Great Gospel Domination Minstery

Great Gospel Domination Minstery We are preach his dies and reseruction .

በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ፣ ከክብሩ ባለጠግነት በመንፈሱ በኩል ኀይል እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤ኤፌሶን 3፥16Focus on JesusGospel is Christ Great Gospel Domi...
16/04/2026

በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ፣ ከክብሩ ባለጠግነት በመንፈሱ በኩል ኀይል እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤
ኤፌሶን 3፥16

Focus on Jesus

Gospel is Christ

Great Gospel Domination Minstery

ወንጌል ከአንደበት ባለፈ በኑሮ የሚገለጥ በመሆኑ ነቅተን እንኑር።
27/11/2025

ወንጌል ከአንደበት ባለፈ በኑሮ የሚገለጥ በመሆኑ ነቅተን እንኑር።

ፕሮቴስታንት (Protestantism) ከ16ኛው ክፍለ ዘመን የአውሮፓ ተሐድሶ (Reformation) እንቅስቃሴ የመነጨ የክርስትና ዋነኛ ቅርንጫፍ ነው።​"ፕሮቴስታንት" የሚለው ቃል የመጣው "...
15/10/2025

ፕሮቴስታንት (Protestantism) ከ16ኛው ክፍለ ዘመን የአውሮፓ ተሐድሶ (Reformation) እንቅስቃሴ የመነጨ የክርስትና ዋነኛ ቅርንጫፍ ነው።
​"ፕሮቴስታንት" የሚለው ቃል የመጣው "ተቃውሞ" ወይም "መቃወም" ከሚለው ቃል ነው። ይህ ስያሜ በዋነኝነት የተሰጠው በእንቅስቃሴው መጀመሪያ ላይ የነበሩ መሪዎች በወቅቱ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታዩትን ሥርዓቶች፣ ትምህርቶች እና ተግባራት በመቃወማቸው ነው።
​መሠረታዊ አስተምህሮዎቹ (አምስቱ ሶላዎች):
​ፕሮቴስታንትነት በአብዛኛው በአምስት ዋና ዋና መርሆዎች (ሶላዎች - Solas) ላይ የተመሠረተ ነው፦

1,​መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ (Sola Scriptura):
የመጨረሻውና ብቸኛው ሥልጣን ያለው የሃይማኖት ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እንደሆነ ያምናሉ። ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት ወይም ከጳጳሳት ውሳኔዎች ይበልጣል ።

2,​እምነት ብቻ (Sola Fide):
ሰው የሚጸድቀው ወይም የሚድነው መልካም ሥራዎችን በመስራት ሳይሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለው እምነት ብቻ እንደሆነ ያስተምራሉ።

3,​ጸጋ ብቻ (Sola Gratia):
መዳን በሰው ጥረት ወይም ብቃት ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር የሚገኝ ያልተገባ ጸጋ ብቻ እንደሆነ ያምናሉ።

4,​ክርስቶስ ብቻ (Solus Christus): በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው ብቸኛው መካከለኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ስለዚህ ወደ ሌሎች ቅዱሳን መጸለይ ወይም መማለጃ መጠየ፡ አያስፈልግም ይላሉ።

5,​ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ (Soli Deo Gloria):
ክብርና ምስጋና ሁሉ የተገባው ለፈጣሪ እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ያምናሉ።

​ማርቲን ሉተር
​የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ ዋና መሪ ጀርመናዊው ካህንና የነገረ-መለኮት ምሁር የነበሩት ማርቲን ሉተር ናቸው። ሉተር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን 'የንስሀ ደብዳቤ' ሽያጭን በመቃወም በ1517 ዓ.ም. 95 የተቃውሞ ጽሑፎችን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ላይ ለጥፏል።
​ከዚያ ሪፎርሜሽን በኋላ ​ፕሮቴስታንትነት ወደ ብዙ የተለያዩ ቅርንጫፎች ተከፋፍሏል፤ ከእነዚህም ዋና ዋናዎቹ:
​ሉተራን (Lutheran)
​ሪፎርምድ (Reformed) / ፕሬስባይቴሪያን (Presbyterian)
​አንግሊካን (Anglican) / ኤጲስ ቆጶሳዊ (Episcopal)
​ባፕቲስት (Baptist)
​ሜቶዲስት (Methodist)
​አድቬንቲስት (Adventist)
​ጴንጤቆስጤ (Pentecostal) - በአብዛኛው "ጴንጤ" የሚለው አጠራር በኢትዮጵያ ለፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መጠሪያ ሆኖ ያገለግላል።
​በኢትዮጵያ ደግሞ እንደ መካነ ኢየሱስ፣ ቃለ ሕይወት፣ ሙሉ ወንጌል፣ መሰረተ ክርስቶስ የመሳሰሉት አብያተ ክርስቲያናት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ናቸው።

"በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤"ሮሜ 12:10።
07/10/2025

"በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤"

ሮሜ 12:10።

 !በትላንትናው ዕለት በሲዳማ ክልል በቦና ወረዳ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገናል፤ በዘንድሮ መርሐግብር Kingdom Youth Mission Ministry ለቦና ወረዳ ለ15 ተማሪ...
06/10/2025

!
በትላንትናው ዕለት በሲዳማ ክልል በቦና ወረዳ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገናል፤ በዘንድሮ መርሐግብር Kingdom Youth Mission Ministry ለቦና ወረዳ ለ15 ተማሪዎች ድጋፍ ለማድረግ ያቀደው ቢሆንም በሐዋሳ ከተማ ለ3 ተማሪዎችና በቦና ወረዳ በኦሎንሶ ከተማ ለ20 ተማሪዎች፣ በአጠቃላይ በሲዳማ ክልል በዘንድሮው መርሐግብር ለ23 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጎላቸዋል። በዚህ ሁሉ ከጎናችን ሳይለይ የረዳን እግዚአብሔር ይመስገን! ደግሞም ራዕያችሁ ራዕያችን በማለት በጸሎት፣ በገንዘብ ከእኛ ጋር ለዚህ ዓላማ የተሰለፋችሁ ሁላችሁም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተባረካችሁ ሁኑ! የአመት ሰው ይበለን! ተባረኩ!

በዚህ አጋጣሚ የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁንና ፍቅራችሁን ግለጹልን!

https://youtube.com/?si=Fplk-wR-yKL3cSzt

ተግባራዊ ደቀ መዝሙርነትን፣ የቅዱሳን ኀብረትንና ፍቅርን ችላ በማለት ለስሜታዊ ጩኸት ብቻ ያጋደለ ትኩረት መስጠት የሞራል ልዕልናችንን ስለሚነፍግ ተሰሚነትን ያሳጣል። ኹል ጊዜና በኹሉ ቦታ ለ...
28/09/2025

ተግባራዊ ደቀ መዝሙርነትን፣ የቅዱሳን ኀብረትንና ፍቅርን ችላ በማለት ለስሜታዊ ጩኸት ብቻ ያጋደለ ትኩረት መስጠት የሞራል ልዕልናችንን ስለሚነፍግ ተሰሚነትን ያሳጣል። ኹል ጊዜና በኹሉ ቦታ ለእግዚአብሔር ቃል እውነት እንወግን። በጭንቅላታችን የገባው ዕውቀት ከልባችን ዝንባሌ ጋራ በፍቅር መጣጣም ይጠበቅበታል። በዕውቀትና በፍቅር የምንተገብረው ነገር በቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይኾን በዙሪያችን ላሉት ኹሉ ይፈይዳል። በጥቅሉ ጤናማውን ክርስቲያናዊ ትምህርት መፈለግ መተኪያ እየገኝለትም። ኾኖም ጤናማ ትምህርት ጤናማ የኑሮ ጠባይ ይከተለዋል። አክብሮተ እግዚአብሔር ያልተለየው ርቱእ ሕይወት (orthopraxy) እና ርቱእ ጥልቅ ፍቅር (orthodpathy) ከርቱእ እምነት (orthodoxy) ጋራ የተቆራኘ እና ከእርሱ የሚመነጭ ነው፤ አይነጣጣሉም።

_ድፍርስ ጅረቶች፥ ገጽ. 321

"ድፍርስ ጅረቶች" የተሰኘው የመጋቢ Solomon Abebe Gebremedhin መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊው የነገረ መለኮት እውነት ወደ ተግባራዊ ክርስትና ኑሮ እንዲወርድ ምጋቢያዊ ጥሪ የሚያቀርብ ነው። ይኽ ሥራ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይኾን ለመንግሥት፣ የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ ለተሠማሩ ተቋማት እና ለኹሉም ቤተ እምነት በእጅጉ የሚጠቅም!

በዚኽ ሥራ፥ ጥልቅ የነገረ መለኮት ግንዛቤ ከሰፊ ጥናት ጋራ ተዳምሮ በውብ የሥነ ጽሐፍ አቀራረብ ሸጋ በኾነ መልኩ ተሰናስኖ ቀርቧል። ይኽ ሥራ ደረቅ የነገረ መለኮት እና የሥነ ሰብእ ዕውቀት አያስጨብጠንም። ይልቁንም እምነታችን ወደ መሬት እንዲወርድ ልባችነነ፣ ነፍሳችንንና ኅሊናችንን በእጅጉ ይሞግታል።

እግረ መንገዳችንን ደግሞ የቋንቋና የትርጓሜ ቃላት ባለጠጋ ከኾነው መጋቢ ሰለሞን በርካታ ዐዳዲስ ቃላት፣ ትርጓሜያቸውንና ውብ የሥነ ጽሑፍ ዘይቤ እንሸምታለን!!

የመጽሐፉ ምረቃ ዛሬ ነው። ግርርርርርርር ብለን መጥተን እናስመርቀው!!

እንደጻፈው!

"መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” ሐዋ. ሥራ 4፤12፤
08/09/2025

"መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”

ሐዋ. ሥራ 4፤12፤

08/08/2025

ከኢየሱስ ጋር መኖር ይሻላል።

29/07/2025
29/07/2025

Kingdom Youth Mission Ministry

Kingdom Youth Mission Ministry 🙏
22/06/2025

Kingdom Youth Mission Ministry 🙏

22/02/2025

ሂዱ...

Address

Awassa

Telephone

+251926464183

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Great Gospel Domination Minstery posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Great Gospel Domination Minstery:

Share

Category