Birhanu law tendency

Birhanu law tendency Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Birhanu law tendency, Legal, Finote Selam.

ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ ያውቃሉ ?• የህግ ምንነትህግ የሚለው ቃል በማህበረሰቡ ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ቃል ነው፡፡ በተለይ ህግ አስገዳጅ መሆኑን የሚረ...
04/10/2022

ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ ያውቃሉ ?

• የህግ ምንነት

ህግ የሚለው ቃል በማህበረሰቡ ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ቃል ነው፡፡
በተለይ ህግ አስገዳጅ መሆኑን የሚረዳው ለመሆኑ ቀደም ባለው ጊዜ በየዕለት ኑሮ ፀብ ሲገጥመው እንኳን “በህግ አምላክ” ብሎ ፀብ የማብረድ ልምድ የነበረው መሆኑ ማሳያ ነው፡፡ ሆኖም ማህበረሰቡ ህግን የሚረዳው በተለምዶአዊው አረዳድ እንጂ የዘርፉ ባለሞያዎች በሚረዱበት መልኩ አይደለም፡፡

በመሰረቱ ህግ ለሚለው ቃል ትርጓሜ መስጠት ቀላል አይደለም፡፡ ምክንያቱም የተለያዩ ምሁራን ቃሉን በተለያየ መንገድ የሚገልፁት በመሆኑ ነው፡፡ እንዲሁም የቃሉ ፍቺ ሊደረስባቸው በሚፈለጉት የተለያዩ ዓላማዎች ምክንያት ሊለያይ ይችላል።
ለህግ ቃላት ትርጉም በመስጠት የሚታወቀው ብላክስ ሎው የህግ መዝገበ ቃላት በተሻሻለው ስድስተኛ እትሙ (Black’s Law Dictionary, 6th ed.,) ለህግ ትርጉም ሲሰጥ law is “a body of rules of action or conduct prescribed by controlling authority, and having binding legal force, which must be obeyed and followed by citizens subject to sanctions or legal consequence is a law.” ወደ አማርኛ በግርድፉ ሲመለስ ስልጣን ባለው አካል የተደነገገ የተግባር ወይም የምግባር ደንብ እና አስገዳጅ የህግ ኃይል ያለው አካል ነው። ይህንንም ዜጎች ሊታዘዙት እና ሊከተሉት የሚገባ ሆኖ ማዕቀብ ወይም ህጋዊ ውጤት የሚጥል ህግ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

በመሆኑም የአንድ ሀገር ሕግ፡- ሰላምን ለማስጠበቅ፣ ነባራዊ ሁኔታውን ለማስጠበቅ (maintain the status quo)፣ የግለሰብ መብቶችን ለማስጠበቅ፣ አናሳዎችን ከብዙኃን ለመከላከል ( protect minorities against majorities)፣ ማኅበራዊ ፍትህን ለማስፈን( promote social justice) እና ሥርዓት ያለው ማህበራዊ ለውጥ እንዲኖር ለማድረግ( provide for orderly social change) ያገለግላል።

• የህግ መሰረታዊ ባህሪያት
የህጎችን የተለመዱ ባህሪያት እና ተፈጥሮ መፈተሽ የህግ ጽንሰ-ሀሳብን ለመገንዘብ የሚረዳ ሲሆን ከእነዚህ ባህሪያት እና ተፈጥሮዎች መካከል እንደ ወሰኝ ወይም አስፈላጊ የሚታሰቡት አጠቃላይነት(ህግ በሁሉም ሰው ላይ በተመሳሳይነት (uniformity) እና እኩልነትን (Equality) የሚፈፀም መሆኑ)፣ መደበኛነት (ህግ ማህበራዊ ባህሪን በመፍቀድ፣ በማዘዝ ወይም በመከልከል ልማዶችን የሚፈጥር መሆኑ) እና ማዕቀብ ወይም ቅጣትን (ህግን ያላከበረ ቅጣት የሚጠብቀው መሆኑን) ያካትታሉ፡፡

• ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ
በወንጀልም ሆነ በፍትሐ ብሄር ጉዳይ ህጎቹ ስልጣን ባለው የህግ አውጪ አካል ወጥተው ከፀደቁበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንደሚውሉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ዜጎች የህጎቹን መኖር ወይም መውጣት የማወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይኸውም ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም የሚለው የህግ መርህ በላቲን Ignorantia juris non excusat ወይም በእንግሊዘኛ "ignorance of the law excuses not" ከሮማውያን ህግ የተወሰደ ሲሆን ህግን የማያውቅ ሰው ይዘቱን ባለማወቅ ብቻ ህጉን በመተላለፍ ከተጠያቂነት ሊያመልጥ እንደማይችል የሚገልጽ የህግ መርህ ነው። እንዲሁም የህግ ስህተት (mistake of la

Address

Finote Selam

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Birhanu law tendency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category