Esayas Lema Enna

Esayas Lema Enna Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Esayas Lema Enna, Corporate lawyer, Arba minch Ethiopia �, Arba Minch'.

03/07/2026

ጠቅላያችን ዶክተር አቢይ አህመድ በደማቋ አርባምንጭ ከተማ ተከስተዋል🙏🙏🙏❤

የአመቱ ምርጡ ከንቲባ፦ ዶክተር መስፍን መንዛ ማሞ — የለውጥና የዕድገት ተምሳሌትአንድን ከተማ ወደ ላቀ ከፍታ ለመውሰድ ራዕይ ያለው መሪ፣ ቁርጠኛ ልብ እና ህዝባዊ ወገንተኝነት ወሳኝ ናቸው።...
03/07/2026

የአመቱ ምርጡ ከንቲባ፦ ዶክተር መስፍን መንዛ ማሞ — የለውጥና የዕድገት ተምሳሌት

አንድን ከተማ ወደ ላቀ ከፍታ ለመውሰድ ራዕይ ያለው መሪ፣ ቁርጠኛ ልብ እና ህዝባዊ ወገንተኝነት ወሳኝ ናቸው። የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ *ዶክተር መስፍን መንዛ* ይህንን እውነት በተግባር በማሳየት፣ በጥሩ ስራቸውና በህዝብ ተጠቃሚነት ላይ ባተኮረ አመራራቸው “የአመቱ ምርጡ ከንቲባ” ለመባል ይገባቸዋል ።

ዶክተር መስፍን ከተማዋን በሁሉም ዘርፍ ለማዘመንና የነዋሪዎችን ህይወት ለመቀየር ሌሊትና ቀን እየሰሩ ይገኛሉ። ለአርባምንጭ ሁለንተናዊ ለውጥ መምጣት መሰረት የሆኑት አበይት የስራ ስኬቶቻቸው ተዘርዝሮ አያልቅም። ለአብነት :_

1. ዘመናዊና ጠንካራ የተቋማት ግንባታ (Institutional Building)

ማንኛውም ዘላቂ ልማት የሚረጋገጠው ተቋማት ሲገነቡና አሰራር ሲዘምን እንደሆነ የሚረዱት ከንቲባው፣ በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚከተሉትን ስራዎች አከናውነዋል፦

* *የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን፦* የህዝብ እንግልትን የሚቀንሱ፣ ቢሮክራሲን የሚያስወግዱና ግልፅነት የሰፈነባቸው አሰራሮችን በተቋማቱ ውስጥ ዘርግተዋል።
* *የአመራርና የባለሙያ አቅም መገንባት፦* አስፈፃሚው አካል ለህዝብ ጥያቄ ፈጣንና ፍትሃዊ ምላሽ መስጠት እንዲችል ቀጣይነት ያላቸው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችንና የክትትል ስርዓቶችን መስርተዋል።
* *ዲጂታላይዜሽን(መሬት አስተዳደር )፦* የከተማዋን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በመደገፍ ነዋሪዎች ቀልጣፋና ከሌባ የጠራ አገልግሎት እንዲያገኙ አድርገዋል።
ፀጥታና አስተማማኝ ሰላም ማስከበር

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት እንደመሆኑ መጠን፣ አርባምንጭ የሰላምና የደህንነት ተምሳሌት እንድትሆን ትልቅ ስራ ሰርተዋል፦

* *የህዝብና የፀጥታ አካላት ቅንጅት፦* “የአርባምንጭ ሰላም የነዋሪዎቿ ኩራት ነው” በሚል መርህ፣ ህዝቡና የፀጥታ መዋቅሩ ተቀናጅተው የሚሰሩበትን የጋራ መድረክ ፈጥረዋል።
* *የቱሪስትና የኢንቨስትመንት ቀጠና ማድረግ፦* ከተማዋ አስተማማኝ ሰላም ያላት በመሆኑ ኢንቨስተሮች ያለ ምንም ስጋት እንዲሰማሩ፣ ቱሪስቶችም በነፃነት መጥተው እንዲጎበኙ ምቹና አስተማማኝ ድባብ ፈጥረዋል።
* *የወጣቶች ተሳትፎ፦* ወጣቶችን በሰላም ግንባታና በልማት ስራዎች ላይ በንቃት በማሳተፍ የከተማዋን ሰላምና መረጋጋት ዘላቂ እንዲሆን አድርገዋል።

*"እውነተኛ መሪነት ማለት የህዝብን አደራ በአግባቡ መወጣት፣ የሃገርን ሃብት ከብክነት መከላከል እና ለነገዋ ከተማ ጠንካራ መሰረት መጣል ነው፤ እኛ የምንሰራው ለዚህ ነው።" ዶክተር መስፍን መንዛ

የትኩረት አቅጣጫ እና የተመዘገበ ውጤትና ለውጥ
👉የተቋማት አቅም የህዝብ ቅሬታ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስና ቀልጣፋ አገልግሎት መስፈን
👉 አላስፈላጊ ወጪዎች ተቀንሰው የልማት ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ መደረጉ
👉የከተማዋ ሰላም አርባምንጭ በደቡብ ኢትዮጵያ ካሉ እጅግ አስተማማኝና ማራኪ የሰላም ቀጠናዎች አንዷ መሆኗ

ዶክተር መስፍን መንዛ ማሞ አርባምንጭን ስሟንና የተፈጥሮ ፀጋዋን የሚመጥን ዘመናዊ ከተማ ለማድረግ የሚያደርጉት ጉዞ ፍሬ እያፈራ ይገኛል። በተቋማት ግንባታ፣ በበጀት ቁጠባና በሰላም ማስከበር ረገድ ያሳዩት ድንቅ አፈፃፀም የአመቱ ምርጡ ከንቲባ የሚለውን ታላቅ ክብር በሙሉ ድምፅ እንዲጎናፀፉ አድርጓቸዋል።

*ክብርና ምስጋና ለህዝብ አገልጋዩ መሪያችን ዶክተር መስፍን ማሞ! አርባምንጭ በርስዎ አመራር ወደፊት መጓዟን ትቀጥላለች!*

በጠንካራ የመሪነት ብቃት አርባምንጭ አሸብርቃለች !!
21/06/2026

በጠንካራ የመሪነት ብቃት አርባምንጭ አሸብርቃለች !!

Address

Arba Minch Ethiopia �
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Esayas Lema Enna posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Esayas Lema Enna:

Shortcuts

Share