የህይወትና የፍቅር ጥቅሶች-For Life and Love quotation

የህይወትና የፍቅር ጥቅሶች-For Life and Love quotation Every Time I look at the keyboard, I see that U and I are always together.

03/08/2026

ብታውቂ

ስትስቂ!
ጠፈርን እንደምታደምቂ፣
መንፈስን ካዚም እስራት እንደምታላቅቂ፣
ብታውቂ!

ስትስሚ!
አጥንት እንደምታለመልሚ፣
ታማሚ ልብ እንደምታክሚ፣
ብታውቂ!

ስታወሪ!
ዱዳ እንደምታናግሪ፣
መነኩሴውን ከሱባዔ፣
ፈላስፋውን ከጉባዔ፣
እንደምትጠሪ፣
ብታውቂ!

እንኳንስ በኔ ልትስቂ፣
ከራስሽ ጋር ፍቅር ይዞሽ፣
አይሽ ነበር ስትማቅቂ!!!

ከበእውቀቱ

ውዴ...ተራርቆ ፍቅር አይመች አይደላኝከናፍር አንገትህ ደረትህ ናፈቀኝወይ አንተ ዝቅ በል ወይ እኔን ከፍ አ'ርገኝ!😏
01/08/2026

ውዴ...
ተራርቆ ፍቅር አይመች አይደላኝ
ከናፍር አንገትህ ደረትህ ናፈቀኝ
ወይ አንተ ዝቅ በል ወይ እኔን ከፍ አ'ርገኝ!😏

01/08/2026

እንዴት ነሽ ስላት
ሳቅ ታበዛለች
ትጫወታለች ፤

< አለሁ ! >
ትላለች - እንደሞላላት
ቁስሏን የማላውቅ እዬመሰላት ፤

የዐይኗ መደፍረስ
የገጿ ሽክረት
የአንጀቷ ማረር
የልቧ ቁስለት

ጥልቅ ስቃይዋን እዬነገረኝ ፤
እርሷ ግን ሁሌም አንድ የምትለኝ ፤

- - - - - - - - - አለሁ ደህና ነኝ !

ልዩ ፍጥረት ናት
አይደረሱባትም ፤

ስሟ ሕይወት ነው
ካልተሸከሟት አይረዷትም ፤

በሕመሟ መሳቅ
በቁስሏ ማጌጥ
ታውቅበታለች ፤

ልክ እንደ መሬት
ውኃ'ን ከእሳት ጋር ታቻችላለች ፤

ከራስ ቅራኔ
ከራስ ጋር ሙግት ቢኖርባትም ፤
ከመሳቅ በቀር
በሰው ፊት ማልቀስ አይኾንላትም ፤

ደህና ነኝ ከሚል
ከአንድ ቃል በቀር ——
ሌላ አይወጣትም ፤

እወድዳታለሁ ፤

ደህና ነኝ ስትል
ደህና እንዳልሆነች አውቅባታለሁ።
አይ ሕይወት
©By Tewodros kassa

31/07/2026

ዋ !!!
አይኔ ወደደሽ ስልሽ፣
አይኑን አጥፋው ብለሽ ገባሽ አሉ ስለት
ምኞትሽ ሰመረ
አይኖቼ ጠፉልሽ ይኸው አንደዘበት።
ግን መች ተውሻለው
በልቤ ብሩህ አይን ዛሬም አይሻለው።
ደሞ አንደዚ ስልሽ አትወጅኝምና
ልቡንም አጥፋልኝ ብለሽ ትሳይና
ፀሎት ያልቅብሻል እሞትብሽና።

Address

Bahir Dar
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የህይወትና የፍቅር ጥቅሶች-For Life and Love quotation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የህይወትና የፍቅር ጥቅሶች-For Life and Love quotation:

Shortcuts

Share

Category