ዜና ሀዋሳ

ዜና ሀዋሳ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዜና ሀዋሳ, Legal, Awassa.
(1)

05/08/2025
09/05/2025
29/08/2024

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሶስት ወራት የመሰረተ ልማት አፈፃፀም እየተዘዋወሩ ተመለከቱየሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የ...
13/12/2023

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሶስት ወራት የመሰረተ ልማት አፈፃፀም እየተዘዋወሩ ተመለከቱ

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሶስት ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ የተሰሩ ስራዎችን በመዘዋወር ተመልክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ምልከታውን ባደረጉበት ወቅት እንደገለፁት በሶስት ወራት ውስጥ የህዝብ ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ስራዎች በከተማ አስተዳደሩ እየተሰራ እንደሆነ መመልከታቸውን ገልፀው በቀጣይ ግዜያት በዕቅድ ተይዘው ለሚሰሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

ከተማዋ በአረንጓዴ ልማትና በፅዳት የቀደመ ስሟን ሊያስጠብቅ የሚችል ስራ በሁሉም አከባቢ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበው በመሰረተ ልማት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንደገለፁት ሀዋሳ የተሞክሮ ማዕከል መሆኗል ሊያስቀጥል የሚችል ስራዎች በሶስት ወራት ውስጥ እየተሰራ እንደሆነ መመልከታቸውን ገልፀው የከተማ አስተዳደሩ አመራር ህዝቡን በማስተባበርና አሻግሮ የማየት አቅሙን በማሳደግ እየሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

ዘገባው የሲዳማ ብ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
ታህሳስ 03-2016 ዓ.ም
ሀዋሳ

✔️የሰላም ተምሳሌት ✔️የውበት  መሰረት ✔️የቱርዝም ማዕከል✔️ የአብሮነት ማሳያ  ✔️ የዘመናዊነት መገለጫ ✔️ የእድገት  ልኬት ✔️ የብልፅግና አርማሀዋሳ ❤️❤️❤️ 24 ሰዓት በእድገት ...
03/12/2023

✔️የሰላም ተምሳሌት ✔️የውበት መሰረት ✔️የቱርዝም ማዕከል✔️ የአብሮነት ማሳያ ✔️ የዘመናዊነት መገለጫ ✔️
የእድገት ልኬት ✔️ የብልፅግና አርማ
ሀዋሳ ❤️❤️❤️ 24 ሰዓት በእድገት ጎዳና❤️❤️❤️

"ለነ ቡጁጊ አለንላችሁ እንበላቸው" ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በከተማችን ሀዋሳ በኪነ ጥበብ፥ በማህበራዊ ጉዳዮች፥በበጎ አድራጎት፥ በሰላምና ፀጥታ፥ በስፖርት በጠቀስኳቸውና ባልጠቀስኳቸው ዘርፎች ...
22/11/2023

"ለነ ቡጁጊ አለንላችሁ እንበላቸው"

ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በከተማችን ሀዋሳ በኪነ ጥበብ፥ በማህበራዊ ጉዳዮች፥በበጎ አድራጎት፥ በሰላምና ፀጥታ፥ በስፖርት በጠቀስኳቸውና ባልጠቀስኳቸው ዘርፎች የገዛ ጥቅሙን ትቶ ለከተማው ብሎም ለክልሉ ዕድገት ካለ ሹመት እንቅልፍ ያጣው ወንድማችን አለማየሁ ሽፈራው (አሌክስ ፕሮሞሽን) በድንገት ካጣነው ቀናቶች ተቆጥረዋል።

በህልፈቱ ከትንሽ እስከ ትልቅ፥ ከመሪ እስከ ተመሪ፥ ከመደበኛው ህዝብ እስከ ምሁራን፥ ከሸማች እስከ ነጋዴ፥ ሰርጋቸውን ካደመቀላቸው አንስቶ በሃዘናቸው እስከቆመላቸው ድረስ ሺህዎች በሀዘን ዳዋ ተውጠዋል።

ጊዜው ላለፈው አሊ የምናለቅስበት ሳይሆን ላሉት የአብራኩ ክፋዮች ለነ ቡጁጊ የምንደርስበት ነው፤ አሊ ከነ በጎ አሻራው ካደገበት ማህበረሰብ አልፎ ለሃገር በእልፍ መንገዶች አሻራውን አኑሯል። ካለምንም መጦሪያና ካለምንም መኖሪያ ሁለት ልጆቹን ከነባለቤቱ ለኛ ለወዳጆቹ ትቶልን አልፏል፡፡

ነገ ረቡዕ ማለትም ህዳር 12/2016 ዓ.ም ከ11:00 ጀምሮ በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል "ዝክረ-አሊ" የተሰኘ መድረክ አዘጋጅተናል።

በመርሃ ግብሩም
-የህሊና ፀሎት
-የጧፍ ማብራት ስነ-ስርዓት
-በአሊ የህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን ዶክመንተሪ
-አሊን የሚዘክሩ የስነ-ፅሁፍ ትሩፋቶች
- አሊን የሚዘክሩ የስነ-ፅሁፍ ትሩፋቶች
-የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እና የተለያዩ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል።

በዕለቱ የከተማውና የክልሉ ባለስልጣናት፥ አርቲስቱ ማህበረሰብ፥ ሙዚቀኞችና የስነፅሁፍ ቤተሰብ፥ የሟች ቤተሰቦች፥ ባለሃብቶች፥መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት፥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገለፀው ሰዓት በስፍራው ይገኛሉ፡፡

በዚህ ታሪካዊና የአለንላችሁ መሰናዶ ላይ የሚዲያ አጋሮችም የሚገኙ ሲሆን

፨ የደ/ሬ/ቴ/ድርጅት
፨የሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ
፨ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት
፨ጌጡ ተመስገን ይገኙበታል፡፡
ሌሎችም በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ይታደማሉ።
ውድ ቤተሰቦች ቅንና በጎ ሰው ሐብቱ የሰው ፍቅር እንደመሆኑ ባለመቅረትና ዝግጅቱን በመታደም ወዳጅጓደኛዎን ይዘው በመገኘት ታሪካዊ አደራችንን እንወጣ።

"አሊዬ እኛ እያለን ልጆችህ አይጎሳቆሉም"

ለብዙሃን እንዲደርስ share በማድረግ እንዲሁም copy paste በማድረግ በግል ገፃችሁ በመለጠፍ መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ ይተባበሩን።

 #ዛሬ ሀዋሳ 138 ስራ አጦችን ወደ ስራ አስገብታለች ።ይህ ዘርፍ ቁርጥኛ መሪ በማጣቱ ዘርፉ በብዙ ተጎድቶ እንደከረመ የአደባባይ ሀቅ ነው።ከብደር ስርጪት እስከ ቦታ ድጋፍ ወይም እንዲህ ሼ...
15/11/2023

#ዛሬ ሀዋሳ 138 ስራ አጦችን ወደ ስራ አስገብታለች ።

ይህ ዘርፍ ቁርጥኛ መሪ በማጣቱ ዘርፉ በብዙ ተጎድቶ እንደከረመ የአደባባይ ሀቅ ነው።ከብደር ስርጪት እስከ ቦታ ድጋፍ ወይም እንዲህ ሼድ ገንብቶ መስጠት በሀዋሳ ከተማ ከቆመ ረዥም ጊዜ እንዳስቆጠረ ይታወቃል። ዛሬ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ስራ በድግሪና ዲኘሎማ ተመረቀው ለተደራጁ ኢንተርኘራይዞች የመሸጫ ቦታ ማስተላለፉ እጂግ የሚበረታታ ነውና በርቱ ለማለት እንወዳለን። በከተማው ያለውን ስራ አጥ ማስተፈስ ብቻ ሳይሆን የዛሬውን ግልፀኝነት የሰፈነበትን የቦታ ድጋፍ (ሼድ) የተመለከቱ የከተማው ወጣቶች በየክፍለ ከተማቸው ለመደራጀትና ስራ ፈጣሪ ለመሆን እጅግ ታላቅ ተስፋ ይሰንቃሉ ብለን እንጠብቃለን። ዛሬ ከ30 ኢንተርኘራይዞች ጋር ነው ርክክብ የተደረገው ይህ ማለት በአባላት ብዛት በትንሰሹ 138 ድግሪ እና ዲፕሎም ምሩቃን የሚጠጉ ናቸው።ዛሬ ሀዋሳ 138 ስራ አጦችን ወደ ስራ አስገብታለች ።

ምንጭ፡-ዜና ንጋት

የኤፌዴሪ ኢንዱስትሪ ምንስቴር ምንስትር አቶ መላኩ አለበል በሐዋሳ ከተማ በመገኘት የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን ጉብኝት አድርገዋል። ህዳር 03/2016 ዓ.ም   የኤፌዴሪ ኢንዱስትሪ ምንስቴር ምን...
13/11/2023

የኤፌዴሪ ኢንዱስትሪ ምንስቴር ምንስትር አቶ መላኩ አለበል በሐዋሳ ከተማ በመገኘት የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን ጉብኝት አድርገዋል።

ህዳር 03/2016 ዓ.ም

የኤፌዴሪ ኢንዱስትሪ ምንስቴር ምንስትር አቶ መላኩ አለበል በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሐዋሳ ከተማ ተገኝተው ግርን እስታር ጨው ማምረቻ፣ ያሬድ እንጂኔሪንግ : በቅርቡ ስራ የምጀምረውን ሱፐር ኦቨ አግሮ አግሮቴክ የእንሰሳት መኖ ማቀነባበርያ ፋብርካና በታቦር ሴራምክስ ኢንዱስትሪ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የኤፌዴሪ ኢንዱስትሪ ምንስቴር ምንስትር አቶ መላኩ አለበል እንደተናገሩት አገራችን የያዘችውን የልማት ጎዳና ለማፋጠን አምራች እንዱስትሪዎችን ማበረታታት ያስፈልጋል፣ በመሆኑም ከውጭ የምናስገባውን የተለያዩ ምሮቶችን በአገር ውስጥ በመተካት የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በተጨማሪ ሚንስቴሩ በቀጣይ ዉጠታማነትን ልያሻሽሉ እና ከፈደራል ተቋማት በኩል በምያስፈልጉ ድጋፋች ዙርያ ከኢንዱስትሪዎች ባለበቶችና ስራስካጆች ጋር ተወያይተዋል !

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና እንደተናገሩት በክልላችን አምራች እንዱስትሪዎች ውጠታማ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ድጋፉ ተጠናክሮ እንደምቀጥል ተናግረዋል ‼️

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ።ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል በሐዋሳ ከተማ ዛሬ ተካሄዷል።የግድቡ ዋንጫ...
13/11/2023

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ።
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል በሐዋሳ ከተማ ዛሬ ተካሄዷል።

የግድቡ ዋንጫ በከተማዋ በነበረው የሶስት ቀናት የገቢ ሜሰባሰቢያ ቆይታ 27 ሚሊየን ብር ማሰባሰብ መቻሉን የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ በገቢ ማሰባሰቢያ መድሩኩ ገልፀዋል።

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ደረጃ እስካሁን በተደረገ የገቢ ማሰባሰብ ስራ ከ756 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የሲዳማ ክልል የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ሀሜሶ በመድረኩ ገልፀዋል።

ግድቡ ወደክልላችን ከገባበት ከህዳር 29ቀን 2015 ዓም ጀምሮ መላው የክልሉ ህዝብ ባለው አቅም ሁሉ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል ያሉት አቶ ክፍሌ ሀሜሶ የገቢ ማሰባሰብ ስራው በሁሉም የክልሉ ዞኖችና ከተማዎች እስከ ህዳር 20/2016 ዓም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።

የህዳሴ ግድብ ለመላው ኢትዮጵያውያን በራስ አቅም ጀምሮ የመጨረስ እና የአንድነታችን ማሳያ መሆኑን የገለፁት ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ በከተማ ደረጃ ለማሳካት ከተሰጠው እቅድ አኳያ ከመቶ 30 ፐርሰንት በላይ ማሳካት መቻሉን በመጥቀስ የከተማውን አጠቃላይ ማህበረሰብ በማሳተፍ የገቢ ማሰባሰብ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

የግድቡ ዋንጫ በሐዋሳ ከተማ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የነበረውን ቆይታ አጠናቆ በተካሄደው በማጠቃለያ መድረኩ የክልል፣ የከተማና የዞን የስራ ኃላፊዎች፣ የከተማው ባለሀብቶች፣ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂዳል።

በመጨረሻም ዋንጫው በቀጣይ ወደሚጓዝበት በሲዳማ ብሔራዊ ክልል የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የከተማና መሰረተልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፊሊጶስ ናሆም ከሐዋሳ ከተማ ዋንጫውን በክብር ተረክበዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር በነገው እለት በሐዋሳ ይጠናቀቃል።በዚህ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ታላላቅ የከተማችን ባለሀብት፣ የከተማዋ ነዋሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች...
12/11/2023

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር በነገው እለት በሐዋሳ ይጠናቀቃል።

በዚህ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ታላላቅ የከተማችን ባለሀብት፣ የከተማዋ ነዋሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች በተለያየ መልኩ ለግድባችን ግንባታ አሻራቸውን ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እርሶም የዚህ ታሪካዊ ዋንጫ እና የግድባችን ግንባታ ላይ አሻራዎን ያኖሩ ዘንድ ተጠርተዋል!!!

ነገ ከጥዋቱ 2:30 ጀምሮ በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ቀጠሮዎን ያድርጉ ‼️

✍️✍️

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የታላቁን የህዳሴ ግድብ ዋንጫ  ተረከበ።በርክከብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለፁት ታላቁ የኢትዮጵ...
11/11/2023

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የታላቁን የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ተረከበ።

በርክከብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለፁት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ያለማንም እርዳታና ድጋፍ ተገብንቶ እየተገባደደ እንደሆነ በመግለፅ ግድባችን ሙሉ በሚሉ ተጠናቆ ሀይል እንዲያመነጭ ህዝባዊ ተሳትፏችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል።

የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በንግግራቸው ታለቁ የህዳሴ ግድብ ግንባ ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንቲባው ተናግረዋል።

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ክፍሌ ሀሜሶ በገለፃቸው በሀዋሳ ከተማ የተጀመረው የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ርክክብና የገቢ ማሰባሰብ መርሃ ግብር በክልሉ በሌሎች ዞኖችም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የታላቁን የህዳሴ ግድብ ዋንጫን ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በተረከበበት ወቅት በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ም/ር መስተዳድርና ትም/ት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ በራሳ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ፣ የክልልና የሀዋሳ ከተማ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ምንጭ:- የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

"ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የ3ተኛ ዙር የመንግሥት አመራሮች የአቅም ግምባታ ስልጠና በሀዋሳ ማዕከል ተጀመረ።ዜና ሀዋሳ ሐዋሳጥቅምት 30/2016በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ...
10/11/2023

"ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የ3ተኛ ዙር የመንግሥት አመራሮች የአቅም ግምባታ ስልጠና በሀዋሳ ማዕከል ተጀመረ።

ዜና ሀዋሳ
ሐዋሳ
ጥቅምት 30/2016

በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ማዕከል የሚካሄደው 3ተኛ ዙር "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል መሪ ቃል የመንግሥት አመራሮች የአቅም ግምባታ ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የስልጠና ቆይታቸው በማስመልከት እንደተናገሩት የፍቅር እና የሰላም ወደሆነው ወደ ሲዳማ ክልል እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በሀዋሳ ማዕከል በሚኖራቸው ቆይታ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ከሁሉም አካባቢዎች የመጣችሁ ሰልጣኞች ከስልጠናው በሚያገኙት ልምድ እራሱን በማብቃት ሀገራችን ለጀመረችው የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ እንዲያውለው በማለት በጋራ ሀገራችንን ላይ መግባባትን በመፍጠር ለብፅግናዋ የሚተጋ ቆራጥ አመራር መሆን ይገዋባል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ማዕከል ከ2200 በላይ የመንግስት አመራሮች የአቅም ግምባታ ስልጠና ዛሬ ጀምሯል።

ምንጭ፦ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

Address

Awassa

Telephone

+251912553233

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዜና ሀዋሳ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዜና ሀዋሳ:

Share

Category