የገደብ ከተማ ኮሙኒኬሽን

የገደብ ከተማ ኮሙኒኬሽን Communication service

‎የምክክር ኮሚሽን የኢትዮጵያ ሰላም ጸንቶ እንዲኖር የሚያደርግ ነው ሲሉ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር አስታወቀ ‎‎( #ገደብ ነሐሴ 16/2018 ዓ/ም) የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪው ዝናቡ ወልዴ(...
22/08/2026

‎የምክክር ኮሚሽን የኢትዮጵያ ሰላም ጸንቶ እንዲኖር የሚያደርግ ነው ሲሉ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር አስታወቀ

‎( #ገደብ ነሐሴ 16/2018 ዓ/ም) የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪው ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ በምክክር የውስጥ ችግሮቿን ለመፍታት የወሰደችው እርምጃ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል ።

‎አስተዳዳሪው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በሰላምና በውጤት መጠናቀቁን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

‎ኢትዮጵያ ለዘመናት በአብሮነትና በአንድነት የዘለቀ የመኖር እሴት ያላት ሀገር ናት ።

‎ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያን አንድነት ለማፍረስ በውስጥና በውጭ ጠላት የተደረገ ሴራ ለማክሸፍ ኢትዮጵያ ላለፉት አራት ዓመታት አጀንዳ በማሰባሰብ ምክክር ስታካሂድ መቆየቷን አስተዳዳሪው ገልጸዋል ።

‎ይህም አሁን ላይ ፍሬ አፍርቶ የመጨረሻ ደረጃ ውጤት ሀገርን ማጽናት መሆኑን ማየት መቻሉን ነው ዶክተር ዝናቡ የገለጹት ።

‎በቀጣይም ቀሪው ሂደቶች የሚጠናቀቁ እንዳለ ሆኖ ጉባኤው በቀረበው አጀንዳ ላይ በመምከር የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በድጋሚ በአለም ገኖ እንዲታይ በማድረጉ በዞኑ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል ።

‎በቀጣይም የምክክር ኮሚሽን በየደረጃው የሚያካሂዳቸው ሂደቶች በስኬትና በውጤት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል ።

‎@የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት !

የጌዴኦ ዞን ድንበር ተሻጋሪ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ ቡድን  በወላይታ ዞን የችግኝ ተከላ አካሄዱዲላ፦ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም (ጌዴኦ ቴሌቪዥን)የጌዴኦ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ...
22/08/2026

የጌዴኦ ዞን ድንበር ተሻጋሪ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ ቡድን በወላይታ ዞን የችግኝ ተከላ አካሄዱ

ዲላ፦ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም (ጌዴኦ ቴሌቪዥን)

የጌዴኦ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ድንበር ተሻጋሪ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ ቡድን በወላይታ ዞን የበጎ አድራጎት ሥራዎችንና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብሮችን አከናውኗል።

የጌዴኦ ዞን ወጣቶች በወላይታ ዞን ጉብኝት ባደረጉት ወቅት በተለያዩ የማኅበረሰብ አገልግሎትና የበጎ አድራጎት ሥራዎ ሠርተዋል። ተግባሩም በወጣቶችና በማኅበረሰቡ መካከል ያለውን ትስስር፣ አንድነትና ወንድማማችነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ የዲሞክራሲ ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጀማል ቦቶ በወቅቱ በሰጡት መልዕክት ወጣቶቹ በቆይታቸው አረካ ከተማንና ታዋቂውን የአጆራ ፏፏቴ እንደጎበኙ ጠቁመው፣ የጉዞው ዓላማ ከበጎ አድራጎት ሥራ ባሻገር የልምድ ልውውጥንና የወንድማማችነት ትስስርን ማጠናከር መሆኑን አመላክተዋል።

የበጎ ፈቃደኞቹ ቡድን ከወላይታ ሶዶ ተነስቶ ወደ አረካ ከተማ በመጓዝ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን አከናውኗል። በዚህም ወጣቶቹ ለተማሪዎች የደብተርና የእስክሪብቶ ድጋፍ አበርክተዋል።

በመቀጠልም ወጣቶቹ ታዋቂውን የአጆራ ፏፏቴ በመጎብኘት የተለያዩ ልምዶችን የተለዋወጡ ሲሆን፣ ጉብኝቱ የተለያዩ አካባቢዎችን ከማወቅ ባሻገር የወጣቶችን ትስስር ለማጠናከር ያለውን ሚና አሳይቷል።

የጌዴኦ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢዩኤል ተሾመ፣ “በጎ ሥራ ድንበር አይገድበውም” በሚል መርህ የተጀመረው የበጎ ፈቃድ ተግባር በቀጣይም ቀጣይነት እንደሚኖረው ተናግረዋል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ሜጋና የቦንቤ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አስደሳች አይዴ በበኩላቸው፣ ወጣቶቹ አካባቢያቸውን ተሻግረው በመምጣት ላደረጉት የበጎ ተግባር ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል። የወጣቶች እርስ በርስ ትስስርና የበጎ ፈቃድ ተሳትፎ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

በምህረት አክሊሉ
ፎቶ፦ ሜሮን ንጉሴ

ይህንንና ሌሎችን ዘገባዎች ለመከታተል በነዚህ ድህረ ገጾች ይከታተላሉ
‎ ዩቱብ https://youtube.com/?feature=shared

‎ቴሌግራም https://t.me/gedeotvofficial

‎ቲክቶክ https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-96GXGnq7yeD

የጌዴኦ ዞን ወጣቶች ክንፍ አመራሮች ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ እና ወጣት ለወጣት ግንኘነት ለማጠናከር ወላይታ ዞን ገብተዋል‎የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት "በጎ...
22/08/2026

የጌዴኦ ዞን ወጣቶች ክንፍ አመራሮች ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ እና ወጣት ለወጣት ግንኘነት ለማጠናከር ወላይታ ዞን ገብተዋል

የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ቃል ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ እና ወጣት ለወጣት ግንኘነት ለማጠናከር ወላይታ ሶዶ ከተማ ገብተዋል።

‎የጌዴኦ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ አቶ እዩኤል ተሾመ በንግግራቸው፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶችን በጋራ ዓላማ ስር የሚያስተሳስር እና የማህበረሰብ ችግሮችን በገዛ አቅማቸው የመፍታት ባህልን የሚያሳድግ ዋና መሳሪያ ነው ብለዋል።

‎የወላይታ ሶዶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዲሞክራሲና ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጀማል በለቼ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክትና አቀባበል አድርገዋል።

‎ይህ የድንበር ተሸጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት በዞኖቹ መካከል ያለውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ህዝባዊ ወንድማማችነት የበለጠ ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀ አህጉራዊ እና ክልላዊ የልማት እንቅስቃሴ አካል እንደሆነ ገልጸዋል።

‎ወደ ወላይታ ሶዶ ያመራው የልዑካን ቡድን በከተማው የወላይታ ዞን ወጣቶች ክንፍ አመራሮች እና የሶዶ ከተማ ወጣቶች ክንፍ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

‎የልዑካን ቡድኑ በሶዶ ከተማ እና በአካባቢው በሚቆይበት ጊዜ በችግኝ ተከላ፣ በደም ልገሳ ላይ በነቃ ሁኔታ ይሳተፋል።

‎የወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ታደለ ሜጋ በበኩላቸው፤ የጌዴኦ ዞን ወጣቶች ላሳዩት የወንድማማችነት ስሜት እና የበጎ ፈቃድ ስራ ዝግጁነት ምስጋና አቅርበው ተግባሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

‎ይህ አይነቱ የድንበር ተሸጋሪ መርሃ ግብር ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላም፣ ልማት እና አብሮነት በማጠናከር ረገድ የሚጫወቱትን አወንታዊ ሚና የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል።

‎በተጨማሪም ከወጣት አደረጃጀት ጋር በጋራ በመሆን በአንድ ላይ በመሳተፍ የልምድ ልውውጥ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ተግባራትን ያከናውናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

‎ይህ አርአያነት ያለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሌሎች አካባቢዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና የወጣቶችን አቅም ለበጎ ተግባር ማዋል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምንጭ፡ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በግንዛቤ እጥረት የሚፈጠሩ ወንጀሎችን ለማስቀረት ለሞተረኞች የንቃተ-ሕግ ግንዛቤ ትምህርት ተሰጠገደብ ከተማ፣ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም (የመንግሥት ኮሙኒኬሽን) — በጌዴኦ ዞን በገደብ ከተማ ...
21/08/2026

በግንዛቤ እጥረት የሚፈጠሩ ወንጀሎችን ለማስቀረት ለሞተረኞች የንቃተ-ሕግ ግንዛቤ ትምህርት ተሰጠ

ገደብ ከተማ፣ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም (የመንግሥት ኮሙኒኬሽን) — በጌዴኦ ዞን በገደብ ከተማ አስተዳደር በግንዛቤ እጥረት ምክንያት የሚፈጸሙ ወንጀሎችንና በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርሱ ጉዳቶችን በዘላቂነት ለመከላከል ያለመ የንቃተ-ሕግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ለሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ተሰጥቷል ።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቱን የገደብ ከተማ አስተዳደሩ ፍትህ፣ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ዩኒት ከፖሊስ ጽሕፈት ቤት ጋር በመቀናጀት የተዘጋጀ ነው።

ማህበረሰቡ በቂ የሕግ እውቀት እንዲጨብጥ ማድረግ ዜጎች ራሳቸውንም ሆነ አካባቢያቸውን ከማንኛውም ዓይነት ወንጀል የመከላከል አቅማቸውን ማሳደግ ተጠናክሮ የሚተገብር ስራዎች መሆኑን ተገልጿል ።

አሽከርካሪዎች የሕግ የበላይነትን በማክበር ረገድ ግንባር ቀደም ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተጨማሪ ሊከሰቱ የሚችሉትን ደንብ መጣስና የህይወትና ንብረት ጉዳቶችን ለማስቀረት የሚያስችሉ ትምህርታዊ መልእክቶችን ተላልፏል ።

አሽከርካሪዎች የትራፊክ ሕጎችን በጥብቅ በመከተል የሰው ህይወት የመታደግ አደራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ዘገባው የገደብ ከተማ የመንግሥት አገልግሎት ነው ።

በገደብ ከተማ ለዓመታት የዘለቀው የምክር ቤቱ የቢሮ ጥያቄ ምላሽ አገኘገደብ ከተማ ፣ ነሀሴ 15/2018 የመንግሥት ኮሙኒኬሽን በገደብ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዘንድ ለበርካታ ዓመታት ዋነ...
21/08/2026

በገደብ ከተማ ለዓመታት የዘለቀው የምክር ቤቱ የቢሮ ጥያቄ ምላሽ አገኘ

ገደብ ከተማ ፣ ነሀሴ 15/2018 የመንግሥት ኮሙኒኬሽን

በገደብ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዘንድ ለበርካታ ዓመታት ዋነኛ ጥያቄ ሆኖ የቆየው የራሱ ቢሮ ማጣት ችግር በመጨረሻ እልባት ማግኘቱ ተገልጿል ።

ምክር ቤቱ ለረጅም ዓመታት በኪራይ ቤት ውስጥ ሲያከናውን የነበረውን አገልግሎት አጠናቆ ወደራሱ ቢሮ ተዛውሯል።

የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አቶ ተገኝ ተሰማ እንደገለጹት፤ ምክር ቤቱ የህዝቡን የመልካም አስተዳደርና የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች በጥልቀት በመገምገምና መፍትሔ እንዲያገኙ በመከታተል ረገድ ከፍተኛ ሚና ሲጫወት የቆየ ተቋም ነው ብለዋል።

ሆኖም የራሱ ቢሮ አለመኖሩ በስራው ላይ ተጽዕኖ ፈጥሮ መቆየቱን ጠቁመው፣ ከተማ አስተዳደሩ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ አሁን ላይ የራሱን ቢሮ ማግኘት በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

አፈ-ጉባኤው ለዚህ መፍትሔ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ም/አፈ-ጉባኤ መዓዛ መኩሪያ በበኩላቸው የቢሮ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ ፣ ሌሎችም ጥያቄዎች አንድባንድ እንደሚፈቱ ማሳያ ነው ብለዋል ።

የገደብ ከተማ ከንቲባ አቶ ታርኩ ሮቤ በበኩላቸው፣ ተቋሙ በኪራይ ቤት ውስጥ በርካታ ዓመታትን ማሳለፉን አስታውሰው፣ ወደራሱ ቢሮ መዛወሩ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ ተነሳሽነት እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

አክለውም፣ የህዝብ አደራ የተቀበለ ተቋም ወደራሱ ቢሮ መግባቱ አሰራሩን የበለጠ ያጠናክረዋል ያሉ ሲሆን ፣ በያዝነው የበጀት ዓመትም የማህበረሰቡን ጥያቄዎች የሚመልሱ በርካታ ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን በርሶ በበኩላቸው፤ ከተማዋ በቅርብ ጊዜ መዋቀሯን ተከተሎ የሁሉም ተቋማት የቢሮ ጥያቄ በአንድ ጊዜ ለመመለስ ፈታኝ ቢሆንም፣ ደረጃ በደረጃ የመፍትሔ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት የምክር ቤቱን ቢሮ ጨምሮ የፖሊስ፣ የማዘጋጃ ቤት፣ እንዲሁም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮዎችን የቦታ ችግር መፍታት መቻሉን አብራርተዋል።

ዘገባው የገደብ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው ።

ቀልጣፋና ዉጤታማ ተግባቦት ስርዓት በመዘርጋት የሚዲያ ተቋማቶች በትኩረት ሊሰሩ ይገባል :- የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ‎‎( #ገደብ፣ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም) የጌዴኦ ዞ...
20/08/2026

ቀልጣፋና ዉጤታማ ተግባቦት ስርዓት በመዘርጋት የሚዲያ ተቋማቶች በትኩረት ሊሰሩ ይገባል :- የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

‎( #ገደብ፣ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም) የጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በዞኑ ከሚገኙ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች ጋር የሚዲያ ፎረም ምስረታና የዉይይት መድረክ አካሂዷል ።

‎የፎረም ምስረታዉም በዞኑ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማቶችና ባለሙያዎች የእርስ በእርስ ግኑኝነቶችን በማጠናከር ረገድ ተቀናጅተው እንዲሰሩ ፋይዳዉ የጎላ መሆኑ ተገልፃል።

‎በመድረኩ ላይ የተገኙት የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አየለ፦የሚዲያ ፎረም ምስረታ በዞኑ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማቶች ነጋራ ቅንጅትና ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩና ሙያዊ ብቃትን እንዲያጎለብቱ እጅጉን ይረዳል ብለዋል።

‎ሚዲያ የተሠሩ ተግባራት በህዝቡ ዘንድ አመኔታ እንዲኖራቸው ከማድረግ አኳያ የጎላ ሚና እንዳለው የሚገልፁት አቶ አዲሱ ይህም ለሀገር ግንባታ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል ።

‎ሚዲያን ለበጎ ተግባር ማዋል የሀገር ግንባታን ያጠናክራል ፣ማህበረሰባዊ ለዉጥን ያመጣል ይህም ከህብረተሰቡ የሚነሱ የልማት ጥያቄዎችን ለመንግሥት በማቅረብ እና ከመንግስት ደግሞ ወደ ህዝብ በማድረስ እንደ መሸጋገሪያ ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል።

‎የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ወ/ሮ ዜና ማሞ፦ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዋነኛው ተልዕኮ ሁሉ አቀፍና አዳዲስ የኮሙኒኬሽን መገናኛ ቴክኖሎጂዎቻችንን በመጠቀም ለህብረተሰቡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶችን እንዲሁም በመረጃ የበለፀገ ህብረተሰብ የሚፈጥርና የአከባቢ ገጽታን የሚገነባ መሆኑን ገልፀዋል።

‎የፎረሙ ምስረታም በዞኑ ከሚገኙ የሚዲያ ተቋማቶች ጋር በመቀናጀት ለህብረተሰቡ የመረጃ እጥረት እንዳያጋጥም ፣የተሰሩ ስራዎችን በበለጠ ሁኔታ መረጃዎች በትክክለኛው መንገድ እንዲሰራጭ ፣የሀሳብ ልዉዉጥ ለማድረግ ፣ሙያዊ ብቃትን ለማጎልበት እና ማህበረሰባዊ ለዉጥ ለማምጣት እንዳስፈለገ ነው ኃላፊዋ የጠቆሙት ።

‎የመረጃ ተደራሽነትን ይበልጥ በማሳለጥ ቀልጣፋና ዉጤታማ የመረጃና የተግባቦት ሥርዓትን በመዘርጋት ለህብረተሰቡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን እንዲሁም ግልጽና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማድረስ በትኩረት ተቀናጅተን ልንሰራ እንደሚገባው ወይዘሮ ዜና ማሞ አሳስበዋል።

‎በፎረም ምስረታው የተገኙ የሚዲያ ተቋምናየዘርፉ ባለድርሻዎች የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ይህንን የሚዲያ ምስረታና የዉይይት መድረክ በማዘጋጀቱ ምስጋናቸውን አቅርበዉ ይህም የእርስ በእርስ የሚዲያ ግኑኝነቶችን ለማጠናከር እጅጉን እንደሚረዳ ገልፀዋል ።

‎የግኑኝነት አግባቦችን በማሳለጥ ተግባራቶችን በየደረጃው እየለዩ ማስኬድ ይገባል ያሉት ተሳታፊዎች ቀልጣፋና ዉጤታማ የመረጃና ተግባቦት ስርዓት በመዘርጋት የሚዲያ ተቋማቶች በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

‎በፎረም ምስረታዉም አብይና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላቶች ተመርጠው የጋራ መግባባት ተፈጥሮ ዉይይቱ ተጠናቋል ።

‎ @የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት!

የገደብ ከተማ ገቢዎች ዩኒት የ2018 ገቢ አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ የምክክር መድረክ አካሄደገደብ፣ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም (ኮሙኒኬሽን)፦ በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ዩ...
20/08/2026

የገደብ ከተማ ገቢዎች ዩኒት የ2018 ገቢ አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ የምክክር መድረክ አካሄደ

ገደብ፣ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም (ኮሙኒኬሽን)፦ በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ዩኒት የ2018 የገቢ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 የገቢ ዕቅድ ላይ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ ከአመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሂደዋል ።

በ2019 በጀት አመት ከ196 ሚልዮን በላይ ለመሰበሰብ ታቅዶ እየተሰራበት መሆኑ ተገልጿል ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የገደብ ከተማ ከንቲባ አቶ ታሪኩ ሮቤ እንደገለጹት፣ የህዝብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመመለስ፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን ለማስፋፋትና የከተማዋን የፈርጅ ለውጥ እውን ለማድረግ የውስጥ ገቢን አማጦ መሰብሰብ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ከንቲባው አክለውም የ2019 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ከቀደሙት ዓመታት ከፍ ያለ በመሆኑ የተጣለውን ግብ ለማሳካት የታክስ አሰበሰቡን ማዘመንና የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ርብርብ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የከተማው የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን በርሶ በበኩላቸው፣ በከተማዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ የገቢ አቅም እያደገ መምጣቱን ጠቁመው፤ ባለፈው በጀት ዓመት የተከናወኑት አበይት የልማት ስራዎችና የተገዙት የተለያዩ የመሰረተ ልማት ማሽነሪዎች ለገቢው እድገት ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ የተገኙ ፍሬዎች መሆናቸውን አብራርተዋል።

በመድረኩ የውይይት ሰነድ ያቀረቡት የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ካሳሁን ቡቹ፣ ገቢ ለከተማዋ ፈጣን እድገትና ልማት ዋነኛ መሪ ሞተር መሆኑን በማንሳት፣ በበጀት ዓመቱ የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

በምክክር መድረኩ ማጠቃለያም የታቀደውን ገቢ ሙሉ በሙሉ ለመሰብሰብ፣ የታክስ አሰራርን በማዘመን የከተማን ልማት ለማፋጠን የሚያስችሉ ተግባራዊ ውሳኔዎች ላይ ተደርሷል።

ዘገባው የገደብ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው።

የጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚዲያ ፎረም ምስረታ ውይይት እያካሄደ ነው‎‎( #ዲላ ነሐሴ 14-2018 ዓ/ም) አገልግሎቱ በዞኑ የሚዲያ ፎረም ምስረታ ውይይት እያካሄደ ይገኛል...
20/08/2026

የጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚዲያ ፎረም ምስረታ ውይይት እያካሄደ ነው

‎( #ዲላ ነሐሴ 14-2018 ዓ/ም) አገልግሎቱ በዞኑ የሚዲያ ፎረም ምስረታ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

‎በምስረታው የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አየለ፣ የጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ወይዘሮ ዜና ማሞ ጨምሮ በዞኑ የምቀሳቀሱ የሚዲያ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ይገኙበታል።

‎@የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት!

የገደብ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ጸጥታ ዙሪያ ከጸጥታ ኮሚቴ ጋር የምክክር መድረክ አካሄደገደብ፣ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም (ኮሙኒኬሽን)፦ የገደብ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰብ የጸጥታ ኮሚቴ...
20/08/2026

የገደብ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ጸጥታ ዙሪያ ከጸጥታ ኮሚቴ ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

ገደብ፣ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም (ኮሙኒኬሽን)፦ የገደብ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰብ የጸጥታ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን የአካባቢውን ደህንነት ማስጠበቅ እና የልማት ስራዎችን ማፋጠን በሚያስችሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተመካከሩ።

በምክክሩ የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን፣ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የሚያደርጋቸው የምሽት ጥበቃ (ሮንድ) እና መረጃዎችን ጥቆማ የማድረግ ስራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑ ተመልክቷል።

በወቅቱ የገደብ ከተማ ከንቲባ አቶ ታሪኩ ሮቤ እንደገለጹት፣ ዘላቂ ሰላም ለመልካም አስተዳደርና ለልማት ስራዎች ዋነኛ መሰረት ነው ብለዋል።

ከንቲባው አክለውም ከተማዋን ሰላማዊ ቀጠና ለማድረግ የታለሙ ጥረቶች ግባቸውን እንዲመቱ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ያለው ቅንጅት ሊጎለብትና እያንዳንዱ ነዋሪ ለሰላሙ ዘብ ሊቆም እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የጸጥታ ኮሚቴ አባላቱ በበኩላቸው አካባቢያቸውን ከማንኛውም ስጋት ለመጠበቅ ከአስተዳደሩ ጋር በትብብር የመስራት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል።

በማጠቃለያም ገደብ ከተማን ለነዋሪዎች ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የተቀናጁ እርምጃዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ዘገባው የገደብ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው

የገደብ ከተማ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር ዩኒት የሪፎርም ሥራዎችን ተከትሎ በሚተገበረው የትምህርት አመራር ምደባ ላይ ኦረንቴሽን ሰጠ #(ገደብ ከተማ ፣ ነሀሴ 13/2018 ዓ.ም የመንግስት ኮ...
19/08/2026

የገደብ ከተማ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር ዩኒት የሪፎርም ሥራዎችን ተከትሎ በሚተገበረው የትምህርት አመራር ምደባ ላይ ኦረንቴሽን ሰጠ

#(ገደብ ከተማ ፣ ነሀሴ 13/2018 ዓ.ም የመንግስት ኮሙኒኬሽን )

የገደብ ከተማ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር ዩኒት በትምህርት ሴክተሩ እየተከናወኑ ባሉ አዳዲስ የሪፎርም ስራዎች ዙሪያ ከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ የትምህርት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ኦሬንተሽን ሰጥተዋል ።

በከተማው የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ታደለ በየነ መድረኩ በትምህርት ጥራት ማሻሻያ ስራዎች ላይ የትምህርት አመራሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፣ የሪፎርም ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የተናበበ አሰራር እና ቁርጠኛ አፈጻጸም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

የዘርፍ አስተባባሪ አቶ ማርቆስ ተሰማ በሪፎርሙ ስራዎች ዙሪያ የተዘጋጀ አጠቃላይ የኦሬንተሽን ሰነድ ለአመራሮቹ አቅርበዋል።

ሰነዱ የሪፎርሙን ዋና ዋና ሂደቱን ይዘዋል ፣ በዚህም ከትምህርት አመራሩ የሚጠበቁ ውጤቶችን በዝርዝር አካቷል።

በመጨረሻም አመራሮቹ በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በቀጣይ በከተማዋ ትምህርት ቤቶች መሬት ላይ ወርዶ የሚሰራበትን የትግበራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ዘገባው የገደብ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው

Address

Gedeb Gedeo
Dilla

Telephone

+251913354266

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የገደብ ከተማ ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category