LAW Firm of Ethiopia

LAW Firm of Ethiopia በዚህ ገፅ፥ የሕግ መረጃዎችን፥ሕጎችንና መመሪያዎችን እንለዋወጣለን። ልምድና ዕውቀታችንን እንካፈልበታለን። 945888893

ሰምኑን በፋይዳ መታወቂያ ላይ በስሕተት የተመዘገቡ መረጃዎች ስለሚታረሙበት አግባብ የፋይዳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለፍ/ቤቶች የጻፈውን ደብዳቤ ተጋርተን እንደነበር ይታወቃል:: በደብዳቤው መሠረት ስ...
27/08/2026

ሰምኑን በፋይዳ መታወቂያ ላይ በስሕተት የተመዘገቡ መረጃዎች ስለሚታረሙበት አግባብ የፋይዳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለፍ/ቤቶች የጻፈውን ደብዳቤ ተጋርተን እንደነበር ይታወቃል::
በደብዳቤው መሠረት ስሕተቶችን በቅድሚያ መርምሮ የማስተካከል ሥልጣን የጽ/ቤቱ እንደሆነ፣ ፍ/ቤቶች ሥልጣን የሚኖራቸው ጽ.ቤቱ አገልግሎቱን አልሰጥም ካለ ወይም በሰጠው አገልግሎት ቅርታ ካለ ብቻ እንደሆነ ነው::
ይሁንና በዚህ መሠረት ተገልጋዮች በቅድሚያ ከጽ/ቤቱ መፍትሔ ፍለጋ ሲሄዱ ተከታዩ ምላሽ እየተሰጣቸው እንደሆነ የተለያዩ የኅ/ሰብ ክፍሎች ለመረዳት ችለናል::
ይህም የሆነ ያልተገናዘበ ነገር እንዳለ ያሳያል::🤔
Hasena

26/08/2026
26/08/2026

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 63/2017ን አስመልክቶ ውይይት አካሄደ

ሳውላ ፣ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም – የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከከተማው መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋር አዋጅ ቁጥር 63/2017ን አስመልክቶ ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሙሉነህ ወ/ፃድቅ በሰጡት ማብራሪያ፣ የባህል ፍርድ ቤቶች መቋቋም በሕብረተሰቡ መካከል ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ከማስፈን ባለፈ፣ ጊዜና ወጪን ለመቆጠብ እና የመደበኛ ፍርድ ቤቶችን የሥራ ጫና ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

በመሆኑም የባህል ፍርድ ቤቶችን የማቋቋም ሂደት በትኩረት እንደሚሰራበት የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ የባህል ፍርድ ቤቶች ሲቋቋሙ የሰው ልጆችን እኩልነት፣ ማህበራዊ መስተጋብርን፣ ሞራልና ክብርን በጠበቀ መልኩ እውነትና ፍትህን ያለምንም አድልዎ መስጠት እንዳለባቸው አብራርተዋል።

የፍርድ ቤቱ ም/ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር መብራቱ በለጠ በበኩላቸው፣ አዋጁ ሲተገበር በሕገ-መንግስቱና በዓለም አቀፍ ስምምነቶች የተደነገጉ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች፣ እንዲሁም ዜጎች ፍትህ የማግኘት መብት በመጠበቅ ያለምንም አድልዎ ዳኝነት መሰጠት እንዳለበት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በውይይቱም የባህል ፍርድ ቤቶች መቋቋም ወደ መደበኛ ፍርድ ቤቶች የሚገባውን የጉዳይ ፍሰት ከመቀነስ ባለፈ፣ ለተከራካሪዎች ፈጣንና ተደራሽ የፍትህ አማራጭ ለመፍጠር እና በማህበረሰቡ ውስጥ ለሚነሱ ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ ከመፍጠር አኳያ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተመላክቷል።

በመድረኩ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሙሉነህ ወ/ፃድቅ፣ ም/ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር መብራቱ በለጠ፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ንዑስ ዳኝነት አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊና የጉባኤው አባላት፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዳኞች፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እንዲሁም የመስማትና መወሰን ሥራ ሂደት አስተባባሪ ተሳትፈዋል።

ተሳታፊዎቹም የአዋጁን አስፈላጊነት፣ የባህል ፍርድ ቤቶች አተገባበርና በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ ሊኖራቸው የሚችለውን ሚና በሚመለከት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።

ዘገባው፦ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽን ነው።

26/08/2026

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በባህላዊ ፍርድ ቤቶች አዋጅ 63/2017 ዙሪያ የግንዛቤ ስልጠና ሰጠ

ሳውላ፤ ነሐሴ 20/2018 ዓም | የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በስሩ ለሚገኘው የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋምና እውቅና ለመስጠት በወጣው አዋጅ ቁጥር 63/2017 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ኦሬንቴሽን፣ አዋጅ ቁጥር 63/2017ን በተግባር በማዋል ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን በከተማው ውስጥ እንዴት ማቋቋም እንደሚቻል ከመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ጋር ውይይት በማድረግ በቀጣይ አፈጻጸም ላይ የጋራ መግባባት ተደርሷል።

በስልጠናው ወቅት በተለይም የጋሞ ማህበረሰብ ያለው የዳበረ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት “ዱቡሻ” አዋጁን በተግባር ለማስፈጸም ጉልህ እድል እንደሚፈጥር ተጠቅሷል። ይህንን እሴት በመጠቀም በከተማው ውስጥ ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ማቋቋም ለፍትሕ ተደራሽነትና ለማህበራዊ እርቅ ጉልህ ፋይዳ እንዳለውም ተገልጿል።

በመጨረሻም የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ክብርት ሰራዊት ሀጎስ፣ በ2019 የበጀት ዓመት በከተማው ውስጥ የባህላዊ ፍርድ ቤቶችን በማደራጀትና እውቅና በመስጠት ሥራውን በቁርጠኝነት እንደሚያስጀምሩ አረጋግጠዋል።

ምንጭ፦ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽን።

Gamo Zone High Court ጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት💪
26/08/2026

Gamo Zone High Court ጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት💪

26/08/2026

There is a paradox in the current .
I think the Ethiopian current landscape needs . This means on the one hand the country wants to ensure access to by its citizens in a fair manner. On the other hand, it has been investing in selected under the name of boarding and special secondary schools. We can imagine the disparity among all the cares and investments that are made for selected and privileged students and those lower performing as well as average students living and learning in urban and rural areas of the country. If this unfair provision of education perpetuates, the creation of strong social classes will be inevitable. It seems that the country is pursuing the that states the rich will get richer and the poor will get poorer or the Matthew Principle that underscores that people with initial advantages accumulate more success, while those with disadvantages fall further behind. Therefore, there is a need for minimizing this big gap if access to quality education is to be considered as a in the Ethiopian context.

Muluken Tadesse💪💪💪
21/08/2026

Muluken Tadesse💪💪💪

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ 1 ሚሊዮን ለሚደርሱ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሕግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት መዘጋጀቱን አሳወቀ።

ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም.

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ በክረምቱ ወራት 1 ሚሊዮን ለሚደርሱ ሕብረተሰብ ክፍሎች የሕግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት መዘጋጀቱን የቢሮው ሀላፊ አቶ ሙሉቀን ታደሰ ገልጸዋል ።

መርሃ ግብሩ በክልሉ ሁሉም ዞኖች፣ ሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች፣ በወረዳዎችና በከተማ አስተዳደሮች የሚካሄድ ሲሆን ከነሐሴ 11 እስከ 15/2018 ዓ.ም የሕግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ተደርጎ እንደሚካሄድም አሳውቀዋል ።

በተጨማሪም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን የሕግ ጉዳዮች በእውቀት እንዲመለከቱ፣ ከሕግ ጥሰት እንዲርቁ፣ መብታቸው ሲጣስ ተገቢውን ሕጋዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ እና ግጭቶችን በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ማስቻል የመርሃ ግብሩ ዓላማ መሆኑን ጠቅሰዋል ።

ይህንን ግብ ለማሳካትም የሕግ ግንዛቤ ሥልጠናው በሁሉም ዞኖች፣ በሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች፣ በወረዳዎችና በከተማ አስተዳደሮች በስፋት እንዲደርስ እንደሚደረግ ሀላፊው ተናግረዋል ።

በየአካባቢው ከሚስተዋሉ የሕግ ችግሮችና ከሕብረተሰቡ ፍላጎት በመነሳት ተገቢው የሕግ ርዕስ ተመርጦ ተግባራዊ ግንዛቤ እንዲሰጥ ይደረጋል። ይህም የሕግ እውቀትን ከማስፋት ባለፈ ዜጎች ሕግን በተግባር እንዲጠቀሙ ያግዛል።

እንደ ሀላፊው ገለፃ የሚሰጠው የሕግ ግንዛቤ እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታና የሕብረተሰቡ ፍላጎት በተለያዩ የሕግ ርዕሶች ላይ ያተኩራል።

ለመርሃ ግብሩ ስኬትም የዞንና የሪጂዮ ፖሊስ ከተማ ፍትህ መምሪያዎች፣ የወረዳና የከተማ ፍትህ ጽ/ቤቶች በቅንጅትና በኃላፊነት እንዲሠሩ አሳስበዋል።

በአጠቃላይ የታቀደው የሕግ ግንዛቤ መርሃ ግብር ዜጎች ሕግን እንዲያውቁና እንዲያከብሩ፣ መብታቸውን በሕጋዊ መንገድ እንዲያስከብሩ፣ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እና የሕግ የበላይነትን በክልሉ ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ብሮ!!🙏🙏
21/08/2026

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ብሮ!!🙏🙏

21/08/2026

New Criminal Procedure and Evidence Code.
Enjoy reading.

በኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ላይ በስሕተት የተመዘገበ መረጃ ካለ ተቋሙ አጣርቶ በራሱ የማስተካከል ሥልጣን አለው:: ስለሆነም  ፍርድ ቤቶች “በፋይዳ መታወቂያ ላይ የተፈጠረ ስሕተት ...
21/08/2026

በኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ላይ በስሕተት የተመዘገበ መረጃ ካለ ተቋሙ አጣርቶ በራሱ የማስተካከል ሥልጣን አለው::
ስለሆነም ፍርድ ቤቶች “በፋይዳ መታወቂያ ላይ የተፈጠረ ስሕተት ይታረምልኝ” የሚሉ አቤቱታዎችን በቀጥታ ተቀብለው የማየት ሥልጣን የላቸውም::
ፍ/ቤቶች የዚህ ዓይነት አቤቱታዎችን መቀበል የሚችሉት ተቋሙን አስተዳደራዊ መፍትሔ ጠይቀው ካልተሰጣቸው ወይም የተሰጣቸው መፍትሔ ላይ ቅሬታ ካላቸው ብቻ ነው:: " የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም) ለፍ/ቤቶች የጻፈው ደብዳቤ

"ጠበቆች ደንበኞቻችሁን በዚህ አግባብ እንደምታማክሩ ይሁን::)👴🏽🤠😃
Hasena🤞

Address

Arba Minch'

Telephone

+251912670051

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when LAW Firm of Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to LAW Firm of Ethiopia:

Shortcuts

Share