04/06/2026
ጥልቅ የሀዘን መግለጫ
በአሩሲ አካባቢ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች እና በቤተክርስቲያን ላይ የተፈፀመው ዘግናኝ ግድያ እና ጥቃት ሰብአዊነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን፣ በሀገሪቱ ህገ-መንግስት እና አለምአቀፍ ስምምነቶች የተረጋገጡ መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶችን በከፋ ሁኔታ የጣሰ ድርጊት ነው።ይህ ድርጊት ከህግ አንጻር ስንመለከተው፦
የመኖር መብት (Right to Life): ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው። ይህ ጥቃት በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 14 እና 15 ላይ የተደነገገውን የተቀደሰ የመኖር መብት የገፈፈ ነው።
የእምነት ነፃነት (Freedom of Religion): በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 27 መሰረት ማንኛውም ሰው የመረጠውን እምነት የመያዝ እና የማከናወን መብቱ የተጠበቀ ቢሆንም፣ ይህ ጥቃት የእምነት ተቋማትን እና አማኞችን ኢላማ በማድረግ መብቱን ጥሷል።
የመንግስት ግዴታ (Duty of the State): መንግስት የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ እና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ቀዳሚ ኃላፊነት አለበት (አንቀጽ 52)።
ጥሪያችን፦
1ኛ.የሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት በጥቃቱ የተሳተፉ ወንጀለኞችን በአስቸኳይ ለህግ እንዲያቀርቡ።
2ኛ.በግፍ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች ተገቢው ፍትህ እና ካሳ እንዲሰጥ።
3ኛ.ወደፊት መሰል የህግ ጥሰቶች እንዳይደገሙ ዘላቂ የህግ ከለላ እንዲደረግ
4ኛ.መንግስት የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ እና ጥፋተኞችን ለህግ የማቅረብ ኃላፊነቱን ይወጣ ህግ ባለበት ሀገር የንፁሃን ደም በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም በንፁሃን ላይ የሚፈፀም ግፍ ይቁም በማለት ጥሪያችንን እያቀረብን
በአጠቃላይ በአሩሲ በሰው ህይወት እና በእምነት ተቋማት ላይ የተፈፀመው ጥቃት የዜጎችን በሰላም የመኖር እና የማመን መብት በከፍተኛ ደረጃ የሚጥስ አሳዛኝ ድርጊት ነው። በግፍ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ጥልቅ ሀዘናችንን እየገለጽን፣
ለሟች ቤተሰቦች እና ለመላው የቤተክርስቲያን ልጆች መጽናናትን፣ለሀገራችን ሰላምን እንመኛለን።
የህግ የበላይነት ይከበር፤ በንፁሃን ላይ የሚፈፀም ግፍ በህግ ይጠየቅ!
#ፍትህ #የህግየበላይነት #አሩሲ #ኢትዮጵያ
ሙሉጌታ ንጉሴ ታደሰ ጠበቃ ና የህግ አማካሪ