Jano Health Science and Business College

Jano Health Science and Business College Higher Educational and Vocational Service

https://forms.gle/WR7uzWf2mDiRJ9sd8
17/04/2026

https://forms.gle/WR7uzWf2mDiRJ9sd8

የተማሪ እርካታ ጥናት አምስት ዋና አላማዎች ፡ 1) የትምህርት ጥራትን መገምገም 2) በማስተማር ዘዴዎች፣ በኮርስ ይዘት እና በአካዳሚክ ድጋፍ የተማሪዎችን እርካታ ለመገምገም። 3) ተቋማዊ አ...

የቅጥር ማስታወቂያ
31/12/2025

የቅጥር ማስታወቂያ

ጃኖ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነሰ ኮሌጂ‎ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያለ‎ኮሌጃችን በዓሉ የሰለም የፍቅር የጤና እንዲሁም የደስታ እንዲ...
26/09/2025

ጃኖ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነሰ ኮሌጂ
‎ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያለ
‎ኮሌጃችን በዓሉ የሰለም የፍቅር የጤና እንዲሁም የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

"ጃኖ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነሰ ኮሌጂ"
"ኑ እንደ አባቶቻችን ሸማ ጥበብን እና እውቀትን በጃኖ ይልበሱ"

ለጃኖ ጤና ሳይንስ  እና ቢዝነስ ኮሌጂ ተማሪዎች ሰራተኞች መምህራን እና ባለ ድርሻ አካላት በሙሉ እንኳን ለ 2018 ዓ.ም አዲስ አመት በሠላም አደረሳችሁ::አዲሱ አመት ከመላ ቤተሠባችሁ ጋር...
16/09/2025

ለጃኖ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጂ ተማሪዎች ሰራተኞች መምህራን እና ባለ ድርሻ አካላት በሙሉ እንኳን ለ 2018 ዓ.ም አዲስ አመት በሠላም አደረሳችሁ::አዲሱ አመት ከመላ ቤተሠባችሁ ጋር የሠላም የደስታ እና የፍቅር እንዲሆንላች ይመኛል።
"ኑ እንደ አባቶቻችን ሸማ ጥበብን እና እውቀትን በጃኖ ይልበሱ" እያለ

ጃኖ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ አስመረቀ፡፡በደብረታቦር ከተማ የሚገኘው ጃኖ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ በዲፕሎማና በዲግ...
28/06/2025

ጃኖ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ አስመረቀ፡፡

በደብረታቦር ከተማ የሚገኘው ጃኖ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ በዲፕሎማና በዲግሪ መርሀ ግብር ሲያስተምራቸው የቆዩትን 204 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉት የጃኖ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ስራአስኪያጅ አቶ ታድሎ ተስፋው እንዳሉት ትምህርት ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያጋጠሙትን ሰውሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች ተቋቁሞ በእውቀትና በክህሎት የበለፀገ የሰው ሀይልን ለማፍራት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ተመራቂዎች ከዚህ ለመድረስ የራሳቸው ውጣ ውረድ እንደተጠበቀ ሁኖ የቤተሰብና የሀገር ውለታ ያለባቸው መሆኑንም ጠቁመው የቤተሰባቸውንና የሀገራቸውን ውለታ መመለስ የሚጠበቅባቸው መሆኑን አስገንዝበው በየተማሩባቸው የትምህርት ዘርፎች ጠንክረው በመስራት ራሳቸውንና ማህበረሰባቸውን መጥቀም እንዳለባቸውም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይኢየሱስ ሰለሞን ባደረጉት ንግግር እንዳሉት ተመራቂዎች የነበሩትን ሰውሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች ተቋቁመው ከዚህ መድረቸሳው ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ተናግረው የተሰጣችውን የእውቀትና የክህሎት ስልጠና በአግባቡ ተጠቅመው በየተማሩበት የትምህርት ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በሰለጠኑባቸው የሙያ መስኮች ስራ ፈጣሪ እንጅ ስራ ፈላጊ ሳይሆኑ ራሳችውን፣ ቤተሰባቸውንና ሀገራቸውን ለመጥቀም በርትታው ሊሰሩ እንደሚገባም ጠቁመው በቀጣይ ህይዎታችሁ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ሳትበገሩ ችግሮችን በማስተዋልና በጥበብ በማለፍ ስኬታማ ለመሆን ጠንክራችሁ መስራት አለባችሁም ብለዋል፡፡

የጃኖ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ተማሪዎች ተወካይ ማስሬ አወቀ በምረቃው ላይ እንደተናገረው የኮሌጁ መምህራንና ሌሎች ሰራተኞች ለተማሪዎች አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ሲያደርጉላቸውና ሲግዟቸው እንደቆዩ ጠቁሞ መምህራኖቻቸው ተማሪዎችን በእውቀትና በክህሎት ለማብቃት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እንዳስተማሯቸው ገልጿል፡፡

ኮሌጁ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች ነጻ የትምህርት እድል መስጠቱ የሚያስመሰግን መሆኑንም ተናግሮ የከተመዋ ማህበረሰብ በጥሩ ሁኔታ ሲያግዛቸው እና እንክብካቤ ሲያደርግላቸው መቆየቱንም ጠቅሶ በነበራቸው ቆይታ ሁለንተናዊ እገዛና ድጋፍ ያደረጉላቸውን አካላት አመስግኗል፡፡

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ በየዲፓርትመንቱ አብላጫ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች ሜዳሊያ የተበረከተላቸው ሲሆን ከሴቶችም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተመራቂዎች ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በኮሌጁ ላቅ ያለ ውጤት ያመጡት ማህሌት ደርበውና ዮናታን አረጋዊ ከዳታቤዝ ማኔጅመንት ዲፓርትመንት እንዲሁም አዳምጤ በጋሸው ከነርሲንግ ዲፓርትመንት ሁላቸውም 4 ነጥብ ይዘው የተመረቁ ሲሆን ለሁሉም የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የዳታቤዝ ማኔጅመንት ዲፓርትመንት ተመራቂዋ ማህሌት ደርበው በዲፓርትመንት፣ በሴቶችና በአጠቃላይ በኮሌጁ የተዘጋጁትን ሽልማቶች መውሰድ ችላለች፡፡

ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ/ም

ውድ የጃኖ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ተማሪዎች ፣መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ  ህዝብ "እንሆ ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለ...
06/01/2025

ውድ የጃኖ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ተማሪዎች ፣መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ "እንሆ ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች "የተባለው ይፈጸም ዘንድ ሁሉ ሆነ ማቲ 1፤23 እንኳን ለ2017 ዓ.ም ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ለ 2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በድፕሎማ መርሃ-ግብር: በነርሲግ፣ በህክምና ላቦራቶሪ ፣ ፋርማሲ፤ በአካውንቲንግ እና በዌብ ደቨሎፕመንትና ዳታቤዝ አድሜንስትሬሽን ደረጃ-4 ምዝገባ ላይ መሆናችን ስናበስር ደስታችን ላቅ ያለ ነው። እንዲሁም በዲግሪ መረሀ ግብር በቢስሲ ነርሲንግ፣በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ በአካውቲንግ እና ፋይናንስ፣ እና በቢዝነስ ማኔጅመንት ምዝገባ ላይ መሆናችን ስናበስር ደስታችን ላቅ ያለ ነው።

ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈለጋላችሁ ? ተነስቷል እንጅ እዚህ የለም ። ሉቃ 24:5ውድ የጃኖ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ተማሪዎች ፣መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም መ...
16/04/2023

ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈለጋላችሁ ? ተነስቷል እንጅ እዚህ የለም ። ሉቃ 24:5

ውድ የጃኖ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ተማሪዎች ፣መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ አደረሰን ። በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ ተመኘን ።
በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ ይሁንልን።
ሀገራችን የመጣብንን ክፉ ዘመን በምህረቱ ይመልስልን።
መልካም በዓል።

ኑ የአባቶቻችን እውቀት እና ጥበብ እንደ ጃኖ ይልበሱ።

ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ አስቸኳይ ማስታዎቂያ
13/04/2023

ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ አስቸኳይ ማስታዎቂያ

ውድ የጃኖ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ተማሪዎች ፣መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ  ህዝብ "እንሆ ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለ...
07/01/2023

ውድ የጃኖ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ተማሪዎች ፣መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ "እንሆ ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች "የተባለው ይፈጸም ዘንድ ሁሉ ሆነ ማቲ 1፤23 እንኳን ለ2015 ዓ.ም ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ለ 2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በድፕሎማ መርሃ-ግብር: በነርሲግ፣ በህክምና ላቦራቶሪ ፣ እና በዌብ ደቨሎፕመንትና ዳታቤዝ አድሜንስትሬሽን ደረጃ-4 ምዝገባ ላይ መሆናችን ስናበስር ደስታችን ላቅ ያለ ነው። እንዲሁም በዲግሪ መረሀ ግብር በቢስሲ ነርሲንግ፣በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ በአካውቲንግ እና ፋይናንስ፣ እና በቢዝነስ ማኔጅመንት ምዝገባ ላይ መሆናችን ስናበስር ደስታችን ላቅ ያለ ነው።
ያስታውሱ:- ከመደበኛው መርሃ ግብር በተጨማሪ ከህክምና ትምህርት ፕሮግራሞች በስተቀር በሌሎች የትምህርት ዘርፎች የኤክስቴንሽን ፕሮግራም የምንሰጥ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። በተጨማሪም የማህበረሰባችን የዳሠሳ ጥናት ፍላጎት መሠረት በቅርቡ ሌሎች የጤና ፕሮግራሞች ማስፋፊያ የጠየቅን መሆኑን በደስታ እንገልፆለን ።
ኑ የአባቶቻችን እውቀት እና ጥበብ እንደ ጃኖ ይልበሱ።

27/09/2022

Address

Debre Tabor
01

Telephone

+251989884430

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jano Health Science and Business College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Jano Health Science and Business College:

Share

Category