Seera/ህግ /Law

Seera/ህግ /Law Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Seera/ህግ /Law, Lawyer & Law Firm, Addis Ababa, Dire Dawa.

06/08/2025
26/07/2025
🤣
02/04/2025

🤣

02/04/2025

ከጋብቻ በፊት የነበረ የግል ቤት በትዳር ዉስጥ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ቢደረግለትም የጋራ ንብረት ሊሆን አይገባም፡፡ (የፌደሬሽን ምክር ቤት መስከረም 28-2017 ዓ.ም)

ቀደም ሲል ከጋብቻ በፊት የግል የነበረ ቤት በትዳር ዉስጥ መሰረታዊ በሚባል ደረጃ እድሳት ከተደረገለት ወይም ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ ከተደረገለት ቤቱ የባልና ሚስት የጋራ ይሆናል በማለት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔ ተሰጥቶ ነበር፡፡ ይህ የሰበር ሰሚ ችሎቱ ዉሳኔ ሕገ-መንግስቱን ይቃረናል በሚል የሕገ-መንግስት ትርጉም ለፌደሬሽን ምክር ቤት ቀርቦት የነበር ሲሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ መስከረም 28-2017 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር ተፈጻሚነት የለዉም ብሏል፡፡

ፌደሬሽን ምክር ቤት ዉሳኔ

ከጋብቻ በፊት የግል የነበር ቤት በጋብቻ ዉስጥ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ መደረጉ ቤቱን የጋራ ንብረት አያደርገዉም፡፡ ቤቱን ለማሻሻል እና ለማስፋፋት የወጣ ወጪ ተጣርቶ ወጪዉ በድርሻ እንዲወስዱ ከሚደረግ በስተቀር ቤቱ የጋራ አይሆንም፡፡

⚖️ 𝐌𝐮𝐫𝐭𝐢𝐢 𝐇𝐚𝐚𝐫𝐚𝐰𝐚
𝐌𝐚𝐧𝐧𝐢 𝐌𝐚𝐫𝐞𝐞 𝐅𝐞𝐝𝐞𝐞𝐫𝐞𝐬𝐡𝐢𝐧𝐢𝐢 𝐌𝐅𝐃𝐑𝐈 𝐘𝐚𝐚'𝐢𝐢 𝐅𝐮𝐥𝐛𝐚𝐚𝐧𝐚 𝟐𝟔/𝟐𝟎𝟏𝟕 𝐠𝐚𝐠𝐠𝐞𝐞𝐬𝐬𝐞𝐞 𝐟𝐢 𝐌𝐮𝐫𝐭𝐢𝐢 𝐡𝐢𝐢𝐤𝐤𝐨𝐨 𝐡𝐞𝐞𝐫𝐚𝐚 𝐋𝐚𝐤𝐤.𝟏𝟑𝟎/𝟏𝟔 𝐭𝐚'𝐞𝐞𝐧 𝐤𝐞𝐧𝐧𝐞𝐞𝐧:-
'' Mana Jireenyaa Gaa'ilaan dura horatame hamma fedheeyyuu baasiin guddaan bahee jijjiiramnii irraatti adeemsifayyuu qarshii isa irratti baheetu tilmaamamee adda qooddamu malee manni kun qabeenya waliinii hin ta'u jechuun Murtii Dhaddachi Ijibbaataa Mana Murtii Federaalaa kenne diigee murteessee jira.

01/01/2025

በኢትዮጵያ የወንድ የዘር ፈሳሽ ልገሳ፣ የሰውነት አካል መለገስ እና በህክምና የታገዘ ሞት እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት እና አስተዳድር ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል። አዋጁ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ተጀምረው የማያውቁ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ የጤና አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የሚያደርግ ነው። ለአብነትም መዳን በማይችል እና በስቃይ ውስጥ ያሉ ታማሚዎች በሀኪሞች እርዳታ እንዲሞቱ የሚፈቅደው፣ የሰውነት አካልን ያለ ክፍያ መለገስ፣ የወንድ የዘር ፍሬ እንዲለገስ እና ሌሎችም አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን ይፈቅዳል። ምክር ቤቱ ላለፉት ወራት የተለያዩ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።

05/09/2024
06/08/2024

የሰበር (cassation)፣ ይግባኝ (appeal)፣ እና የፍርድ ክለሳ (judicial review) ልዩነት
====================
በሰ/መ/ቁጥር 214219 ላይ የተሰጠ ትንተና ሆኖ እንደሚከተለው ይቀርባል በመጀመሪያም ተጓዳኝ ጭብጦች ናቸዉ ብለን የያዝናቸዉን ጭብጦች መርምረናል፡፡አንድን የመጨረሻ ዉሳኔ በሰበር በማየት (cassation) ፣ በይግባኝ (appeal) በማየት እና በዳኝነት አይቶ በመከለስ (judicial review) መካከል ያለዉ አንድነትና ልዩነት ምንድነዉ የሚለዉን በቅድሚያ መመልኩቱ ተገቢ ይሆናል፡፡ ከመዝገበ ቃላት ትርጓሜ የተነሳን እንደሆነ ሰበር ወይም cassation በሚል የሚታወቀዉ ቃል በታዋቂዉ ብላክስ ሎዉ መዝገበ ቃላት ላይ እንደተመለከተዉ ካሰር (casser) ከሚል የፈረንሳይኛ ቋንቋ ግስ የመጣ ቃል ሆኖ የቃሉ ጥሬ ትርጉምም የአንድን ፍርድ/ዉሳኔ የተፈጻሚነት ኃይል(force) መስበር እና ሕጋዊ ዉጤት እንዳይኖረዉ ማድረግ (invalidate)፣መሻር ወይም ተግባራዊነቱን ማስቀረት ነዉ የሚል ትርጓሜ የተሰጠዉ ነዉ፡፡ (cassation comes from the French verb casser and its literal meaning is to “quash the force and validity of a judgement.(black’s law dictionary 5ኛ እትም ገጽ 197 ይመለከቷል፡፡) የሰበር ሥርዓት ምንጭ የሲቪል ሕግ ሥርዓት ሲሆን እዛን ግራዊች(Ezan Grouich) የተባለ ሰዉ (The Soviet Codes of Law)በሚል ባሳተሙት መጸሀፋቸዉ ላይ እንደገለጹት በራሽያ ፌዴሬሽን የሰበር ስርዓት የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የሕግ ስህተት ያለበትን የመጨረሻ ፍርድ የተፈጻሚነት ኃይል በመስበር በምትኩ ሌላ ፍርድ የሚሰጥበት ሥርዓት ነዉ ሲል ይገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል Peter Herzos እና Martha Weser እንዲሁም Mauro Cappelletti እና Joseph M. Perillo በፌረንሳይና በጣሊያን የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ላይ እንደቅደም ተከተላቸዉ መጽሐፍት የፃፉ የሕግ ሙሁራን መጽሐፎቻቸዉ ላይ የሰበር ሥርዓት በእነዚህ አገራት አንድ የይግባኝ የሚታይበትን ሂደት የጨረሰ የሕግ ስህተት ያለበት የመጨረሻ ፍርድ የመጨረሻ የዳኝነት አካል በሆነዉ ፍርድ ቤቶቻቸዉ ታይቶ የሚሻርበት ወይም ወደ ሥር ፍርድ ቤት በመመለስ የሚወስኑበት እንጂ የራሳቸዉን አዲስ ዉሳኔ የሚሰጡበት እንዳልሆነ ይገልጻሉ፡፡

ከዚህ የምንገነዘበዉ በሰበር የሚታየዉ በመጨረሻ ፍርድ ቤት እንደሆነ ፣በሰበር የሚታየዉም ፍርድ በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠ ፍርድ ሆኖ በይግባኝ የሚታየበትን ሂደት የጨረሰ የሕግ ስህተት ያለበት የመጨረሻ ፍርድ እንደሆነ እና ፈረንሳይና ጣሊያን የሰበር ፍርድ ቤቶች የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ ከመሻር ባለፈ እንደ ራሺያ ፌዴሬሽን ፍርድ ቤት አዲስ ዉሳኔ እንደማይሰጡ ነዉ፡፡

በአገራችን “ስለሰበር” ምንነት ትርጓሜ የሰጠ ሕግ ባይኖርም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2(4 እና 5) ስለመሠረታዊ የሕግ ስህተት እና ስለመጨረሻ ዉሳኔ ከተሰጠዉ ትርጓሜ የምንገነዘበዉ በሰበር የሚያየዉ የፌዴራሉ የመጨረሻ ዳኝነት አካል በሆነዉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተደራጀ ሰበር ሰሚ ችሎት መሆኑ፣ የሚያያዉም ዉሳኔ በዚሁ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት እና በበታች መደበኛ ፍርድ ቤቶች ታይቶ የተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተትን ብቻ ሳይሆን በሕግ የመዳኘት ሥልጣን በተሰጠዉ አካል፣በተቋማት ወይም በአማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴዎች የተሰጠ እና ለጉዳዩ እልባት የሚሰጥ ፍርድ ፣ብይን፣ትእዛዝ፣ዉሳኔ እና/ወይም የይግባኝ ሂደቶችን የጨረሰ ፍርድ ፣ብይን፣ትእዛዝ ወይም ዉሳኔን እንደሚጨምር ተደንግጓል፡፡እንዲሁም በአገራችን እስካሁን በሰበር ችሎቱ ከዳበረዉ ዳኝነታዊ ፍልስፍና(judicial jurisprudence) እንደሚታወቀዉ ሰበር ችሎት ያለዉ ሥልጣን መሰረታዊ የሕግ ስህተት አርሞ ዉሳኔዉን ከመሻር እና ጭብጥ ይዞ ከመመለስ ባለፈ በጉዳዩ ላይ አዲስ ዉሳኔ የመስጠት ሥልጣን ጭምር እንዳለዉ ነዉ፡፡ ይህም የእኛ አገር የሰበር ሥርዓት ከሌሎች ከላይ ከተጠቀሱት ዉሳኔዎችን በሰበር የማየት ሥርዓት ከዘረጉ አገራት ሥርዓት አንጻር ሲነጻጸር መሰረታዊ የሕግ ስህተት ከማረም አኳያ ሰፊ ሥልጣን እንዳለዉ የሚያስገነዝብ ነዉ፡፡ይህም የሆነዉ በሕገ መንግስቱ ይህ ሥርዓት እንዲዘረጋ መነሻ ምክንያት የሆነዉ የሕግ አተረገጓጎም ወጥነት የማምጣትና በዚህም ዜጎች በእኩልነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ዓላማ በተሟላ መልኩ ከግብ እንዲደርስ ለማድረግ እንደሆነ ይታመናል፡፡

በሌላ በኩል ዳኝነታዊ ክለሳ (judicial review) ከላይ በተጠቀሰዉ መዝገበ ቃላት ላይ፡ A court's power to review the actions of other branches or levels of government; esp.,the courts' power to invalidate legislative and executive actions as being unconstitutional. …And a court's review of a lower court's or an administrative body's factual or legal findings.(black’s law dictionary 9ኛ እትም ገጽ 924). የሚል ትርጓሜ የተሰጠዉ ሲሆን ይህም በግርድፉ ሌሎቹ የመንግስት አካላት (ሕግ አዉጭዉ እና ሕግ አስፈጻሚዉ) እንደቅደምተከተላቸዉ የሚያወጡት ሕግ ፣ የሚፈጽሟቸዉ ተግባራት እና የሚያስተላልፋቸዉ ዉሳኔዎች ሕገ መንግስታዊ መሆን አለመሆናቸዉን (constitutionality) እና ሕጋዊነታቸዉን (legality) ፍርድ ቤቶች የሚከልሱበትንና ጉድለት ካለባቸዉም ተግባራዊ እንዳይሆኑ የሚወስኑበትን ሥርዓት የሚመለከት ነዉ የሚል ይዘት ያለዉ ነዉ፡፡

እንዲሁም ከተለያዩ የሕግ ድርሳናት መገንዘብ እንደሚቻለዉ በዳኝነታዊ ክለሳ (judicial review) የሚታዩ ጉዳዮች እንደየአገራት የሕግ ሥርዓት ሊሰፋና ሊጠብ የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሕግ አዉጪዉ የወጣ ሕግ እና የተላለፈ ዉሳኔ ፣የሕግ አስፈጻሚዉ ወይም የአስተዳደር አካላት ተግባራትና ዉሳኔዎች በዳኝነት አካል የሚከለስበት ሥርዓት በሰፊዉ የሚታወቅ ነዉ፡፡አገራት በሕግ አዉጭዉ የወጣ ሕግ ወይም የተላለፈ ዉሳኔ እንደዚሁም በአስፈጻሚዉ/በአስተዳደር አካል የሚፈጸሙ ተግባራት ወይም የሚተላለፉ ዉሳኔዎችን ሕገ መንግስታዊነት እና/ወይም ሕጋዊነት (Constitutionality and legality) በዳኝነት አይተዉ እንዲከልሱ ለመደበኛ ፍርድ ቤት ወይም ለሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ሥልጣን ይሰጣሉ፡፡ሕገ መንግስትን መተርጎምን የሚጠይቁ የሕገ መንግስታዊነትና ሕጋዊነትን ጥያቄዎችን ተቀብለዉ ሕገ መንግስትን ተርጉመዉ የሕግ አዉጪዉን ሕግና ዉሳኔ እንዲሁም የሕግ አስፈጻሚዉን ሕግ፣ዉሳኔ ወይም ሌላ ተግባር በዳኝነት አይተዉ እንዲከልሱና የመጨረሻ ዉሳኔ ኢንዲሰጡ አሜሪካ እና ሕንድ የመሰሉ አገራት ለመደበኛ ጠቅላይ ፍርድ ቤቶቻቸዉ ሥልጣን የሚሰጡ ሲሆን እንደ ጀርመን ፣ኦስትሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ያሉ አገራት ደግሞ ለሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቶቻቸዉ ሥልጣን ይሰጣሉ፡፡
እነዚህ ፍርድ ቤቶች አንድ ሕግ ወይም አስተዳደራዊ ዉሳኔ ሕገ መንግስቱን የሚጥስ ወይም የሚቃረን እንዲሁም የሕጋዊነት ጉድለት አለበት የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረስ ሕጉን ከሕግነት ተራ በማስወጣት ተፈጻሚ እንዳይሆን ለማድረግ የአስተዳደር ዉሳኔዉም ተግባራዊ እንዳይሆን ለመወሰን የሚከተሉበት

አካሄድም እንደዚሁ የተለያየ ነዉ፡፡ አሜሪካ የዳኝነታዊ ክለሳ የምታደርግበት ሞዴል ያልተማከለ ዳኝነታዊ ክለሳ ሥርዓትን (The decentralized model of judicial review) ሲሆን በዚህ ሞዴል መሰረት የክለሳ ጥያቄዉ ከበታች ፍርድ ቤት ጀምሮ በየደረጃዉ ይግባኝ ሥርዓት በሚመስል አካሄድ ታይቶ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ የመጨረሻ አስገዳጅ ዉሳኔ ተሰጥቶበት እንዲቋጭ ታደርጋለች፡፡ እንደጀርመን ያሉት ደግሞ የክለሳ ጥያቄዉ በቀጥታ ለሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ የሚያደርግ ሥርዓት(The centralized model of judicial review) የሚከተሉ ሲሆን በዚሁ ፍርድ ቤት ክለሳ ተደርጎ የመጨረሻና አስገዳጅ ዉሳኔ እንዲሰጥበት ያደርጋሉ፡፡በደቡብ አፍሪካ ደግሞ የአንድ ሕግ ሕገ መንግስታዊነትና እና የአንድን የአስተዳደር/የአስፈጻሚ አካል ተግባር/ዉሳኔ ሕገ መንግስታዊነትና ሕጋዊነት በተመለከተ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የሕገ መንግስታዊነት ትርጉም (Preliminary Constututional Interpretation) ሕገ መንግስቱን ተርጉሞ እንዲወስን ሥልጣን ትሰጥና የሕገ መንግስታዊነት ጥያቄ የተነሳበት ሕግ እና የሕገ መንግስታዊነትና የሕጋዊነት ጥያቄ የተነሳበት የአስፈጻሚ/የአስተዳደር አካል ተግባር/ዉሳኔ ተፈጻሚነት እንዳይኖራቸዉ የመጨረሻዉን ዉሳኔ የመሰጠት ሥልጣን የሚኖረዉ ሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ነዉ የሚል ሥርዓት በሕገ መንግስቷ እንደዘረጋች በዘርፉ የተጻፉ ድርሳናት ያሳያሉ፡፡
የእኛን አገር ስርዓት የተመለከትን እንደሆነ በሦስቱ የመንግሥት አካላት መካከል ማለትም በሕግ አውጭው፣ ሕግ አስፈጻሚው እና በሕግ ተርጓሚው መካከል በፌዴራልና በክልል ሕግጋተ መንግስታት በተመለከተዉ አግባብ የሥልጣን ክፍፍል ያለ ቢሆንም በመካከላቸው የእርስ በእርስ ክትትልና ሚዛኑን ተጠብቆ (check and balance) እየተሰራ መሆኑ የሚረጋገጥበት ሥርዓት ከሌለ ተቋማቱ በሕግ የተጣለባቸውን የዜጎችን ሠብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ማክበርና ማስከበር አይችሉም፡፡ በአንጻሩ የእርስ በእርስ ክትትልና ሚዛኑን ጠብቆ የመስራት መርህ አተገባበር አለአግባብ ጣልቃ መግባትን ካስከተለ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝንና የተጣለባቸውን ግዴታ እንዳይወጡ ሊያደርጋቸው ስለሚችል ቁጥጥሩ በሕግ በተዘረጋው ሥርዓት አግባብ መፈጸም አለበት፡፡
አስተዳደራዊ አካላት የሚሠጧቸው ውሳኔዎች በፍ/ሕ/ቁጥር 401/1 እንደተመለከተው ከተሠጣቸው ሥልጣን በማለፍ ከወሰኑ (ultra virus) ወይም በተሠጣቸው ሥልጣን ስር ሆኖ ነገር ግን በሕጉ የተመለከቱትን አስገዳጅ ሁኔታዎችና ፎርም ሳይከተሉ የሚፈጽሙት ተግባር ወይም ውሳኔ ፈራሽ ነው፡፡ በአስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ የዳኝነት ክለሳ መኖር ካለበት ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ የመንግሥት አካላት የሥልጣን ክፍፍል መርሕ ነው፡፡ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 79/1 መሠረት የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡ ይህም ከሕገ-መንግሥታዊ ክርክሮች (constitutional disputes) ውጭ ማንኛውም በፍርድ ቤት ታይተው ሊወሰኑ የሚችሉ ጉዳዮች (justiciable matters) ላይ ፍርድ ቤቶች ዳኝነታዊ ክለሳ የማድረግ (judicial review) ተፈጥሮአዊ የሆነ ዳኝነታዊ ሥልጣን (inherent judicial power) እንዳላቸው ያሳያል፡፡ በፍርድ ቤት ታይተው ሊወሰኑ የሚችሉ ጉዳዮች የሚለውም የጉዳዮቹ ባሕሪ በፍርድ ቤት ሥልጣን ሥር ሊወድቁ የማይችሉ፣ አከራክሮ ሊፈጸም የሚችል ውሳኔ ሊሰጥባቸው የማይችሉ ጉዳዮችን የሚመለከት ሲሆን በሌላ በኩል ጉዳዮቹ በፍርድ ሊታይ የሚችሉ እንኳን ቢሆን ሌሎች የመንግሥት አካላት በሕገ- መንግሥት ባለው የሥልጣን ክፍፍል መርሕ መሠረት ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን (constitutionally mandated powers) መሠረት አድርገው የሚወስኗቸው ጉዳዮችንም ይጨምራል፡፡ በሌላ በኩል የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 78/4 እና 37 ላይ የተደነገገዉ አንድ ላይ ሲነበብ በሕግ የተደነገገን የዳኝነት ሥርዓትን የሚከተል የዳኝነት ነክ አካላት በሕግ የመዳኘት ሥልጣን ሊሰጣቸው እንደሚችል ያስገነዝባል፡፡ የእነዚህ አካላት የዳኝነት ሥልጣን በተፈጥሮ የሚገኝ ሳይሆን በግልጽ ሕግ ለመዳኘት ሥልጣን ሲሰጣቸውና የሚሰሩበት የተደነገገ የዳኝነት ሥርዓት ሲኖራቸውና ይህን ተከትለው ሲሰሩ የሚኖራቸው ሥልጣን ነው፡፡ ይህም በዘመናዊው የመንግሥት ሥርዓት መንግሥት ብዙ ጉዳዮች ላይ ሠፊ ሥልጣን ያለው አስፈጻሚዉ አካል በመሆኑ በመሆኑ ለመንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል የዳኝነት ነክ ሥልጣን አስፈላጊ በመሆኑ፣ የተወሰኑ ጉዳዮች

ደግሞ ፍሬ ነገሮችን ለመመልከት ልዩ ዕውቀት (specialization) የሚጠይቁ በመሆኑ እና ፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን የሥራ ጫና ለማቃለል ሥራ ላይ ይውላሉ፡፡
ነገር ግን ጠንካራና አስተማማኝ የዜጎች ሰብዓዊ መብት የሚከበርበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የሕግ የበላይነትን ማስፈን ወሳኝ ነው፡፡ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት መግቢያ ላይ እንደተመለከተው የሕግ የበላይነትን የተረጋገጠበት አሰራር መዘርጋት የሕገ-መንግሥቱ ዋነኛ ዓላማ ሲሆን አንዱ መስፈርት ደግሞ የዜጎችን በፍርድ ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮች በነፃና ገለልተኛ ፍርድ ቤት እንዲታይ መደረጉ ነው፡፡የሕግ የበላይነት መርሕ ሰፊ ሀሳቦችን የያዘ ቢሆንም በሕግ ሥልጣኑ የተገደበ መንግሥት እንዲኖርና የዜጎች መብት የተከበረበት ሥርዓትን ለመፍጠር የሚረዳ ነው፡፡ በፌዴራሉ ሕገ-መንገሥት መግቢያ ላይ የተመለከተዉ የሕግ የበላይነት ዓላማ ከግብ የሚደርሰዉ የመንግስት አካላት ለሚወስዱት እርምጃ ተጠያቂ መሆንና ኃላፊነት መውሰድ ሲችሉ ነዉ፡፡ይህም ከሚረጋገጥባቸዉ መንገዶች አንዱ በሰጡት አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ መብቱ የተነካበት ሰዉ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲችልና ፍርድ ቤቶችም ተገቢዉን መንገድ ተከትለዉ ጥያቄ የቀረበበት ዉሳኔ ሕጋዊነትን የተከተል መሆን አለመሆኑን በዳኝነት ማየት ሲችሉ ነዉ፡፡ እንዲሁም የአስተዳደር አካላት የሠጡት ውሳኔ በሕጉ የተዘረጋውን ሥርዓት የተከተለና ዜጎች ተገቢው የመሰማት መብት (due process of law) ያገኙ ስለመሆኑ ቁጥጥር ለማድረግ በአስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ የዳኝነት ክለሳ ያስፈልጋል፡፡
በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 79(1) መሠረት የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37 ላይ ሰዎች ፍትሕ የማግኘት መብት ያላቸው በመሆኑ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች በፍርድ ሊዳኙ የሚችሉ እስከሆኑ ድረስ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ ጉዳዮችን እንዲመለክት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 78 መሰረት ሥልጣን በተሰጠው ፍርድ ቤት ቀርቦ መታየቱ ነጻ የዳኝነት አካል ያስፈለገበት ዓላማ ሊሳካ የሚችልበትና ሰዎች ያላቸውን መብት በሕግ ማስከበር የሚችሉበት ዋነኛ መሣሪያ አስተዳደራዊ ዉሳኔ በዳኝነታዊ ክለሳ ማየት መቻል ነው፡፡ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃም አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ የዳኝነት ክለሳ አስፈላጊ መሆኑን ያሰገነዝባል፡፡ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 13(1) ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና ማስከበር ኃላፊነት ከተሰጣቸው አካላት ዋነኛው የዳኝነት አካሉ በመሆኑ የአስተዳደር አካላት ከዜጎች ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይኖር ለመከላከል ሆነ ጥሰት ሲኖር ዜጎች ጥሰቱን የሚያሳርሙበት ዕድል ስለሚያስፈልግ አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ የዳኝነት ክለሳ የግድ የሚል ስለመሆኑ ያስገነዝባል፡፡ ስለሆነም ከፍርድ ቤት ውጭ በሕግ የዳኝነት ነክ ሥልጣን በተሰጣቸዉ አካላት የሚሰጡ ዉሳኔዎችንም ሆነ በሕግ በተሰጣቸዉ ኃላፊነት የሚሰጧቸዉ አስተዳደራዊ ዉሳኔዎች በዳኝነታዊ ክለሳ ሂደት በማለፍ በፍርድ ቤት መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
በሌላ በኩል የይግባኝ(Appeal) አቀራረብ ሥርዓት ምንነት የተመለከትን እንደሆነ ይግባኝ የሚባልበት ሥነ ሥርዓት በዋናነት በበታች መደበኛ ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ በየተዋረዱ ባሉት የበላይ መደበኛ ፍርድ ቤቶች በሕግ በተዘረጋዉ ሥርዓት መሰረት እንደገና የሚመረመርበትን የሚመለከት ነዉ፡፡ (የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 12/2 321 እና አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 54 ይመለከቷል፡፡) በተጨማሪም አስተዳደራዊ ዉሳኔ ወይም የዳኝነት-ነክ ሥልጣን የተሰጠዉ አካል(Quasi-judicial organ) የሰጠዉ ዉሳኔ በየደረጃዉ በተቋቋመና በከፍተኛዉ የዳኝነት-ነክ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ወይም በሕግ በግልጽ ከተደነገገም እነዚሁ አካል የሰጡት ዉሳኔ በከፍተኛዉ መደበኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ የሚታይበትን ሥነ ሥርዓት የሚመለከት ነዉ፡፡(ለአብነት በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 69/2፣98/4፣ 115/2፣ 153/8፤ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 29(1 እና 4) እና በአዋጅ ቁጥር 714/2003 እና ይህንን አዋጅ በተካዉ አዲስ አዋጅ ላይ በተመሳሳይ በአንቀጽ 56(1 እና 4) እና በሌሎችም ላይ ተደነገገዉ ይመለከቷል፡፡የይግባኝ ሥርዓትን ከዳኝነታዊ ክለሳ የሚለዩትም ምክንያቶች በይግባኝ ጊዜ በልዩ ሁኔታ በሕግ እስካልተገደበ ድረስ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በበታች ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረዉን ማስረጃ የመመርመርና የመመዘን፣በዉስን ሁኔታዎች አዲስ ማስረጃ መቀበልንና

የበታች ፍርድ ቤቶች ወይም የዳኝነት-ነክ አካል የሰጡት ዉሳኔ የሕግ ወይም የፍሬ ነገር ድምዳሜ ስህተት አለበት ብሎ ሲያምን ዉሳኔዉን ሽሮ አዲስ ዉሳኔ መስጠትን ጭምር የሚያካትት ሲሆን በዳኝነታዊ ክለሳ ደግሞ ሕግ አዉጪዉ ያወጣዉ ሕግ፣ሕግ አስፈጻሚዉ የፈጸመዉ ተግባር(የወሰነዉ ዉሳኔ) እንዲሁም የዳኝነት-ነክ ሥልጣን የተሰጠዉ አካል የወሰነዉ የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ ብቻ ተመስርቶ ሕገ መንግስታዊ ወይም ሕጋዊ መሆን አለመሆኑን በመከለስ ሕገ መንግስታዊ ወይም ሕጋዊ አይደለም የሚል ከሆነ ተፈጻሚ እንዳይሆን መወሰን ወይም ዉሳኔዉን ሽሮ እንደገና ታይቶ እንዲወሰን መመለስ አሊያም የክለሳ ጥያቄዉን ዉድቅ በማድረግ ዉሳኔዉን ማጽናት እንጂ የራሱን አዲስ ዉሳኔ አይሰጥም፡፡

ከላይ በዝርዝር ከተመለከትነዉ ከተለያዩ አገራት ልምድ፣ በአገራችን በተለያዩ ሕግጋት እና በዳኝነት ሥራ ከዳበረዉ ተመኩሮ (judicial jurisprudence) ከተንጸባረዉ የምንገነዘበዉም አንድን ዉሳኔ በሰበር የማየት፣ በይግባኝ የማየት እና በዳኝነት አይቶ የመከለስ ሥርዓት በጽንሰ ሀሳብ ደረጃም ሆነ በአተገባበራቸዉ የተለያየ የክርክር አመራርንና መነሻ ምክንያትን የሚጠይቁ እንደሆኑ ነዉ፡፡በአገራችን በፌዴራል ደረጃ በልዩ ሁኔታ በሕግ በግልጽ በተቃራኒዉ አስካልተደነገገ ድረስ አንድ በፍርድ ቤት፣ በአስተዳደር አካል ወይም ዳኝነት ነክ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል የተሰጠ ዉሳኔ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ሊመረመር የሚችለዉ እንደነገሩ ሁኔታ በሕግ በተዘረጋዉ በይግባኝ እና በዳኝነታዊ ክለሳ ሥነ ሥርዓት ታይቶ የመጨረሻ ዉሳኔ ካገኘ በኋላ ብቻ ነዉ፡፡ምክንያቱም የሰበር ሰሚ ችሎት ሥልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ብቻ መርምሮ ስህተቱን የሚያርም ዉሳኔ መስጠት በመሆኑ ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አካል የተሰጠ ዉሳኔ በተለይም በዳኝነታዊ ክለሳ ሊታይ የሚችል ዉሳኔ በዳኝነታዊ ክለሳ ሳይታይ በቀጥታ ለሰበር ሰሚ ችሎት የሚቀርብ ከሆነ በመደበኛ ፍርድ ቤት በክለሳ ሥርዓት ሊመረመሩ የሚችሉና ፍሬ ነገሮችን ከማስረጃ አንጻር ጭምር መመርመርንና ማረጋገጥን የሚጠይቁ የክርክር ነጥቦች ወይም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልሆኑ ስህተቶች የሚታረሙበትን ሂደት የሚገድብ ይሆናል፡፡

እንዲሁም አንድ አስተዳደራዊ ዉሳኔ የመጨረሻ ነዉ ተብሎ እንደነገሩ ሁኔታ በይግባኝ ፣በዳኝነታዊ ክለሳ ቀጥሎም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ከሆነ በሰበር ሥርዓት ታይቶ የማይታረም ከሆነ የሕገ መንግስት የበላይነት መርህ ፣የዲሞክራሲያዊ መንግስት መገለጫ የሆነዉ የተጠያቂነት መርህ እና የዲሞክራሲያዊ መንግስት የሥልጣን ክፍፍል መሠረታዊ መርህ የሆነዉ የመንግስት አካላት እርስ በእርሳቸዉ የሚኖራቸዉ የሥልጣን ክትትልና ሚዛን የመጠበቅ (Check and Balance) መርህ እንዲሸራረፍ ያደርጋል፡፡በመሆኑም በሕግ በልዩ ሁኔታ በቀጥታ ለሰበር ቀርቦ እንዲታይ እስካልተደነገገ ድረስ በሰበር ከመታየቱ በፊት እንደነገሩ ሁኔታ በይግባኝ ወይም በዳኝነታዊ ክለሳ ሥነ ሥርዓት ሊታይ ይገባል፡፡
ምንጭ:- Habesha Legal Advocates LLP

Address

Addis Ababa
Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Seera/ህግ /Law posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share