Elias Solomon legal adviser and advocator

Elias Solomon legal adviser and advocator Now a day,am doing business on legal advising,advocating,teaching,preparing many legal documents services with fair price.

29/08/2022
15/07/2022

በአዲስ አበባ ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ ተደረገ:: እንዲህ ዓይነቱን ህገ ወጥነትና አጭበርባሪነትን የመዋጋት ሥራ በሁሉም ቦታ መቀጠል አለበት!!!!

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ያወጣውን የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ውድቅ አደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ÷ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን 2014 የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ዕጣው የተሰረዘውም የከተማ አስተዳደሩ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱ በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ሲጀመር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነት መኖሩ በመረጋገጡ ነው ተብሏል፡፡

በእጣው የሚካተቱት 79 ሺህ ቆጣቢዎች መሆን ሲገባው ÷ ምርመራ ሲደረግ ግን በእጣው ውስጥ የተካተቱት ሰዎች ቁጥር 172 ሺህ መሆኑ ተረጋግጧል ነው ያሉት፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ፥ የህዝብ አመኔታን መቼም ቢሆን አንዘነጋም፤ ክብራችን ህዝብን በፍትሃዊነት ማገልገል ስለሆነ ሌቦችና እምነታቸውን ሽጠው የሚበሉ ሁሉ ለጊዜው ቢታገሉንም አያሸንፉንም፤ እውነት ምንግዜም ታሸንፋለች ብለዋል፡፡

የህዝብን ሀብት በቴክኖሎጂ ውንብድና ከመዘረፍ ማዳን እንደተቻለ ጠቅሰው ፥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ስራ ላይ አጠራጣሪ ጉዳዮች ከገጠሙ ጊዜ አንስቶ በማጣራት ሂደት ለደገፉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ይህ ማለትም 93 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በተጭበረበረ መንገድ ዕጣ በሚወጣባት የቴክኖሎጂ ሲስተም ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 01 ቀን 2014 በወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የዳታ ማጭበርበር ድርጊት በመከሰቱ ሁኔታውን እያጣራ እንደሚገኝ እና በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሆነ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

ከተማ አስተዳደሩ ከ14ኛ ዙር የ20/80 እና ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ባለሙያዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ

በዚህም መሰረት፦

1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነቱ የተነሳ

በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-

1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ

2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን፦ ዳይሬክተር

3ኛ. ሀብታሙ ከበደ፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

4ኛ. ዬሴፍ ሙላት፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

5ኛ. ጌታቸው በሪሁን፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

6ኛ. ቃሲም ከድር፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

7ኛ. ስጦታው ግዛቸው፦ ሶፍትዌሩን ያለማ

8.ኛ. ባየልኝ ረታ፦ ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ

9ኛ. ሚኪያስ ቶሌራ ፦ የቤቶች ኢንፎሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያ

10ኛ .ኩምሳ ቶላ፦ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር

በቀጣይም ሂደቱን እየተከታተለ ለህዝቡ ማድረሱን እንደሚቀጥል ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

15/07/2022


⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
የቀበሌ ቤትን የተከራየ ማንኛውም ሰው በሞት ሲለይ ወይም ከአካባቢው በተለያየ ምክንያት ሲለቅ ቤቱን ለቤቶችና አስተዳደር ቢሮ እንዲመልስ ይደረጋል።ሆኖም ሟች በተከራየው ቤት ውስጥ የሚከተሉት ፦👇⚖️
1/ 🎯የተከራይ ሚስት ወይም ባል ስለመሆናቸው ሕጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ሲቀርብ ቤቱን መረከብ ይችላል ።

2/ 🎯የተከራይ ልጆችና በሕጋዊ መንገድ በጉዲፈቻ ያደጉ ልጆች በቤቱ ውስጥ እየኖሩ ስለመሆናቸው በወረዳው ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ሲረጋገጥ ቤቱን የሚረከቡ ይሆናል።

3/ 🎯ዕድሚያቸው ከ18 ዓመት በታች ሆነው በቤት ውስጥ መኖር የጀመሩና ሟች እስከሞተበት ቀን ድረስ ቤት ውስጥ ከወላጆቻቸው ተለይተው እንደ ልጅ መኖራቸው በወረዳው የቤተሰብ አባላት መመዝገቢያ ቅፅ ውስጥ መመዝገቡ ሲረጋገጥ ቤቱን የሚረከቡ ይሆናል።

4/🎯በችግር ምክንያት ከተከራይ ጋር በጥገኝነት የሚኖር የባል ወይም የሚስት እናት ወይም አባት ስለመሆናቸው በቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ሲረጋገጥ ቤቱን ሊረከቡ ይችላሉ።

5/ 🎯 ከላይ ከ 1-4 የተገለፁት ሁሉ ወራሾች ስለመሆናቸውና በስማቸው ወይም በትዳር አጋራቸው ስም የጋራ መኖሪያ ቤት፣የግል መኖሪያ ቤት ፣የቤት መስሪያ ቦታ ከመንግሥት የተከራዩት ቤት የሌላቸው ወይም ከ1997 ዓ.ም ቡኃላ ቤት በሽያጭ ወይም በስጦታ ያላስተላለፋ መሆኑ በማስረጃ ሲረጋገጥ ቤቱን በቀድሞ ኪራይ ተመን መሠረት በአዲስ ውል እንዲከራዩ እነዚህ ሰዋች ይፈቀድላቸዋል ማለት ነው ።
ተከራይሚስትለባልንጀራው፣ለልጅ፣ለሞግዚት፣የኪራይ ውል በስሙ እንዲያድሱለት ህጋዊ ውክልና መስጠት ይችላል።ነገር ግን ተከራይ ከነዚህ አካላት ውጪ ለሌላ ወገን በውክልና ስም ቤቱን አስተላልፎ አምስት አመትና ከዚያ በላይ በቤት ውስጥ ካልኖረ የቤት ኪራይ ውል እንዲቋረጥ በማድረግ መንግስት ቤቱን ይረከባል ማለት ነው።ይህም የመንግስት ቤቶች አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 5/2011 ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል።
Lawyer.Henok Taye
ለተጨማሪ መረጃ በtelegram 👇🎯
https://t.me/HenokTayeLawoffice

23/06/2022

ጠበቆች ሊለይዋቸው የሚገቡ አራት የደንበኛ ዓይነቶች - “ጀማሪ” ደንበኛ
Liku Worku Jan 11 2022


ጠበቆች ከደንበኞቻቸው፣ ከፍርድ ቤት፣ ከፍትሕ ሥርዓት እና ከሌሎች የሥራ ባልደረቦች(ጠበቆች) ጋር ያላቸው ግንኙነት ለጥብቅና ሙያ ሥነ-ምግባር መሠረት ሲሆኑ እነዚህን ግንኙነቶች ጠንቅቆ መረዳት የጥብቅና ሙያ ኃላፊነትን በአግባቡ ለመረዳት ይረዳል።

ይህ ጽሑፍ ጠበቆች ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመረዳት የሚያስችል ስለደንበኞች ዓይነቶች ለመጠቆም የተዘጋጀ ነው። በዚህ ጽሑፍ የምድብ አንድ የደንበኛ ዓይነት “ጀማሪ ደንበኛ/ባለጉዳይ” የሚለውን ለማየት እንሞክራለን። ምንም እንኳን ሁሉም ደንበኞች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አራት ምድቦች ውስጥ በትክክል የሚገጣጠሙ ባይሆንም ደንበኞች ከሚያሳዩት ጸባይ እና ተነሳሽነት ደንበኞችን በአራት መመደብ ይችላል።

የጠበቃ እና የደንበኛ ግንኙነት የሚመሰረተው ጠበቃ የጠበቃ አገልግሎትን ለሚፈልግ ሰው የሕግ እርዳታ ለመስጠት ሲስማማ ነው። የጠበቃ-ደንበኛ ግንኙነት ብዙ ገፅታዎች ያሉት ሲሆን ደንበኞችን አስመልክቶ ሁለቱ መሠረታዊ የጠበቃ ግዴታዎች ብቃት ያለው የሙያ አገልግሎት መስጠትና እና ይህንን ተግባር በትጋት የመሥራት ኃላፊነት ናቸው።

ጠበቆች የደንበኛ ዓይነቶችን መረዳታቸው ለደንበኞች አያያዝ እና አስተዳደር ጠቃሚ ችሎታን ይጨምርላቸዋል። የተለያዩ ደንበኞችን ጸባይን መረዳት ዓመታትን ሊወስድ ይችላል፣ ስለዚህ ከተለመዱ ደንበኞች በስተጀርባ ያሉትን መሠረታዊ ነገሮች ማወቅ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።

“ጀማሪ” ደንበኛ
ይህ ባለጉዳይ ከጠበቆች ጋር ልምድ የሌለው ነው፤ በመሆኑም ስለሕግ፣ ስለሚጠይቀው ወይም ስለሚጠየቀው ጉዳይ፣ ስለፍርድ ቤት፣ ስለጠበቃና ደንበኛ ግንኙነት የሚየውቀው ነገር የለም። በአጠቃላይ ይህ ባለጉዳይ ለሕግ ዘርፉ አዲስ ነው። በዚህም ምክንያት ሕግ እና ለሕግ ሥነ-ሥርዓት ፍርሐት አላቸው። በጉዳዩ በደረጃው ሁሉ ሁሉንም ነገር ማየት እና መጠየቅ ይፈልጋሉ፤ በትንሽ ነገር ይደሰታሉ፤ በጥቃቅን ነገር ይበሳጫሉ።

እንዲህ ዓይነቱን ባለጉዳይ መረዳት አስፈላጊ ነው። ጉዳያቸው ቀላል እና አስደሳች ቢሆን እንኳን እነዚህ ባለጉዳዮች በጣም አድካሚና አሰልቺዎች ናቸው። እንደዚህ ዓይነት ደንበኞችን ለመርዳት ምርጡ መንገድ ሁሉንም ነገር በዝርዝር ማብራራት ነው። ለሕጻን ልጅ እንደማስረዳት ሁሉንም ነገር ማስረዳት ተገቢ ነው። ለዚህ ነው እንደዚህ ዓይነት ደንበኞች አድካሚና አሰልቺዎች የሚሆኑት። በእያንዳንዱ ደረጃ በትዕግስት ነገሮችን ማብራራት ያስፈልጋል፤ በዚህ ደረጃ ነገሮችን ካላብራሩ ስለጉዳዩ መሠረታዊ የሆነ መረጃ እንኳን ለማግኘት ይቸገራሉ፤ እና ለጉዳይዎ ተጨማሪ መረጃ የሚያመጡልዎትን ጥያቄዎችን ለማንሳት እድሉን የሚያገኙት በየደረጃው በሚደረግ ማብራሪያ ነው። ይህንን ማብራሪያ የማያደርጉ ከሆነ እንደ ደካማ ጠበቃ ይቆጠራሉ።

ስለጉዳዩ በዝርዝር የሚጠየቁትን ትተን የሚከተሉትን አሰልቺ ጥያቄዎች ለመመለስ መዘጋጀት አለብዎት፦


ክሱ ለምን እዚህኛው ፍርድ ቤት ሆነ? ለምን የዳኝነት ይከፈላል? ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት እንደጠበቃ ገንዘብ ይቀባለል? አይቀንስም? ይህንን ክፍያ በኋላ ፍርድ ቤቱ ይመልስልኛል? ስንት ዳኞችና ናቸው ጉዳዩን የሚያዩት? በስንት ጊዜ ውሳኔ ይሰጣሉ? ውሳኔ የሚሰጥበት ቁርጥ ያለ ጊዜ ልትነግረን ትችላለህ? ከዳኞችም ሱፍ ለምን አይለብሱም? ለምን ዳኛው ቢሮ ውስጥ ጠራህ/አስተናገደህ? ፍርድ ቤቶች ሽንት ቤት የላቸውም? ፍርድ ቤቱ የቀጠረን ሰዓት ለምን አያከብርም? ለምርመራ ምን ማለት ነው? አሁንም ቀጠሮ? ቃል ክርክር ምን ማለት ነው? አዲስ ማስረጃ ማስገባት አይቻለም? ለምን ዳኛው ጋር ሔደን በዝርዝር ጉዳዩን እንዲረዳ አናደርገውም? ጉዳዩን የሚያየው አንድ ዳኛ ብቻ ነው? ለምን ሌሎች ዳኞች አላዩትም? ችሎት ጸሐፊ ምንድነው? ሬጂስትራርስ? አቤቱታ ምንድነው? የአቤቱታ ቀን ለምን ሁሉ ጊዜ አይሆንም? ጠበቆች ለምን ፕሮቶኮል አይጠብቁም? ጠበቆችም እንደባለጉዳይ ነው ሚታዩት? ጠበቃዬ እስከሆንክ ለምን ይህንንም ጉዳይ አታማክረኝም? ከተከራካሪ ወገን ጠበቃ ጋር ለምን ትነጋገራለህ? ጉዳዩን ለምን በዝርዝር ለፍርድ ቤቱ አልተናገርክም? ሌላኛው ጠበቃ ሁለቴ ተናግሮ አንተ አንድ ጊዜ ብቻ ለምን ተናገርክ? ስልክህን ለምን አታነሳም? በፈለኩህ ጊዜ ላገኝህ አልቻልኩም፥ ምን ይሻላል? ………. ወዘተ


እነዚህና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እየመለስክ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ባለጉዳዩንም ስለሕግ እና ስለሥነ-ሥርዓት እያሰለጠንክ ካልሔድክ መጨረሻህ አያምርም። ጀማሪ ደንበኞች/ባለጉዳዮች ከላይ የተመለከተው አንድ የሚያደርጋቸው ጸባይ ቢኖርም የተለያዩ ዓይነቶች ናቸው። ለምሳሌ፦ እርግጠኛ ያልሆኑ ባለጉዳዮች፣ አጣዳፊ ባለጉዳዮች፣ ምላሽ የማይሰጡ ባለጉዳዮች፣ ከእውነት የራቁ ባለጉዳዮች፣ ስሜታዊ ባለጉዳዮች፣ ስለወጪ በጣም የሚጨነቁ ባለጉዳዮች፣ ስራዎን በቅርበት የሚከታተሉ ባለጉዳዮች፣ ቆራጥ ወይም አጋዥ ባለጉዳዮች ሊሆኑ ይችላሉ።

በመሆኑም ባለጉዳይዎ ጀማሪ መሆኑን የተረዱ እንደሆነ በዋናው ጉዳይ ላይ ከሚያጠፉት ጊዜ በላይ እንደባለጉዳዩ ዐይነት ዝርዝር ምላሽ መስጠት እና ባለጉዳዩን መያዝ እንዴት እንዳለበዎት መረዳት ያስፈልጋል።

17/06/2022

TAXATION BLOG
በማሻሻያ አዋጅ 1160/2011 በጉምሩክ ወንጀሎች ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች
By Wondiye Birhanu
አዋጅ ቁጥር-1160/2011 የጉምሩክ አዋጅ 859/2006 ማሻሻያ አዋጅ ሲሆን በዚህ አዋጅ የጉምሩክ አዋጅ 859/2006 ውስጥ ባሉት አንዳንድ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡ ከተደረጉ ማሻሻያዎች በዋናነት የሚጠቀሰው በአከራካሪ የወንጀል ድንጋጌዎች ላይ የተደረገው ማሻሻያ ሲሆን በዚህ ፅሁፍ በማሻሻያ አዋጁ የተሸሩ፣የተሸሻሉና እንደ አዲስ የተካተቱ የወንጀል ድንጋጌዎች አጠር ባለመልኩ ተዳሰዋል፡፡

1. የኮንትሮባንድ ወንጀል፡-

2. በድብቅ ወይም ከህጋዊ መተላለፊያ መስመር ውጪ[1]/smuggling or out of legal route/

በጉምሩክ ማሻሻያ አዋጅ 1160/2011 መሰረት መሻሻያ ከተደረገባቸው አንዱ የጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 168/1 ነው፡፡

የአዋጅ 859/2006 አንቀፅ 168/1- ድንጋጌ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

“ማንኛውም ሰው እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የጉምሩክ ህጎችን በመተላለፍ የተከለከሉ፣ገደብ የተደረገባቸው ወይም የንግድ መጠን ያላቸውና የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ያልተፈፀመባቸው ዕቃዎችን በድብቅ ወይም ከህጋዊ መተላለፊያ መስመሩ ውጪ ወደ ሀገር ካስገባ፣ከሀገር ካስወጣ፣ከሀገር ለማስገባት፣ወይም ለማስወጣት ከሞከረ፣ወይም በህጋዊ መንገድ የወጡ እቃዎችን በህገ-ወጥ መንገድ መልሶ ካስገባ ከአምስት አመት በማያንስ ከአስር አመት በማይበልጥና ከ50 ሺ-200 ሺ በሆነ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል”

ከላይ በተመለከተው የህግ ድንጋጌ ውስጥ ያለው “በድብቅ ወይም ከህጋዊ መተላለፊያ መስመሩ ውጪ” የሚለው ሀረግ በፍርድ ቤት፣በጠበቆችና በአቃቢያነ ህግ መኃከል የክርክር ነጥብ ነበር፡፡ አንድ ሰው በኢትዮጵያ አየርመንገድና በመሳሰሉት ህጋዊ የመተላለፊያ መስመሮች ወደ ጉምሩክ ክልል ዕቃ ይዞ ቢገባ፣የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ያልተፈፀመበት ህጋዊ ዕቃ በኪሱ ይዞ በነዚህ ህጋዊ የጉምሩክ መተላለፊያ መስመር ላይ ቢያዝ ይዞ የተገኘው ዕቃ ደበቀ ሊባል ይችላል?---የሚለው ጉዳይ የክርክር ነጥብ የነበረ ሲሆን በአጠቃላይ የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ያልተፈፀመባቸውን ዕቃዎች ሳይደብቅ ወደ ጉምሩክ ክልል ገብተው የሚያዙ መንገደኞችን በሚመለከት ድንጋጌው የክርክር መነሻ ነበር፡፡


በጠቅላይ ዕቃቤ ህግ በኩል ሲቀርብ የነበረው ክርከር መደበቅ ማለት ከታክስ ስርዓት መደበቅ(smuggling) እንጂ አካላዊ መደበቅ(concealing) ባለመሆኑ መታየት ያለበት እቃው በተለምዶ መደበቅ በሚባል ሁኔታ(act of concealing) ወደ ጉምሩክ ክልል መግባት አለመግባቱ ሳይሆን ቀረጥና ታክስ የተከፈለበት መሆን አለመሆኑ ነው በሚል ነበር፡፡ በዚህ ክርክር መሰረት ወደ ጉምሩክ ክልል የገባ ማንኛውም ዕቃ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለበት ከሆነ እንደተደበቀ እቃ ይቆጠራል፡፡

በጉምሩክ ማሻሻያ አዋጅ 1160/2011 አንቀፅ 44 መሰረት የአዋጅ 859/2006 አንቀፅ 168/1 ሙሉ በሙሉ የተሰረዘ ሲሆን በማሻሻያ አዋጁ የክርክር መነሻ የነበረው በድብቅ ወይም ከህጋዊ መተላለፊያ መስመሩ ውጪ የሚለው ሀረግ ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
በአዋጅ 859/2006 መሰረት በአንቀፅ 168/1 ጥፋተኛ የተባለ ሰው ከ5-10 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከ50 ሺ-200 ሺ ብር በሆነ የገንዘብ መቀጮ የሚቀጣ ሲሆን በማሻሻያ አዋጅ 1160/2019 አንቀፅ 44 መሰረት በቅጣት ላይ ማሻሻያ አልተደረገም፡፡
የጉምሩክ ማሻሻያ አዋጅ 1160/2011 አንቀፅ 44 ወይም አዲሱ አንቀፅ 168/1 የኮንትሮባንድን ወንጀል እንደሚከተለው ደንግጎታል፡-
“ማንኛውም ሰው ይህን አዋጅ ወይም ባለስልጣኑ የሚያስፈፅማቸውን ሌሎች ህጎች ወይም በእነዚሁ ህጐች መሰረት የወጡ ደንቦችን ወይም መመሪያዎችን በመተላለፍ የተከለከለ፣ ገደብ የተደረገበት ወይም የጉምሩክ ሥነ ስርዓት ያልተፈፀመበት ዕቃ ወደ ጉምሩክ ክልል ያስገባ ወይም ከጉምሩክ ክልል ያስወጣ ወይም ለማስወጣት ወይም ለማስገባት የሞከረ ወይም በህጋዊ መንገድ የወጣውን ዕቃ በህገ ወጥ መንገድ መልሶ ያስገባ እንደሆነ የዕቃው መወረስ እንደተጠበቀ ሆኖ ከብር 50 ሺ- 200ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮና ከአምስት እስከ አሥር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል”



2. የጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀል



ሌላኛው ማሻሻያ የተደረገበት የወንጀል ድንጋጌ የጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 169 ላይ የተመለከተው የጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀል ተግባር ሲሆን በአዋጅ 1160/2011 አንቀጽ 45 እና 46 መሠረት የተደረጉ ማሻሻያዎችና እንደ አዲስ የተካተቱ ንዑስ አንቀፆች እንደሚከለው ቀርቧል፡፡



የተከለከለ ዕቃን በሚመለከት[2]


ማንኛውም ሰው ክልከላ የተደረገበት ዕቃ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የተከለከለን ዕቃ በህጋዊ ዕቃ ከላላነት ወደ ጉምሩክ ክልል ይዞ መግባት/ማስገባትና ማስወጣት፣ለማስገባትና ማስወጣት የሞከር እንደሆነ የወንጀል ተግባር የፈፀመ ስለ መሆኑ በአዋጅ 859/2006 አንቀፅ 169/1 ላይ ተደንግጎ የነበረ ሲሆን ድርጊቱ መፈፀሙ በፍርድ ቤት ከተረጋገጠ ከ5-10 በሆነ ፅኑ እስራትና ከ50 ሺ-200 ሺ ብር በሆነ የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል፡፡ ሆኖም በረቂቅ አዋጅ ላይ ቅጣትን በሚመለከት ማሻሻያ እንዲደረግበት ሀሳብ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም ማሻሻያ አዋጁ ሲፀድቅ በአንቀፅ 169/1 ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ አልተደረገም፡፡



ተደብቆ የተገኘ እቃ


ሌላኛው የጉምሩክ ማጭበርበር ተግባር ክልከላ ከተደረገባቸው ዕቃዎች ውጭ ያሉትን ተደብቀው የሚገኙ ሌሎች ዕቃዎችን የሚመለከት ሲሆን ይህም በአዋጅ 859/2006 አንቀፅ 169/2 በግልፅ ተደንግጎ ነበር፡፡



በአዋጅ 859/2006 አንቀፅ 169/2 ላይ እንደተመለከተው፡-



“ተደብቆ የተገኘው ዕቃ ዋጋ በዴክለራሲዮን ላይ ከተገለፀው ጠቅላላ ዋጋ 50 በመቶ በላይ ሆኖ ከተገኘ ዕቃዎችን በመደበቅ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት የሞከረ ማንኛውም ሰው ከ5-10 አመት ፅኑ እስራትና ከ50ሺ-100 ሺ በሆነ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል”

ከአዋጅ 859/2006 አንቀፅ 169/1 እና 169/2 መረዳት የሚቻለው ማንኛውም ሰው በህጋዊ ዕቃ ከላላነት ክልከላ የተደረገበትን፣ገደብ የተደረገበትን[3]ና የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ያልተፈፀመበትን ዕቃ ይዞ ወደ ጉምሩክ ክልል የገባ/ያስወጣ፣ለማስገባትና ለማስወጣት የሞከረ እንደሆነና እቃው ገደብ የተደረገበትና መግለጫ ያልተሰጠበት/የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ያልተፈፀመበት በሚሆንበት ግዜ የዕቃው ዋጋ በዴክለራሲዮን ከተገለጣ ጠቅላላ ዋጋ ከ50% በላይ ሲሆን በጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑ ነው፡፡


አንቀፅ 169/2 ላይ ያከራክር የነበረው የንፅፅር መሰረት(base) ቀረጥና ታክስ መሆኑ ቀርቶ ዋጋ መሆኑ ሲሆን ተደብቆ የተገኘው ዕቃ በፐርሰንት ለማስቀመጥ በሚደረግ ስሌትም ተደብቆ የተገኘው ዕቃ ከ50 ፐርሰንት በላይ መሆኑ የሚታወቀው ከተያዘው ጠቅላላ ዕቃ ዋጋ ጋር ነው ወይስ የተደበቀው ከስሌት ወጥቶ በዴክለረሲዮን ላይ ከነበረው ዋጋ ጋር ነው የሚለው ነጥብ የክርክር መነሻ ነበር፡፡

ሆኖም አዋጅ 859/2006ን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ 1160/2011 አንቀፅ 45 ላይ እነዚህ የክርክር ነጥቦች መፍትሔ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በአንቀፅ 45 ላይ በተተካው አዲስ አንቀፅ 169/2 እንደተመለከተው፡-

“ማንኛውም ሰው በዲክላራሲዮን ያልተመዘገበ ወይም ትክክለኛ መግለጫ ያልተሰጠበት ዕቃ በህጋዊ ዕቃ ከለላነት ወደ አገር ውስጥ ያስገባ ወይም ወደ ውጪ የላከ ወይም ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ወይም ከአገር ለማስወጣት የሞከረ እንደሆነ የተገኘው የቀረጥና ታክስ ልዩነት ህጋዊ በሆነው ዕቃ ላይ ከተከፈለው ወይም ሊከፈል ከሚገባው ጋር ሲነፃፀር ከሃምሣ በመቶ በላይ ከሆነ እና በልዩነት የተገኘው ቀረጥና ታክስ መጠን ከብር አንድ ሚሊዬን በላይ ከሆነ ከሦስት እስከ አምስት በሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል”

ከአዋጅ 1160/2011 አንቀፅ 45-(169/2) ላይ መረዳት እንደሚቻለው የንፅፅር መሠረት ዋጋ ሳይሆነ ቀረጥና ታክስ ነው፡፡
ሌላኛው አዲስ የተተካውን አንቀፅ 169/2 ድንጋጌ ለየት ሚያደርገው ንፅፅርን የሚመለከት ሲሆን በአዲሱ ህግ መሰረት በዴክለራሲዮን ላይ ያልተመዘገበው ዕቃ ወይም ትክክለኛ መግለጫ ያልተሰጠበት ዕቃ ቀረጥና ታክስ የሚነፃፀራው ህጋዊ በሆነው ዕቃ ላይ ከተከፈለው ወይም ሊከፈል ከሚገባው ቀረጥና ታክስ ጋር መሆኑ ነው፡፡
በአዋጅ 859/2006 አንቀፅ 169/2 መሰረት የንፅፅር ግኝት ከ50% በላይ ሲሆን በወንጀል የሚያስጠይቅ ሲሆን አዲስ በተተካው አንቀፅ 169/2 መሰረት ደግሞ የንፅፅሩ ግኝት ከ50% በላይ መሆን በራሱ የወንጀል ክስ ለማቅረብ በቂ አይደለም፡፡ በንፅፅሩ በልዩነት የተገኘው ቀረጥና ታክስ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ሊሆን ይገባል፡፡ መግለጫ ሳይሰጥበት የተገኘው ዕቃ ቀረጥና ታክስ መግለጫ ከተሰጠበት ዕቃ አንፃር በፐርሰንት ሲሰላ ቀረጥና ታክሱ ከ50% በላይ ሆኖ በገንዘብ ግን ሲታይ ከአንድ ሚሊዮን ብር በታች ከሆነ የወንጀል ተግባር አይሆንም፣የሚቀርብ የወንጀል ክስም አይኖርም፡፡
ሌላኛው የተሻሻለው ነጥብ ቅጣት ሲሆን በተሻራው አንቀጽ 169/2 መሰረት ፍርድ ቤት የወንጀል ተግባሩ መፈፀሙን ሲያረጋግጥ ከ5-10 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና ከ50ሺ-100ሺ የገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ ሲሆን በአዲሱ ማሻሻያ የገንዘብ መቀጮ ቀሪ የተደረገ ሲሆን የእስራት ቅጣቱም ቀንሶ ከ3 እስከ 5 አመት ፅኑ እስራት ሆኖ ተደንግጓል፡፡


አዲስ የተካተቱ ንዑስ አንቀፆች
ከቀረጥ ነፃ ጋር የተያያዙ የማጭበርበር ተግባራት
የአዋጅ 859/2006 አንቀፅ 169 ሁለት ንዑስ አንቀፆችን ብቻ ይዞ የነበረ ሲሆን በአዋጅ 1160/2011 አንቀፅ 45 እና 46 መሰረት የተሸሻለው አንቀፅ 169 ግን 5 ንዑስ አንቀፆችን ይዟል፡፡

አዲስ በአዋጅ 1160/2011 መሰረት ከተካተቱ የጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀሎች ውስጥ ሁለቱ የቀረጥ ነፃ መብትን የሚመለከቱ ሲሆን ሌላኛው ሀሰተኛ ሰንደን የሚመለከት ነው፡፡

169/3፡-

‘‘ማንኛውም ሰው የቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ሳይኖረው የቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ያለው በማስመሰል በማንኛውም የተጭበረበረ ሁኔታ ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት ዕቃን ወደ ጉምሩክ ክልል ያስገባ/ያስወጣ፣ለማስገባትና ለማስወጣት የሞከረ እንደሆነ 7-10 አመት እና ከ 100 ሺ-200 ሺ በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል’’

ይህ ድንጋጌ በዋናነት ከቀረጥ ነፃ መብት ጋር የተያያዘ ሲሆን ማንኛውም ሰው ቀረጥ ነፃ መብት ሳይኖረው ማንኛውንም የማጭበርበር ተግባራትን ተጠቅሞ ማለትም ሀሰተኛ የቀረጥ ነጻ መብት ስልጣን ካለው አካል የተሰጠ ስለመሆኑ የሚያሳዩ ሰነዶችን በማዘጋጀትና በማቅረብ አቅራቢው ህጋዊ የቀረጥ ነጻ መብት ያለው በማስመሰል ቀረጥና ታክስ ሳይከፈል ዕቃን ወደ ጉምሩክ ክልል ያስገባ/ያስወጣ፣ለማስገባትና ለማስወጣት የመሞከር ተግባር የሚመለከት ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ድንጋጌ በቀረጥ ነፃ ላይ የሚፈፀም የጉምሩክ ማጭበርበር ተግባርን የሚመለከት ነው፡፡
ሌላኛው ከቀረጥ ነፃ ጋር የሚገኝ የጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀል በማሻሻያ አዋጅ 1160 /2011 አንቀፅ 46-(169/5) ላይ የተመለከተው ሲሆን በዚህ ንዑስ አንቀፅ መሰረት የእንቨስትመንት ዕቃን ከቀረጥና ታክስ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ ማንኛውም ሰው፡-
ተመሳሳይ መብት ለሌለው ሶስተኛ ወገን ያስተላለፈ፣የሸጠ፣ያከራየ፣መብቱ ከተሰጠበት ዓላማ ውጭ አገልግሎት ላይ ያዋለ እንደሆነ፣
ለእንቨስትመንት ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ለሽያጭ አከማችቶ የተገኘ እንደሆነ፣
ቅጣት፡-የዕቃው ውርስ እንደተጠበቀ ሆኖ ከ 5-7 አመት በሚሆን ፅኑ እስራት እና በ200 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡


በሀሰተኛ ሰነዶች የሚፈፀም የጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀሎች


የጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀሎች ለጉምሩክ ስነ-ስርዓት በሚቀርቡ ሀሰተኛ ሰነዶች፣መግለጫዎች፣መረጃዎችና ሌሎች የማጭበርበር ዘዴዎች ሊፈፀም ይችላል፡፡

ከሀሰተኛ ሰነድ ጋር ተያይዞ የሚፈፀም የጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀሎች በማሻሻያ አዋጅ 1160/2011 አንቀፅ 169/4 ላይ የተካተተ ሲሆን የድንጋጌው ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

አንቀፅ 169/4፡- ማንኛውም ሰው፡-

ማንኛውም ሰው ሊከፈል የሚገባውን ቀረጥና ታከስ ላለመክፈል ወይም ለማሳነስ በማሰብ፣

ሀሰተኛ ሰነድ ለጉምሩክ ስነ-ስርዓት አፈፃፀም ማቅረብ፣
ሀሰተኛ መረጃ ወይም መግለጫ ለጉምሩክ ያቀረበ፣
ለጉምሩክ የሚቀርቡ ሰነዶችን የሰረዘ፣የደለዘ፣የፋቀ ወይም አስመስሎ የሰራ፣
ሌሎች መንኛውም የማጭበርበር ተግባር የሰራ እንደሆነ፣
ቅጣት፡- ከአምስት ዓመት በማያንስና ከአስር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና በብር 200ሺህ የገንዘብ መቀጫ ይቀጣል፡፡
በአጠቃላይ ከተደረገው ማሻሻያ መረዳት እንደሚቻለው የጉምሩክ መሻሻያ አዋጅ 1160/2011 ከዚህ በፊት በዐቃቤ ህግና በጉምሩክ ኮሚሽን/ገቢዎች ሚኒስተር፣በፍርድ ቤት፣ዐቃቤ ህግና ጠበቆች መኃከል የክርክር መነሻ የነበሩትን ነጥቦችን ግልጽነት በተሞላበት ሁኔታ ያካተተና ወንጀልነቱ ቀሪ ተደርጎ ከነበረው ከቀረጥ ነፃ መብት ጋር በተያያዘ ይነሱ ለነበሩት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥ በመሆኑ ስራ ላይ ያለውን አዋጅ 859/2006ን ሙሉ በማድረግ የጉምሩክ ህግ ፍትሓዊነትና ተገዢነትን ከማረጋገጥ አንፃር በጎ ተፅኖ ይኖረዋል፡፡



[1]የጉምሩክ መተላለፊያ መስመር በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 2/17 ላይ ትርጉም የተሰጠው ሲሆን በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ያሉ ገቢና ወጪ ዕቃዎች እንዲጓጓዙበት በባለስልጣኑ የተወሰነ ማናቸውም መንገድ ነው፡፡

[2] የተከለከለ ዕቃ ለሚለው ሀገረግ በአዋጅ 859/2006 አንቀፅ 2/30 ትርጉም የተሰጠው ሲሆን በኢትዮጵያ ህግ ወይም ኢትጵያ ባፀደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ፣ከሀገር እንዳይወጡ ወይም እንዳይተላለፍ የተከለከለ ማንኛውም ዕቃ ማለት ነው፡፡

[3] ገደብ የተደረገበት ዕቃ በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 2/31 ላይ ትርጉም የተሰጠው ሲሆን በህግ በተደነገገ ስነ-ስርዓት መሰረት ስልጣን ባለው አካል በተሰጠ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ወደ ሀገር እንዳይገባ. ወይም እንዳይወጣ ወይም እንዳይተላለፍ ገደብ የተደረገበት ዕቃ ነው፡፡
, መልካም ንባብ

29/04/2022

#የውል ማሻሻያ

ተዋዋይ ወገኖች በተለያየ ጊዜና በተለያዩ ምክንያቶች ለህግና ለሞራል ተቃራኒ ካልሆነ፣ ሊተገበር የሚችል ከሆነ እና ተያያዥ ምክንያቶች ቀድሞ የነበረው ውል በመለወጥ ማሻሻል ይችላሉ፡፡

በመሆኑም ተዋዋይ ወገኖች ውል ለማሻሻል ወደመስሪያቤታችን ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

መረጃውን ለሌሎች እንዲደርስ በማድረግ ተቋሙ አላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት እንዲሁም ብልሹ አሰራር ለማስቀረት እያደረገ ያለውን ጥረት ያግዙ ፡፡

• በተቋሙ የDARIS ስርዓት የተዘጋጀ እና የሚሞላ ሰነድ ወይም የአገልግሎት ቁጥር፤
•ቀደም ሲል የተመዘገበው ወይም የሚሻሻለው የውል ሰነድ፤
•ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤(ውክልና)
•የተዋዋዮች ጊዜው ያላለፈበት ወይም በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
•ውሉ የሚሻሻለው የማይንቀሳቀስ ንብረት ማስተላለፍ ውልን በሚመለከት ሲሆን ሁለት ምስክሮች እና የታደሰ መታወቂያቸው፤

•የተዋዋዮች ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፣
•የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ እና ቀደም ሲል የተመዘገበው ወይም የሚሻሻለው ቃለ-ጉባኤ ወይም የውል ሰነድ፤
ተገልጋዮች ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች(መረጃዎች) ሙሉ በሙሉ አሟልተው ሲመጡ ውሉን ለማጠናቀቅ 25 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉhttps://t.me/Dars_channel

Address

Ethiopia
Harar
ST.S.ROAD

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Elias Solomon legal adviser and advocator posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Elias Solomon legal adviser and advocator:

Share