Yitayih Biresaw Leyew. የአማራ ልዩ ሀይል፤ሚሊሻና ፋኖ አድናቂዎች ፔጅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • Yitayih Biresaw Leyew. የአማራ ልዩ ሀይል፤ሚሊሻና ፋኖ አድናቂዎች ፔጅ

Yitayih Biresaw Leyew. የአማራ ልዩ ሀይል፤ሚሊሻና ፋኖ አድናቂዎች ፔጅ to promote local product and fating e legal activity

20/05/2026

ዛሬም ዳስ ጥሎ ማልቀሱ በአማራ እናቶች ተጠናክሮ ቀጥሏል😭😭😭
አሊ ደሮ ላይ አንዱ የህዝብ ባስ በጥይት ተመትቶ ሲያመልጥ ሁለተኛው ባስ በታጣቂዎች ተይዞ ከ50 በላይ የአማራ ተወላጅ ተሳሪዎች ታግተው ወደጫካ ሲወሰዱ የቆሰሉና የሞቱም እንዳሉ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ባይሰሙም የውጭ ሚዲያዎች ዘግበውታል😭😭
እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለን😭😭😭

 #ወለጋ  #የደም  #ምድር😭😭😭ይህንን መከራ ከማዬት በላይ ምን አይነት ሲኦል አለ😭😭😭😭
10/03/2026

#ወለጋ #የደም #ምድር😭😭😭
ይህንን መከራ ከማዬት በላይ ምን አይነት ሲኦል አለ😭😭😭😭

ከህግ በላይ ማንም የለም! የዩኒፎርም ክብርና የዜጎች ደህንነትዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ምስል/ቪዲዮ እጅግ ልብ የሚሰብርና የሚሰቀጥጥ ነው አንድ የአይሱዙ ሹፌር "ደርቦ ነድተሃል/ገልብ...
05/03/2026

ከህግ በላይ ማንም የለም! የዩኒፎርም ክብርና የዜጎች ደህንነት

ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ምስል/ቪዲዮ እጅግ ልብ የሚሰብርና የሚሰቀጥጥ ነው አንድ የአይሱዙ ሹፌር "ደርቦ ነድተሃል/ገልብጠኸኝ ነበር " በሚል ሰበብ በመከላከያ ሰራዊት አባል በክላሽንኮቭ ተገዶ ተንበርክኮ ሲደበደብ ማየት ማንንም ሰብአዊ ፍጡር ያሳዝናል።

የትራፊክ ጥፋትም ሆነ አደጋ ቢከሰት ውሳኔ መስጠት ያለበት የትራፊክ ፖሊስና የፍትህ አካላት እንጂ በግል መሳሪያን አውጥቶ መቅጣት አይደለም ዩኒፎርም የህግ ማስከበሪያ እንጂ የጭቆና መገልገያ መሆን የለበትም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የህዝብ አለኝታና የሀገር ጋሻ ነው።

እንዲህ ያሉ ጥቂት ግለሰቦች የሚፈጽሙት የዲሲፕሊን ጉድለትና የግል በቀል ደምና አጥንቱን እየገበረ ያለውን መላውን የሰራዊቱን ስም ያጎድፋል።

ማንኛውም ዜጋ ጥፋተኛ እንኳን ቢሆን ሰብአዊ ክብሩ ተጠብቆ በህግ ፊት የመቅረብ መብት አለው።

አንድን ሹፌር አንበርክኮ መደብደብ የለየለት ወንጀልና ስርዓት አልበኝነት ነው።
የሚመለከተው የመከላከያ ከፍተኛ አመራርና የፍትህ አካላት ይህንን ድርጊት የፈጸመውን ግለሰብ ህግ ፊት ማቅረብ አለባቸው

ሰራዊቱ የህዝብ ወገንተኝነቱን በተግባር እንዲያሳይ እንዲህ ያሉ በስሜት የሚነዱ አባላትንም ከቅዱስ ሙያው እንዲያርቅ ይመከራል

ፍትህ ለተበዳዩ ሹፌር!
ክብር ለህግ የበላይነት!

01/03/2026
በፑንትላንድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት 42  የISIS ታጋዮች መካከል 23ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋገጠየፑንትላንድ የጸጥታ ኃይሎች በሰሜናዊ ሶማሊያ ባካሄዱት መጠነ ሰፊ የካልሚስካድ ኦፕሬሽ...
19/01/2026

በፑንትላንድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት 42 የISIS ታጋዮች መካከል 23ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋገጠ

የፑንትላንድ የጸጥታ ኃይሎች በሰሜናዊ ሶማሊያ ባካሄዱት መጠነ ሰፊ የካልሚስካድ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር የዋሉ የውጭ ሀገር የISIS ታጋዮችን ዝርዝር ይፋ አድርገዋል በዚህ መረጃ መሠረት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ታጋዮች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ማለትም ሀያ ሶስቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ታውቋል

ይህም ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኑ ISIS በኢትዮጵያ ውስጥ ሰፊ የቅጥር እና የማደራጀት ስራ እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ነው

በቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያውያን ስም ዝርዝር እንደሚያሳየው፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ መሆናቸው ስጋቱን ከፍ ያደርገዋል። ከኢትዮጵያውያኑ በተጨማሪ የየመን፣ የቱርክ፣ የሞሮኮ እና የታንዛኒያ ዜጎች በቡድኑ ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ተገኝተዋል።

ይህ አሳሳቢ መረጃ እንደሚያመለክተው አክራሪ ኃይሎች በሀገሪቱ ውስጥ በስውር መረባቸውን በመዘርጋት ወጣቶችን ለሽብር ተግባር እያሰለጠኑ ወደ ጎረቤት ሀገራት እያሰማሩ ይገኛሉ

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ወቅት በሃይማኖት አክራሪዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ በመቀጠል ይህንን ውስጥ ለውስጥ እየተካሄደ ያለን አደገኛ እንቅስቃሴ ከወዲሁ ሊታገለው ይገባል

የሀገሪቱን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅም በስውር የሚንቀሳቀሱ የሽብር መረቦችን የመበጣጠስ ስራ የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው

በመሆኑም መንግስት ከጎረቤት ሀገራት የደህንነት ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር እና በሀገር ውስጥ ያለውን ጥብቅ ክትትል በማስቀጠል ይህንን ስር እየሰደደ የመጣውን የአክራሪነት ስጋት ሳይባባስ ሊያስቆመው እንደሚገባ ተመልክቷል

የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰጠውን ይፋዊ ምላሽ እናቀርባለን
#የኔታ ዩቱብ

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yitayih Biresaw Leyew. የአማራ ልዩ ሀይል፤ሚሊሻና ፋኖ አድናቂዎች ፔጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yitayih Biresaw Leyew. የአማራ ልዩ ሀይል፤ሚሊሻና ፋኖ አድናቂዎች ፔጅ:

Share