17/05/2024
👉በደቡብ ምእራብ ለሚገኙ ጠበቆች በጠበቆች መሀበር ስልጠና ተሰጠ!!!!!!
የሙያ ስነምግባር የሚያከብር ብቃት ያለቸው ጠበቆችን ለማፍራት ተግተን እንሰራለ!!! በሚል መርህን አስቀምጦ የደቡብ ምዕራብ ክልል ጠበቆች ማህበር በክልሉ ርዕሰ ከተማ ቦንጋ በመምህራን ትምህርት ኮሌጅ አዱራሽ በውይይት የተደገፈ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዋናነት የስልጠናው ይዘት አስመልክቶ ፦
1. በጠበቆች ሥነ ምግባር እና የሰነ ምግባር ሙያው ከሚጠይቀው አንፃር ሊኖር የሚገባው የሥነ ምግባር ግዴታዎች ላይ
2. በተገቢው መረጃዎች ላይ በመደገፍ ሥራውን የመስራት እና ተገቢውን መረጃ ለሥራው የሚጠቅመውን ተገቢነቱ ከታመነ ከየትኛውም አካል ቀርቦ መረጃ ጠይቆ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ እና
3. በአዋጁ 1249/13 2/8/ 19/15 2/10/ 2/4/ በዚህ ህግ ""የደንበኛ ማንነት እና የደንበኛ ጉዳይ ምን እነደሆነ እና ምን እንደምመስል እንዲሁም የደንበኛ አቀባበልና የማገልገል ግዴታ እንዲሁም የደነበኛ እምነትን ስለማግኘት " ጠበቃ እና የህግ ምሁር እንዲሁም የጠበቆች ማህበር ሰቢሳቢ የሆኑ አቶ አብዱረህማን / LLB/LLM / በብቃት የተደገፈ በውይይት የተደገፈ ስልጠና ሰጥተዋል።