21/11/2022
Very Important Issue!
በ ሰ/መ/ቁ. 123123 ቅጽ 21 በተሰጠ የህግ ትርጉም ከሳሽ ያቀረበው ክስ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 92 የተደነገገውን አስገዳጅ መስፈርት የማያሟላ መሆኑን በማረጋገጥ ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መዝገቡ ከተዘጋ ምንም አይነት ክስ እንዳልቀረበ የሚያስቆጥርና የይርጋ ጊዜ የማቋረጥ ውጤት የሌለው ነው።
የሰ/መ/ቁ 123123 - በክስ አቀራረብ ሥርዓት ላይ ጉድለት ያለበት መሆኑ ተረጋግጦ የተዘጋ መዝገብ ምንም አይነት ክስ እንዳልቀረበ የሚያስቆጥርና የይርጋ ጊዜ የማቋረጥ ውጤት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 278 (2) (ሀ) እና (3)
ክስ ስታቀርብ ክሱን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 92 ማረጋገጥ ከረሳህና በሬጅስትራርም ሳይታረም መዝገቡ ለችሎት ከቀረበ ፍርድ ቤቱ ስነ-ስርዓት አላሟላም በሚል መዝገቡን ይዘጋዋል። ቀጥሎ ያለው መፍትሔ ሌላ ክስ ማቅረብ ነው። አዲሱ ክስ ደግሞ የይርጋ ጊዜን አያቋርጥም።
(Abyssinia law)