ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል

ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል ✅ወክሎ መከራከር
✅የማማከር አገልግሎት
✅ክስና መልስ ማዘጋጀት
✅ይግባኝ እና ይግባኝ መልስ ማዘጋጀት
✅+251910214108

የቤት ስጦታ ዉል አስፈላጊ የሆኑ 10 ቅድመ ሁኔታዎች(ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል)✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅1.  የቤት ስጦታ ውል በሕግ ፊት የጸና እንዲሆን በሰጪና በተቀባይ መካከል በጽሑፍ ተዘጋጅ...
21/05/2026

የቤት ስጦታ ዉል አስፈላጊ የሆኑ 10 ቅድመ ሁኔታዎች
(ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል)
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
1. የቤት ስጦታ ውል በሕግ ፊት የጸና እንዲሆን በሰጪና በተቀባይ መካከል በጽሑፍ ተዘጋጅቶ በውልና ማስረጃ
ፊት መቅረብና መመዝገብ አለበት።
2. የቤቱ ስመ ንብረት ማስረጃ (ካርታ) ሰጪው የቤቱ እውነተኛ ባለቤት መሆኑንና ንብረቱን የመስጠት ሕጋዊ መብት እንዳለው ለማረጋገጥ ያገለግላል።
3. የሰጪና የተቀባይ የታደሰ መታወቂያዎች ውልና ማስረጃ ላይ ቀርበው የሚፈርሙትን አካላት ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ የሚጠየቁ መሠረታዊ ሰነዶች ናቸው።
4. የጋብቻ ሁኔታ ማስረጃ ቤቱ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት መሆን አለመሆኑን በማጣራት የሕጋዊ አጋርን መብት ለመጠበቅ ወሳኝ ሚና አለው።
5. የግብር ዕዳ አለመኖሩን የሚያሳይ ማረጋገጫ (ክሊራንስ) ንብረቱ ከመዞሩ በፊት ለወረዳው ገቢዎች ጽሕፈት ቤት የሚገባው የመንግሥት የቤት ግብር በሙሉ መከፈሉን ያረጋግጣል።
6. ከእግድ ነፃ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ቤቱ በባንክ ብድር ዋስትና ወይም በፍርድ ቤት ክርክር ምክንያት ያልታገደ መሆኑን ለማረጋገጥ ይቀርባል።
7. የቤት ግምት ምንም እንኳ ዝውውሩ በነጻ የሚደረግ ቢሆንም፣ ለመንግሥት የሚከፈለውን የቴምብር ቀረጥና የስም ማዞሪያ ክፍያ ለማስላት ግድ ይላል።
8. እነዚህ ሰነዶች በሙሉ ተሟልተው ሲቀርቡ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የስጦታ ውሉን መርምሮ በሕጋዊ መንገድ ያጸድቀዋል።
9. ውሉ ከጸደቀ በኋላ የባለቤትነት መብቱ ከሰጪው ወደ ተቀባዩ እንዲዛወር ሰነዶቹ ለሚመለከተው የመሬት ማዘጋጃ ቤት ጽሕፈት ቤት ይመራሉ።
10. በመጨረሻም ማዘጋጃ ቤቱ የቀድሞውን የባለቤትነት ካርታ በመሰረዝ በተቀባዩ ስም አዲስ ሕጋዊ የቤት ካርታ ያዘጋጃል።
ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል

የከተማ መሬትና ቤት ይዞታ ሥመ-ንብረት ዝውውር ለመፈጸም መሟላት ያለባቸው ሕጋዊ መስፈርቶች፣ የሰነድ ማስረጃዎችና የአፈጻጸም መመሪያ"🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑መግቢያ​የከተማ መሬትና ቤት ይዞታ...
21/05/2026

የከተማ መሬትና ቤት ይዞታ ሥመ-ንብረት ዝውውር ለመፈጸም መሟላት ያለባቸው ሕጋዊ መስፈርቶች፣ የሰነድ ማስረጃዎችና የአፈጻጸም መመሪያ"
🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
መግቢያ
​የከተማ መሬትና ቤት ይዞታ ማስተላለፍ እንዲሁም የሥመ-ንብረት ዝውውር ሥርዓት፤ በከተሞች የሚታየውን ፈጣን የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ዕድገት በሥርዓት ለመምራት፣ የባለቤትነት መብትን ለማረጋገጥና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን ቁልፍ ሚና አለው። ይሁን እንጂ ይህ ሂደት ሕጋዊ መሠረቱን ጠብቆ ካልተከናወነ በዜጎች ንብረት፣ በፋይናንስ ተቋማትና በከተማው ሁለንተናዊ ልማት ላይ ከፍተኛ የሕግና የኢኮኖሚ መተረማመስን ሊያስከትል ይችላል።
​በመሆኑም ይህ መመሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 33 ንዑስ አንቀፅ 2 ላይ የተቀመጡትን መሠረታዊ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው። የመመሪያው ዋና ዓላማ በግዥና ሽያጭ፣ በስጦታ፣ በውርስ እንዲሁም በባንክ ሐራጅ አማካኝነት የሚከናወኑ የቤትና የይዞታ ዝውውሮች ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ወጥነት ባለው መንገድ እንዲመሩ ማድረግ ነው።ስለሆነም በጉዳይ ላይ በአጭሩ ምልከታ እናደርጋለን =====
በስመ ንብረት ዝውውር ወቅት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 33 ንዑስ አንቀፅ 2 አንፃር ሲታይ፦
ሀ/ የከተማ ቤትና ይዞታ ስመ-ንብረት ዝውውር ስለመፈጸም የሚከተሉት ማስረጃዎች/ሰነዶች ሲሟሉ የስመ ንብረት ዝውውር የሚፈጸም ይሆናል፤
✅ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት/ካርታ፣
✅ጸድቆ የተሰጠ የግንባታ ፕላን፣ የስራ ዝርዝር ግምት ወይም የጸደቀ የነባር ግንባታ ፕላን፣
✅ጸድቆ በተሰጠው የግንባታ ፕላን መሰረት ስለመገንባቱ እና ግንባታው ያለበት ደረጃ የተረጋገጠበት ማስረጃ/50% እና በላይ/፤
✅ውዝፍ የሊዝ ኪራይ ዕዳ የሌለበት ስለመሆኑ የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ወይም ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳውን ገዥው ለመክፈል በፊርማ ያረጋገጠበት የስምምነት ደብዳቤ ፣
✅በንብረቱ ላይ የባንክ እዳ/የፍ/ቤት ዕግድ የሌለበት ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሲቀርብ፣
✅ የቤትና ይዞታ ስም ዝውውር ጥያቄው የቀረበው በህግ ባለመብት/በውርስ/በፍርድ አፈጻጸም ወይም በውክልና ከሆነ ይህንኑ የሚገልጽ ማስረጃ፤
✅ በግለሰቦች ግዥና ሽያጭ ወይም ስጦታ ስምምነት ከሆነ በዉልና ማስረጃ በአካል ቀርቦ በእማኞች የተፈረመ የስምምነት የውል ማስረጃ ሲቀርብ፣
ለ/ በሽያጭ/በስጦታ የሚተላለፍ ቤትና ይዞታ ስም-ዝውውር መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፣
✅ግንባታው በዋስትና ያልተያዘ እንዲሁም እዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም እዳው በሚመለከተው አካል በደብዳቤ መነሳቱ ሲረጋገጥ፣
✅ የቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋገጥና በፍትህ ወይም በመሪ ማዘጋጃ ቤት ፊት ቀርቦ ሲጸድቅ፣
✅ ግንባታው ጸድቆ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት 50 በመቶና በላይ የተሰራ መሆኑ በባለሙያ ተረጋግጦ ሲቀርብ፣
✅ በይዞታው ላይ ውዝፍ የቦታ ኪራይ የሌለበት ስለመሆኑ ወይም ውዝፍ የቦታ ኪራይ ክፍያ አጠናቆ የከፈለ ስለመሆኑ የቀረበ ክፍያ ደረሰኝ ማረጃ ሲቀርብ፣
✅ የአገልግሎትና የገቢዎች ክፍያ በቤቱ ግምት መሰረት ስለመከፈሉ ሲረጋገጥ፣
ዝውውሩ የሚፈፀመው በሊዝ በተገኘ ይዞታና ግንባታ ላይ ከሆነ
✅ የሊዝ ይዞታ ባለቤትነት ኦሪጅናል ካርታና ውል ሲቀርብ፣
✅ በሊዝ ውል መሰረት ክፍያው የተጠናቀቀና ሌሎች ግዴታዎቹን የተወጣ መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም የሊዝ እዳው ያልተጠናቀቀ ከሆነ ስም የሚዞርለት ወገን እዳውን ለመክፈል እና ነባሩን የሊዝ ውል ግዴታዎች የተቀበለ ስለመሆኑ ከከተማው በጽሁፍና በፊርማ አረጋግጦ ሲያቀርብ፣
✅ በሊዝ የተገዛን የመሬት ይዞታ ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ በቅድሚያ በገባው የሊዝ ውል መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የሚፈለገውን የግንባታ ደረጃ ያሟላ መሆኑ ወይም የግንባታ ፈቃድ የጊዜ ገደብ ያላለፈ ወይም የግንባታ ማራዘሚያ የተፈቀደለት መሆኑ ሲረጋጥ፣
✅ የከተማ ቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋጥና በዉልና ማስረጃ ቀርቦ ሲጸድቅ ይሆናል፡፡
ሐ/ በውርስ የተገኘ ይዞታና ቤት የባለቤትነት ስመ-ንብረት ዝውውር አፈፃፀም፣
(ሀ) በውርስ የተላለፈ ነባር ይዞታ ዝውውር ለመፈፀም መሟላት ያለባቸው፡-
✅ የሚዛወረው የመሬት ይዞታ ወይም ቤት ህጋ የባለቤትነት ማስረጃ/ካርታ ሲኖረው፣
✅ ወራሾች የውርስ ባለመብትነትን የሚያረጋግጥ የፍርድ ቤት ውሳኔ ማስረጃ ሲያቀርቡ፣
✅ ወራሾች በውርስ ያገኙትን ይዞታ ወይም ቤት በየግላቸው የባለቤትነት ማስረጃ ለመያዝ ሲፈልጉ ለእያንዳንዳቸው ድርሻ መጠን በፍ/ቤት የፀደቀ ማስረጃ ሲያቀርቡ ወይም የሁሉም ወራሾች የጋራ ስምምነት በውል አፅዳቂ አካል ጸድቆ ሲቀርብ፣
✅ የእያንዳንዱ ወራሽ የድርሻ መጠን በፍርድ ቤት ያልተረጋገጠ ከሆነ የስም ዝውውሩ በሁሉም ወራሾች ስም በጋራ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
የፍርድ ቤቱ የውርሱ ውሳኔ የይዞታ ክፍፍልን የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ የሚፈፀመው የወቅቱን አነስተኛ የይዞታ መጠን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ካልሆነም በተነፃፃሪ የመሬት ይዞታ ድርሻ ህግ ወይም በጋራ ሰነድ/ካርታ መሰረት ይስተናገዳል፡፡
ይዞታው በውሉ መሰረት ግንባታ ለመጀመር የተሰጠውን የጊዜ ገደብ ያለፈበት እና ግንባታው ያልተጀመረ ከሆነ በውርስ ሊተላለፍ አይችልም፡፡
✅በሊዝ የተያዘ ይዞታ ለህጋዊ ወራሽ የሚተላለፈውና ዝውውር የሚፈፀመው፡-
✅ አውራሹ በገባው የሊዝ ውል ግዴታ መሰረት አመታዊውን የሊዝ ክፍያ የፈፀመና ሌሎች የሊዝ ግዴታችን በተገቢው መንገድ የተወጣ ሲሆን፣
✅ ወራሽ አውራሽ የገባቸውን የውል ስምምነቶች(የሊዝ መብት፣ክልከላና ኃላፊነት) ሙሉ በሙሉ የተቀበለ መሆኑን በፊርማው ሲያረጋግጥና ውዝፍ ክፍያ ካለ ከፍሎ ደረሰኝ ሲያቀርብ ይሆናል፡፡
✅ በሊዝ ውሉ መሰረት አውራሹ በህይወት እያለ ለግንበታ መጀመሪያ የተሰጠው የጊዜ ገደብ ካለፈና ግንባታ ካልጀመረ ውሉ ተቋርጦ ቦታው ለከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ተመላሽ ይሆናል፡፡
አውራሽ በይዞታው ላይ ግንባታ ያልጀመረው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑ ከተረጋጠ አውራሽ በህይወት ቢኖር ኖሮ በመመሪያው መሰረት ሊፈቀድለት የሚችለው የግንባታ መጀመሪያ የማራዘሚያ ጊዜ ለወራሽ ሊፈቀድለት ይችላል፡፡
መ/ በባንክ ሃራጅ የሚሸጥ እና የሚወረስ ቤት የባለቤትነት ስም ዝውውር
✅ በባንክ የተሸጠ ቤት የባለቤትነት ስም ዝውውር ለመፈፀም በሐራጅ ጨረታው አሸናፊ የሆነው ሰው ያሸነፈበትን ዋጋና ለዝውውሩ በውል የገባቸው ግዴታዎች ተገልፀው ከባንኩ የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤና ውል ሲቀርብ፣
✅በባንክ ዋስትና ተይዞ የነበረው ይዞታ የባለቤትነት ማረጃ/ካርታ በማህደሩ ውስጥ ካለው ሰነድ ጋር ተገናዝቦ ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ፣
✅ይዞታው በሌላ ባንክ ብድርና ዋስትና ያልተያዘ ወይም እገዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ፣
✅ በሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ዋስትና የተመዘገበ ዋስትና ያለው ባንክ መኖሩ ከተረጋገጠ ባንኩ ስለ ይዞታው መሸጥ ሲፈቅድ፣
✅ በባንክ ሃራጅ ሽያጭ እንዲዞር የተጠየቀው ቤትና ይዞታ የተሟላ ሰነድ የሌለው/ሰነድ አልባ ከሆነ በቅድሚያ በሥራ ላይ ባለው የሰነድ አልባ መመሪያ መሰረት ሰነድ ተሰጥቶት ሲቀርብ፣
✅ ባንኩ ንብረቱን ባለበት ሁኔታ የሚረከብ ከሆነ የቤቱና ይዞታው ግምት እንደማንኛውም ቋሚ ንብረት ግምት ተሰልቶ ተገቢውን የአገልግሎትና የገቢ ክፍያ ሲፈጸም፣
✅ ቤቱና ይዞታው ባንኩ በሚያወጣው ጨረታ የሚሸጥ ከሆነ ባንኩ ያቀረበው የጨረታ መነሻ ዋጋ በከተማው በኩል ተገቢ መሆኑ ተረጋግጦ በጨረታ ሲሸጥ እና የስም ማዛወሪያ ክፍያዎችን ስለመፈጸሙ የክፍያ ደረሰኝ ማስረጃ ሲያቀርብ የሥመ-ንብረት ዝውውሩ የሚፈጸም ይሆናል
ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል
📍 አድራሻ፦ አዲስ አበባ | ደሴ (ወሎ) | ኮምቦልቻ
📞 ስልክ፦ +251910214108
📧 ኢሜይል፦ [email protected]
📱 ቴሌግራም፦ https://t.me/adem2141

የቤት ሽያጭ ውል መደረጉን ክደው ተከራክረው እያለ የሥ/ፍ/ቤቶች ሽያጭ ውል መደረጉ በሰው ምስክር ተረጋግጧል  በሚል ሻጮች ቤቱን ለገዢ እንዲያስረክቡ በማለት የተሰጠ ውሳኔ የማይንቀሳቀስ ሽያ...
20/05/2026

የቤት ሽያጭ ውል መደረጉን ክደው ተከራክረው እያለ የሥ/ፍ/ቤቶች ሽያጭ ውል መደረጉ በሰው ምስክር ተረጋግጧል በሚል ሻጮች ቤቱን ለገዢ እንዲያስረክቡ በማለት የተሰጠ ውሳኔ የማይንቀሳቀስ ሽያጭ ውል አደራረግ ሥርዓት በሚመለከት የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723(1) የተደነገገውን የፌ/ሰ/ሰ/ችሎት በሰ/መ/ቁ 21448 ላይ ከሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሚቃረን በመሆኑ ተሽሯል በማለት በዚህ የሰበር ውሳኔ የተሰጠው የህግ ትርጉም ቀብድ እንደከፈሉ ገልፀው ክስ ቢያቀርቡም ከሥር ፍ/ቤት ጀምሮ ክፍያው ቀብድን የሚመለከት ሳይሆን ከዋናው ሽያጭ ገንዘብ ውስጥ በቅድመ-ክፍያ ብር 1 ሚሊዮን መክፈላቸውን በመረጋገጡ ከጅምሩ በዚህ ረገድ የቀረበው የቀብድ ከፍያለው መከራከሪያ ውድቅ ሆኖ ነገር ግን በፍ/ብ/ህ/ 1723 መሰረት በውል አዋዋይ ፊት ያልተደረገ የቤት ሽያጭ ውል በሻጩ ተክዶ ክርክር በቀረበበት ሁኔታ ውል ስለመኖሩ በምስክር ሰምቶ በማረጋገጥ እንደ ሽያጭ ውሉ ሊፈፅም(ቤቱን እንዲያስረክብ) እና ቀሪ ገንዘብ ተቀብለው ቤቱን ሻጮች ሊያስረክቡ ይገባል ተብሎ የተሰጠ ውሳኔን መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት የፌ/ሰ/ሰ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 215762 እንዲታረም የተደረገበት መዝገብ ነው።
ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል

ጉዳዩ የገጠር እርሻ መሬት ሽያጭ ዉል ሕገ-ወጥ ነዉ ተብሎ ሲፈርስ ገዥ በመሬቱ ላይ ካለማዉ ቋሚ ተክል ጋር በተያያዘ የሚኖረዉን መብት የሚመለከት ነው
20/05/2026

ጉዳዩ የገጠር እርሻ መሬት ሽያጭ ዉል ሕገ-ወጥ ነዉ ተብሎ ሲፈርስ ገዥ በመሬቱ ላይ ካለማዉ ቋሚ ተክል ጋር በተያያዘ የሚኖረዉን መብት የሚመለከት ነው

በፍትሐ-ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ  ክስ የማቅረብ መብት  እና ጥቅም  @✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅                 መግቢያ   ▶️ማንኛውም ማህበረሰብ ሊገመት የሚችል፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የ...
20/05/2026

በፍትሐ-ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ክስ የማቅረብ መብት እና ጥቅም @
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
መግቢያ
▶️ማንኛውም ማህበረሰብ ሊገመት የሚችል፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ የፍትሕ ሥርዓት እንዲኖረው የሥነ-ሥርዓት ሕጎች ሚና ምትክ የሌለው ነው። የፍትሐ-ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ዋና ዓላማ ክርክሮች በዘፈቀደ ሳይሆን በተቀረጹ ሥርዓቶች ተመርተው፣ ምክንያታዊ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ፣ አነስተኛ የሰውና የገንዘብ ሀብት በማውጣት ፍትሐዊ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ ነው። ይህንን ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትሕ (Procedural Justice) ለማረጋገጥ ደግሞ ተከራካሪ ወገኖች ወደ ዳኝነት መድረክ ከመግባታቸው በፊት ሊያሟሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ ቅድመ-ሁኔታዎች በሕጉ ተደንግገዋል።
▶️ከእነዚህ መሠረታዊ የሕግ ደንቦች መካከል አንዱ እና ዋነኛው «ክስ የማቅረብ መብት » የሚባለው የሕግ ጽንሰ-ሀሳብ ነው። በፍትሐ-ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 32 እና 33 ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው፣ አንድ ሰው ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ ዳኝነት ለመጠየቅ ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ወይም ሀብት ላይ በሕግ ወይም በውል የተረጋገጠ መብት ወይንም ጥቅም (Vested Interest) ሊኖረው ይገባል። ይህ መርህ ፍርድ ቤቶች ያለበቂ የህግ መሠረት የሚቀርቡ ፍሬ-ቢስ ክሶችን በመመርመር፣ ተከሳሽን መጥራት ሳያስፈልግ በቁጥር 231(1/ሀ) መሠረት ገና ከጅምሩ ውድቅ በማድረግ የፍርድ ቤቱንና የዜጎችን ወጪና ጊዜ እንዳይባክን ለመጠበቅ ያስችላቸዋል። በአንጻሩ ደግሞ፣ የክሱ ይዘት መብትና ጥቅም መኖሩን በሚያሳይበት ጊዜ፣ በተከሳሽ በኩል የሚነሱ የመብት ክህደቶች ወይም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት (በቁጥር 244(2/መ) መሠረት) የሚቀርቡ መከራከሪያዎች በሥነ-ሥርዓቱ መሠረት ተጣርተው በማስረጃ ሊወሰኑ የሚገባቸው መሆኑን ሕጉ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ያስቀምጣል።
▶️ይህ ጽሑፍ በፍትሐ-ብሔር ክስ የማቅረብ መብት መኖርን፣ ከሳሽ በክሱ ላይ ሊያሳያቸው ስለሚገቡ አስገዳጅ ፍሬ-ነገሮች፣ እና ፍርድ ቤቶች የቀረበውን ክስ መነሻ በማድረግ ተከሳሽን ከመጥራት በፊትና በኋላ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ የሕግ ሥነ-ሥርዓቶችና ኃላፊነቶች በጥቂቱ ይዳስሳል።
✅ፍርድ ቤቶች ክርክሮችን በዘፈቀደ ሳይሆን በሥነ-ሥርዓት ሕግ
መሠረት መምራት ይኖርባቸዋል፡፡ የፍትሐ-ብሔር ሥነ-ሥርዓት
ሕግ መሠረታዊ ዓላማ እና ግብ የፍትሐ-ብሔር ክርክሮች
ምክንያታዊ በሆነ በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ የሰውና የገንዘብ
ሀብት ታይተው ፍትሐዊ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡፡ ይህን
ዓላማ ለማሳካት ይቻል ዘንድም የእኛ አገር ፍትሐ-ብሔር ሥነ-
ሥርዓት ሕግ የተለያዩ ደንቦችና መርሆዎችን ደንግጓል፡፡ በክርክር
ሂደት እነዚህን ደንቦች እና መርሆዎች እንደየ አግባብነታቸው ሥራ
ላይ ማዋል የተከራካሪ ወገኖችን የመሰማት መብት ያገናዘበ፣
የተከራካሪ ወገኖች ብሎም የፍርድ ቤቱ ወጪ እና ጊዜ ያላግባብ
እንዳይባክን በማድረግ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትሕን በማረጋገጥ
በመጨረሻም በጉዳዩ ላይ ፍትሐዊ ውሳኔ እንዲሰጥ በማድረግ
ረገድ የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ ስለመሆኑም መገንዘብ
ያስፈልጋል፡፡
✅ በፍትሐ-ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ዕውቅና ከተሰጣቸው መርሆዎች እና ደንቦች ውስጥ አንዱ አንድ የፍትሐ- ብሔር ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል ሊቀርብ የሚችልበትን ቅድመ ሁኔታ የሚመለከት ደንብ ሲሆን፣ ይህም በሕጉ ቁጥር 32 እና ተከታዮቹ ላይ የተመለከተው ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ አንዱ ከሳሽ የመሆን ችሎታ በሚል ርዕስ በቁጥር 33 ላይ የተደነገገው ሲሆን ለተያዘው :ጉዳይ አግባብነት ያለው በቁጥር 33/2/ ላይ የተደነገገው ነው፡፡
የድንጋጌውም ይዘት “ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ወይም ክሱ
በተመሠረተበት ሀብት ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑ
ካልተረጋገጠ በቀር ማናቸውም ሰው ክስ ለማቅረብ
አይፈቀድለትም” የሚል ሲሆን እንግሊዝኛው “No person may
be a plaintiff unless he has a vested interest in the subject matter of the suit” በማለት ተደንግጓል።እንደሚታወቀው አንድ ሰው አንድን የፍትሐ-ብሔር ክስ ይዞ ወደ ፍርድ ቤት ወይም በሕግ ስልጣን ወደ ተሰጠው የዳኝነት አካል የሚሄደው ዳኝነት ፍለጋ ነው፡፡ ስለሆነም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ በቁጥር 33/2 መሠረት ከሳሽ በሕግ አግባብ ሊወሰንለት የሚችል ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ መብት ያለው መሆኑን በክሱ እንዲያሳይ ይጠበቃል፡፡
✅ይህ በመሆኑም ከሳሽ ክሱን በሚያቀርብበት ጊዜ ለክሱ ወይም ለጠየቀው ዳኝነት ምክንያት ናቸው የሚላቸውን ፍሬነገሮች በዝርዝር የመግለጽ ግዴታ ያለበት ሲሆን፣ ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የቀረበውን ክስ የሚቀበለው ክርክሩ ቢቀጥል በከሳሽ ጥያቄ መሠረት ሊወሰን የሚችል ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ መብት ስለመኖሩ የከሳሽ ክስ ይዘት የሚያሳይ መሆኑን በቅድሚያ ሲያረጋግጥ ነው። ከሳሽ የሚያቀርበው ክስ ለክሱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮችና የተፈጠሩበትን ጊዜና ስፍራ እንዲሁም ተከሳሹ ለክሱ ተጠሪ ወይም ኃላፊ የሚሆንበትን ምክንያት ሊይዝ እንደሚገባ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 33/3 እና 222 (1/ሸ) እና (ረ) ላይ በአስገዳጅመልክ የተደነገገበት አንዱምክንያትም ይሄውእንደሆነ ይታመናል፡፡
✅በዚህም መሠረት ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት
የቀረበውን ክስ ይዘት በማየት ከሳሹ ክሱን ለማቅረብ
የሚያስችለው ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ መብት ያለው
መሆኑን ወይም ያቀረበው ክስ የጠየቀውን ዳኝነት ሊያሰጠው
የማይችል መሆኑን የክሱን ይዘት ብቻ በማየት እንዳስፈላጊነቱ
የክሱን ይዘት ለጉዳዩ አግባብነት ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ
መርምሮ ክርክሩ ቢቀጥልም ለከሳሽ ሊወሰን የሚችል መብት
ስለመኖሩ የከሳሽ ክስ የማያሳይ መሆኑን ካረጋገጠ ተከሳሽን መጥራት ሳያስፈልግ ክሱን ውድቅ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት
የሕጉ ቁጥር 231(1/ሀ) ድንጋጌ ያስገነዝባል፡፡
✅በሌላ በኩል የክሱ ይዘት ሲታይ ከሳሽ በጉዳዩ ላይ መብት
እና/ወይም ጥቅም ያለው መሆኑን ወይም በክርክር ሂደት
ቢረጋገጥ ለከሳሽ ሊወሰን የሚችል መብት/ ጥቅም መኖሩን
የሚያሳይ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ካረጋገጠ ክሱን ተቀብሎ ተከሳሽ
መልስ እንዲሰጥበት የማድረግ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን፣ ክሱ ከሳሽ
በጉዳዩ ላይ መብትና ጥቅም ያለው መሆኑ የሚያሳይ በሆነበት
ሁኔታ ተከሳሽ በሚሰጠው መልስ ከሳሽ ከነገሩ መብትና ጥቅም
የለውም ወይም ከሳሽ ለክሱ መሠረት ያደረገው ፍሬ ነገር
ስለመኖሩ ክዶ መከራከሩ ከሳሽ በነገሩ መብትና ጥቅም የለውም
ወደሚል ድምዳሜ የሚወስድ አይሆንም፡፡ ይልቁንም ተከሳሽ
በዚህ መልኩ የሚያቀርበው ክርክር በክርክር ሂደት ተጣርቶ ውሳኔ
ሊሰጥበት የሚገባው ነው፡፡ በእርግጥ ተከሳሽ እንደመጀመሪያ
ደረጃ መቃወሚያ ሊያነሳ ከሚችላቸው ክርክሮች ውስጥ አንዱ
ከሳሽ መብትና ጥቅም የለውም የሚለውን ሊያካትት እንደሚችል
በሕጉ አንቀጽ 244(2/መ) ላይ ተመልክቷል፡፡
✅ ሕጉ በዚህ መልኩ ሲደነገግ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ከመጥራቱ በፊት ከሳሽ በነገሩ ላይ መብት እና/ ወይም ጥቅም ያለው መሆን ያለመሆኑን ሳያጣራ ተከሳሽ መልስ እንዲሰጥበት ሊያደርግ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ በዚህ ረገድ የሚያቀርበውንመቃወሚያ ከከሳሽክስ ይዘት
አንፃር በመመርመር በመጀመሪያ መቃወሚያው ላይ ውሳኔ
የመስጠት ኃላፊነት ያለበት ሲሆን፤ ነገር ግን ይህን የሚያደርገው
በክርክር ሂደት በማስረጃ ተረጋግጦ ውሳኔ ሊሰጥበት የሚገባውን
የፍሬ ነገር ክርክር ሊሆን አይገባም።
ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል
📍 አድራሻ፦ አዲስ አበባ | ደሴ (ወሎ) | ኮምቦልቻ
📞 ስልክ፦ +251910214108
📧 ኢሜይል፦ [email protected]
📱 ቴሌግራም፦ https://t.me/adem2141

የመኖሪያ ቤት ስጦታ ፎርም
20/05/2026

የመኖሪያ ቤት ስጦታ ፎርም

የማይንቀሳቀስ ንብረት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በማቅረብ ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም ❗️ሰ/መ/ቁ.229608✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33(2) መሰረት ከሳሽ ባቀረበው ክስ ላይ መብትና ጥ...
19/05/2026

የማይንቀሳቀስ ንብረት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በማቅረብ ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም ❗️
ሰ/መ/ቁ.229608
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33(2) መሰረት ከሳሽ ባቀረበው ክስ ላይ መብትና ጥቅም የለውም ተብሎ የሚወሰነው ክስ ባቀረበበት ጉዳይ ላይ መብት ያለው ስለመሆኑ ማስረጃ ሳያቀርብ ሲቀር ነው፡፡ አመልካች በስር ፍ/ቤት ክስ ባቀረበበት ንብረት ላይ መብትና ጥቅም ያለው ስለመሆኑ የተለያዩማስረጃዎችን (በሰበር አቤቱታው ላይ የተዘረዘሩ) ከክሱ ጋር አያይዞ አቅርቦ ሳለ የስር ፍ/ቤቱ አመልካች ክሱን ለማቅረብ መብትና ጥቅም የለውም በማለት ክሱን ውድቅ በማድረግ የሰጠው ብይን እና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው፡፡ የስር ፍ/ቤት መብትና ጥቅም የማይንቀሳቀስ ንብረት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በማቅረብ ብቻ እንደሚረጋገጥ አድርጎ ብይን የሰጠ ሲሆን ይህም የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 36320(ቅጽ 9) በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ክስ ለማቅረብ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማቅረብ ግዴታ አለመሆኑን እና ባለይዞታነት በሌላ መንገድ ሊረጋገጥ እንደሚችል ከሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ውጪ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ነው
ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምሽት የንግድና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የወጣ ደንብ ቁጥር 185/2017https://t.me/adem2141
19/05/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምሽት የንግድና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የወጣ ደንብ ቁጥር 185/2017
https://t.me/adem2141

ሙሉ የውክልና ስልጣን መስጫ ፎርም
19/05/2026

ሙሉ የውክልና ስልጣን መስጫ ፎርም

19/05/2026
የሰራተኛ ቅጥር ውል  ስምምነት ?
19/05/2026

የሰራተኛ ቅጥር ውል ስምምነት ?

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share