Waj/Nageenyaa fi Callisaa Bul/Magaalaa Baatee የባቲ ከተማ አስተዳዳር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Bati
  • Waj/Nageenyaa fi Callisaa Bul/Magaalaa Baatee የባቲ ከተማ አስተዳዳር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት

Waj/Nageenyaa fi Callisaa Bul/Magaalaa Baatee የባቲ ከተማ አስተዳዳር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Waj/Nageenyaa fi Callisaa Bul/Magaalaa Baatee የባቲ ከተማ አስተዳዳር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት, Legal, Bati.

 #8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነውየካቲት 20/2018 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣የሰላም ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ...
27/02/2026

#8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

የካቲት 20/2018 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣የሰላም ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር 8ኛውን ሀገራዊ የሰላምና ጸጥታ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል ያሉ ሲሆን ለዚህ ውጤት መሳካትም የሕዝባችን የሰላም ፍላጎት፣ተግቶ የሚሰራ አመራር መኖር ፣የጸጥታ አካላት ጥምረት እና ለዘመናት የኖሩ ማኅበራዊ እሴቶቻችን ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው ብለዋል፡፡

መንግሥት ለሰላም ሁልጊዜም ቅድሚያ ይሰጣል ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ በተሳሳተ መንገድ በመሄድ ትጥቅ ይዘው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ አድርጓል ብለዋል፡፡

አክለውም የመንግሥት ፍላጎት ሁልጊዜም ቢሆን ሰላም መሆኑን ገልፀው ፤ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የሕዝባችን እና የጸጥታ አካላት ጥምረት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡

8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ ዓላማ በወቅታዊ ሀገራዊ የሰላምና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት እና የልምድ ልውውጥ በማድረግ በፌዴራል እና በክልል የሰላምና የጸጥታ ተቋማት መካከል ቅንጅትን፣ ተግባራዊ ትብብርን እና የጋራ መግባባትን ማጠናከር ነው፡፡፡

በመድረኩ ላይ የፌዴራል እና የክልል የሰላምና የጸጥታ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
------------------------------------

  የታሪክ ማስታወሻ ብቻ ሳይሆን 🎯 ለብሔራዊ ክብራችን ያለንን ቁርጠኝነት ያስመሰከርንበት🎯 ለነፃነታችን ያሳየነው ወደር የለሽ ፅናት ለዓለም ያበሰርንበት 🎯 ዳግም እንዳይደፍሩን አድርገን ለወ...
26/02/2026

የታሪክ ማስታወሻ ብቻ ሳይሆን
🎯 ለብሔራዊ ክብራችን ያለንን ቁርጠኝነት ያስመሰከርንበት
🎯 ለነፃነታችን ያሳየነው ወደር የለሽ ፅናት ለዓለም ያበሰርንበት
🎯 ዳግም እንዳይደፍሩን አድርገን ለወራሪዎች እና ለጨቋኞች የማይበገረው ኢትዮጵያዊ ክንዳችንን ያሳየንበት ዘመን ተሻጋሪ እሴታችን ነው፡፡

#ዛሬ 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ስናከበር ድሉ ከትላንቱ የዓድዋ ጦርነት ባሻገር ለዛሬው ሀገራዊ ግንባታ እና ለነገው የብሔራዊ ከፍታ እንደ መነሻ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

#ዓድዋን በአግባቡ ከተጠቀምንበት የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ሆኖ እንደኖረው ሁሉ ዛሬም
📌 ለኢትዮጵያ የውስጥ ሰላም
📌 ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና
📌 ለሁለንተናዊ የኢትዮጵያ ብልፅግና ትልቅ የሥነ-ልቦና ስንቅ ነው፡፡

#ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

 #የባቲ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤትለሊት ላይ  ሰላም አስከባሪያችን እና ሚሊሻዎቻችን ባደረጉት ደፈጣ የተያዙ ኮብላዮች ወንድ. 36 ሴት 9 ድምር 45 ወደመጡበት ቄያቸዉ እንዲመለ...
26/02/2026

#የባቲ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት
ለሊት ላይ ሰላም አስከባሪያችን እና ሚሊሻዎቻችን ባደረጉት ደፈጣ የተያዙ ኮብላዮች ወንድ. 36 ሴት 9 ድምር 45 ወደመጡበት ቄያቸዉ እንዲመለሡ ተደርጓል።

 #የባቲ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከመጂሊስ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ወጣቶችን በማደራጀት በየአካባቢያቸዉ ያሉትን መስጂዶችን እና የአካባቢያቸዉን ሰላም ለመጠበቅ ሰፊ ዉይይ...
26/02/2026

#የባቲ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከመጂሊስ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ወጣቶችን በማደራጀት በየአካባቢያቸዉ ያሉትን መስጂዶችን እና የአካባቢያቸዉን ሰላም ለመጠበቅ ሰፊ ዉይይቶችን በማድረግ ሁሉም ወጣቶች ወደ ስራ ለመግባት እንዲሆኑ ተደርጓል

19/6/2018
#ባቲ

" ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት የመጡትን የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግን ተቀብዬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። የኢትዮጵያ እና እስራኤልን ግንኙነት በማጤን በወል ፍላጎታችን ላይ ...
25/02/2026

" ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት የመጡትን የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግን ተቀብዬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። የኢትዮጵያ እና እስራኤልን ግንኙነት በማጤን በወል ፍላጎታችን ላይ ተመስርተን ትብብራችንን የምናሳድግባቸውን መንገዶች ተመልክተናል።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር)

አድዋ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት በመቆም ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን በማይሻር የአሸናፊነት ማህተም እንዲፀና ያደረጉበት አንጸባራቂ ድል ነዉ፡፡አድዋ የኢትዮጵያውያን የአብሮነት እና የጽናት ውጤት...
25/02/2026

አድዋ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት በመቆም ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን በማይሻር የአሸናፊነት ማህተም እንዲፀና ያደረጉበት አንጸባራቂ ድል ነዉ፡፡

አድዋ የኢትዮጵያውያን የአብሮነት እና የጽናት ውጤት ነው፡፡

የአድዋ ድል የኅብረ ብሔራዊነት ውጤት እንደመሆኑ ዛሬ ላይ ያለን ኢትዮጵያዊያን የብሔር፣የእምነት፣የፖለቲካ፣የቋንቋ እና መሠል ልዩነቶች ሳይገድበን ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ልናጠናክር ይገባል።

ከአድዋ ድልን ብቻ ሳይሆን መተባበርን፣አንድነትን፣መቻቻል እና ፍቅርን ጭምር ነው የተማርነው

ወጣቶች የአድዋ ድል የመደመር ውጤት እና የጋራ ድል መሆኑን በውል በመገንዘብ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት እንዲጎለብት እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሊሰሩ ይገባል።

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

18/6/2018
#ባቲ

የባቲ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከቴክኒክና ሙያ ት/ቤት የሰላም ክበብ አደረጃጀት ተማሪዎችና መምህራን ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት መደረግ ተችሉዋል።17/6/2018 ...
24/02/2026

የባቲ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከቴክኒክና ሙያ ት/ቤት የሰላም ክበብ አደረጃጀት ተማሪዎችና መምህራን ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት መደረግ ተችሉዋል።
17/6/2018
#ባቲ

 #ሀገር ማገልገል ክብር ነዉ።💯✅ክብር ንፋስና ብርድ ሳይበግረዉ የሚያገለግሉት መከላከያ ሰራዊታችን💯✅
23/02/2026

#ሀገር ማገልገል ክብር ነዉ።💯✅ክብር ንፋስና ብርድ ሳይበግረዉ የሚያገለግሉት መከላከያ ሰራዊታችን💯✅

ኢትዮጵያዊነት፦🎯 በብዙ ኅብር ያሸበረቀ🎯 ብዝኃነትን በውስጡ ያቀፈ🎯 አንድ ዓይነትነትን የማይጠይቅ አንድነት🎯 በአኩሪ ታሪክ የከበረ የወል ማንነታችን🎯 በእሴቶች፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ መልክዓ ...
23/02/2026

ኢትዮጵያዊነት፦
🎯 በብዙ ኅብር ያሸበረቀ
🎯 ብዝኃነትን በውስጡ ያቀፈ
🎯 አንድ ዓይነትነትን የማይጠይቅ አንድነት
🎯 በአኩሪ ታሪክ የከበረ የወል ማንነታችን
🎯 በእሴቶች፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ መልክዓ ምድሮች እና አኩሪ ማንነቶች የደመቀ አንድነት ነው።

ዜጎቿም፦
👉🏿 የጋራ አኩሪ ታሪክ
👉🏿 የጋራ ማኅበራዊ እሴቶች
👉🏿 የጋራ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ሀብቶች
👉🏿 በደም የተሳሰረ ኅብረ-ብሔራዊ ማንነት አሏቸው።

እኛ ኢትዮጵያዊያን፡-
🗝 በርካታ የወል ማንነቶች ያሉን
🗝 በጋራ የመበልፀግ ፀጋ እና ዕድል ያለን
🗝 የተጋመደ የጋራ ሀገራዊ ማንነት ያለን ህዝቦች ነን።

የወል ማንነታችን የሆነውን ኢትዮጵያዊነታችንን ያገኘነው የግዛት አንድነት የምንጋራ ሕዝቦች በመሆናችን ብቻ ሳይሆን በብዙ ተጋድሎ፣ በደም የፀና የጋራ ታሪክ እንዲሁም የደም ትስስር ያለን ሕዝብ በመሆናችን ነው።

ከተናጠል እና ቡድን ማንነት ጎን ለጎን መሄድ የሚችሉ ተመጋጋቢ፣ የአንዱ መኖር ለአንዱ ጥቅም እና አቅም የሚሆንበት ነው።

የኃይማኖት፣ የባህል፣ የፖለቲካ እና የአመለካከት ልዩነቶች የነበሩ እንዲሁም ሁል ጊዜም የሚኖሩ ስለሆኑ በነዚህ ሳይወሰኑ የጋራ ማንነት የሆነውን ሀገራዊ የወል ማንነት በማጠናከር ለጋራ ሰላም እና ብልፅግና በአብሮነት መቆም አሁን ያለንበት ጊዜ እና ሁኔታ የሚፈልገው ነገር ነው።

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊
------------------
#ባቲ

 #የባቲ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ በአሁን ሰዐት በከተማችን ዳርዳር በህገወጥ መልኩ ሲጓዙ የነበሩ ኮብላዮችን በፌደራል ፖሊስ በሚሊሻ በጋራ በመሆን እልህ አስጨራሽ በሆነ መልኩ በቁጥጥር...
21/02/2026

#የባቲ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ በአሁን ሰዐት በከተማችን ዳርዳር በህገወጥ መልኩ ሲጓዙ የነበሩ ኮብላዮችን በፌደራል ፖሊስ በሚሊሻ በጋራ በመሆን እልህ አስጨራሽ በሆነ መልኩ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሉዋል።
#ህገወጥ ተግባሮችን
#በጋራ እንከላከል
14/6/2018
#ባቲ

 #ከቀኑ 6:10-ላይ-በህገወጥ-መልኩ-(13)-ኮብላዮችን- ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አንድ ሹፌር ከነ ተሽከርካሪዉ በቁጥጥር ስር መዋል ተችሉዋል።13/6/2018 #ባቲ
20/02/2026

#ከቀኑ 6:10-ላይ-በህገወጥ-መልኩ-(13)-ኮብላዮችን- ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አንድ ሹፌር ከነ ተሽከርካሪዉ በቁጥጥር ስር መዋል ተችሉዋል።
13/6/2018
#ባቲ

ነጠላ ትርክቶችን በአሰባሳቢ የወል ትርክት ለመተካት በሀገር ደረጃ በመንግሥትም አቅጣጫ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራበት ያለ ተግባር ነው።  የወል ማንነትን የሚያጠናክሩ እሴቶችን🖊ማጎልበት...
19/02/2026

ነጠላ ትርክቶችን በአሰባሳቢ የወል ትርክት ለመተካት በሀገር ደረጃ በመንግሥትም አቅጣጫ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራበት ያለ ተግባር ነው።

የወል ማንነትን የሚያጠናክሩ እሴቶችን
🖊ማጎልበት
🖊ለትውልድ ማስተላለፍ እና
🖊ማኅበራዊ ግንኙነትን ማጠናከር ናቸው።

🕊 አስተማማኝ ሰላምን ለመገንባት እንዲሁም ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ማንነት የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን ከፍ ማድርግ አስፈላጊ ነው።

🕊 በሀገራዊ አንድነት የሚያሰባስበንን የጋራ ትርክት ለመገንባት ዋና ዋና ጉዳዮችን ከሀገራችን ታሪካዊ እና ተፈጥሮአዊ እውነታዎች ጋር አጣጥሞ መረዳትም እንዲሁ ተገቢ ነው።

🕊 ሀገራዊ ምክክርን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት ፕሮግራሞች የሀገር አንድነትን የሚያስተሳስሩ ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች እና የልማት ትልሞችን ማሳካት ሌላው የአሰባሳቢ ትርክት ማጎልበቻ መንገድ ነው። ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ለብሔራዊ መግባባትም ጉልህ አስተዋፅኦም ያበረክታሉ፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

#ባቲ

Address

Bati

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Waj/Nageenyaa fi Callisaa Bul/Magaalaa Baatee የባቲ ከተማ አስተዳዳር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category