀጥታ ለደረሰ የገንዘብ ኪሳራ (ለምሳሌ፡ ደንበኛ ማጣት ወይም ከሥራ መባረር)።
🧠 የሞራል ካሳ፦ ለደረሰበት የአእምሮ ስቃይና የክብር መዋረድ የሚሰጥ ሲሆን፣ በሕጉ የተቀመጠው ጣሪያ 1,000 ብር ነው።
⚖️ በሪዕት (Equity) መወሰን (ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2102)፦ የጉዳቱን መጠን በትክክል ማስላት ባይቻል እንኳ፣ ፍርድ ቤቱ የጉዳቱን ከባድነት አይቶ ፍትሐዊ የካሳ መጠን የመወሰን ሙሉ ሥልጣን አለው (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር መ/ቁ 137918)።
⚠️ ከባድ ማስጠንቀቂያ!
በማኅበራዊ ሚዲያ (Facebook, TikTok...) የሚፈጸሙ የስም ማጥፋት ድርጊቶች በፍትሐብሔር የገንዘብ ካሳ ከማስጠየቅ ባለፈ፣ በወንጀል ሕግ አንቀፅ 613 መሠረት በወንጀል ጭምር ዘብጥያ ሊያስወርዱ ይችላሉ!
⚖️ የሕግ አማካሪ (Law Advisor)