Very important documentations for life

Very important documentations for life business, comedy, health, others

20/06/2021

✍️ #ሰውነት #ላይ #የሚወጣ #ሸንተረር #መከላከያ #ዘዴዎቹ #ምንድን ናቸው?

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

♥♥ #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥

📌 ክብደትን መጠበቅ
📌 የተመጣጠነ ምግብን መጠቀም
📌 በቫይታሚን እና በሚኒራል የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ
📌 በቂ ውሃን መጠጣት (8-12) ብርጭቆ ውሃ መጠጣት
📌 ቫይታሚን ኤ መውሰድ ወይም በምግብነት መልኩ መጠቀም፡፡
📌 ሬት(አሎቬራ)
📌 የኮኮናት ዘይት
📌 ስኳር

👉 #አዘገጃጀት ፡- አንድ ስኒ ስኩዋር ከ¼ ስኒ አልመንድ(ለውዝ) ዘይት ወይም ኮኮናት ዘይት፣የሎሚ ጠብታዎች በመደባለቅ በሳምንት አራት ከቀን በመጠቀም 8-10 ደቂቃ ማሸት

👉 👉 #ማንኛውም ከጤና ጋር ከተያያዙ ችግሮች ላይ ለመመካከር ካሻዎ 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 1 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!

👉 👉 #በሚከተሉት #የማህበረሰብ #ትስስር #ድህረገጾች #ይከታተሉን፡-
✅ የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
👉👉👉 http://tiny.cc/gf606y

✅ የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
👉👉 T.ME/DOCTORALLE8809

የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦ subscribe
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ

(በጤና ባለሙያ ሄርለም)

08/06/2021

🚨 ⤵️
/ በነፃ ለማውረድ ከስር ይጫኑ ⤵️⤵️
👉 https://t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 https://t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 https://t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 https://t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn

🛡️ ተጨማሪ ማብራሪያ በቪዲዮ ለመከታተል ⤵️
➡️ https://bit.ly/3qO8YAP
➡️ https://bit.ly/3qO8YAP

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪና ጠበቃ
0911 190 299


📱 0911-190-299


#አመለካከት 🇪🇹 #ሀበሻ

05/06/2021

✍ #የጠቆረ #ከንፈር #እንዴት #ማቅላት #ይቻላል

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

♥♥ #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥

👉 #ከንፈር እንዲጠቁር የሚያደርጉ ምክንያቶች

📌 ከፍተኛ ለሆነ የፀሃይ ጨረር መጋለጥ
📌 በአለርጂ ተጠቂ ከሆኑ
📌 ጥራታቸውን ያልጠበቁ የከንፈር ላይ ቅባቶችን መጠቀም
📌 ሲጋራ ማጨስ
📌 አልኮል ከመጠን በላይ መጠጣት እና ጫት መቃም
📌 የሰውነታቸን ሆርሞኖች አለመጣጣም

👉 # የጠቆረ ከንፈር ለማቅላት የሚረዱ ዘዴዎች ፡-

📌 ሎሚ ፡- ሎሚ የሞቶ ሴሎችን ለማንሳት እና የጠቆረ ቆዳን ለማከም ይረዳናል

አዘገጃጀት -ሎሚውን በመጭመቅ ማታማታ ከ1-2 ውር ከንፈር መቀባት

📌 ፅጌሬዳ አበባ ፡- ፅጌሬዳ አበባ የጠቆረ ቆዳን ለማከም ይረዳናል

አዘገጃጀት - ፅጌሬዳ አበባ በማዘጋጀት በአነስተኛ ውሃ ላይ መዘፍዘፍ እና ማቆየት ከዛም ውሃው ውስጥ ማር ወይም ወተት በመደባለቅ መቀባት ይህን በቀን ውስጥ ከ3-4 ጊዜ እየደጋገሙ ይቀቡ

📌 የወይራ ዘይት ፡- የወይራ ዘይት ከንፈር በቂ የሆነ እርጥበት እንዲኖረው በማድረግ እንዲለሰልስ ያደርገዋል

አዘገጃጀት - ማታ ላይ ሁልጊዜ የወይራ ዘይቱን መቀባት

📌 ስኳር ፡- ስኳር የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ቀርፎ በማንሳት አዲስ ከንፈር እንዲኖሮት ያደርጋል

አዘገጃጀት - 3 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ስኳር በማዘጋጀት በላዩ ላይ 2 የሻይ ማንኪያ ቅቤ በመጨመር ማዋሃድ ከዛም ከንፈሮን ማሳጅ እያደረጉ ይቀቡ ይህንንም በሳምንት በተደጋጋሚ ያድርጉ

📌 ኩከምበር ፡- ኩከምበር የጠቆረ ቆዳን ለማከም ይረዳናል

አዘገጃጀት - ኩከምበር ቆርጦ በማዘጋጀት በቁራጩ ከንፈርን ማሸት ይህንንም በቀን 1 ጊዜ ያድርጉ

📌 ማር ፡- ማር ማታ ላይ በስሱ በመቀባት ማሳጅ ማድረግ ከዛም ጠዋት ላይ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ

📌 እንጆሬ ፡- እንጆሬውን በመቁረጥ ማታ መቀባት ከዛ ከ1 ሰአት በኋላ ወይም አሳድሮ መቀባት

👉 ምንጊዜም ማታማታ ከንፈሮ ላይ የተቀቡትን ሊፒስቲክ ወይም ቻፒስቲክ ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት ይልመዱ ፣ከለር ያላቸውን ሊፒስቲኮች አያዘውትሩ እና በቀን ውስጥ በቂ ውሃ ይጠጡ

👉👉 ከከንፈር መጥቆር ጋር በተያያዘ እንዲሁም በማንኛውም የጤና ችግሮች ጋር በተያያዘ ለመመካከር 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!

👉?? #በሚከተሉት #የማህበረሰብ #ትስስር #ድህረገጾች #ይከታተሉን፡-

✅ የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
👉👉👉 http://tiny.cc/gf606y

✅ የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
👉👉 T.ME/DOCTORALLE8809

✅ የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦ subscribe
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ

( #በጤና #ባለሙያ #ሄርለም)

03/06/2021

🚨 🚨 / በነፃ ለማውረድ ከስር ይጫኑ ⤵️⤵️
👉 https://t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 https://t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 https://t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 https://t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn

🛡️ ተጨማሪ ማብራሪያ በቪዲዮ ለመከታተል ⤵️
➡️ https://bit.ly/3qO8YAP
➡️ https://bit.ly/3qO8YAP

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪና ጠበቃ
0911 190 299


📱 0911-190-299


#አመለካከት 🇪🇹 #ሀበሻ

26/05/2021

✍ #የአንጀት #ቁስለት

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

♥♥ #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥

⏩ #የአንጀት ቁስለት የምንለው የሕመም ዓይነት የሚከሰተው በቫይረስ ፣ በባክቴሪያ ፣ እና በፓራሳይት አማካኝነት የተበከለን ምግብ በምንመገብበት ወቅት ነው. እነዚህ ተህዋስያን ምግብን በምናበስልበት ወቅት ሊበከሉ ስለሚችሉ ለምንመገበው ምግብ ንፅህና ጥንቃቄ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡

👉 #የአንጀት #ቁስለት #ምልክቶች

📌 ማቅለሽለሽ
📌 ማስመለስ
📌 ተቅማጥ
📌 ክብደት መቀነስ
📌 የሆድ መነፋት፣ መጮህና የሆድ ድርቀት
📌 በቆዳ ላይ እጅብ ያለ ሽፍታ መውጣት
📌 የፈስ መብዛት፣ ማስማጥና በፊንጢጣ ደም መውጣት
📌 የሆድ ቁርጠት እና ትኩሳት ናቸው፡፡ እነዚህ ምልክቶች ለቀናት ሊቆዮ ይችላሉ፡፡

👉👉 #ለአንጀት #ቁስለት #ተጋላጭንትን #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች

📌 በእድሜ የገፉ ሰዎች ሕመም የመከላከል አቅማቸው እየተዳከመ ስለሚመጣ ተጋላጭ ይሆናሉ፣
📌 ነፍሰጡር ሴቶች ለአንጀት ቁስለት ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው
📌 ሕፃናት በሽታን የመከላከል አቅማቸው ጠንካራ ስላልሆነ በቀላሉ ለአንጀት ቁስለት ይጋለጣሉ
📌 ተጓዳኝ ሕመም ያለባቸው ሰዎች እንደ ስኳር ሕመም ፣ ጉበት ሕመም ፣ በኤድስ የተጠቁ ሕሙማን ተጋላጭነታቸው የሰፋ ነው፡፡

👉👉 #ሐኪምዎን #ማማከር #የሚገባዎ #መቼ #ነው?

📌 በተደጋጋሚ የሚያስመልስዎ ከሆነ
📌 ደም የቀላቀለ ትውከት ወይንም ተቅማጥ ከኖረ
📌 ከ3 ቀናት በላይ የሚቆይ ተቅማጥ ከኖረ
📌 ከፍተኛ የሆነ የሆድ ቁርጠት ካለ
📌 ከፍተኛ ትኩሳት ካለዎት
📌 ከፍተኛ የውሃ ጥማት ፣ የአፍ መድረቅ ፣ የድካም ስሜት ፣ ማዞር እና አነስተኛ የውኃ ሽንት ካለዎት ናቸው፡፡

👉 👉 #የምግብ #መመረዝን #ለመከላከል #ምን ማድረግ #ያስፈልግናል?

📌 የእጅን፣ ምግብ ማብሳያን እና መመገቢያ ቁሳቁሶችን ንፅሕና መጠበቅ
📌 ጥሬ /ያልበሰሉ/ ምግቦችን አለመመገብ
📌 ምግብዎን በፅዱ ቦታ ማስቀመጥና በተስማሚ የሙቀት መጠን ማብሰል
📌 ምግብዎን ለማቆየት ከፈለጉ በማቀዝቀዣ ውስጥ በማስቀመጥ እንዳይበከል መከላከል፡፡

👉 3 ቀናት በላይ የሚቆይ ተቅማጥ ፣ከፍተኛ የሆነ የሆድ ቁርጠት እና በተደጋጋሚ ማስመለስ ከተመለከቱ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ተገቢ ነው!!! የዚህ ችግር ተጠቂ ከሆኑና ስለ ህመሙ ያሎትን ጥያቄዎች ለማቅረብ 8809 ይደውሉ ባለሙያዎችን ያማክሩ !!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!

📌 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረገጾች ይከታተሉን
✅ የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
👉👉👉 http://tiny.cc/gf606y

✅ የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
👉👉👉 T.ME/DOCTORALLE8809

✅YouTube:👉
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ

( #በጤና #ባለሙያ #ሄርለም)

26/05/2021

✍️ #ህጻናት #ላይ #ድንገተኛ #የሆኑ #አደጋዎች #ቢያጋጥሙ #ልንሰጣቸው #የሚችሉ #የመጀመሪያ #እርዳታዎች

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

♥♥ #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥

⏩ #ነስር

🔹 የአፍንጫ መድማት የተለመደና በአብዛኛው ህፃናቶች ፀሀይ ሲመታቸው ይከሰታል። ለዚህም ህፃኑ ቀጥ ብሎ እንዲቀመጥ ማድረግ ይህም የህፃኑን አፍንጫ ደምስር የደም ግፊት በመቀነስ ደም መፍሰስ እንዳይኖር ያደርጋል።
🔹 በአውራ ጣትና በጠቋሚ ጣት የህፃኑን አፍንጫ ቆንጥጦ በመያዝ በአፉ እንዲተነፍስ ማድረግ። አፍንጫውን ይዘው ከ 5-10 ደቂቃ መቆየት።
🔹 በህፃኑ አፍንጫ አካባቢ በረዶ ለመያዝ መሞከር።
🔹 በድጋሚ የአፍንጫ መድማት እንዳይኖር ህፃኑ አፍንጫውን እንዳይነካ ማድረግ።

👉👉 እነዚህ ሁኔታዎች ካሉ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ያድርጉ፦
🔹 ከ 2 ደቂቃ በላይ አፍንጫው የሚደማ ከሆነ
🔹 ከደም መድማት በኃላ አደጋ፣ መውደቅ ወይም የራስ ቅል አካባቢ ጉዳት ካለ።

⏩ #በስለት #ነገሮች #መቆረጥ ( #ቁስል)

🔹 በንጹህ ጨርቅ የሚፈሰውን ደም ማቆም
🔹 ጨርቁ በደም ከተነከረ በባንዴጅ ከላይ በድጋሚ መጠቅለል
🔹 ደሙ አሁንም ካልቆመ ቁስሉን ከልብ በላይ ከፍ ማድረግ ወይም ማንጠልጠል ።
🔹 ደሙ ከቆመ በኃላ በንጹህ ውሃ እና ሳሙና ቁስሉን ማጠብ ወይም ማጽዳት።
🔹 ፀረ ባክቴሪያ ጠብታ መድሃኒቶችን መጠቀም።
🔹 ከዚያም ቀስሉን ሙሉ ለሙሉ በጨርቅ ወይም ባንዴጅ ጠቅልሎ ማሰር (የደም ዝውውር እንዳይስተጓጐል በጣም አጥብቀው አይሰሩት።

⏩ #ቃጠሎ ( #የእሳት #አደጋ)

🔹 የቃጠሎውን ቦታ በቀዝቃዛ የቧንቧ ውሃ ቢያንስ ለ 5 ደቂቃ ወይም ህመሙ እስከሚቀንስ ያፍሱበት። ውሃ ውስጥ መንከርም ሌላ አማራጭ ነው።
🔹 በቃጠሎ ቦታ በፍጽም በረዶ አያድርጉበት ምክንያቱም በረዶ በቁስሉ ላይ ማድረግ ሀይለኛ ቅዝቃዜ በቆዳችን ላይ ጉዳት ስለሚያስከትሉ ለበለጠ ጉዳት ይዳርገዋል።
🔹 የቃጠሎው ቦታውን ስቴራይል(sterile) በሆነ ጐዝ ባንዴጅ ሳናጠብቅ በስሱ መሸፈን ይህም የሚጠቅመን የተቃጠለውን ቆዳችን አየር እንዲያገኝና ህመሙ እንዲቀንስ ያደርገዋል። 🔹 ብናኝ ያለው ጥጥ በፍጽም አይጠቀሙ።
🔹 ህመሙን ለመቀነስ ማስታገሻ መጠቀም
🔹 ቀላል የቃጠሎ አደጋ ያለምንም ህክምና ይድናል። ነገር ግን ኢንፌክሽን እንዳይከሰት መከታተል ይኖርብናል። ለምሳሌ የህመም መጨመር፣ መቅላት፣ ትኩሳት፣ እብጠት ምልክቶችን መከታተል አለብን እነዚህ ምልክቶች ከታዮ ኢንፌክሽን ሊከሰት ስለሚችል የህክምና እርዳታ ማግኝት ያስፈልጋል።

⏩ #ስብራት

🔹 የአጥንት መሰበር ሲከሰት የህክምና እርዳታ ማግኝት ግድ ነው ነገር ግን የህክምና እርዳታ እስከምናገኝ የሚከተለውን እናድርግ
🔹 የደም መፍሰስ ካለ በንጹህ ጨርቅ ወይም ስቴራይል ባንዴጅ በመጠቀም ማቆም።
🔹 ህክምና እስከምናገኝ ህመሙን ለመቀነስ እና እብጠት እንዳይኖር በረዶ መጠቀም። በረዶውን ቀጥታ ቆዳችን ላይ ከማድረግ ይልቅ በጨርቅ ወይም ፎጣ ጠቅልሎ መጠቀም።
🔹 ህፃኑ እንዳይንቀሳቀስ ማድረግና ስብራትን በእንጨት ወይም በሌላ ነገር መጠገን ስልጠና እስካልወሰድ ድረስ ምንም እንዳይነኩት።
🔹 ህፃኑ እራሱን ስቶ ከወደቀ፣ የትንፋሽ እጥረት ካለበትና ቶሎ ቶሎ የሚተነፍስ ከሆነ ህፃኑን በጥንቃቄ በጀርባው በማስተኛት ጭንቅላቱን ከሆዳችን በታች ዝቅ በማድረግ እና እግርን ወደላይ ከፍ በማድረግ
የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጠት ተገቢ ነው።

⏩ #መርዛማ #ነገሮች #መውሰድ

🔹 አፍና ከንፈር አካባቢ የማቃጠልና መቅላት ምልክቶች ይታያሉ ይህም መርዛማ ፈሳሽ መጠጣታቸውን ጠቋሚ ነው።
🔹 ከአፋቸው የሚወጣው የኬሚካል ሽታ በማሽተት በቀላሉ መለየት ለምሳሌ ጋዝ ወይም የቀለም ማቅጠኛ
🔹 ማስመለስ፣ ለመተንፈስ መቸገር፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ግርታ ያጋጥማል።
🔹 የህክምና እርዳታ እስከምናገኝ ድረስ የሚከተሉትን እናድርግ
🔹 የወሰድት መርዝ የቤት ማጽጃ ወይም ሌሎች ኬሚካሎች ከሆኑ እቃው ላይ የተፃፈውን ማንበብ
🔹 መርዙ በልጅዎ ልብስ፣ ቆዳ ወይም አይን ላይ ከፈሰሰ ልብሳቸውን በፍጥነት ማውለቅና በቆዳ እና አይን ላይ ቀዝቃዛ ንጹህ ውሃ ማፍሰስ ወይም ለ20 ደቂቃ ሻወር እንዲወስድ ማድረግ 🔹 ወደ ህክምና ስንወስደው መርዙ የተቀመጠበትን እቃ ይዞ መሄድ

⏩ #ትንታ/መታፈን

🔹 ህፃናት ጎጂ ነገር መሆኑን ሳያውቁት ትናንሽ ነገሮችን ይውጣሉ፡፡ ትንታ የሚፈጠረው የዋጡት ቁስ አካል በመተንፈሻ ቧንቧ ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ሲሆን በዚህ ጊዜ አየር እንዳይገባና ወደ አእምሮ የሚሄደውን ኦክስጂን ያግደዋል/ያቋርጠዋል፡፡
🔹 🔹 የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እንዴት ይሰጣል?
🔹 ከህፃኑ ጀርባ በመቆም እጅዎን በልጁ ወገብ በማሳለፍ ልጁን በትንሹ ዘንበል ማድረግ
🔹 ከልጁ እንብርት በላይ በአንድ እጅዎ ሆድን በስሱ መምታት
🔹 ሁለት እጅዎን አጣምረው ይዘው ሆድን በደንብ ጫን ጫን ማድረግ
🔹 የተቀረቀረው አካል እስከሚወጣ ድረስ ይደጋግሙት፡፡

👉👉 #ህጻን ልጆ በድንገት አደጋ ቢያጋጥመው የመጀመሪያ እርዳታ ከባለሙያ ጋር እየተማከሩ ይስጡ! ከዚህና ተያያዥ በሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ ጥያቄ ካሎት በቤቶ ሆነው ወደ 8809 ላይ በመደወል ከባለሞያዎችን በቀጥታ በመገናኘት ይመካከሩ፡፡ ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን፡-
✅ የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
👉👉👉 http://tiny.cc/gf606y

✅ የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
👉👉👉 T.ME/DOCTORALLE8809

✅ የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦ 👉
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ

( #በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)

25/05/2021

‼️ አዲሱን አዋጅ በነፃ ያውርዱ ⤵️
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
#አመለካከት 🇪🇹 #ሀበሻ

24/05/2021

🚨 ⤵️⤵️

የውሎ አበል ማለት አንድ ተቀጣሪ የተቀጠረበትን ሥራ ለማከናወን መደበኛ የስራ ቦታው ከሚገኝበት ከተማ ውጪ ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ በሚሄድበት ጊዜ ለመኝታ ፣ለምግብ ፣ለመጠጥና ለተዛማጅ ወጪዎች የሚከፈል አበል ነው፡፡

#የውሎ አበል ከግብር ነፃ የሚደረግበት ሁኔታ

1.በሀገር ውስጥ ለሚደረጉ ጉዞች የሚከፈል ውሎ አበል፤
ሀ.አንድ ተቀጣሪ የሚከፈለው ቀን ውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 500 ወይም ከደሞዙ 4% ከሁለቱ ከፍተኛ ከሆነው መጠን ባልበለጠ ብቻ ነው፡፡

ለ. ለፊደል ተራ ሀ አፈፃፀም አንድ ተቀጣሪ የአልጋ አበል ያለገደብ ወይም በተወሰነ ገደብ በደረሰኝ የሚወራረድለት ከሆነ በደረሰኝ መሰረት ለአልጋ የተከፈለው ገንዘብ ከግብር ነፃ የሚደረግ ሲሆን ለቁርስ ፣ ምሳ፣ እራት የመሳሰሉ ወጪዎች የሚሰጠው የውሎ አበል ከግብር ነፃ ሊደርግ የሚችለው ከብር 300 ወይም ከደሞዙ 2.5 % ከሁለቱ ከፍተኛ ከሆነው መጠን ባልበለጠ ብቻ ነው፡፡

ሐ.ለማንኛቸውም ድጅት ስራ አስኪያጅ ወይም ምክትል ስራ አስኪያጅ የሚከፈለው የውሎ አበል ከግር ነፃ የሚደረገው ከብር 1000 ወይም ከወርሓዊ ደሞዙ 5 በመቶ ከፍተኛ ከሆነው መጠን ባልበለጠ ብቻ ነው ፡፡

መ.ለፊደል ተራ ሐ አፈፃፀም አንድ ስራ አስኪያጅ ወይም ምትል ስራ አስኪያጅ የአልጋ አበል ያለገደብ ወይም በተወሰነ ገደብ በደረሰኝ የሚወራረድለት ከሆነ በደረሰኙ መሠረት ለአልጋ የተከፈለው ገንዘብ ከግብር ነፃ የሚደረግ ሲሆን ፣ ለቁርስ ምሳ፣ እራ እና ለመሳሰሉ ወጪዎች የሚሰጠው የውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ወይም ከወርሓዊ ደሞዙ 3 በመቶ ከፍተኛ መጠን ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

2.ወደ ውጪ ሀገር ለሚደረጉ ጉዞዎች የሚከፈል የውሎ አበል ፣
ሀ.አንድ ተቀጣሪ የተቀጠረበትን ስራ ለማከናወን ወደ ውጪ ሀገር ለሚያደርገው ጉዞ የሚከፈለው የውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው መንግስት ከተሿሚዎች ወጪ ለሌሎች ተቀጣሪዎች ከወሰነው የውሎ አበል ልክ ባልበለጠ ብቻ ነው፡፡
ለ.የማናቸውም ድርጅት ስራ አስኪያጅ ወይም ምክትል ስራ አስኪያጅ ከድርጅቱ ስራ ጋ በተገናኘ ወደ ውጪ ሀገር ለሚያደርገው ጉዞ የሚከፈለው የውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚያደርገው መንግስት ከተሿሚዎች ውጪ ለሌሎች ተቀጣሪዎች በወሰነው የውሎ አበል ልክ ላይ 20 በመቶ ተጨምሮበት ይሆናል፡፡

3.ለተራ ቁጥር 2 ድንጋጌ ቢኖርም በሀገር ውስጥ ለሚደረግ የስራ እንቅስቃሴ የኮንስትክሽን ማሽነሪ ኦፕሬተሮች የሚከፈል የውሎ አበል ከ25 ኪ.ሜ ባነሰ ወይም በበለጠ ርቀት ቢሆንም የተከፈለው የውሎ አበል ከግብር ነፃ ይሆናል፡፡

4.በተራ ቁጥር 2 እና 3 የተገለፀው ቢኖርም የመንግስት መስሪያ ቤት ለተሿሚዎች እና ለተቀጣሪዎቻቸው ከመደበኛ የስራ ቦታቸው ውጪ ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀው በመሄድ ለሚያከናውኑት ስራ የሚከፍሉት የቀን ውሎ አበል ሙሉ በሙሉ ከግብር ነፃ ተድርጓል፡፡

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪና ጠበቃ
0911 1902 99

‼️ መመሪያውን በነፃ ያውርዱ ⤵️
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
👉 t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
#አመለካከት 🇪🇹 #ሀበሻ

24/05/2021

ደስተኛ ለመሆን ፈጣሪን ፈርተን እንኑር!!!!

10/05/2021

🚨 የሥራ ውል ⤵️

#አመለካከት 🇪🇹 #ሀበሻ

Address

Bahir Dar
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Very important documentations for life posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Very important documentations for life:

Share

Category