Taaboori sinu Quchumi Mootimmate Xaadooshshe/ታቦር ክ/ከተማ መንግስት ኮሙንኬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • Taaboori sinu Quchumi Mootimmate Xaadooshshe/ታቦር ክ/ከተማ መንግስት ኮሙንኬሽን

Taaboori sinu Quchumi Mootimmate Xaadooshshe/ታቦር ክ/ከተማ መንግስት ኮሙንኬሽን This is official Page Of Tabor Subcity Government communication.

29/08/2024
18/07/2024

2016 እንደ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያከናወናቸው ተግባራት

🏳️ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ከማጠናከር አንፃር
🏳️ የሚዲያ ግንኙነትን ማጠናከር፣
🏳️ የአስተዳደሩን የልማት ግቦች ወደ ህዝብ ማድረስ፣
🏳️ የህዝብን ጥያቄ ወደ አስተዳደሩ ማድረስ፣
🏳️ የፕሬስ ኮንፍረንሶችን ማዘጋጀት፣
🏳️ የተለያዩ የሚዲያ ዘገባዎችን ማሰናዳት፣
🏳️ አሉታዊ ወሬዎችን ማስተካከል፣
🏳️ የህዝብ የልማት ተሳትፎዎችን ማስተዋወቅ፣
🏳️ የከተማዋን ገፅታ መገንባት፣
🏳️ ወቅታዊ መረጃዎችን ማቅረብ፣
🏳️ የባለሙያዎችን አቅም መገንባት፣
🏳️ የፕሮጄክቶችን ወቅታዊ ሁኔታ መግለፅ፣
🏳️ በህትመት መረጃ ማሰራጨት፣
🏳️ የህዝብ ቅሬታዎችን ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ፣
🏳️ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት ማስተዋወቅ፣
🏳️ የኢንቨስትመንት አማራጭ ማስተዋወቅ፣
🏳️ የከተማዋን የማህበራዊ ተቋማት ማስተዋወቅ፣
🏳️ የከተማዋን ውበትና ፅዳት በሚዲያ ማገዝ፣
🏳️ የህዝብ አስተያየቶችን ለሚመለከተው አካል ማድረስ፣
🏳️ የአዳራሽ የፎቶ አውደ ርዕይ ማዘጋጀት፣
🏳️ የመስኮት ኤግዚቢሽን ማዘጋጀት፣
🏳️ የሚዲያ ፎረም ማዘጋጀት፣
🏳️ የሚዲያ ጥቆማ መስጠት፣
🏳️ ምላሽ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ምላሽ መስጠት፣
🏳️ የሚዲያ ድርሻን መወጣት እና በመሳሰሉት ረገድ፣
🏳️ የልማት ጉብኝቶችን መዘገብ፣
🏳️ መልዕክቶችን መቅረፅ፣
🏳️ የትርጉም ስራዎችን ማከናወን፣
🏳️ የሚዲያ ልማት ስራዎችን ማከናወን፣
🏳️ የቴሌቭዥን እና የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፣
🏳️ የህዝብ ፎረሞችን ማዘጋጀት፣
🏳️ የሚዲያ አማራጮችን በማስፋት መጠቀም፣
🏳️ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮችን ማሳደግ፣
🏳️ ክልላዊና ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የዘገባ ስራ፣ መስራት፣
🏳️ የስፖርት ቱሪዝሙን አቅም በሚዲያ ማገዝ፣
🏳️ የክልሉን መስህቦች የማስተዋወቅ ስራ መስራት፣
🏳️ ሁነቶችን መፍጠር እና የመሳሰሉትን በማከናወን የሚጠበቅበትን ሚና መወጣት ችሏል።

ይህን ጥረታችንን በ2017 በላቀ መልኩ በአስተዳደሩና በነዋሪው መካከል ያለንን ግንኙነት በማጠናከር የኮሙኒኬሽን ሚናችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል።

"በጎ ፈቃደኛነት ለማህበረሰብ ለውጥ"የሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ የበጋ ወራት በጎ ፈቃድ መዝግያና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ መርሐ ግብር አካሄደ።የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ...
17/07/2024

"በጎ ፈቃደኛነት ለማህበረሰብ ለውጥ"

የሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ የበጋ ወራት በጎ ፈቃድ መዝግያና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ መርሐ ግብር አካሄደ።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌቱ ማሞ ሰው ተኮር የበጎ ፍቃድ ተግባራት እንደ ከተማ የአቅመ ደካሞችን በማገዝ እና ቤታቸውን በማሳደስ እንደ ከተማ ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል ብለዋል።

ይህ ተግባር እንደ ከተማ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል አቶ ጌቱ።

የሀዋሳ ከተማ ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ወ/ፃዲቅ በበኩላቸው የበጎ ተግባር ስራዎች እንደ ከተማ የአቅመ ደካማ አረጋዊያንን ቤት በመጠገን እና በመደገፍ እንዲሁም የደም ልገሳ እና መሠል እንቅስቃሴዎች ላይ ትኩረቱን በማድረግ እየተከናወኑ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

ኃላፊዋ አክለውም ወጣቱ በክረምት ወቅት በመልካም ተግባራት ላይ ተሳትፎ በማድረግ የበኩሉን አስተዋፆኦ ማበርከት እንዳለበት ተናግረዋል።

የታቦር ክ/ከተማው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበራ ሌላሞ በበኩላቸው የክ/ከተማ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ ስራ በተለያዩ ተግባራት ግንባር ቀደም በመሆን እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ ሀይል በቀጣይም በመሰል ተግባራት ላይ ትኩረቱን እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌቱ ማሞ፤ የሀዋሳ ከተማ ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ወ/ፃዲቅ፤ የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊነት አቶ ታረቀኝ ለገሰ ፤የሀዋሳ ከተማ ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ሀደራ ሀርቃ፤ የታቦር ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ናሆም ዳዊትን ጨምሮ የክ/ከተማው ጠቅላላ አመራሮችና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተገኝተዋል።

ምንጭ የታቦር ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም
ሀዋሳ

"የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ " በሚል መሪ ቃል የ6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ  መርሃ ግብር በታቦር ክፍለ ከተማ ተካሄደ።በመርሃ ግብሩ የታቦር ክ/ክፍለ ከተማ ዋና አስተዳ...
17/07/2024

"የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ " በሚል መሪ ቃል የ6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በታቦር ክፍለ ከተማ ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ የታቦር ክ/ክፍለ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበራ ሌላሞ እንደተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የመተባበርና የአንድነት ውጤት ማሳያ መሆኑን ገልጸው የሚተከሉ ችግኞች የአየር ንብረት ለውጡን ከመከላከል ባሻገር ለከተማው ውበት የሚሰጡና ለምግብነት የሚውሉ በመሆናቸው መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ የሁላችንም ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

አቶ አበራ አክለውም የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በማስቀጠል ሁላችንም በተባበረ ክንድ ለአካባቢያችን ውበት፣ ጥላና ምግብ የሚሆኑ ችግኞችን መትከል ይገባናል በማለት በቀጣይም የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ላይ የከተማ ፣ የክፍለ ከተማና የቀበሌ አመራሮች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ነዋሪዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

የታቦር ክ/ከተማ መ /ኮሙኒኬሽን
ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም
ሀዋሳ

"የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በሀዋሳ ታቦር ተራራ ላያ ተካሄደ።በመርሀግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የከተማዋ ከንቲባ አቶ መኩሪያ...
12/07/2024

"የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በሀዋሳ ታቦር ተራራ ላያ ተካሄደ።

በመርሀግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የከተማዋ ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ መሪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ውጤታማነቱ የሀገርን ገፅታ እስከመገንባት የደረሰ ነው ብለዋል።

ሀገርን አረንጓዴ ከማልበስ በተጓዳኝ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በህዝቦች ዘንድም ፍቅርን እና አንድነትንም በመትከል ወንድማማችነትን ያሰረፁ መሪ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎም በከተማዋ ሀዋሳ ብቻ በ2016 ነአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በ3.2 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በተደረገው ጥረት እስካሁን 1.9 ሚሊዮን ችግኝ ተተክሏል ብለዋል።

በበጋ የተፋሰስ ልማት ስራን በማጠናከር በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መፍጠር ከቻልን ሀዋሳን ይበልጥ ውብ የቱሪስት መዳረሻ እንድናደርጋት በማለትም ነው ከንቲባው የገለፁት።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽቤት ሀላፊ አቶ ብሩክ ሰለሞን በበኩላቸው እንደ ከተማ ሁሉም ነዋሪ በተለያዩ አካባቢዎች ከሚያደርገው የችግኝ ተከላ ባሻገር በየቤቱ ለምግብነት የሚጠቅሙ እፅዋትን በመትከል የበኩሉን አሻራ ማኖር አለበት ብለዋል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ ሀላፊ አቶ አበባየሁ ላሊማ በበኩላቸው ዛሬ ብቻ በከተማዋ 200 ሺህ ችግኞች ተተክለዋል ብለዋል።

እስከ አሁን እንደ ከተማ በተደረገ የአረንጓዴ መርሀግብር ብቻ ከከተከሉ ችግኞች የፅድቀት መጠን 86 በመቶ በላይ መድረሱን ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የሀዋሳ ከ /አስ/መ/ኮሙኒኬሽን/ መምሪያ
ቀን 5/11/16 ዓ/ም

የታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር የ2016 ዕቅድ አፈፃፀምና የ2017 በጀት አመት ዕቅድ ዙሪያ የግምገማ መድረክ አካሄደ።የክ/ከተማ አስተዳደሩ 2016 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት...
10/07/2024

የታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር የ2016 ዕቅድ አፈፃፀምና የ2017 በጀት አመት ዕቅድ ዙሪያ የግምገማ መድረክ አካሄደ።

የክ/ከተማ አስተዳደሩ 2016 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ነው ውይይት እየተደረገበት የሚገኘው።

የካቢኔ አባላት በቀረበው ሪፖርትና ዕቅድ ዙሪያ ደካማና ጠንካራ ጎኖች እየተፈተሹ እና ከትግበራ አንፃር ያሉ ማነቋዎችን እየለዩ እየገመገሙ ይገኛል።

በዚህ መድረክ የከተማዋ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያም አመራሩ በመገምገም አቅጣጫ አስቀምጧል ።
የታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር መ/ኮሙንኬሽን
ሀዋሳ
ሀምሌ 3/2016 ዓ.ም

በታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ተገመገመ።  የታቦር ክ/ከተማ መ/ኮሙኒኬሽን      ሰኔ11/2016ዓ.ም የታቦር ክ/ከተማ አስተዳደሪ አቶ አበራ ሌላሞ ...
18/06/2024

በታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ተገመገመ።

የታቦር ክ/ከተማ መ/ኮሙኒኬሽን
ሰኔ11/2016ዓ.ም

የታቦር ክ/ከተማ አስተዳደሪ አቶ አበራ ሌላሞ የግምገማ ሂደቱን የመሩ ሲሆን በክ/ከተማው በሰላምና ጸጥታው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት እና የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች በተመለከተ ከክ/ከተማው ከጸጥታ አባላት እና ከቀበሌ አመራሮች ጋር በመሆን የተሰሩ ተግባራት ተገምግሟል

በቀጣይም የጸጥታ አካሉ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰላምን ህዝባዊ በማረግ ጠንክረው በጋራ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰራው የአንድ ማዕከል የዕድሳት ግንባታ በታቦር ክ/ከተማ ተጀመረ። የታቦር ክ/ከተማ ስራ አሰሪና ሰራተኛ የቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሞዴል የሆነ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስ...
14/06/2024

በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰራው የአንድ ማዕከል የዕድሳት ግንባታ በታቦር ክ/ከተማ ተጀመረ።

የታቦር ክ/ከተማ ስራ አሰሪና ሰራተኛ የቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሞዴል የሆነ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋም ለመገንባት ከተለያዩ አካላት ገቢ በማሰባሰብ በዛሬው ዕለት የዕድሳት ግንባታው ተጀምሯል።

በዕድሳት ማስጀመሪያው የሀዋሣ ከተማ የስራ ሀላፊዎች ፣ የታቦር ክ/ከተማ አስተዳዳሪ፣ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እና የማዕከሉ ሰራተኞች በመገኘት ስራውን አስጀምረዋል።

የታቦር ክ/ከተማ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አበራ ሌላሞ እንዳሉት የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ቀልጣፋና ምቹ ለማድረግ ለሚደረገው ግንባታ በገንዘብና በተለያየ ድጋፍ ላደረጉ አካላት አመስግነዋል።

የዕድሳት ስራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀመርም ተወዳዳሪ ማዕከል በመሆን ለሌሎች ተሞክሮ መሆን እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

የሀዋሣ ከተማ አስተዳደር ስራ አሰሪና ሰራተኛ ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ታሪኩ ጥላሁን በበኩላቸው ማዕከሉ መገንባቱ ተቋሙ የተሞክሮ ማዕከል እንዲሆን በር ከፋች ነው ሲሉ ገልፀው ለአገልግሎት ሰጪዎችም ምቹና የተሻለ የስራ ቦታ ከመፍጠር አኳያ ጠቃሚም ነው ብለዋል።

ሀላፊው አክለው የስራ ዕድሉ ላይ ተጨባጭ የሆነ ለውጥ ለማምጣት ከባለሙያዎች ጠንካራ የስራ መንፈስ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

የታቦር ክ/ከተማ ስራ አሰራና ሰራተኛ ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ታምራት ታሪኩ እንዳሉት ማዕከሉን በዘመናዊ መንገድ እንዲገነባ የተደረገው ድጋፍ አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ አገልግሎቱን ለማዘመንና ለተሻለ ለውጥ ለመስራትና ተወዳዳሪ ለመሆን እንሰራለን ብለዋል።

በመጨረሻም በአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራጅተው እየሰሩ ከሚገኙ ማህበራት መካከል የኤልሻሎም ጠቅላላ ኤሌክትሮኒክስ ማዕከል ተጎብኝቷል።

በህገወጥ ንግድ በተሰማሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ተገለፀ።የታቦር ክ/ከተማ መ/ኮሙኒኬሽን      ግንቦት 29/2016ዓ.ም የታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ...
06/06/2024

በህገወጥ ንግድ በተሰማሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ተገለፀ።

የታቦር ክ/ከተማ መ/ኮሙኒኬሽን
ግንቦት 29/2016ዓ.ም

የታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በህገወጥ የጎዳና ንግድና በህገወጥ የቤንዚን ሽያጭ በተሰማሩ አካላት ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኑን የታቦር ክ/ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኤርምያስ ለማ ገልፀዋል።

ሀላፊው አክለው በክ/ከተማው ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ላይ ቁጥጥርና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

በታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር የ 11ወር የሥራ አፈጻጸም ተገመገመ።  የታቦር ክ/ከተማ መ/ኮሙኒኬሽን      ግንቦት 24/2016ዓ.ም የታቦር ክ/ከተማ አስተዳደሪ አቶ አበራ ሌላሞ የግምገማ ሂ...
01/06/2024

በታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር የ 11ወር የሥራ አፈጻጸም ተገመገመ።

የታቦር ክ/ከተማ መ/ኮሙኒኬሽን
ግንቦት 24/2016ዓ.ም

የታቦር ክ/ከተማ አስተዳደሪ አቶ አበራ ሌላሞ የግምገማ ሂደቱን የመሩ ሲሆን በ2016ዓ.ም ባለፉት 11 ወራት በክ/ከተማው የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ከክ/ከተማው ካቢኔ አባላት ጋር በመሆን የተሰሩ ተግባራት ተግምግሟል።

በግምገማው ሂደቴ ጥሩ ውጤት የተመዘገበባቸው ስራዎች መኖሩን አንስተው ያሉትን ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና ደካማ ጓኖች በማረም በቀጣይ የተሻለ ለውጥ ጠንክረው በጋራ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

Address

Tabor
Awassa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Taaboori sinu Quchumi Mootimmate Xaadooshshe/ታቦር ክ/ከተማ መንግስት ኮሙንኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category