23/04/2026
2_*ታሪክ ተጽፏል!*_
🎯ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመላው አፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው ተሾሙ። ይህ ሹመት የአንድ መሪ ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመረችው ጉዞ ግቡን እየመታ መሆኑን ለዓለም ያበሰረ ታላቅ ድል ነው። *_አፍሪካ የኢትዮጵያን ብልህነት መርጣለች!_*
📌ይህ ታላቅ ድል የመጣው በዘፈቀደ ሳይሆን፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ በተከናወኑ ግዙፍ ስራዎች ነው። የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም፣ የዲጂታል መሰረተ ልማት ዝርጋታ እና የኢ-መንግሥት አገልግሎቶች ተግባራዊ መሆን ሀገራችንን በአህጉሪቱ ቀዳሚ አድርጓታል። አፍሪካ ይህንን ሹመት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በመስጠት፣ የኢትዮጵያን የፈጠራ ስነ-ምህዳር እንደ አህጉራዊ ተምሳሌት መቀበሏን አረጋግጣለች።