Think Legal: law and fact digests

Think Legal: law and fact digests Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Think Legal: law and fact digests, Legal, Debra Markos.

15/02/2025
ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ  ከፍተኛ ጥቅም/ጉዳት  ደርሷል ሊባል የሚችልበትን አግባብ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም በሰ/መ/ቁ 258571 ትርጉም ...
15/02/2025

ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጥቅም/ጉዳት ደርሷል ሊባል የሚችልበትን አግባብ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም በሰ/መ/ቁ 258571 ትርጉም ሰጥቶበታል ፡፡
በሙስና ወንጀል ክስ በወንጀሉ የተገኘ ጥቅም ወይም የደረሰ ጉዳት ከፍተኛ ነው ብሎ ለመፈረጅ የቅጣት አወሳሰን ማንዋሉ ላይ የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን መሰረት በማድረግ ሳይሆን መወሰን ያለበት ጥቅሙ በተገኘበት ወይም ጉዳቱ በደረሰበት ወቅት ገንዘቡ ያለውን የመግዛት አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። በሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 31(2) ስር በእምነት ማጉደል ወንጀል የተገኘውን ጥቅም ወይም የደረሰውን ጉዳት ከፍተኛነት በሚል የተገለጸውን የወንጀል ማክበጃ ግዙፋዊ ፍሬ ነገር ለቅጣት አወሳሰን ዓላማ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ላይ የተመለከተውን መሠረት በማድረግ ሊተረጎም አይገባም፡፡ ይልቁንም ይህ የድንጋጌው ግዙፋዊ ነገር ሊተረጎም የሚገባው የኢኮኖሚ ዕድገት ሁኔታ አመላካቾችን እና የብር የመግዛት አቅም፣ ህጉ ሊያሳካ ያሰበውን ዓላማ፣ የወንጀል ህግ አጠቃላይ ዓላማና ግብ፣ እንዲሁም የወንጀል ህግ አተረጓጎም መርህ መሠረት ባደረገ እኳኃን የተገኘው ጥቅም ወይም የደረሰው ጉዳት መጠን ከግምት እየገባ ተፈጸሚ ሊደረግ ይገባል በማለት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል ::

አበዳሪ ባንክ በመያዣ የተቀበለውን ንብረት ብድሩ ከመሰጠቱ አስቀድሞ ተበዳሪው የግብር ዕዳ የሌለበት  ስለመሆኑ ማስረጃ እስከያዘ ድረስ ቀጥተኛ በሆኑ የግብር/ታክስ ዕዳዎች ቢኖርበትም አበዳሪው...
12/02/2025

አበዳሪ ባንክ በመያዣ የተቀበለውን ንብረት ብድሩ ከመሰጠቱ አስቀድሞ ተበዳሪው የግብር ዕዳ የሌለበት ስለመሆኑ ማስረጃ እስከያዘ ድረስ ቀጥተኛ በሆኑ የግብር/ታክስ ዕዳዎች ቢኖርበትም አበዳሪው በመያዣ በተሰጠው ንብረት ላይ የቀዳሚነት መብት የሚኖረው ስለመሆኑ የተሰጠ ውሳኔ የመ/ቁጥር 235004

08/04/2024

ሰ/መ/ቁ. 184371 /ያልታተመ/
***
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 106560 መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ/ም በዋለው ችሎት እና በሰበር መዝገብ ቁጥር 116583 ታህሳስ 4 ቀን 2008 ዓ/ም በዋለው ችሎት ከመሬት ይዞታ ክርክር ልዩ ባህር እና ጉዳዩን በተለይ የሚገዛው ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 በኋላ የወጣው ልዩ ሕግ አዋጅ ቁጥር 456/1997 መሠረት የተከራካሪ ወገኖች መደበኛ ነዋሪነት የተለያየ ቢሆንም/ባይሆንም የተከራካሪዎቹ ማንነት ከግምት ውስጥ ሳይገባ የገጠር መሬት ይዞታን በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮችን በመጀመሪያ ደረጃ የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የገጠር መሬት ይዞታው የሚገኝበት ክልል የገጠር መሬት አዋጅ በሚደነግገው መሰረት መሆኑን አገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
በመሆኑም ተከራካሪዎቹ ነዋሪነታቸው በተለያየ ክልል መሆኑ ጉዳዩን የፌዴራል ጉዳይ አያደርገውም ።

06/04/2024

ንብረትን ለመሸጥ ለመለወጥ የውክልና ሥልጣን የተሰጠው ተወካይ ንብረቱን አስይዞ መበደር የሚችል ስለመሆኑ- የሰበር ችሎት መ/ ቁጥር 17320 ቅፅ 5
ንብረትን ለመሸጥ ለመለወጥ ብሎም ለሦስተኛ ወገን ለማስተላለፍ በሚል የተሰጠ ውክልና ንብረቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችል ስልጣን እና ችሎታን የሚያጐናጽፍ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3ዐ49(2) ፣ 2206(1) ያስረዳል።
ቤት የመሸጥ የመለወጥና ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ሰው ቤት በመያዣነት የማስያዝ ስልጣን አለው ወይስ የለውም የሚለው ጥያቄ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 22ዐ6 ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ አንጻር መመዘን ያለበት ሲሆን የንብረቱን ባለቤትነት ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ሰው ከዚህ መለስ የሆኑ ተግባራትን የመፈፀም ችሎታ እንዳለውና በተለይም ንብረቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችል ስልጣን እና ችሎታ እንዳለው “ ለራሱ ዕዳ ዋስትና እንዲሆን አንዱን የማይንቀሣቀስ ንብረት በዕዳ መያዣነት አድርጎ ለመስጠት የሚችለው የማይንቀሣቀሰውን ንብረት ለመሸጥ ችሎታ ያለው ሰው ነው “ ከሚለው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3ዐ49 ንዑስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡
አንድ ሰው ቤቱን እንዲሸጥ እንዲለውጥና ለሶስተኛ ወገን እንዲያስተላልፍ የሰጡት የውክልና ስልጣን ተወካዩ ቤቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችለው ስልጣንና ችሎታ የሚያጎናጽፈው መሆኑንን የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 22ዐ6 ንዑስ አንቀጽ 1 እና የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3ዐ49 ንዑስ አንቀጽ 2 ይደነግጋሉ፡፡ ይህም ማለት ወካይ የሰጡት የውክልና ስልጣን ቤቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችል የውክልና ስልጣን ጭምር ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ወካዩ ቤቴን እንዲሸጥ እንዲለወጥ እንጂ በመያዣነት እንዲያስይዝ የውክልና ስልጣን አልሰጠሁም ማለት አይችልም፡፡ ይህም ተወካይ በተሰጠው የውክልና ስልጣን መሠረት ቤቱን በመያዣያነት ያስያዘ እንደሆነ ገንዘብ የተበደረ ለመሆኑ ብቃት ያለው ማስረጃ ነው፡፡ ይህም ለተወካዩ የውክልና ስልጣን ከሰጠበት ቀን ጀምሮ ተወካይ ቤቱን በመያዣነት የማስያዝ ስልጣን የሕግ ችሎታ ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ተወካይ የመያዣ ውል የተዋዋለው የተሰጠው ልዩ ውክልና ከመሻሩ በፊት ከሆነ ተወካይ ከሌሎች ሰዎች ጋር የፈፀመው የመያዣ ውል ሕጋዊ ውጤትና ተፈጻሚነት ያለው ነው፡፡ ተወካይ ውል ሲዋዋል ቤቱን የመሸጥ የመለወጥ ለሶስተኛ ወገን የማስተላለፍና በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 22ዐ6 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3ዐ49 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ቤቱንበመያዣነት ለማስያዝ የማያስችለው ስልጣንና ችሎታ ባለው ጊዜ ውስጥ ውሉን የተዋዋሉ መሆኑ ወይም አለመሆኑ ነው፡፡ የተደረገው የመያዣ ውል ወካይ አረጋግጠው በሰጡት የውክልና ማስረጃ መሠረተ ከሆነ ተወካይ የወካይን ቤት ለመሸጥ፣ ለመለወጥ ለሦስተኛ ወገን ለማስተላለፍ እና ፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 22ዐ6 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3ዐ49 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ቤቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችለው ስልጣንና ችሎታ ይኖረዋል።

መመሪያ ቁጥር 48/2014 (የመመሪያ ቁጥር 44/2013 ፍሬ የማይሰጡ ቋሚ ገቢ የሚያስገኙ አትክልቶች ካሳ አሰላልን በተመለከተ ለማሻሻል የወጣ)
07/05/2022

መመሪያ ቁጥር 48/2014 (የመመሪያ ቁጥር 44/2013 ፍሬ የማይሰጡ ቋሚ ገቢ የሚያስገኙ አትክልቶች ካሳ አሰላልን በተመለከተ ለማሻሻል የወጣ)

Address

Debra Markos

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Think Legal: law and fact digests posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category