የጠበቃ ይትባረክ አስፋው ቢሮ The Law Office of Yitbarek Asfaw

  • Home
  • Ethiopia
  • Dire Dawa
  • የጠበቃ ይትባረክ አስፋው ቢሮ The Law Office of Yitbarek Asfaw

የጠበቃ ይትባረክ አስፋው ቢሮ The Law Office of Yitbarek Asfaw Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የጠበቃ ይትባረክ አስፋው ቢሮ The Law Office of Yitbarek Asfaw, Lawyer & Law Firm, Dire Dawa.

እንኳን አደረሠን ወገኖች​Justice was served not by a sword, but by an empty tomb. The resurrection is a reminder that no matter h...
12/04/2026

እንኳን አደረሠን ወገኖች

​Justice was served not by a sword, but by an empty tomb. The resurrection is a reminder that no matter how loud the world’s "guilty" verdict is, God’s vindication is louder.

Happy Easter!

ᴊᴜꜱᴛɪᴄᴇ ɪꜱ ʙʀᴇᴡɪɴɢ. ☕️⚖️
29/12/2025

ᴊᴜꜱᴛɪᴄᴇ ɪꜱ ʙʀᴇᴡɪɴɢ. ☕️⚖️

I read somewhere that "Legal solutions aren't one-size-fits-all. They require focus, patience, and a commitment to excel...
23/12/2025

I read somewhere that "Legal solutions aren't one-size-fits-all. They require focus, patience, and a commitment to excellence."



A Very Blessed Tuesday

𝗧𝗵𝗲 𝗯𝗲𝘀𝘁 𝗮𝗿𝗴𝘂𝗺𝗲𝗻𝘁𝘀 𝗮𝗿𝗲𝗻'𝘁 𝘄𝗼𝗻 𝗶𝗻 𝘁𝗵𝗲 𝗰𝗼𝘂𝗿𝘁𝗿𝗼𝗼𝗺; 𝘁𝗵𝗲𝘆 𝗮𝗿𝗲 𝘄𝗼𝗻 𝗶𝗻 𝘁𝗵𝗲 𝗾𝘂𝗶𝗲𝘁 𝗵𝗼𝘂𝗿𝘀 𝗼𝗳 𝘁𝗵𝗲 𝗺𝗼𝗿𝗻𝗶𝗻𝗴 𝗯𝗲𝗳𝗼𝗿𝗲 𝘁𝗵𝗲 𝘄𝗼𝗿𝗹𝗱 𝘄𝗮𝗸𝗲𝘀 𝘂𝗽...
22/12/2025

𝗧𝗵𝗲 𝗯𝗲𝘀𝘁 𝗮𝗿𝗴𝘂𝗺𝗲𝗻𝘁𝘀 𝗮𝗿𝗲𝗻'𝘁 𝘄𝗼𝗻 𝗶𝗻 𝘁𝗵𝗲 𝗰𝗼𝘂𝗿𝘁𝗿𝗼𝗼𝗺; 𝘁𝗵𝗲𝘆 𝗮𝗿𝗲 𝘄𝗼𝗻 𝗶𝗻 𝘁𝗵𝗲 𝗾𝘂𝗶𝗲𝘁 𝗵𝗼𝘂𝗿𝘀 𝗼𝗳 𝘁𝗵𝗲 𝗺𝗼𝗿𝗻𝗶𝗻𝗴 𝗯𝗲𝗳𝗼𝗿𝗲 𝘁𝗵𝗲 𝘄𝗼𝗿𝗹𝗱 𝘄𝗮𝗸𝗲𝘀 𝘂𝗽. 𝗟𝗲𝘁'𝘀 𝗴𝗲𝘁 𝘁𝗼 𝘄𝗼𝗿𝗸."**

Good Morning Cloudy Dire Dawa

የጠበቃ Meseret Ayalew  የፌዴራል ጠበቆች ማህበር ፕሬዝዳነትነት እንድትሆን  እደግፋለሁ፡፡ ጠበቃ መሠረት አያሌዉ በስራዋ ትጉህ፣ ከሙያ አጋሮቿ ጋር ተግባቢ፣ ለፍትህ ጉዳይ በእዉቀት ...
24/11/2025

የጠበቃ Meseret Ayalew የፌዴራል ጠበቆች ማህበር ፕሬዝዳነትነት እንድትሆን እደግፋለሁ፡፡ ጠበቃ መሠረት አያሌዉ በስራዋ ትጉህ፣ ከሙያ አጋሮቿ ጋር ተግባቢ፣ ለፍትህ ጉዳይ በእዉቀት እና ድፍረት የምትቆም ወጣት ነገር ግን በቂ ልምድና ብቃት ያላት ጠበቃ ነች፡፡ አንደበተ-ርቱዕ፣ ቀጥተኛና ፣ አርቃ የምታስብ ጎበዝ ጠበቃ! አብረን በኮሚቴ በሰራንበት ወቅት መሲ ለሙያዉና ለማህሩ ያላትን ሙያዊ ቅናት እንዲሁም የስራ ትጋት ለማየት ችያለሁ፡፡ ለማህሩ ያላት ግልጽና ትልቅ ራዕይ በፕሬዝዳንትነት ብትትረጥ ዉጤተማ እንደምትሆን አያጠራጥርም፡፡ ጠበቃ መሠረት ባለትዳር፣ ልጆች ያሏት በሙያዋም ገና በወጣትነት ዕድሜዋ አንቱ የተባለች መሆኗን ስናይ ለማሀበራችን ፕሬዝዳትነት ከእሷ የተሻለ ማግኘት ይከብዳል፡፡

በመሆኑም መሲን ምረጡ!
በጠበቃ Yitbarek Asfaw

That's truly heartbreaking news. Please accept my deepest condolences for the tragic train accident that occurred last n...
21/10/2025

That's truly heartbreaking news.

Please accept my deepest condolences for the tragic train accident that occurred last night in the Shinile Zone.

​The loss of 14 lives, including the long-serving train driver, Shimeles Birhanu, is a devastating blow to our community. My thoughts are with the families and loved ones of all those who perished, and I hope they can find some measure of comfort during this impossibly difficult time.

​I am also sending my sincere wishes for a full and speedy recovery to the over 29 people who were wounded. May they receive the best possible care.

​The dedication of people like Shimeles Birhanu, who served for so long, won't be forgotten. This is a profound tragedy, and the entire Dire Dawa community grieves with you.

Yitbarek Asfaw

08/08/2025

ጠበቃ፣ ህገ-መንግስታዊ ሙያን የመምረጥ መብትና ታክስ

ይህ አጭር ፅሁፍ ጠበቆች በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት የተረጋገጠላቸውን ሙያቸውን የመምረጥ መብት ከስራቸው ባህሪ አንፃር ከጥብቅና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ፣ ከንግድ ህጉ እና ከሀምሌ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሀምሌ 10/2017ዓ.ም ከፀደቀው የፌደራል ገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንፃር ዳሰሳ ለማድረግና የግል ምልከታን ለማስፈር ነው፡፡ መልካም ንባብ!

በሀገራችን ኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት ውስጥ ለህግ የበላይነትና ፍትህ መስፈን የፍትህ ተቋማት ማለትም ፍ/ቤቶች፣ የዓ/ህግ ፅ/ቤት (ፍትህ ሚኒስቴር)፣ የፖሊስ ተቋም ዋነኛ ተዋናይና ጠበቆች ደግሞ በዚህ ሂደት ውስጥ የማይተካ ሚና እንዳላቸው የሚታወቅ ነው፡፡

የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 41 (2) ሁሉም ኢትዮጵያዊ መተዳደሪያውን፣ ሥራውንና ሙያውን የመምረጥ መብት አለው በማለት በግልፅ ህገ-መንግስታዊ ጥበቃ በማድረግ ደንግጓል፡፡ በዚህም መሰረት በርካታ የህግ ባለሙያዎች ከዳኝነት፣ ከዓቃቤ ህግነት፣ ከነገረፈጅነት እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲ መምህርነት ወደ ጥብቅና አገልግሎት ሙያ ተቀላቅለው ወይም ጎን ለጎን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

የፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀፅ 37 እና ተከታዮቹ አንቀፆች የፀና የጥብቅና ፈቃድ ያላቸው ቢያንስ ሁለት እና ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች አንድ ላይ በመሆን የጥብቅና ድርጅት (LAW FIRM) ማቋቋም እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 47 (1) (ሠ) መሰረት በጥብቅና ድርጅት ውስጥ የሚሰራ ጠበቃ በግል የጥብቅና አገልግሎት መስጠት እንደማይችል ተከልክሏል፡፡

በሌላ በኩል የኢፌዲሪ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀፅ 534 (1) መሰረት ባለአንድ አባል ኃ.የተ.የግ ማህበር መመስረት እንደሚቻል እና ይህም ወደ ስራ እንደተገባ ይታወቃል፡፡ የፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጁ አንቀፅ 39 (5) የጥብቅና ድርጅት የጥብቅና ስራ መስራቱ የንግድ ወይም የኢንቨስትመንት ሥራ እንደማያሰኘው ይደነግጋል፡፡

የፌደራል ገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 መግለጫ ተ.ቁ 4.4 አራተኛ ፓራግራፍ ላይ እንደተገለፀው በሙያ ስራ ላይ የተሰማሩ ግብር ከፋዮች አዕምሮአቸውን ተጠቅምው በአነስተኛ ወጪ ስራቸውን የሚያከናውኑ በመሆኑ እቃ ገዝተው ለሚሸጡ የተዘጋጀው በጠቅላላ ሽያጭ ላይ የተመሰረተው የማስከፈያ ምጣኔ ለሙያ ስራ ተፈፃሚ እንዲሆን ማድረግ ፍትሀዊ አይሆንም፡፡

በዚህም መሰረት የሙያ ስራ የሚሰሩ የሂሳብ መዝገብ አቅርበው ግብር መክፈል እንደሚገባቸው በአዋጁ ረቂቅ (በኋላ በገንዘብ ሚ/ር በኦቪሻል ደብዳቤ ለሚመለከታቸው አካላት የተሰራጨው) ላይ እንደተመለከተ ከደነገገ በኋላ በአንቀፅ 3 ላይ የግብር ከፋይ ደረጃዎች “ሀ” እና “ለ” እንደሆኑ በመደንገግ ዝርዝሩ አዋጁ ላይ የተመለከተ ሲሆን በተጨማሪነትም የህግ አገልግሎት “የቴክኒክ አገልግሎት” በሚል የተካተተ ሲሆን በአዋጁ አንቀፅ 16 (አዲስ አንቀፅ 50) (2) መሰረት የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የግብር አከፋፈል በተመለከተ ግብሩ የሚጣለው እና የሚከፈለው በግብር ዓመቱ ውስጥ ከአገልግሎት ሽያጭ (የጥብቅና አገልግሎትን በተመለከተ) በሰበሰቡት ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ ላይ ነው ይላል፡፡ አንቀፅ 16 (5) መሰረት በህግ ሙያ የተሰማሩ ግብር ከፋዮች በዚህ አዋጅ ለደረጃ “ሀ” የሚጠየቀውን ሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ በአዋጁ አንቀፅ 32 (10) መሰረት ኃ.የተ.የሽ.ማህበር ወይም በሙያ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የሚያወጡት ወጪ ተቀናሽ የሚሆንበት ሁኔታ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ እንደሚወሰን ያስቀምጣል፡፡
የፌደራል ገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ጠበቆችን በተመለከተ በፊት ከነበረው አሰራር የተደረጉ ለውጦች
ጠበቃ በአዋጁ መሰረት ደረጃ “ሀ” ወይም ደረጃ “ለ” ግብር ከፋይ ሆኗል፡፡ ደረጃ “ሐ” በቁርጥ ግብር የሚከፈልበት አሰራር እንዲቀር ሆኗል፡፡

ደረጃ “ሀ” ግብር ከፋይ የጠበቃ ድርጅት ወይም ግለሰብ ጠበቃ ዓመታዊ የአገልግሎት ሽያጭ ገቢው ከብር ሁለት ሚሊየን በላይ የሆነ ሰው እንደሆነ የተመለከተ በመሆኑ ግለሰብ ጠበቃ ዓመታዊ የአገልግሎት ሽያጭ ገቢው ከብር ሁለት ሚሊየን በታች ከሆነ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋይ ነው፡፡ አብዛኛው ጠበቃ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋይ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡

በአዋጁ መሰረት ማናቸውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ አለበት፡፡
ጠበቃ፣ ህገ-መንግስታዊ ሙያን የመምረጥ መብት፣ የንግድ ህጉና የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ፣
ጠበቆች በግለሰብ ደረጃ በፈለጉት አግባብ በግልም በጋራ ሙያቸውን በኢፌዲሪ ህገ-መንግስትአንቀፅ 41 (2) መሰረት የመምረጥ ህገ-መንግስታዊ መብት ያላቸው በመሆኑ በፌደራል ጥብቅና ፈቃድ አስተዳደር አዋጅ አንቀፅ 37 መሰረት የተጣለው የሁለት ሰዎች ቅድመ ሁኔታ/ገደብ/ የጥብቅና ድርጅት የመክፈት ጉዳይ በንግድ ህጉ በተፈቀደው መሰረት ባለአንድ አባል የህግ አገልግሎት (የጥብቅና ድርጅት) በአስቸኳይ ሊፈቀድ ይገባል፡፡ ይህም በህገ-መንግስቱ መሰረት ማንኛውም ሰው የፈለገውን ሙያ የመምረጥ መብት ካለው አንድ ጠበቃ ብቻውን/ብቻዋን የጥብቅና ድርጅት ለማቋቋም ሲፈቀድ በንግድ ህጉ በባለአንድ ሰው ኃ.የተ.የግ.ማህበር በተመለከተው አግባብ ይሆናል፡፡ ይህ ከተፈቀደ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ጉዳይ ከግለሰብ እና ከስራ የባንክ ሂሳብ አጠቃቀም ሂደትና ታክስ አከፋፈል ስርዓት ላይ ወደፊት ሊፈጠሩ የሚችሉ አላስፈላጊ አለመግባባቶችን ያስቀራል፣ የግለሰቦችን ህገ-መንግስታዊ በፈለጉት መንገድ ሙያቸውን የመምረጥና የመስራት መብት ያረጋግጣል፡፡

📌 የመፍትሄ ሀሳብ
የፌደራል ጠበቆች ማህበር ጠበቆች ወይም የጥብቅና ድርጅቶች መብታቸው እንዲከበር እንዲሁም ግዴታቸውን እንዲወጡ የራሱን አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም የፌደራል ገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አተገባበር ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮችን አስቀድሞ መፍትሄ ለመስጠት ይረዳ ዘንድ በአንድ በኩል በተ.ቁ 2 ላይ የተገለፀውን ሀሳብ ቢመለከተው፣ ቢያጤነውና የመፍትሔ እርምጃ ቢወስድ መልካም ነው ባይ ነኝ፡፡ በሌላ በኩል ማህበሩ ከግብር ሰብሳቢው እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ለ2018 የግብር በጀት ዓመት ግለሰቦች ጠበቆች የስራ የባንክ ሂሳባቸውን ወጥ በሆነ መንገድ እንዲከፍቱና እንዲያዝመዘግቡ እና ከግል የባንክ ሂሳባቸው የሚለዩበትን አሰራር እንዲበጅ ስራዎችን ቢሰራና በተረጋጋ መንፈስ የተጣለባቸው ሀላፊነት እንዲወጡ ቢደረግ፣

በፌደራል ገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጁ አንቀፅ 32 (10) መሰረት ኃ.የተ.የሽ.ማህበር ወይም በሙያ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የሚያወጡት ወጪ ተቀናሽ የሚሆንበት ሁኔታ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ እንደሚወሰን በተገለፀው አግባብ ግልፅ የሆነ መመሪያ እንዲወጣ የራሱን አስተዋፅኦ ቢያደርግ፣ የሂሳብ መዝገብ በሚያዝበት ወቅት ደረሰኝ ሳይኖር (ባርኮድ ያለው የእጅ በእጅ ደረሰኝ ህትመት ተጠይቆ ያልደረሰላቸው ወይም ደረሰኝ የሌላቸውን በተመለከተ) የሂሳብ መዝገብ የሚያዝበትና የማይያዝበት አግባብና ተያያዥ ጉዳዮችን ከነሀሴ 01/2017ዓ.ም ጀምሮ የፌደራል ፍ/ቤቶች የከፊል የእረፍት ጊዜ ወቅት የፌደራል ጠበቆች ማህበር በበላይነት ሊመራው፣ ሊከታተለውና ሊያስፈፅመው የሚገባው ጉዳይ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡
* አብዱሰላም ሳዲቅ፤
ጠበቃና የህግ አማካሪ
(LLB, LLM)

06/08/2025
06/08/2025

Address

Dire Dawa

Telephone

+251920494943

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጠበቃ ይትባረክ አስፋው ቢሮ The Law Office of Yitbarek Asfaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share