Samuel Eshine ሳሙኤል እሽኔ

Samuel Eshine ሳሙኤል እሽኔ Jesus Christ is salvation!




👉This is my official page on facebook! student of law,
(1)

25/10/2025

"...If it's out of your control;let it go!"

25/10/2025

"Waayi wolqa lexxannohu, itannohehu woy adhe harannohehu
noosi dhuki bikka afittokkinni dhukikki
bikkinni kofate wo'naalatto wooyteeti,hayyosi afittokkinni hayyokki bikkinni kofate wo'naalatto wooyteeti,hedosi afittokkinni hedokki bikkinni harannota hoolate wo'naalatto wooyteeti."If it's out of your control,let it go!
own view!

"Uurrootto baayichi xeicha ikkino daafiralla,huurokki macciishshama gibbinonsana loworicho cooyrootto,bare uuyinoonninsa...
21/10/2025

"Uurrootto baayichi xeicha ikkino daafiralla,huurokki macciishshama gibbinonsana loworicho cooyrootto,bare uuyinoonninsa daafira jaware cooyidhino;bare ho'linoonnihe daafira jawuri afiikki giddo hawaqamino,konnira xeichunni ilaala fulate siqqokki dhukano laayiri;
Mito wooyte duurrootto baaycho callaho qarruna kaphunniti huuronsa halaalunnite atetenni sa'e macciishshiishano hooltinohe,kayiinni halaalu bubbe dagge insata huuronsa ufuuffe hoolte atete halaalu huurora baaycho uytanno,huurokkino macciishshantanno,baaychikkino soorramanno ,kassasannohehuno ho'lanno,halaale loosi,amadoottore jawaantetenni gumuli aleegge fulateno gelege'li." Eshine Kachara

"ጊዜ የፈታው፣የታርካዊ እስረኛ ሊሆን አይገባም!"        @ የራሴ አንደበት
21/10/2025

"ጊዜ የፈታው፣የታርካዊ እስረኛ ሊሆን አይገባም!"
@ የራሴ አንደበት

“ሰው ሁኑ፤ ሰውነት ይቀድማል” ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ(የክብር ዶ/ር)ተቀዳሚ ሙፍቲ የሕዝበ ሙስሊሙ ብቻ ሳይሆኑ በምክራቸውና በተግሳፃቸው በመላው ኢትዮጵያዊያን መወደድንና ክብርን የ...
19/10/2025

“ሰው ሁኑ፤ ሰውነት ይቀድማል” ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ(የክብር ዶ/ር)

ተቀዳሚ ሙፍቲ የሕዝበ ሙስሊሙ ብቻ ሳይሆኑ በምክራቸውና በተግሳፃቸው በመላው ኢትዮጵያዊያን መወደድንና ክብርን የተጎናፀፉ ታላቅ አባትና መሪ፣ የሀገር ሽማግሌና ዋርካ በመሆን ኢትዮጵያዊያንን በእምነት፣ በጎሳና በብሔር የማይነጣጥሉ አባት ሲሆኑ በአንድ ወቅት ለመላው ኢትዮጵያዊያን “ሰው ሁኑ፤ ሰውነት ይቀድማል” በሚለው ምክራቸውና ተግሳፃቸው ይታወሳሉ፡፡

ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው ኢትዮጵያዊያን መጽናናትን እመኛለሁ 😭😭

19/10/2025

የእስረኛ ማምለጥና ማስመለጥ የወንጀል ተጠያቂነት
*******************************************
በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት ከአንቀጽ 18 እስከ 23 ድረስ የተደነገጉት አንቀጾች ከወንጀል የፍትሕ ሥርዓት ጋር የተገናኙ ሲሆኑ አራቱ ቀዳሚ አንቀጾች በሕግ ስለተያዙ ሰዎች መብት፣ የተከሰሱ ሰዎች እና በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች መብትን በተመለከተ የተደነገጉ ናቸው፡፡ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 13 መሠረት በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ ሕግ አውጭ፣ ሕግ አስፈጻሚ እና የዳኝነት አካሉ በህገ-መንግስቱ የተካተቱትን በሕግ የተያዙ ሰዎች፣ የተከሰሱ እና በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች መብትን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነትና ግዴታ ያለባቸው መሆኑ ተደንግጓል፡፡ በሕግ አግባብ የተያዙ ወይም የታሰሩ ሰዎችም ቢሆን የማረሚያ ወይም የማረፊያ ቤት ህጎችና ደንቦች፣ እንዲሁም የወንጀል ህጉን የማክበር ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ በዚህ አጭር ጽሑፍ በሕግ አግባብ የተያዙ ወይም የታሰሩ ሰዎች ከእስር ማምለጥ እና እስረኛ እንዲያመልጥ መርዳት የሚያስከትለውን የወንጀል ተጠያቂነትን ለማየት እንሞክራለን፡፡

የእሥረኛ ማምለጥ
በቂና አሳማኝ ማስረጃ ከተገኘ፣ ማንኛውንም ሰው መጠርጠርና ተጠርጣሪውን በሕግ መሠረት በቁጥጥር ሥር አውሎ፣ ምርመራ አድርጎ ክስ በማቅረብ ጥፋተኝነታቸው በማስረጃ የተረጋገጠባቸውን ሰዎች በሕጉ መሠረት እንዲቀጡ ማድረግ መሠረታዊ የሕግ ዓላማና መርህ ነው፤ እንዲሁም አንደኛው የሕግ አስፈፃሚዎች ሥልጣንና ተግባር ሲሆን፣ የኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 1 ላይ እንደተመላከተው ሰዎች በወንጀል ተጠርጥሮም ሆነ የእስራት ቅጣት ተወስኖባቸው የሚታሰሩት የሕዝብን ወይም የሰዎችን ጥቅምና ሰላም በማስከበር የወንጀል ሕጉን ዓላማ ለማሳካት እንጂ ሌላ ግለሰባዊ ወይም ተቋማዊ ዓላማና ግብ የለውም፡፡ በመሆኑም በሕግ አግባብ የተያዙ ወይም የታሰሩ ሰዎች ከሕግ አግባብ ውጪ በሆነ መንገድ ከእስር ማምለጥ ወንጀል እንደሆነ ተደንግጓል፡፡

በሕግ አግባብ የተያዙ ወይም የታሰሩ ሰዎች ማለት ምን ማለት እንደሆነ በወንጀል ህጉ የተሰጠ ትርጉም ባይኖርም በሕግ አግባብ የተያዙ ወይም የታሰሩ ሰዎች ማለት በፍርድ ቤት በወንጀል ጥፋተኛ መሆናቸው ከተፈረደ በኋላ የታሰሩ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን በወንጀል ተጠርጥሮ የተያዙና በምርመራ ላይ የሚገኙትን ጭምር የሚያካትት እንደሆነ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 461 ላይ ከተደነገገው እንገነዘባለን፡፡ በመሆኑም የእስረኛ ማምለጥ ወንጀል ጥፋተኛው የተፈረደበትም ይሁን ገና ያልተፈረደበት፣ በመደበኛ አስራትም ይሁን በማረፊያ ቤት አስራት እንዲቆይ የተደረጉ ሰዎችን እንደሚያካትት ከድንጋጌው መረዳት ይቻላል፡፡

ስለሆነም ማንም ሰው በሕግ አግባብ ተይዞ ወይም ታስሮ ካለበት ቦታ በሰዎች ወይም በንብረት ላይ ምንም የኃይል ተግባር ሳይፈጽም ያመለጠ እንደሆነ፤ ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እሥራት እንደሚቀጣ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 461(1) ላይ የተደነገገው ያመለክታል፡፡ ወንጀሉ የተፈፀመው በሰዎች ላይ ዛቻ ወይም የኃይል ተግባር በመፈፀም ወይም በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ እንደሆነ፤ ከሦስት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እሥራት እንደሚያስቀጣም አንቀጽ 461(2) ይደነግጋል፡፡ ጥፋተኛው በመጀመሪያው ወንጀል የተፈረደበት ወይም የሚፈረድበት ሲሆን ስለወንጀሎች መደራረብ ወይም ስለተደጋጋሚነት የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደ አግባብነቱ ተፈፃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉም ተደንግጓል፡፡

የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶታየ ህዝባዊነት ዳር እስከዳር በርቶለሰላም ለፍትህ ለህዝቦች ነፃነትበእኩልነት በፍቅር ቆመናል ባንድነትመሰረተ ፅኑ ሰብዕናን ያልሻርንህዝቦች ነን ለስራ በስራ...
13/10/2025

የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ
ታየ ህዝባዊነት ዳር እስከዳር በርቶ
ለሰላም ለፍትህ ለህዝቦች ነፃነት
በእኩልነት በፍቅር ቆመናል ባንድነት
መሰረተ ፅኑ ሰብዕናን ያልሻርን
ህዝቦች ነን ለስራ በስራ የኖርን
ድንቅ የባህል መድረክ ያኩሪ ቅርስ ባለቤት
የተፈጥሮ ፀጋ የጀግና ህዝብ እናት
እንጠብቅሻለን አለብን አደራ
ኢትዮጵያችን ኑሪ እኛም ባንቺ እንኩራ።

ሰንደቅ-ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!!

Deep down! Keep moving forward only in silence! Give no response! 😔
11/10/2025

Deep down! Keep moving forward only in silence! Give no response! 😔

የቆየ ፍትሕን እንደተነፈገ ይቆጠራል!የህዝብ ሰቆቃ ይብቃ!ፍትሕ ለአርቤጎና ህዝብ!
10/10/2025

የቆየ ፍትሕን እንደተነፈገ ይቆጠራል!
የህዝብ ሰቆቃ ይብቃ!
ፍትሕ ለአርቤጎና ህዝብ!

Baga nagaan ayyaana irreechaa walumaan geenye!
03/10/2025

Baga nagaan ayyaana irreechaa walumaan geenye!

Address

Wolde Amanuel Road
Awassa
ET

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Samuel Eshine ሳሙኤል እሽኔ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Samuel Eshine ሳሙኤል እሽኔ:

Share

Category