05/09/2026
በክልሉ የህግ የበላይነትን በማስከበር የህዝብና የመንግስት ጥቅም ለማስጠበቅ በተሰራው ስራ ተጨባጭ ውጤት መምጣቱን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።
( ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሴክተር ጉባኤ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
ቢሮው ''ጠንካራ የፍትህ ሥርዓት ለጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ'' በሚል መሪ ቃል የ2018 አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ነው ከባለድርሻና ከህዝብ ክንፍ አካላት ጋር እየመከረ ያለው።
የቢሮው ሀላፊ አቶ አክመል አህመዲን በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት በክልሉ የህግ የበላይነት በማስከበር የህዝብና የመንግስት ጥቅም ለማስጠበቅ በቅንጅት በተሰራው ስራ ተጨባጭ ውጤት መጥቷል።
በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶች ከለፉት ዓመታት ለውጥ የታዬባቸው መሆኑን የተናገሩት ሀፊው በበጀት ዓመቱ በድርድር እና በክስ ከ378 ሚሊዮን ብር በላይ ማስመለስ ተችሏል ብለዋል።
በፍትህ ትራንስፎርሜሽን የመሠረተ ማህበረሰብ ፍትህ አንዱ በመሆኑ ይህን ተግባር ወደ መሬት በማውረድ የባህላዊ ፍርድ ቤት አዋጅ በማጽደቅ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል።
ይህም በፍርድ ቤት የጉዳዮች መጨናነቅ ከመቀነሱም በላይ በተከራካሪ ወገኖች መካከል እርቀ ስለም በማዉረድ አብሮ የመኖር ባህል እንድዳብር አድርጓል ብለዋል።
የባለጉዳዮችንም ውጣውረድ እና ወጪ የሚቀንስ በመሆኑ በመሆኑ ቀጣይም በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ እንድቀጥል ተገቢው ክትትል እና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የፍትህ ተደራሽነትንም ለማረጋገጥ ቢሮው ሁለት ምድብ ጽ/ቤት በሆሳዕና እና በወልቂጤ ከተማ በመክፈት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ልማዳዊ አሠራር ተቋሙን ለብልሹ አሰራር በመዳረግ የተቋሙን እምነት የሚሸረሽር መሆኑን የገለፁት አቶ አክመል አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በክልሉ የአንድ መሶብ የአገልግሎት ማዕከላት ላይ የፍትህ ተቋማትን አገልግሎቶች የማስገባት ስራው ተጠናክሮ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በቀጣይ ከመሬት ወረራና ብልሹ አሰራር፤የጥላቻ እና ሀሰተኛ ማህበራዊ ሚዲያ በላይ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጠንካራ የምርመራ ሥራ በመስራት የተመዘበረ ሀብት የማስመለስና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ የሚሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በመድረኩ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ አቶ ንጉሴ አስረስ ዶ/ርን ጨምሮ የክልል፣የዞንና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ባለሙያዎች፤ ባለድርሻ አካላት እና የህዝብ ክንፍ አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
👉የክ መ ኮ