የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት/North shoa zone high court/

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት/North shoa zone high court/ ይህ ፔጅ በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሚያከናዉናቸዉን የዳኝነት ስራዎችና ሌሎች የአስተዳደር ስራዎችን ለህዝብ የሚያሳዉቅበት ነዉ

21/08/2026
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች ጋር በቨርችዋል ውይይት አደረጉደ/ብርሃን፡ ነሀሴ 14/2018 ዓ/ም (ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት)የሰሜን ሸዋ ዞን ...
20/08/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች ጋር በቨርችዋል ውይይት አደረጉ
ደ/ብርሃን፡ ነሀሴ 14/2018 ዓ/ም (ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት)

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የባህል ፍርድ ቤት ፎክል ፐርሰን የሆኑት ክቡር ዳኛ አቶ ትእዛዙ ጌታቸው በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የባህል ፍርድ ቤቶችን አፈፃፀም አስመልክቶ በተዘጋጀው የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ የተሳተፉ ሲሆን በተገኙ ግብአቶችና ግምገማዎች ላይ በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስር ላሉ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች በቨርችዋል ገለፃ አድርገዋል፡፡

በገለፃቸውም በ25 ወረዳ ፍርድ ቤቶች ላይ የነበረው የባህል ፍርድ ቤቶች አፈፃፀም የተለያዬ እንደነበር ገልፀው በጥንካሬ የተሰሩ ስራዎችን አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸው እና በክፈተት ታዩትን ጉዳዮች በዝርዝር አንስተው በስፋት ውይይት አድርገውባቸዋል፡፡

የፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ዮሐንስ ወንድሙ በወረዳ ፍርድ ቤች ላይ ያለውን አጠቃላይ የባህል ፍርድ ቤት አፈፃፀም የሰሩትን ወረዳ ፍርድ ቤቶች አመስግነው ምንም ያልጀመሩትንና አስቻይ ሁኔታ እያለ ወደ ስራ ያልገቡ ወረዳ ፍርድ ቤቶችን በስፋት አንስተው ገምግመዋል፡፡ ከክልል በተነሱትና በክፍተት በታዩት ላይም በቀጣይ ሳምንት ለ2 ቀናት ለወረዳ ፕሬዚዳንቶችና ለባህል ፍርድ ቤት ፎካል ፐርሰን ባለሙያዎች ግምገማ ነክ ስልጠና የተዘጋጀ ስለሆነ ውይይት እንደሚያደርጉባቸው በትኩረት አቅጣጫቸው ላይ አስቀምጠዋል፡፡

20/08/2026

ባሕርዳር፣ ነሐሴ 14/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

ማስታወቂያ

በአይ.ሲ.ቲ የሥራ መደቦች ፈተና ለመውሰድ ተመርጣችሁ የፈተና ቦታ እንዲቀየርላችሁ ላመለከታችሁ፤

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ27/04/2018 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች የአይ.ሲ.ቲ የስራ መደቦች ላወጣው የስራ ማስታወቂያ ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም ወደ ቀጣይ የፈተና ሂደት ያለፉ ተወዳዳሪዎችን ዝርዝር አስታውቋል፡፡

በየዘርፎቹ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልተው ያልተካተቱ ተወዳዳሪዎች ቅሬታቸውን እስከ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም እንዲያስገቡ በተቀመጠው መሰረት፣ ቅሬታ ያላቸው አመልካቾች ቅሬታቸውን አስገብተው በመታየት ላይ ሲሆን፣ ለፈተና አልፋችሁ በተለያየ ምክንያት ከአመለከታችሁበት አካባቢ ውጭ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች የፈተና ቦታ ይቀየርልን ብላችሁ በጠየቃችሁት መሰረት የፈተና ቦታ ቅያሬ የተደረገላችሁ መሆኑን እያስታወቅን፣ ከስር በተቀመጠው አግባብ በእለቱ ለፈተና እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፤ የሌሎች ቅሬታ አቅራቢዎች ማመልከቻ በመታየት ላይ ሲሆን፤ በቅርቡ የምናስታውቅ ይሆናል።

የሰሜን ሸዋ ዞን የዳኝነትና የፍትህ አካላት የትብብር መድረክ የ2018 እቅድ አፈጻጸም እና የ2019 እቅድ ላይ ውይይት አደረጉደ/ብርሃን፡ ነሀሴ 12/2018 ዓ/ም (ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ...
18/08/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን የዳኝነትና የፍትህ አካላት የትብብር መድረክ የ2018 እቅድ አፈጻጸም እና የ2019 እቅድ ላይ ውይይት አደረጉ
ደ/ብርሃን፡ ነሀሴ 12/2018 ዓ/ም (ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት)
በዛሬው እለት የሰሜን ሸዋ ዞን የዳኝነት እና የፍትህ አካላት የትብብር መድረክ አብይና የቴክኒክ ኮሚቴ በ2018 እቅድ አፈጻጸም እና በ2019 ዓ.ም እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማድረኩን ያስጀመሩት ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንትና የትብብር መድረኩ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ዮሐንስ ወንድሙ እንደገለፁት የትብብር መድረኩ አባል ተቋማት ነጻነታቸውን ባከበረ መልኩ የፍትሕ አስተዳደሩን ውጤታማ ለማድረግ በሚያገናኟቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ እቅድ በማውጣት እና አፈጻጸሙን በሚመለከት አብይ ኮሚቴውና በቴክኒክ ኮሚቴው በእየጊዜው እየገመገመ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።

የአፈፃፀም ሪፖርቱን ያቀረቡት የቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ እና የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪና ዳኛ ክቡር አቶ ቦጋለ ጌታቸው ሲሆኑ በ2018 ዓ.ም በጥንካሬ የተከናወኑ ተግባራትና በእጥረት በተስተዋሉ ጉዳዮች በዝርዝር አቅርበዋ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ሌላው የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ላይ በጥንካሬና በእጥረት ከተስተዋሉት እንዲሁም ከተዘጋጀው የምክክር መድረክ ግብአት በመውሰድና ከአባል ተቋማቱ ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ የ2019 በጀት አመት እቅድ የታቀደ ሲሆን በእቅዱም ላይ ሰፊ ውይይት አድርገው የሚያሰራ እቅድ መሆኑን ከተወያዩ በኋላ የ2019 እቅድን አፅድቀዋል፡፡

በመጨረሻም መድረኩን ያጠቃለሉት የሰሜን ሸዋ ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊ እና የትብብር መድረኩ ም/ሰብሳቢ ክቡር አቶ ደመረ ቸሬ በበኩላቸው፣ የትብብር መድረኩ ለፍትሕ ፈላጊው ህዝብ የተቀናጀ ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ እና አመኔታን ያተረፈ የዳኝነት እና የፍትሕ አገልግሎት በላቀ ትብብር መስጠት መሆኑን ገልጸው፣ ሁሉም የትብብር መድረኩ አባል ተቋማት በጀመሩት የላቀ ቁርጠኝነት እና የትብብር መንፈስ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተለያዩ የአይ.ሲ.ቲ መደቦች ላወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ለፈተና የተጠሩ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር
14/08/2026

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተለያዩ የአይ.ሲ.ቲ መደቦች ላወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ለፈተና የተጠሩ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር

⚖️📲 የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ43 ፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን አሠራርን ተግባራዊ እያደረገ ነው።የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት የፍርድ ቤቶች የዕቅድ አፈጻ...
11/08/2026

⚖️📲 የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ43 ፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን አሠራርን ተግባራዊ እያደረገ ነው።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት የፍርድ ቤቶች የዕቅድ አፈጻጸም እና በ2019 በጀት ዓመት ተግባራት ዙሪያ ከሚመለከታቸው የዘርፉ መሪዎች ጋር እየመከረ ነው።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው ባለፉት ሦስት ዓመታት የፍትሕ እና የዳኝነት ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል። በዚህም በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል ነው ያሉት።

📁📲 ከትራንስፎርሜሽን ትግበራ ስኬቶች መካከል የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች በውጤታማነት ተጠቃሽ እንደኾኑም ጠቅሰዋል።

በፍርድ ቤቱ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የዲጂታላይዜሽን ሥርዓት ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን፤ ጊዜን የሚቆጥብ፤ ወጪን የሚቀንስ እና የተገልጋዮችን እንግልት የሚያስቀር አሠራር መኾኑን አብራርተዋል።

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ ዳይሬክተር መኳንንት አገኘሁ (ዶ.ር) በፍርድ ቤቱ የተጀመረው የዲጂታላይዜሽን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዲጂታላይዜሽን አሠራርን የጀመረው የዲጂታል የመሠረተ ልማቶችን በመዘርጋት መኾኑንም አብራርተዋል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከወረዳ ፍርድ ቤት እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ የራሱ የኾነ የኔትወርክ ዝርጋታን ማከናወን ችሏል ነው ያሉት።

🗄️ በተጨማሪም የዳታ ማዕከል ማቋቋም፤ ስማርት ችሎቶችን ማደራጀት፤ ኢ-ፋይሊንግ ሥርዓትን መተግበር፤ የደኅንነት ካሜራዎችን መትከል እና ሞባይል መተግበሪያዎችንና ሌሎችንም ሥርዓቶች መተግበር እንደኾነ ጠቅሰዋል። 📱

በመጀመሪያው ዙር በተሠራው የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን 14 የከፍተኛ ፍርድ ቤቶችን እና የባሕር ዳር ማረሚያ ቤትን በኔትወርክ በማስተሳሰር ወደ ዲጂታል ሥርዓት ማስገባት እንደተቻለ ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

በሁለተኛ ዙር የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች ደግሞ እንደ ክላስተር በሚያገለግሉ 27 የወረዳ ፍርድ ቤቶች ላይ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል። እስከአሁን ድረስ በ43 ፍርድ ቤቶች በኔትዎርክ በማስተሳሰር የዲጂታል ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉንም አብራርተዋል።

የዲጂታል ሥርዓት በመተግበሩ በበጀት ዓመቱ ከ51 ሚሊዮን ብር በላይ ባለጉዳዮችን ከወጪ ማዳን መቻሉንም አንስተዋል። ፍርድ ቤቱ ደረጃውን የጠበቀ አሠራር እንዲተገብር የዲጂታል አሠራሩ ከፍተኛ መደላድል መፍጠሩንም ጠቁመዋል።

በቀጣይ የ2019 የበጀት ዓመት የተጀመሩትን የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች በሌሎች የወረዳ ፍርድ ቤቶች ለማዳረስ ትኩረት እንደሚደረግ አመላክተዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አየነ ተስፌ ፤ በተጀመረው የዲጂታል አሠራር ከዞን የሚነሱ ባለጉዳዮች ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መምጣት ሳይጠበቅባቸው አገልግሎቱን እንዲያገኙ ያስቻለ ስለመኾኑም ጠቁመዋል።

በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ ወረዳ ፍርድ ቤቶች መካከልም የወልድያ ከተማ እና የላሊበላ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች ተግባራዊ እየተደረገባቸው እንደሚገኙም ጠቅሰዋል።

ዘገው የአሚኮ ነው

11/08/2026

Address

Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት/North shoa zone high court/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share