Dawit Amare law office DALOF

Dawit Amare law office DALOF የህግ አገልግሎት ለማስተዋወቅ ሰለ ህግ ለማወቅ እና ለማሶወ?

24/04/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Abu Yusuf Meni, Fekereselame Agere, Birhanu Gurmesa, Kasa Sitot Alemu, Yetwala Bayhbrhanu, Teshome Diriba, Mulat Sugebo Bersumihret, Angel Workineh, Dejene Molla, Naf Nati, Dereje Gemtessa, Abayneh Herana, Tewodros Taye Nigatu, Bekele Solomon, De Eve, Qasker Macammad, Chimdi Lami, Getahun Tumoro, Samuel Yoseph, እንደሰው ቢሆን, Chale Moke, Ashenafi Awoke, ጀመል አህመድ, ኤርያድ ህገኛው

06/07/2022

Hongera!

Uganda's cabinet has approved the adoption of Swahili as an official language. Swahili, which originated in East Africa, is one of the world's 10 most widely spoken languages with about 200 million speakers.

https://bbc.in/3OOJcJE

19/05/2022

የፍርድ ቤት ውሳኔ :የመጨረሻ ትእዛዝ:ብይን በሚዲያ ለመተቸት የሚፍቅድ ሆነ የሚከለክል ህግ አለ ወይ? የሚተችስ ከሆነ
የግድ ጉዳዬ ለመተቸት የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት የመጨረሻ ውሳኔ ሊሰጥ ይገባል ወይ ? በሚለው ጭብጥ ላይ ሙያዊ አሰተያየታችሁን ወዲ በሉ

10/10/2021

Provisional Rules of Procedure
Chapter II: Agenda
Rule 6
The Secretary-General shall immediately bring to the attention of all representatives on the Security Council all communications from States, organs of the United Nations, or the Secretary-General concerning any matter for the consideration of the Security Council in accordance with the provisions of the Charter.

Rule 7
The provisional agenda for each meeting of the Security Council shall be drawn up by the Secretary-General and approved by the President of the Security Council.

Only items which have been brought to the attention of the representatives on the Security Council in accordance with rule 6, items covered by rule 10, or matters which the Security Council had previously decided to defer, may be included in the provisional agenda.

Rule 8
The provisional agenda for a meeting shall be communicated by the Secretary-General to the representatives on the Security Council at least three days before the meeting, but in urgent circumstances it may be communicated simultaneously with the notice of the meeting.

Rule 9
The first item of the provisional agenda for each meeting of the Security Council shall be the adoption of the agenda.

Rule 10
Any item of the agenda of a meeting of the Security Council, consideration of which has not been completed at that meeting, shall, unless the Security Council otherwise decides, automatically be included in the agenda of the next meeting.

Rule 11
The Secretary-General shall communicate each week to the representatives on the Security Council a summary statement of matters of which the Security Council is seized and of the stage reached in their consideration.

Rule 12
The provisional agenda for each periodic meeting shall be circulated to the members of the Security Council at least twenty-one days before the opening of the meeting. Any subsequent change in or addition to the provisional agenda shall be brought to the notice of the members at least five days before the meeting. The Security Council may, however, in urgent circumstances, make additions to the agenda at any time during a periodic meeting.

The provisions of rule 7, paragraph 1, and of rule 9, shall

05/10/2021

Under Article 9 of the Vienna Convention on Diplomatic Relations, a receiving state may "at any time and without having to explain its decision" declare any member of a diplomatic staff persona non grata. A person so declared is considered unacceptable and is usually recalled to his or her home nation. If not recalled, the receiving state "may refuse to recognize the person concerned as a member of the mission".A person can be declared a persona non grata before that person even enters the country. በዚህ ስምምነት መሰረት የኢትዬጵያ እንኮንን ከበቂ በላይ ምክንያት ኖሮት በዲፕሎማሲያዊ ግንኝነቱ ወሰጥ ዲፕሎማቱን ያለ ምክንያት የላከው ሀገር ወይም አለም አቀፍ ድርጅት እንዲሰበስበው የማድረግ እና በተቀባይ ሀገር በኩል ተቀባይነቱ ያጣ መሆኑን መግልጵ የሚቻልበትን ሰነድ እያለ የቀኝ ግዛት ሰነድ ይመስል ምንድነው ኢትዬጵያ መብት የላትም የሚሉት ይገርማል ?

22/07/2021

የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ
=====================
በወንጀል ጉዳይ የጥፋተኛነት ውሳኔ ከተሰጠ በኃላ ዓቃቤ ህግ ቅጣቱ ከብዶ እንዲወሰን ተከሳሽ ደግሞ እንዲቀልለት በየፊናቸው የሚያቀርቧቸው ምክንያቶች
ዓቃቤ ህግ እና ተከሳሽ የማክበጃ እና የማቅለያ ምክንያቶች የማቅረብ እና አስፈላጊ ሲሆንም በማስረጃ የማስደገፍ መብት ያላቸው ስለመሆኑ ከወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 149 (3) እና (4) ድንጋጌ አጠቃላይ ይዘት እና መንፈስ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን ፍርድ ቤቶችም የእነዚህን መብቶች ተግባራዊነት ለማረጋገጥ ያስችል ዘንድ ለተከራካሪ ወገኖች ጊዜ ወይም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ የተባለ ሰው በቅጣት ማቅለያነት እንዲያዝለት ያቀረበውን ምክንያት በማስረጃ ማስደገፍ እንዲችል በቂ ጊዜ ባላገኘበት ሁኔታ በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በሚል የማቅለያ ምክንያቱን ውድቅ በማድረግ የሚሰጥ የቅጣት ውሳኔ በወንጀል ሕጉ እና በቅጣት አወሳሰን መመሪያው ስለ ቅጣት አወሳሰን የተቀመጡትን ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ.96168 ቅጽ 17፣ ወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 149(3) እና (4)
በወ/ሕግ ቁጥር 88/2/ ቅጣት ሊወሰን የሚገባው የወንጀል አድራጊውን ያለፈ የሕይወት ታሪክ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ መደንገጉ አንድ አጥፊ ወንጀሉን እስካደረገበት ጊዜ ድረስ የዘወትር ጠባዩ መልካም የነበረ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ለቅጣት ማቅለያነት የማይወሰድበት ምክንያት አይኖርም፡፡ ይህም ሁሉ ታልፎ በወንጀል ሕግ ቁጥር 82/1/ሀ/ የተመለከተው የቅጣት ማቅለያ ወጥነት ያለው የተጣመረ ምክንያት ነው እንኳ ቢባል በሥር ፍ/ቤቶች የቅጣትን አስተያየት አስመልክቶ በግራ ቀኙ በየደረጃው ከሚደረጉት ክርክሮች፣ ከድርጊቱ አፈፃፀምና ወንጀሉን ካቋቋመው ድንጋጌ ወይም ሕግ ጋር ሁሉ ተገናዝቦ ሲታይ በዚህ አከሪካሪ በሆነው ድንጋጌ “እና” ከሚለው ቀጥሎ ካሉት “ወይም” በሚል ምሕጻረ ቃል ከተያያዙት አንዱን ምክንያት ቢሆን እንኳ ተከሳሹ ካሟላ በቅጣት ማቅለያነት ይወሰድለታል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 53612 ቅጽ 10፣ ወ/ህ/ቁ. 80(2)
በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 82/1/ /ሠ/ መሰረት ተከሳሽ በእውነት የተፀፀተ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ሲገነዘብ ቅጣት ሊያቀልለት እንደሚችልና በእውነት ስለመፀፀቱ ከመገለጫዎቹ አንዱ በደል ለደረሰበት ሰው አስፈላጊውን እርዲታ ማድረጉ ሊሆን እንደሚችል ተቀምጧል፡፡ ይሄ ማለት ግን ተከሳሽ ተበዳይን ወደ ሕክምና ማዕክል ማድረሱ ብቻ በፈፀመው ድርጊቱ በእውነት ተፀፅቷል የሚያሰኝ ሳይሆን ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ወይም በይግባኝ የሚያየው ፍርድ ቤት አጠቃላይ የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማትና በማመዛዘን የሚደርስበት መደመደሚያ ነው፡፡ ተከሳሽ ተበዳይን ወደ ሕክምና ማዕክል ማድረሱ አጠቃላይ የክሱን ሂደት ከግምት በማስገባት ተከሳሽ በእውነት ተፀፅቷል የሚያሰኝ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ የማስረጃ ምዘና በመሆኑ በሰበር ሰሚ ችሎት ስልጣን ስር አይወድቅም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 62332 ቅጽ 10፣ ወ/ህ/ቁ. 82(1) ሠ
ጥፋተኛ የተባለ ተከሳሽ ተደራራቢ ወንጀሎች ከመፈጸሙ በፊት የወንጀል ሪከርድ ያልቀረበበት እና የዘወትር ፀባዩም መልካም ስለመሆኑና እንዲሁም የተከሰሰበትን ወንጀል ከፈፀመም በኋላ በመፀፀት ለግል ተበዳይ ገንዘብ መክፈል መጀመሩ ከተረጋገጠ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 82(1)(ሀ)፣ 5(ሠ) ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች በመሆናቸው ቅጣቱ እንዲቀል ያደርጋሉ፡፡
ሰ/መ/ቁ. 95438 ቅጽ 16፣ ወ/ህ/ቁ. 82(1) ሀ እና ሠ

ከሐምሌ 13/2013 ጀምሮ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍትሕ ብሔር የዳኝነት ስልጣን*************************************************************...
21/07/2021

ከሐምሌ 13/2013 ጀምሮ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍትሕ ብሔር የዳኝነት ስልጣን
***********************************************************************
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ 1234/2013 ዓ.ም ጥር 13/2013ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ የሚታወቅ ሲሆን የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሐምሌ 13/2013 ዓ.ም ጀምሮ ከዚህ በታች በተዘረዘሩ የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ስልጣን ይኖረዋል፡፡
• በአዋጁ አንቀፅ 14 መሰረት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአንቀፅ 11 ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጡ የፍትሀብሄር የዳኝነት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በአዋጁ አንቀፅ 3 ( ሕገ መንግስቱን፣ የፌዴራል መንግስቱን ሕች ወይም ኢትዮጵያ የተቀበላቻቸውን እና የጸደቀቻቸው ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች መሰረት በማድግ የሚቀርቡ ጉዳዮች፣ በፌዴራል መንግስቱ ሕግ ተገልጽ በተወሰኑ ባለጉዳዮች፣ በሕገ መንግስት ወይም በፌዴራል መንግስት ሕግ በተገለጹ ቦታዎች)፤
• ከላይ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በአዋጁ አንቀጽ 5 ከሀ-ፐ እና ጀ የፍትሀ ብሄር ጉዳዮች መሰረት በሚቀርቡ የፌደራል ፍትሀብሄር ጉዳዮች እንዲሁም በአንቀፅ 5 (ደ) ለአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው እና በሌሎች ህጎችም ለሌሎች አካላት የተሰጠው የዳኝነት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በአዲስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ በሚነሱ የፍትሀ ብሔር ጉዳዮች እና በሌሎች ህጎች የተጠቀሱ የፍትሀ ብሄር ጉዳዮች የመዳኘት ስልጣን እንዳላቸው፤
• የገንዘብ ተመን ያልወጣላቸው የውርስ ማጣራት፣ የውርስ ድርሻ ክፍፍል እንዲሁም የቤተሰብ ሕጉ መሰረት በማድረግ የሚቀርቡ ክርክሮች እና
• ለአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተማ ፍርድ ቤት እስከ 500 መቶ ሺህ ብር የሚገመቱ የገንዘብ፣ የውል እና የብድር ጉዳዮችን የማስተናገድ ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እስከ #ብር 10 ሚሊዮን ብር የሚደርሱ የገንዘብ ክርክር የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች የሚያስተናገድ ይሆናል፡፡

17/07/2021

ተተኪ ወራሽነት በውርስ ህግ
=================
የተተኪነት ወራሽ ስለመሆን በተመለከተ ለሰዎች አሁንም የመከራከሪያ ነጥብ እንደሆነ የደቡብ ጐንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍትሐብሔር መዝገብ ቁጥር 04033 ታህሣሥ 27 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ በማየት ለመረዳት ይቻላል፡፡
የክርክሩ መነሻ መምህር ሞገስ አለነ በጠበቃ እያታገዙ ያቀረቡት ማመልከቻ ሲሆን ይዘቱም ወላጅ እናቴ ወ/ሮ እማዋይ አለመኔ 1966 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች፡፡ የእናቴ እናት የሆነችው ወ/ሮ ሁሉአገር ውበቴ ደግሞ በ1989 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አያቴ ወ/ሮ ሁሉአገር ውበቴ በወረታ ከተማ የሠራችው መኖሪያ ቤት ያላት ሲሆን ቤቱን የእናቴ እህት የሆነችው ወ/ሮ አሰፉ አዳነ ከባለቤታቸው ከዶክተር ሞገስ አለነ ጋር በመሆን በውርስ የወሰዱት ስለሆነ እኔ አያቴን በእናቴ በወ/ሮ እማዋይ አለምኔ ምትክ በመሆን ወራሽ ስለሆንኩኝ የቤቱ ግምት ግማሹ ይገባኛል በማለት ክስ ያቀረባል፡፡ በዚህ ጉዳይ አንደኛ ተከሣሽ የሆነውንና የወ/ሮ አሰፉ አዳነ ባለቤት የሆኑት ዶ/ር ሞገስ ጥሩነህ በጠበቃቸው አማካኝነት ባቀረቡት መልስ ሟችን ለመውረስ በመጀመሪያ የሟች ውርስ ሲከፈል በሕይወት መኖር አስፈላጊ ነው፡፡ የእሱ አናት ወ/ሮ ሁለአገር ውበቴ ከመሞታቸው ከሃያ ሶስት አመት በፊት ቀድማ የሞተች ስለሆነ የከሣሽ እናት ሟች ወ/ሮ ሁሉአገርን ወርሣ አልሞተችም፡፡ በመሆኑም የከሣሽ እናት የፍትሃብሐር ሕግ ቁጥር 830 በሚደነግገው መሠረት ወ/ሮ እማዋይ ከወሮ ሁሉአገር በፊት ስለሞተችና በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 832 መሠረት ወራሽነቷን አረጋግጣ ሰላልሞተች ከሣሽ ወራሽ መሆን አይችሉም በማለት የተከራከረ ሲሆን ፣ ሁለተኛዋ ተከሣሽና የከሣሽ አክስት የሆነችው ወ/ሮ አሠፉ አዳነ ከሣሹ ከሟች አያቱ ውርስ የእናቱን ድርሻ ሊወስድ ይገባዋል በማለት ክሱን አምና ተከራክራለች፡፡ ፍርድ ቤቱም ከሣሽ በወ/ሮ ሁሉአገር ውበቴ ውርስ ጉዳይ ክስ ለመመስረት የሚያስችለው መብት አለው ወይስ የለውም የሚለውን ጭብጥ ካወጣ በኋላ በሰጠው ውሣኔ፣ በክርክሩ ሂደት እንደተረዳነው የከሣሽ አያት ወ/ሮ ሁሉአገር ውበቴ መሆናቸው አልተካደም፡፡ የከሣሽ እናት ደግሞ ወ/ሮ እማዋይ አለምኔ መሆናቸው የከሣሽ አያት ብቸኛ ወራሾች ደግሞ የከሣሽ እናትና ሁለተኛ ተከሣሽ መሆናቸው በግራ ቀኙ የተካዱ ነጥቦች አይደሉም፡፡ ከዚህ በመነሳት የከሣሽን መብት ስንመለከት ከሣሽ ያቀረበው ጥያቄ የምትክ ወራሽነት ነው፡፡ አንደኛ ተከሣሽ አጥብቆ ያነሣው የመከራከሪያ ነጥብ ይህንኑ አግባብ አይደለም የሚል ነው፡፡ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 842/3/ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ከሟች ልጆች የሚወርሰው ንብረት ባለ ጊዜና እሱ አስቀድሞ የሞተ እንደሆነ በእሱ እግር ተተክተው ተወላጆች መውረስ እንዲችሉ የተደነገገ ነው፡፡ አንደኛ ተከሣሽ እዚህ ላይ ያቀረበው የመከራከሪያ ነጥብ የከሣሽ እና ከከሣሽ አያት ቀድማ የሞተች ስለሆነ አልወረሰችም፡፡ ምክንያቱም ለመውረስ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 830 መሠረት መጀመሪያ ሟች ሲሞት በህይወት መኖር አለበት፡፡ እናቱ ሣትወርስ ከሞተች ደግሞ ተከሣሽ እናቱ የሌላትን መብት ስለማይወርስ ክስ የማቅረብ ስልጣን የለውም የሚል ነው፡፡ በእርግጥ ነው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 830 ላይ አንድ ሰው ለመውረስ ተወራሹ ሲሞት በህይወት መገኘት አለበት፡፡ ወደ ፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 842/3/ ስንመጣ ደግሞ አንድ የሟች ልጅ ሟችን ተክቶ መውረስ እንደሚችል ደንግጓል፡፡ እንደዚህ የሉ እርስ በርሣቸው የሚቃረኑ የሚመስሉ ትርጉም በምናስታርቅበት ጊዜ ደግሞ ሁለቱን ድንጋጌዎች ስራ ላይ እንዲውሉ እንደሆነ አድርጐ መተርጐም ያስፈልጋል፡፡
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 830 መሠረት ተወራሹ ሲሞት ወራሽ በህይወት ከሌለ መውረስ አይችልም ካልን የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 842/3/ ስራ የሌለው አንቀጽ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 842/3/ መተርጐም የሚገባው በአንደኛው ተከሣሽ አተረጓጐም ሳይሆን መጀመሪያ ሣይወርሱ የሞቱና እርሱ ደግሞ ወራሽ ልጆች ትተው ላለፉ ተወራሾች ነው፡፡ በዚህ አተረጓጐም መሠረት ከሣሽ እህቱን ተክቶ የአያቱን ንብረት የመውረስ መብት ስላለው ክስ ማቅረብ ይችላል፡፡ ሁለተኛዋ ተከሣሽና የሟች ወ/ሮ ሁለአገር ልጅ ይህንን አልካደችም ስለሆነም አንደኛው ተከሣሽ በዚህ ረገድ ያቀረበው መከራከሪያ ነጥብ የህግ ድጋፍ የለውም፣ በማለት ሌሎች ነጥቦችንም አንስቶ ውሣኔ ሰጥቷል፡፡



እዚህ ላይ የሚታየው ማችን ለመውረስ በህይወት መኖር አስፈላጊ ሲሆን ወደታች የሚቆጠር ተወላጆች ያሏቸው ሰዎች ሟች ሲሞት በህይወት ባይኖሩም ተወላጆቻቸው እነርሱን በመተካት በሟች ውርስ የሚካፈሉበት የውርስ ስርዓት በአገራችን ሕግ የተፈቀደ ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ያለን የውርስ ሰርዓት ሟች ኑዛዜ ከሌለው ውርሱ የእሱ የቅርብ የስጋ ዘመድ የሆነው እንዲያገኝ የሚፈቅድ ነው፡፡ ስለዚህ የሟች ውርስ ሲከፈት በህይወት መኖር ሟችን ለመውረስ አስፈላጊ መሆን በመርህ ደረጃ ቢቀመጥም በህይወት ቢኖር ኖሮ በሟች ውርስ የመካፈል እድል የነበረው ሰው ተወላጆች እሱን ተክተው በሟች ውርስ የሚካፈሉበት የውርስ ስርዓት በልዩ ሁኔታ አስቀምጧል፡፡ ይህንን መገንዘብና ሁሉንም የሕግ ድንጋጌዎች ተግባር ላይ ማዋል ልንከተለው የሚገባን የሕግ አተረጓጐም ዘዴ ነው፡፡

ከሟች ጋር የስጋ ዝምድና ሣይኖራቸው ወይም በጉድፈቻ ውል መሠረት ሕግ የሚያስቀምጠው አግባብ ሣይተሣሠሩ የስጋ ዝምድናንና ወራሽነትን አስመልክቶ በሚነሱ ክርክሮች ላይ የበለጠ ግንዛቤዎችን ለማዳበር ይረዳ ዘንድ የሚከተለውን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍትሐብሔር ይግባኝ መዝገብ ቁጥር 152/87 የካቲት 10 ቀን 1991 ዓ.ም የሰጠውን ፍርድ ማየቱ ጠቃሚነት ይኖረዋል፡፡
ክርክሩ የተነሣው ይግባኝ ባይ ወ/ሮ ጤና ገሠሠ እና መልስ ሰጭዎች ወ/ሮ ውጭት ገሠሠ አና ሙሉየ ገሠሠ መካከል ነው፡፡ ይግባኙ የቀረበው የሰሜን ጐንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 29 ቀን 1987 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ነው፡፡ የክርክሩ መነሻ የሟች የእማሆይ ስመኝሽ ወርቄ ወራሽነት ጥያቄ ነው፡፡ የአሁን ይግባኝ ባይ በጐንደር ወረዳ ፍርድ ቤት በስራ ፋይል መዝገብ ቁጥር 47181 እናቴ እማሆይ ስመኝሽ ወርቄ ነሐሴ 28 ቀን 1979ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች ስለሆነ ወራሽነቴ ይረጋገጥልኝ በማለት አቤቱታ አቅርባ የወረዳው ፍ/ቤት ተቃዋሚ እንዳለ እንዲቀርብ ጥሪ አድርጐ ተቃዋሚ ባለመቅረቡ አራት ምስክሮች አቅርባ አሰምታለች፡፡ የቀረቡት አራት ምስክሮች እማሆይ ስመኝሽ ወርቄ የጤና ገሠሠ እናት ናት በማለት ስለመሰከሩ ፍርድ ቤቱ ጤና ገሠሠ የሟች ስመኝሽ ወርቄ ወራሽ ናት በማለት ሕዳር 24 ቀን 1981 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል፡፡መልስ ሰጭዎች በበኩላቸው ሟች እማሆይ ስመኝሽ ወርቄ ያሣደገችው መሆኑን ገልፀው ነሐሴ 1 ቀን 1975 ዓ.ም ባደረገችው ግልጽ ኑዛዜ ከባሏ ከአቶ ካሣ ገሠሠ ጋር ያፈራችውን የጋራ ንብረት የእሷ ድርሻ እና የግል ንብረቷ ጠቅላላ ወራሽ እንድንሆን የሾመችን ስለሆነ የሟች የኑዛዜ ወራሾች መሆናችን ይረጋገጥልን በማለት በስራ ፋይል መዝገብ ቁጥር 321/84 አመልክተዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በማያያዝ እማሆይ ስመኝ ወርቄ በአምስት ምስክሮች ፊት ነሐሴ 1 ቀን 1975 ዓ.ም ያደረጉትን ኑዛዜ አቅርበዋል፡፡ የወረዳው ፍርድ ቤት ተቃዋሚ ካለ እንዲቀርብ በጋዜጣ ጥሪ አድርጓል በዚህ መሠረት የአሁን ይግባኝ ባይ በተቃዋሚነት ቀርባ የሟች እማሆይ ስመኝሽ ወርቄ ወራሽ እኔ መሆኔ በስራ ፋይል መዝገብ ቁጥር 47/81 በዚሁ ወረዳ ፍርድ ቤት ሕዳር 24 ቀን 1981 የተረጋገጠ በመሆኑ በሀሰት በተዘጋጀ ኑዛዜ ወራሽነታችን ይታወቅልን በማለት መዝገብ ማስከፈታቸው ተገቢ ስላልሆነ ይሻርልን በማለት ተቃውሞዋን አቅርባለች፡፡ መልስ ሰጭዎች በበኩላቸው ተቃዋሚዋ ከእማሆይ ስመኝሽ ወርቄ ጋር ምንም አይነት የደም ትስስር ሣይኖራት በሀሰት የሟች ልጅ ነኝ ብላ በማስመስከሯ ወራሽነቷን ማረጋገጧ አውቀናል፡፡ በመሆኑም እኛም ለመቃወም የሚያስችላት መብት የሌላት ከመሆኑም በላይ በሀሰት ምስክርነት የወሰደችውን የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ልትመልስ ይገባታል በማለት ተከራክረዋል፡፡ የግራ ቀኙን ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዳ ፍርድ ቤት መልስ ሰጭዎችን ይግባኝ ባይ ወራሽ ነኝ በማለት ስታመለክት የኑዛዜ ጽሑፍ ይዘው ቀርበው ስላልተቃወሙ ከዚህ በኊላ የሟች ወራሽ ነን ብለው መጠየቃቸው ተገቢ ስላልሆነ ጥያቄአቸውን አልተቀበልኩትም በማለት አሰናብቷቸዋል፡፡መልስ ሰጭዎች በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኊላ መልስ ሰጭዎች የሟች እማሆይ ስመኝሽ ወርቄ የኑዛዜ ወራሾች ናቸው፣ ይግባኝ ባይንም ቀደም ሲል የተሰጣትን የወራሽነት ማስረጃ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1000/1 በሚደነግገው መሠረት በሶስት ዓመት ውስጥ ቀርበው ስላልተቃወሙ ለይግባኝ ባይዋ የተሰጠው የወራሽነት ማስረጃ እንደፀና ይቆያል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል፡፡ ይግባኙ የቀረበው ይህንን ውሣኔ በመቃወም ነው፡፡ ይግባኝ ባይ ሟች እማሆይ ስመኝሽ ወርቄ ለመልስ ሰጭዎች ያደረጉት ኑዛዜ በውል አዋዋይ መስሪያ ቤት ፊት ስላልተፈፀመ የወራሽነት ጥያቄው የይርጋ ጊዜ ገደብ ካለፈ በኊላ የቀረበ በመሆኑና መልስ ሰጭዎች የሕግ ምስክሮች አቅርበው ስለአስመሰከሩ አላግባብ የወራሽነት ማስረጃው በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተሰጣቸው ስለሆነ እንዲሻርልኝ በማለት አመልክታለች፡፡መልስ ሰጭዎች በበኩላቸው ይግባኝ ባይ የእማሆይ ስመኝ ወርቄ ልጅ አይደለችም የሀሰት ምስክርነት አቅርባ የወራሽነት ማስረጃ መውሰዷ ሣያንሣት እኛን ለመቃወም የሚያስችላት ሕጋዊ መብት የላትም፡፡ የይግባኝ ባይ ወላጅ እናት እማሆይ አዋጉ ተዋበ በሕይወት ይኖራሉ እኛ የሟች የኑዛዜ ወራሾች ነን፡፡ ስለዚህ የይግባኝ ባይን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ እንዲያሰናብተን በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡ ይግባኝ ባይ መልስ አቅርባለች ይዘቱ ከይግባኙ ቅሬታው ጋር ተመሣሣይ በመሆኑ አልገለበጥነውም፡፡ በስርና በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ከላይ የተለገፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል መዝገቡን እንደመረመርነው /1/ ይግባኝ ባይ የመልስ ሰጭወችን የኑዛዜ ወራሽነት ለመቃወም የማያስችላት ሕጋዊ መብት አላት ወይስ የላትም? /2/ መልስ ሰጭዎች የሟች ጠቅላላ የኑዛዜ ወራሾች ናቸው መባሉ ሕጋዊ ነው ወይስ አይደለም? የሚሉትን ነጥቦች ማየቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ ይግባኝ ባይ በዚህ መዝገብ ሁለት የወረዳ ፍርድ ቤት ውሣኔ በማስረጃነት አያይዛለች፡፡ የመጀመሪያው የወረዳው ፍርድ ቤት በስራ ፋይል መዝገብ ቁጥር 253/75 በአቶ ገሠሠ ካሣ ውርስ ግንቦት 2 ቀን 1975 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ነው፡፡ ይህ ውሣኔ እማሆይ ስመኝ ወርቄ የሟች ገሠሠ ካሣ ሚስት መሆናቸውን ይግባኝ ባይዋ ደግሞ አቶ ገሠሠ ካሣ እማሆይ ስመኝ ወርቄ ሣይሆን ከሌላ ሴት ይግባኝ ባይዋ ጤና ገሠሠ የተወለደች ልጃቸው መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በዚህ ውሣኔ በግልጽ እንደተመለከተው ይግባኝ ባይ የሟች እማሆይ ስመኝ ወርቄ የስጋ ልጅ አይደለችም፡፡ሁለተኛው ይኸው የጐንደር ወረዳ ፍርድ ቤት በስራ ፋይል መዝገብ ቁጥር 47/81 የአራት ምስክሮችን ቃል ከሰማ በኊላ ይግባኝ ባይዋ ጤና ገሠሠ የእማሆይ ስመኝ ወርቄ ልጅና ወራሽ ናት በማለት የሰጠው ውሣኔ ነው፡፡ይህ ውሣኔ የተሰጠው በሁለት የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡ ምስክሮችን ቃል መሠረት በማድረግና ይግባኝ ባይ 1975 ዓ.ም በወረዳው ፍርድ ቤት የአባቷን ወራሽነት ለማረጋገጥ ያቀረበችውን ማስረጃ ባለመገናዘብ ነው፡፡ በአጠቃላይ የይግባኝ ባይ ወላጅ እናት እማሆይ ስመኝ ወርቄ እንደሆኑ ከመሞታቸው በፊት 1975ዓ.ም ይግባኝ ባይ እና ሟች ስመኝ ወርቄ በአንድ ላይ ባስከፈቱት መዝገብ ተረጋግጧል፡፡ ስለዚህ ይግባኝ ባይ ከሟች እማሆይ ስመኝ ወርቄን ያለኑዛዜ የምትወርስበት የስጋ ዝምድናና የደም ትስስር የላትም ይግባኝ ባይ የሟች ልጅ ሣትሆን ልጅ ነኝ በማለት በወራሽነት መቅረቧ ተገቢ ባለመሆኑ የመልስ ሰጭዎችን የኑዛዜ ወራሽነት በመቃወም ክርክር የምታቀርብበት ሕጋዊ ምክንያት የላትም፡፡በመሆኑም መልስ ሰጭዎች የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን በመቃወም ይግባኝ ስላላቀረቡ ወይም የይግባኝ ባይ ይግባኝ እንደደረሣቸው የሥነ ሥርዓት ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት መስቀለኛ ይግባኝ ባለመቅረባቸው ይግባኝ ባይ የሟች እማሆይ ስመኝ ወርቄ ወራሽናት በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማሸር ወይም ለማሻሻል የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ስለማይፈቅዱ እንዳለ የተውነው ሲሆን ይግባኝ ባይዋ ሟችን ለመውረስ የሚያስችላት ሕጋዊ ሁኔታ ሳይኖር የሟችን የኑዛዜ ወራሾች ተቃዋሚ ሆኖ መቅረቧና በይግባኝ መከራከሯ ተገቢ ሆና አላገኘነውም፡፡ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ መልስ ሰጭዎች የሟች እማሆይ ስመኝ ወርቄ ጠቅላላ የኑዛዜ ወራሽ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሟች በግልጽ ያደረገችው ኑዛዜ በማስረጃነት ቀርቧል፡፡ የኑዛዜው ጽሁፍ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 881 የተመለከቱትን ፎርማሊቲዎች የሚያሟላና የሟች ትክክለኛ ቃል መሆኑን የማያሣይ በመሆኑ የከፍተኛው ፍርድ ቤት መልስ ሰጭዎች የሟች ጠቅላላ የኑዛዜ ወራሾች ናቸው በማለት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ከዚህ በማስከተል የሚነሣው ጥያቄ ይግባኝ ባይ የሟች ልጅ ነኝ በማለት የተሰጣትን የወራሽነት የምስክርነት ወረቀት መልስ ሰጭዎች ባለመቃወማቸው ይግባኝ ባይ የሟች የሕግ ወራሽ ሆናለች፡፡ በሌላ በኩል መልስ ሰጭዎች የሟች የኑዛዜ ወራሾች ናቸው ተብሏል፡፡ ስለዚህ ይግባኝ ባይና መልስ ሰጭዎች በሟች ውርስ ላይ ያላቸው መብት እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ይህንን ነጥብ አግባብነት ካለው የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ ስንመለከተው የሟች ውርስ በከፊል በኑዛዜና በከፊል ያለኑዛዜ ሊፈፀም እንደሚችል የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 829/2/ ያመለክታል፡፡ በዚህ የሕግ ድንጋጌ መሠረት ይግባኝ ባይ የሟች ያለኑዛዜ ወራሽ ስትሆን መልስ ሰጭዎች ደግሞ የኑዛዜ ወራሾች ናቸው፡፡ ሟች መልስ ሰጭዎችን ጠቅላላ የኑዛዜ ወራሽ በማድረግ የሾማቸው በመሆኑ ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ ተቀባይ ያገኘ ሰው ያለኑዛዜ ወራሽ እንደሆነ እንደሚቆጠር በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 915/1የተደነገገ በመሆኑ ከላይ በጠቀስናቸው የሕግ ድንጋጌዎች መሠረት የሟች እማሆይ ስመኝ ወርቄ ንብረት፣ ይግባኝ ባይዋ ወ/ሮ ጤና ገሠሠ አንደኛ መልስ ሰጭ ወ/ሮ ሙጭት ገሠሠ ሁለተኛ መልስ ሰጭ ተማሪ ሙሉየ ገሠሠ በወራሽነታቸው ቀርበው እኩል መካፈል ይገባቸዋል በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348/1/ መሠረት አጽንተነዋል በማለት ወስኗል፡፡

ከውሣኔው እንደምንረዳው ከሟች ጋር ምንም አይነት የስጋ ዝምድና ወይም የጉድፈቻ ውል መሠረት ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች የሟች ያለ ኑዛዜ ወራሽ ነኝ በማለት በሚቀርቡበት ሁኔታ መኖሩን ሲሆን በሌላ በኩል አንድ ተከራካሪን አስመልክቶ ጉዳዩን በስር ያየው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ከሥነ ሥርዓት ሕጉ መሠረት ይግባኝ ወይም መስቀለኛ ይግባኝ ካልቀረበበት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ ስህተት ቢኖርበትም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በራሱ አነሣሽነት የማይሽረው መሆኑን ነው፡፡

በአጠቃላይ የሟች ውርስ አስመልክቶ ከሚነሡት በርካታ አለመግባባቶች የሟች ያለ ኑዛዜ ወራሽ ነኝ በሚሉ ነጥቦች ዙሪያ የሚደረግ በመሆኑ የሕጉን ድንጋጌዎች ዓላማና ይዘት በአግባቡ መረዳትና ሥራ ላይ ማዋል ያስፈልጋል፡፡

04/07/2021

የውርስ ጉዳይን የተመለከቱ የይርጋ ገደቦች ከተመረጡ የሰበር ውሳኔዎች ጋር በማጠቃስ የቀረበ!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹1
በማድረግ መረጃዋችን ለሌሎች ያድርሱ ።

ኑዛዜን ለመቃወም የተቀመጠ ጊዜ ገደብ
///////
ኑዛዜ ፈራሽ ነው የሚል ክስ የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በቁጥር 973 ላይ የተመለከተው ተፈጻሚ ሚሆነው ኑዛዜ ፈራሽ ነው የሚለውን ክስ ኑዛዜው ሲነገር በነበሩ ሰዎች የቀረበ እንደሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973/1/ ላይ እንደተገለጸው “ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ወይም የተወከሉ ሰዎች ኑዛዜው አይጸናም ወይም አንዱ በኑዛዜው የተነገረው ቃል አይጸናም በማለት ክስ ለማቅረብ ያላቸውን ሀሳብ መግለጫ ወይም ስለ ክፍያው በሂሳብ አጣሪው የቀረበውን የድልድል አመዳደብ ሀሳብ ለመቃወም ኑዛዜው ከተነበበት አንስቶ በሚቆጠር የአስራ አምስት ቀን ጊዜ አላቸው”፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ ኑዛዜው ሲነበብ ያልነበሩ ሰዎች መቃወሚያቸውን መቼ ሊቀርቡ ይችላሉ ለሚለው በፍ/ሕ/ቁ 974/1/ እና 2 ላይ የተገለጸ ሲሆን በዚህም መሰረት “ በኑዛዜ ንባብ ሥነ-ሥርዓት ላልነበሩ ወይም በኑዛዜው ንባብ ሥነ-ሥርዓት በወኪልነት ላልሰሙ ሰዎች እንዲሁም ኑዛዜው በሌሉበት የተነበበ እንደሆነ ከዚህ በላይ የተገለጸው የጊዜ ገደብ ለመቁጠር መነሻ የሚሆነው ሥለ ክፍያው ድልድልና አመዳደብ ሀሳቡን ከተነገራቸው ቀን አንስቶ ነው”፡፡
በፍ/በ/ህ/ቁ 973/2/ ላይ በተገለጸው መሰረት ኑዛዜ ከፈሰሰበት ጊዜ ከአምስት ዓመት በኋላ ወይም ኑዛዜ የሌለ እንደሆነ ሟች ከሞተ ከአምስት ዓመት በኋላ ስለ ኑዛዜው መጽናትና ስለክፍያው አመዳደብ አጣሪው ያቀረበውን የድልድል ሀሳብ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን መቃወሚያ ሊቀርብበት አይችልም፡፡
ከዚህ በላይ ከተገለጹት የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በተያያዘ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 82585 በቅጽ 15 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ የሰጠ ሲሆን በትርጓሜውም “በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ድንጋጌዎች አቤቱታ አቅርቢው ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ ወይም የተወከለ የመሆን አለመሆን መስፈርት መሰረት በማድረግ ይርጋው መቁጠር የሚጀምርበትን ጊዜ እና ፍጹም የሆነ የይርጋ ጊዜ በቁጥር 974/2/ ከመደንገጋቸው በስተቀር ሁለቱም ድንጋጌዎች ኑዛዜው ፈራሽ ነው የሚል ክስ የሚቀርብበትን ስርዓት የሚደነግጉ በመሆቸው ተያያዥነት አላቸው በማለት ኑዛዜ መኖሩን ማወቅ እና የኑዛዜውን ሙሉ ይዘት ማወቅ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው ሲል በፍ/ብ/ህ/ቁ 973/1/ የተመለከተው የ15 ቀን ጊዜ ገደብ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ ሳይሆን የመግለጫ ማቅረቢያ ጊዜ ነው፡፡ በመሆኑም ስለ ኑዛዜ መኖር እንጂ ስለድልድሉ የማያውቅ ወራሽ መግለጫ የማቅረብ ግዴታ ስለማይኖርበት ጊዜው መቁጠር የሚጀምረው በኑዛዜው የተደረገውን ድልድል ካወቁበት ቀን ጀምሮ ነው” በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
በሟች የተደረገ ኑዛዜ ከውርስ የነቀለኝ በመሆኑ ሊፍርስ ይገባል በማለት ኑዛዜው ሲነበብ በነበረ አመልካች የሚቀርብ የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 መሰረት በተገለጠው የጊዜ ገደብ ነው ወይስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ነው? የሚለው አከራካሪ ጉዳይ በመሆኑ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 152134 በቅጽ 23 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ በውሳኔውም መሰረት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 ስለ ኑዛዜ መነበብ እንዲሁም ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ሰዎች ኑዛዜው እንዲፈርስ አቤቱታ የሚያቀርቡበትን ሥርዓትና ጊዜውን በሚመለከት የሚደነግግ ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል /ነቅሎናል/ በማለት ኑዛዜው እንዲፈርስ የሚቀርብን ወይም የቀረበ አቤቱታን የሚመለከት አይይለም፡፡ በመሆኑም ኑዛዜው ከውርስ የመንቀል ውጤት ያለው በመሆኑ እንዲፈርስ በሚል የሚቀርብ የዳኝነት ጥያቄ ሊታይ የሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት ነውእንጂ በአንቀጽ 973 መሰረት አይደለም በማለት አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የሕግ ትርጓሜ መሰረት ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ አመልካች ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል በማለት የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ህ/ቁ 973 መሰረት ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ አንድ ኑዛዜ ፈራሽ ነው በሚል ስለሚቀርብ መግለጫ እና እንዲሁም መግለጫው እና ክሱ ሊቀርብ ስለሚገባው የጊዜ ገደብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 ተፈጻሚነት የሚኖረው ኑዛዜ ሲነበብ በነበሩ ወይም በተወከሉ ሰዎች ጉዳይ ሲሆን በአንቀጽ 974 ድንጋጌ ደግሞ ተፈጻሚነቱ በኑዛዜ ሥነ-ሥርዓት ባልነበሩ ወይም ባልተወከሉ ሰዎች ጉዳይ ነው፡፡ ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ አመልካች ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል በማለት የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ህ/ቁ 973 መሰረት ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት ነው፡፡
//////
የወራሽነት ጥያቄ ለማቅረብ የተቀመጠ ጊዜ ገደብ🇪🇹
///////
የወራሽነት ጥያቄን ለማቅረብ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የሚመለከቱ የሕግ ድንጋጌዎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000 ላይ የተመለከተ ሲሆን ወደዚህ ነጥብ ከመግባቴ በፊት ወራሽነት ጥያቄ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን እደሚከተለው ለመዳሰስ እሞክራለሁ÷
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 996(1) ላይ በተገለጸው መሰረት ወራሽ የሆነ ሰው የሟቹ ወራሽ መሆኑንና ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ የሚያመለክት የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል በማለት የተገለጸ ሲሆን ይህ ማለት ፍ/ቤቱ የወራሽነት ምስክር እንዲሰጠው ወራሹ ሲፈልግ የሚጠይቀው እንጂ ሟችን ለመውረስ የግድ ከፍ/ቤቱ የወራሽነት ማስረጃ ማምጣት እንዳለበት የሚያስገድድ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በተግባር እንደሚስተዋለው ስመ ንብረቱ ለማዛወር እና ከሌሎች የሟች መብቶች ለመጠቀምና ለመስራት በፍ/ቤቱ የተረጋገጠ የወራሽነት የምስክር ወረቀት መጠየቁ የተለመደ አሰራር ሆኗል፡፡
ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን መሰረት በማድረግ አንድ ሰው ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው ውርሱን ወይም ከውርሱ አንዱን ክፍል በእጁ ያደረገ እንደሆነ እውነተኛው ወራሽ ወራሽነቱን እንዲታወቅለትና የተወሰዱበት የውርስ ንብረቶች እንዲመለሱለት በዚህ ሰው ላይ የወራሽነት ጥያቄ ክስ ሊያቀብበት ይችላል በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 999 ላይ ተደንግጓል፡፡ ስለዚህ ይህን መሰል የክስ አቤቱታ አቤቱታ መቼ ሊቀርብ ይገናል ለሚለው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ ላይ የጊዜ ገደብ ተቀምጧል፡፡
በዚሁ መሰረት ከሳሽ መብቱንና የውርሱን ንብረት በተከሳሽ መያዛቸውን ካወቅ ሶስት ዓመት ካለፈ በኋላ ስለ ወራሽነት ጥያቄ የሚቀርበው ክስ ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም፡፡ በሌላ መልኩ በአንቀጽ 1000(2) ላይ እንደተገለጸው “ሟቹ ከሞተበት ወይም ከሳሹ በመብቱ ለመስራት ከቻለበት ቀን አንስቶ አስራ አምስት አመት ካለፈ በኋላ ከዘር የወረደ ርስት ካልሆነ በቀር የውርስ ጥያቄ ክስ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን ተቀባይነት አያገኝም የሚለው ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ከዚህ በላይ በአንቀጽ 1000(1) እና (2) ላይ የተመለከቱት የጊዜ ገደቦች ከሌሎች የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች በተለይም 1ኛ) አንድ ወራሽ የሟች ኑዛዜ ተጠቃሚ መሆን የሚችለው ኑዛዜ በእጁ እንደሚገኝ ለውርስ አጣሪው አቅርቦ ውርስ አጣሪው ኑዛዜውን በሚነበብበት ሰዓት ራሱ ወይም ወኪሉ ካልነበረ ወራሹ ኑዛዜው ከፈሰሰበት ቀን አንስቶ በአስራ አምስት አመታት ውስጥ መቃወሚያ ካላቀረበ ከዚያ በኋላ ሊቀርብ እንደማይችል በፍ/ሕ/ቁ 974(2) የተመለከተው በፍ/ሕ/ቁ 1000(1) ካለው የጊዜ ገደብ ጋር እንዴት ተጣጥሞ ተግባራዊ ይሆናሉ ከሚለው ጋር ጥያቄ የሚያስነሳ ሲሆን በሌላ መልኩ በፍ/ሕ/ቁ 1000(1) እና (2) አተረጓጎምና አፈጻጸም እንዴት መሆን አለበት በሚል አልፎ አልፎ ጥያቄ ሲያስነሳ ይስተዋላል፡፡ ስለዚህ በእነዚህ የሕግ ማዕቀፎች ላይ የተጠቀሱት የጊዜ ገደቦች በተመለከተ መከተል የሚገባንን የሕግ ትርጓሜ እንደሚከተው ለማብራራት ተሞክሯል÷ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 974/2/ ተፈጻሚ የሚሆነው የሟች ውርስ የሚያጣራ ፤በሕግ በኑዛዜ ወይም በፍርድ ቤት የተሾመ የውርስ አጣሪ ፤ሟች አድርጎታል የተባለው ኑዛዜ አግኝቶ የኑዛዜውን ፎርምን የኑዛዜውን ዋጋ መኖር ፤የሟች ያለኑዛዜ ወራሾች ወይም አራት አካለመጠን ያደረሱ ሰዎች ባሉበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 968 በተመረመረበት ሁኔታ ነው፡፡ ሆኖም ግን ኑዛዜ ያለ መሆኑን ለውርስ አጣሪው ሳያሳውቅ ቀጥታ የኑዛዜ ወራሽ መሆኑ እንዲታወቅለት ለፍ/ቤት አመልክቶ የወራሽነት የምስክር ወረቀት በመውሰድ የሟች ንብረት በእጁ ያደረገ ሰው ወይም በሀሰት የሟች ያለኑዛዜ ወራሽ ነኝ ብሎ የሟችን ንብረት ከወሰደው ሰው ለማስመለስ አግባብ የሆነው የይርጋ ገደብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 968 የተጠቀሰው ሳይሆን በፍብ/ሕ/ቁ 1000/1/ የተመለከተው ተፈጻሚነት ሊኖረው ይገባል፡፡
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ እና 1000/2/ አስመልክቶ የተለያዩ አተረጓገሞች የሚስተዋሉ ሲሆን ለዚህ ጽሁፍ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 30158 ፤26422 እና 34011 በቅጽ 7/6/6/ እንዲሁም በቅጽ 11 በሰ/መ/ቁ 52407 የሰጠውን አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ለመዳሰስ ሞክሬያለው፡፡ በዚሁ አግባብ በፍ/ሕ/ቁ 1000/2/ ላይ ሟች ከሞተ አስራ አምስት አመት በላይ ወይም ተከሳሹ በመብቱ ሊሰራበት ከቻለበት ቀን አንስቶ አስራ አምስት ዓመት ውስጥ ክስ ካልቀረበ አስራ አምስት ዓመት ካለፈው በኋላ ክስ ሊያቀርብ የሚቻለው ከዘር የወረደ ርስት በሆነ ንብረት ላይ ነው፡፡
ርስት የሚለው ቃል በፍ/ሕ/ቁ 1130 እና ስለ ንብረቶች በሚናገረው የፍ/ብሔር የህጉ ክፍል መሬት የሚያመለክት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በኢትዮጲያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል የተዘጋጀው የአማርኛ መዝገበ ቃላት ርዕስት የሚለው መሬትን የሚመለከት መሆኑን ጠቅሶ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ በዚሁ አግባብ ከዘር የወረደ ርዕስት የሚለው ቤትን አያጠቃልልም የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ በርዕስት የሚተላለፍ መሬት ብቻ ማለት ሰለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/2/ መሰረት ለተወላጆች የሚተላለፍ መሬት ብቻ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
በኢፌድሪ ህገ መንግስት መሰረት መሬት የመንግስትና የህዝብ ሀብት በመሆኑ ከዘር የወረደ ርዕስት ካልሆነ በስተቀር በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/2/ ላይ የተገለጸው የተሻረ እና ተፈጻሚነት የሌለው ነው በማለት አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ አፈጻጸምን በተመለከተ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 32407 በቅጽ 11 ላይ ትርጓሜ የሰጠ ሲሆን በዚህም መሰረት በወራሾች መካከል የሚነሳ የውርስ ንብረት ክርክር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ በተደነገገው አግባብ በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ሲሆን ወራሽ በሆነ እና ወራሽ ባልሆነ ተከራካሪ ወገን መካከል የሚቀርበው የውርስ ንብረት ይገባኛል ጥያቄ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1677 እና 1845 መሰረት በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ መብቱ በይርጋ የሚታገድ ይሆናል፡፡
//////
የክፍፍል ጥያቄ በይርጋ የማይታገድ ስለመሆኑ
/////🇪🇹
ወራሾች ተለይተው የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየ የውርስ ሀብት ያለ እንደሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1062 በተገለጸው መሰረት እያንዳንዱ የጋራ ወራሾች ውርሱን እንከፋፈል በማለት በማንኛውም ጊዜ ለመጠየቅ የሚችሉ በመሆኑ የክፍፍል ጥያቄ በይርጋ የማይታገድ ይሆናል፡፡
//////
መደምደሚያ
///////
በአጠቃላይ አንድ ሰው ከዚህ አለም በሞት የተለየ እንደሆነ የውርስ ጉዳዩን በተመለከተ ወራሽ የሆነ ወገን ኑዛዜን ሚቃወምበት፤የወራሽነት ጥያቄ ሚያቀርብበትና ክፍፍል የሚጠይቅባቸው የጊዜ ገደቦች ከዚህ በላይ በተገለጸው አግባብ ተፈጻሚ ሚሆኑ ሲሆን ባለመብት የሆነ ወገን ጥያቄውን በህጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያላቀረበ እንደሆነ ውጤቱ መብቱን እስከማጣት የሚደረስ ይሆናል፡፡

በተጨማሪ
ወራሽነትን ማሳወጅ
ውርስ ይጣራልኝ አቤቱታ ማቅረብ
ውርስ አጣሪ ማሾም
የውርስ ድርሻ ከፍፍል ህጉ ያስቀመጣቸው ሂደቶች እንደሆኑ መዘንጋት የለበትም
source Abyssinialaw.com

02/07/2021

ስለ ንብረት የዋጋ ግምት ጥቂት ነጥቦች
====================
ለፍርድ ቤቶች በሚቀርቡ ክርክሮች ላይ የንብረትን ትክክለኛ የዋጋ ግምት ማወቅ የግድ አስፈላጊ የሚሆንባቸው ጊዜያቶች አሉ፡፡ ለመሆኑ የንብረት የዋጋ ግምት ማወቅ ለምን ያስፈልጋል? የንብረት የዋጋ ግምት ተገምቶ እንዲቀርብ የሚጠይቁ ሕጎች የትኞቹ ናቸው? የንብረት የዋጋ ግምት የመገመት ኃላፊነት በሕግ የተሰጠው ለማን ነው? በአሠራር ደረጃ የንብረት የዋጋ ግምት በማን እና እንዴት እየተገመተ ይገኛል? የንብረት ዋጋ ግምትን አስመልክቶ የሚታዩ ችግሮች ምንድን ናቸው? የንብረት የዋጋ ግምት ሲሰራ በመሠረታዊነት ሊካተቱ የሚገባቸው ነጥቦችስ ምንድን ናቸው? የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦች በዚህ ፅሁፍ በጥቂቱ እንዳስሳለን፡፡

የንብረት የዋጋ ግምት ማወቅ ለምን ይጠቅማል?
የንብረት የዋጋ ግምት ማወቅ የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት፡፡ እነዚህም፡ -

ፍትሐዊና ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት እንዲቻል፤
የፍርድ ቤቶችን የዳኝነት ሥልጣን ለመወሰን እንዲቻል፤
ለፍርድ ቤቶች ተገቢውን የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለማከፈል፤
ጥፋተኛ ተብለው በወንጀል የሚፈረድባቸው ሠዎች ላይ ተመጣጣኝና የተገኘውን ልተገባ የጥቅም መጠን ወይም የደረሰውን የጉዳት መጠን መሠረት ያደረገ ቅጣት ለመወሰን ነው፡፡

ተከራካሪ ወገኖች የንብረት ዋጋ ግምት መጠን እንዲጠቅሱ የሚጠይቁ ሕጎች የትኞቹ ናቸው?

ክስ የሚቀርበው አንድን ንብረት ለማስለቀቅ ወይም ከአንድ ንብረት ላይ ድርሻ ለመጠየቅ በሆነ ጊዜ ክስ የቀረበበትን ንብረት ወይም የንብረቱን ወይም ከንብረቱ ላይ የሚገኘውን የድርሻ የዋጋ ግምት በክስ አቤቱታ ላይ ሊጠቀስ እንደሚገባ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀፅ 222 /1/ /ቀ/ እና 226 /3/ /4/ ላይ ይጠይቃል፤
የፌደራል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም በወጣው በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 11 /1/ እና 14 መሠረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዋጋ ግምታቸው ከብር 500,000.00/አምስት መቶ ሺሕ/ በላይ የሆኑ የፍትሐብሔር ጉዳዮችን እንዲሁም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዋጋ ግምታቸው ከብር 500,000.00/አምስት መቶ ሺሕ/ በታች የሆኑ የፍትሐብሔር ጉዳዮችን አከራክረው የመወሰን ሥልጣን ተሠጥቷቸዋል፡፡ ተከራካሪ ወገኖችም የሚያቀርቡትን የገንዘብ ወይም የንብረት ክርክር የዋጋ ግምት በክሳቸው ላይ መግለፃቸው የፍርድ ቤቶችን የዳኝነት ሥልጣን የሚወስን በመሆኑ በአዋጁና በሥነ ሥርዓት ሕጉ መሠረት በዳኝነት የሚጠይቁትን የገንዘብ መጠን ወይም የንብረት የዋጋ ግምት የመጥቀስ ግዴታ ተጥሏል፤

ስለ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ገንዘብ አከፋፈል በወጣው የ1945 ዓ.ም. አስራ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር 15 የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 177 መሠረት ከሳሽ የሆነ ወገን ዳኝነት በሚጠይቅበት ገንዘብ መጠን ልክ ለፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ሊከፍል እንደሚገባና ተመኑም ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም አንድን ንብረት አስመልክቶ የፍትሐብሔር ክስ የሚያቀረብ ሠው ለፍርድ ቤቶች የዳኝነት የአገልገሎት ክፍያ አከፋፈል እንዲያመች የንብረቱን የዋጋ ግምት በክስ አቤቱታው ላይ የመግለፅ ግዴታ አለበት፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባወጣው የተሻሻለው የቅጣት አወሳስን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሠረት በፍርድ ጥፋተኛ በተባሉ ሠዎች ላይ ቅጣትን ለመጣል በወንጀል ድርጊት የተገኘውን የንብረት ጥቅም ግምት ወይም የደረሰውን የንብረት ጉዳት ግምት ማወቅ አስፈላጊ ከመሆኑም ባለፈ የተጠቀሰው ሕግ የንብረት የዋጋ ግምት መጠን ላይ ክርክር ከተነሳበት የዋጋ ግምቱ ተለይቶ እንዲጠቀስና እንዲቀርብ ይጠይቃሉ፡፡
በሕጉ መሠረት የንብረት የዋጋ ግምት ላይ ክርክር ከቀረበ ግምቱን የሚገምተው ማን ነው? የግምት ሥራውስ እንዴትና በምን መመዘኛ ይሰራል?
በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 250 መሠረት ከተከራካሪ ወገኖች መካከል አንደኛው የሚያቀርበውን የዋጋ ግምት ሌላኛው ተከራካሪ ወገን በዋጋ ግምቱ ባለመስማማት ሊቃወም እንደሚችልና የግምት ክርክር ከተነሳ ደግሞ ፍርድ ቤቶች የሀብቱን ወይም የንብረቱን የዋጋ ግምት በመገመት ለፍርድ ቤቱ እንዲያሳውቁ ምትክ ዳኞችን በመሾም ሊያስገምቱ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡

በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ላይ የንብረት ዋጋ ግምት እንዲገምቱ የሚሾሙ ምትክ ዳኞችም የንብረት ዋጋ ግምቱን ምንን መሠረት በማድረግና እንዴት እንደሚከናወኑ የሚያመለክተው ነገር ባይኖርም ምትክ ዳኞቹ የግምት ሥራ ሲሰሩ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 132 እስከ 135 በተመለከቱ ቅድመ ሁኔታዎችና የአሠራር ሥርዓት መሠረት የዋጋ ግምቱን ገምተው ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በወንጀል ጉዳዮች ላይም ንብረትን አስመልክቶ ዐቃቤ ሕግ የክስ ማመልከቻ ላይ የሚጠቀሱ የንብረት የዋጋ ግምቶችን በተመለከተ ከተከራካሪ ወገን የዋጋ ግምት ተቃውሞና መከራከሪያ ከቀረበ ግምቱን ማን ይገምተዋል? እንዲሁም ግምቱ እንዴት ይሰራል የሚለውን የወንጀል ሕጉ፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉና ተሻሽሎ የወጣው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ የሚሉት ነገር የለም፡፡

በተግባርስ የንብረት የዋጋ ግምት ላይ መከራከሪያ ሲቀርብ ግምቱን የሚሰራው ማን ነው?

በፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ በሚያጋጥሙ የንብረት ዋጋ ግምት ክርክሮች ፍርድ ቤቶች ጥቂት በሚባሉ ጉዳዮቸ ላይ ሊባል በሚችል መልኩ ምትክ ዳኞችን በመሾም የንብረት የዋጋ ግምት ገምተው እንዲያቀርቡ ይደረጋል፤

በበርካታ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ የቤት ወይም የሕንፃ የዋጋ ግምት አከራካሪ በሚሆንበት ጊዜ በፍ/ቤቶች ግምቱ እንዲሰራ የሚደረገው በመሬት አስተዳደር መስሪያ ቤት እና ፍቃድ ያላቸውን የንብረትና ጉዳት ገማች ተቋማትና ግለሰቦችን በፍ/ቤት ሬጂስትራር ፅ/ቤት ጠቋሚነት በመምረጥና በማስገመት ነው፤

ያከራከረው ንብረት ተሸከርካሪ በሚሆንበት ጊዜም የንብረት ዋጋ ግምቱ በመንገድ ትራንስፖርት ፅ/ቤት እና ፍቃድ ባላቸው የግል ተቋማት በኩል ሲገመት ይስተዋላል፤

ያከራከረውን ንብረት ዓይነት መሠረት በማድረግ ያከራከረውን ንብረት ከማስተዳደርና ከማወቅ አንፃር የተሻለ ቅርበት አለው ለሚባል የመንግስት ወይም የግል ተቋም የንብረት የዋጋ ግምት ገምቶ እንዲያቀርብ ሲደርግ ይታያል፤

በተወሠኑ ጉዳዮች ላይም ግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች በስምምነት በሚመርጡት የንብረት ገማች ተቋም ወይም ግለሰብ በኩል የንብረት ዋጋ ግምት ተገምቶ እንዲቀርብ ይደረጋል፤
በሌሎች ጉዳዮች ላይም በከሳሽ ወገን የሚመረጥ አንድ የንብረት ዋጋ ገማች፣ በተከሳሽ ወገን የሚመረጥ አንድ የንብረት ዋጋ ገማች እና በፍርድ ቤት የሚመረጥ አንድ የንብረት ዋጋ ገማች በድምሩ ሶስት የንብረት ዋጋ ገማቾች ተመርጠው ከሶስቱ የንብረት ዋጋ ግምቶች መካከል አማካዩ የዋጋ ግምት የሚወሰድበት አሠራርም ይታያል፡፡

ስንት ዓይነት የቤት ወይም ሕንፃ የዋጋ ግምቶች አሉ?

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 35003 ቅፅ 19 እንደታተመው በዋናነት የቤት ወይም ሕንፃ ዋጋ ግምት ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ይኸውም ንብረት ወይም ቤት ሁለት ዓይነት የዋጋ ግምት እንዳለው እነዚህም የግንባታ ዋጋ /Book Value/ እና የገበያ ዋጋ /Market Value/ እንደሆኑ አመልክቷል፡፡

የግንባታ ዋጋ /Book Value/

በተለምዶ የቤት የግንባታ ዋጋ /Book Value/ የሚታወቀው ቤቱን ለመስራት ለተለያዩ ቁሳቁሶች የወጣውን የቤቱን ወይም የሕንፃውን ወጪና ቤቱ ወይም ሕንፃው የተሰራበትን ይዞታ ለማግኘት የወጣውን ወጪ ታሳቢ በማድረግ የሚገመት የቤት ዋጋ ግምት ዓይነት ነው፡፡

ይህ የቤት ዋጋ ግምት የሚገለፀው ቤቱን ለመገንባት የወጡ ወጪዎችን በመደመር ሲሆን የግንባታ ወጪው የሚሰላው ቤቱ ሲገነባ በነበረበት ጊዜ ባለው ዋጋ ነው ወይስ ክስ ወይም ክርክር በሚደረግበት ጊዜ ያለውን የቁሳቁስ ዋጋ ታሳቢ በማድረግ ነው? የሚለውም ከግንባታ ዋጋ ግምት ጋር ተያይዞ የሚነሳ አከራካሪ ነጥብ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት አስተዳደር ተቋም በኩል ለፍርድ ቤቶች የሚቀርበው የቤት ዋጋ ግምትም በ1988 ዓ.ም. በኮምፒውተር የመረጃ ቋት የተመዘገበ የቁሳቁስና ተያያዥ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ የሚያቀርቡት ዋጋ የግንባታ ዋጋ ነው፡፡

የገበያ ዋጋ /Market Value/

የገበያ ዋጋ ቤት ከሚገኝበት አከባቢ፣ የተሰራበት ቁሳቁስ፣ ስፋትና አጠቃላይ ሁኔታዎችና ሌሎች የንብረት ግምት መሠረታዊ መመዘኛዎች አንፃር ወቅታዊ በሆነ ሁኔታ ቤቱ ለሽያጭ ቢቀርብ ሊያወጣ የሚችለውን የዋጋ ግምት መሠረት ያደረገ የዋጋ ግምት ዓይነት ነው፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በቅፅ 19 የሰ/መ/ቁ 35003 ለይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ግምትን አስመልክቶ ክርክር በሚነሳባቸው ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶት ሊያዝ የሚገባው ቤት ወይም የንብረት ገበያ ዋጋ /Market Value/ እንጂ የግንባታ ዋጋ /Book Value/ ሊሆን እንደማይገባ አመልክቷል፡፡

የንብረት የዋጋ ግምት ሲሰራ ከግምት ሊገቡ የሚገባቸው መሰረታዊ የግምት አሠራር ነጥቦች ምንድን ናቸው?
የንብረት ግምት በሚከናወንበት ጊዜ የግምት ውጤቱ የተለያዩ የመመዘኛ ነጥቦችን መሠረት ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ በዋናነት የንብረት የዋጋ ግምት ውጤቱ በዓይነትና ይዘት ተመሣሣይ የሆኑ ንብረቶች በተመሳሳይ ጊዜ ሊሸጡ የተሸጡበትን የገበያ ዋጋ በማነፃፀር /sales comparison approach/፣ የዓለም አቀፉን የንብረት ግምት መስፈርቶች በዩኒፎርም ስታንዳርስ ኦፍ ፕሮፌሽናልስ፣ /International valuation standards/ ፣ኦፕሬይዛል ፕላክቲስ /universal of standard of professional Appraisal practice /US PAP/ የተቀመጠ ስነ ምግባርና የአፈፃፀም መመዘኛዎችን፣ መሠረት ሊያደርግ ይገባዋል፡፡

በምሳሌነትም የቤት ወይም የሕንፃ ግምትን በተመለከተ ይዞታው ያረፈበትን ስፋት፣ የቦታውን ተፈላጊነት/ location value/ የቤቱን/ሕንፃውን ይዞታ /condition/ ዕርጅና ቅናሽ፣ ግምቱ እንዲሠራ የተፈለገበትን ጊዜ፣ ከመንግስት መሠረተ ልማትና ዕቅድ አንፃር ይዞታው ወደፊት ሊገጥመው የሚችለው ጥሩና መጥፎ ሁኔታዎች፣ ቤቱ ወይም ሕንፃው የተሠራበትን ቁሳቁስ /material/ በሚመለከተው የመንግስት አካል ለይዞታው የተሠጠውን ደረጃ እንዲሁም በስፋት ይዘትና አጠቃላይ ሁኔታ ተመሣሣይነትና ተቀራራቢነት ያላቸው ሌሎች ቤቶች በተመሣሣይ ጊዜ የተሸጠበትን የገበያ ዋጋ በማነፃፀር ግምቱ ሊከናወን ይገባል፡፡

ለፍርድ ቤቶች እየቀረቡ ባሉ ጉዳዮች ላ ንብረት የዋጋ ግምት አንፃር የሚስተዋሉ ችግሮች ምንድን ናቸው?

የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 250 የንብረት የዋጋ ግምት ላይ ክርክር ከተነሳ የዋጋ ግምቱ መከናወን ያለበት በፍርድ ቤት በሚሾሙ ምትክ ዳኞች መሆኑን በግልፅ ቢያስቀምጥም ፍርድ ቤቶች የንብረት የዋጋ ግምት በሌሎች ተቋማት እንዲከናወን ማድረጋቸው በሕጉና በአፈፃፀም መካከል ያለ ክፍተት ነው፣

የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉ የንብረት ዋጋ ግምት የሚከናወነው በምትክ ዳኞች መሆኑን ቢገልፅም ምትክ ዳኞቹ የዋጋ ግምቱን እንዴትና በምን አግባብ እንደሚያከናውኑ የሚያስቀምጠው ነገር አለመኖሩ ምትክ ዳኞቹ በመሠላቸውና ትክክል ነው ብለው በሚያስቡት መንገድ ገምተው እንዲያቀርቡና የአሠላልና አገማመት ልዩነት የሚፈጥር መሆኑ የሕግ ክፍተት ነው፤

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት አስተዳደር ተቋም የመኖሪያ ቤት ግምት ገምቶ እንዲያቀርብ በፍርድ ቤቶች ሲታዘዝ ግምቱን የሚሠራው በ1988 ዓ.ም. የኮምፒውተር የመረጃ ቋት የገባ የጥሬ ዕቃ ዋጋና ተያያዥ መረጃዎች መሠረት በማድረግ በመሆኑ የሚቀርበው የቤት ወይም ሕንፃ የዋጋ ግምት ወቅታዊ ካለመሆኑ በተጨማሪ የግንባታ ወጪ የገበያ ዋጋ ባለመሆኑ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 35003 የሰጠውን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የሚጥስ መሆኑ፤

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ተሽከርካሪን አስመልክቶ የሚሰጡት የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት በኮምፒውተር የመረጃ ቋት ቀደም ሲል ያስገቡትን መረጃ መሠረት ያደረገ ብቻ እንጂ ወቅታዊ የሆነውን የገበያ ዋጋ መሠረት ያደረገ አለመሆኑ፣
በፍርድ ቤቶች ሬጂስትራር በኩል የሚመረጡና የንብረት ግምት የሚያከናውኑ ተቋማትና ግለሰቦች የንብረት የዋጋ ግምት ለማከናወን ፍቃድ አለን በሚል በአብዛኛው የሚያቀርቡት የንግድ ስራ ፈቃድ በኢንሹራንስ የጡረታ ፈንድ ተቋማት እና የዋስትና ስራዎች ዘርፍ የተሰጠ ፍቃድ እንጂ የንብረት ዋጋ ግምት ለመስራት የሚያስችል ባለመሆኑ በእውቀትና ወቅታዊ መረጃ ላይ ያልተመሠረተ የግምት ውጤት እንዲቀርብ መደረጉ፣

የመፍትሔ ሀሣቦች

በሕጉ መሠረት ግምት ለምትክ ዳኞች እንዲከናወን ማድረግ፣

ምትክ ዳኞች በእውቀትና ክህሎት ላይ የተመሠረተ የንብረት ዋጋ ግምት እንዲያከናውኑ ብቁ እንደሆነ ማስቻል፣

የንብረት ግምት ከምትክ ዳኞች በተጨማሪ በሌሎች አካላት እንዲከናወን ካስፈለገ በዚሁ አግባብ ህጉን ማሻሻል፣

የንብረት ግምት የሚሰራበትን አግባብና መመዘኛዎች በሚያመላክት መልኩ ሕጉነ ማሻሻያ፣

የንብረት ግምት እንገምቱና ስራውን እንዲሰሩ የንግድ ሥራ ፈቃድ የሚሰጣቸው ግለሰቦችና ተቋማት በዘርፉ ዕውቀትና ክህሎት ያላቸው መሆኑን በተገቢው ሁኔታ ማረጋገጥ፣

በፍ/ቤቶች ሬጅስትረል ጽ/ቤት በኩል የሚመረጡ የንብረት ገማች ተቋማት የሚያቀርቡት የንግድ ሥራ ፈቃድ በእርግጥም ንብረት ለመገመት የሚያስችል ስለመሆኑ በተገቢው ሁኔታ ማረጋገጥ፣

ተሽከርካዎችን በተመለከተ የሚከናወነው የዋጋ ግምት ስራም ተሽከርካሪው የተመረተበትን ጊዜ፣ተሸከርካሪው ከጉልበትና አቅም አንፃር ያለበትን ሁኔታ፣

የተሽከርካሪው ወቅታዊ ሁኔታ፣ የግምት ጊዜን፣ ተመሣሣይ የምርት ዘመንና ይዞታ ላይ ያሉ ተሽከርካሪዎች እየተሸጡ ያለበትን የገበያ ዋጋና ሌሎች መሠረታዊ ነጥቦች ከግምት ሊያስገባ ይገባል፡፡

የመሬት አስተዳደር ተቋማትና የመንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤቶች በኮምፒውተር የመረጃ ቋት የያዙትን /የሚይዙትን የቤቶችና የተሽከርካሪዎች የዋጋ ግምት ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃን መሠረት ያደረጉ ቢሆኑ፤

ሌሎች ንብረቶችም እንደ ንብረቱ ልዩ ባህሪና ሁኔታ በመመስረት ከጊዜ ተመሣሣይ ንብረቶች ሽያጭ ንፅፅር ይዞታና ሌሎች መመዘኛዎች አንፃር ግልፅና አሳማኝ በሆነ መልኩ የዋጋ ግምቱ ሊከናወን ይገባል፡፡

የንብረት ዋጋ ግምት የሚሠራ ግለሠብ ወይም ተቋም ሊከተላቸው የሚገቡ የሥነ ምግባርና የእውቀት መመዘኛዎች ምንድን ናቸው?

በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባገኘው የንብረት ዋጋ ግምት አሠራር ሂደት ከንብረት ዋጋ ገማቾች የሚጠበቁ የሥነ ምግባርና የእውቀት መመዘኛዎች አሉ፡፡ እነዚህም የንብረት ዋጋ ገማቾች፡ -

የዋጋ ግምቱን ሲሰሩ ነፃና ገለልተኛ እንዲሁም በከፍተኛ ጨዋነት ሊሆን ይገባል፤

ስለሚገመተው ንብረት ዓይነት፣ ተያያዥ ሕጎችና የዳበሩ አሠራሮች እንዲሁም በንብረት የዋጋ አገማመት ስልቶች የሰለጠኑና እውቀት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፤

ዋጋ ለመገመት የሚያገኟቸውን መዛግብት፣ መረጃዎችና ሠነዶች በምስጢር መያዝና ለተፈለገው ዓላማ ብቻ ማዋል ይጠበቅባቸዋል፤

ለንብረት ዋጋ ግምቱ የሚጠቀሟቸውን መረጃዎችና ማስረጃዎች አስተማማኝና እውነትንት ያለው ሊሆን ይገባል፤

ከተከራካሪ ወገኖች ጋር ወይም ግምቱ ከሚሰራላቸው አካላት ጋር የጥቅም ግጭት ሊኖራቸው አይገባም፤

የዋጋ ግምቱን በጥንቃቄ፣ በብቃትና ደረጃውን በጠበቀ መለኩ ሊያከናውኑ ይገባል፤

የሚከፈላቸው የአገልግሎት ክፍያ የሚገመተውን ንብረት ትልቀትና ይዘት፣ ግምቱን ለማከናወን የሚወስደውን ጊዜና ውስብስብነት እንዲሁም ግምቱን ለማከናወን ጥቅም ላይ የሚውለውን ስልት ከግምት ያስገባ ሊሂን ይገባል የሚሉትን በዋናነት ከንብረት ዋጋ ገማቾች የሚጠበቁ የሥነ ምግባር መርሆዎች፣ የእውቀት መመዘኛዎችና የአሠራር ደንቦች ተደርገው ሊወሰዱ ይገባል፡፡
Source:- Abyssinia Law by ABIYOU GIRMA

Address

ልደታ
Adis

Telephone

+251921057079

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dawit Amare law office DALOF posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dawit Amare law office DALOF:

Share

Category