Tesfaalem Melaku Law office

Tesfaalem Melaku Law office This page is about a local business founded in Ethiopia in April 1, 2015.

04/08/2023

Ghana is the 29th country in Africa to abolish capital punishment.

11/08/2020

በኢትዮጵያ ባለፈው 24 ሰዓታት በተደረገ 11881 የላብራቶሪ ምርመራ 584 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው የ20 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። #አንዘናጋ

05/07/2020

"The time for healing of the wounds has come. The moment to bridge the chasm that divides us has come. The time to build is upon us." ~ Nelson Mandela during his Inauguration as President of South Africa, Union Buildings, Pretoria, South Africa, 10 May 1994

www.nelsonmandela.org
www.mandeladay.com
atom.nelsonmandela.org

https://wp.me/p1iMwZ-6bx
26/06/2020

https://wp.me/p1iMwZ-6bx

በኮሮና ቫይረስ (COVID 19) መከሰት ምክንያት የተከሰተውን ሀገራዊ ሁኔታ አስመልክቶ ፍርድ ቤቶች ሊመሩበት የሚገባ አጠቃላይ መመሪያ (Comprehensive Guideline) DOWNLOAD .pdf 1. መግቢያ በአሁኑ ወቅት በዓለማ....

15/06/2020

"I learned that courage was not the absence of fear, but the triumph over it. I felt fear myself more times than I can remember, but I hid it behind a mask of boldness. The brave man is not he who does not feel afraid, but he who conquers that fear." ~ Nelson Mandela from Long Walk to Freedom, 1994

www.nelsonmandela.org
www.mandeladay.com
atom.nelsonmandela.org

09/05/2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚኒስትሮች ኮሚቴ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመግታት የሚያግዙ እና ተጨማሪ የአሰራር ማሻሻያ የሚጠይቁ ሁለት መመሪያዎችን ተወያይቶ ማፅደቁን ምክ.....

31/12/2019
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1497167470429214&id=141260699353238
09/08/2018

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1497167470429214&id=141260699353238

በጋብቻ ውስጥ በመኖር መካከል ያለውን አንድነትና ልዩነት እንዲሁም የሚያስከትለውን ውጤት ከተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንፃር
1. ጋብቻ እና ትዳር ምንድን ነው?
2. እንደባልና ሚስት አብሮ መኖር ማለት ምን ማለት ነው? ለምን? በሀገራችን ያለው ልማድና ማህበራዊ ትግበራ ምን ይመስላል?
3. ጋብቻና እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር በህግ የተሰጠው እውቅና ምንድን ነው? በህግ ያለው ውጤት አንድነትና ልዩነት ምንድን ነው?
መግቢያ
በሰው ልጆች መካከል ጠንካራና ዘለቄታዊ መሰረት ያለው ግንኙነት ከሚፈጠርባቸው መንገዶች ዋናው ጋብቻ ወይም ጋብቻን የመሰለ ጠባይ ያላቸው በአንድ ማህበረሰብ ልማዳዊ የአኗኗር ስልት የሚተገብሩ ጉዳዮች ወይም የሚመሰረቱ ግንኙነቶች መሆናቸው ይታመናል፡፡ እነዚህ ግንኙነቶች ተፈጥሮአዊ ለሆነው ትውልድን የመተካት ቤተሰባዊ ትስስር የመፈጠሪያ አብይ መንገዶች በመሆናቸው በማህበራዊ ሳይንስም ሆነ በህግ እንደ ተፈጥሮአዊ የህብረተሰብ መነሻ ምንጭ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ ይሁንና ጋብቻ መሰል ጠባይ ያላቸው ግንኙነቶች እና ጋብቻ በተለያዩ ሃይማኖቶች፣ እምነቶችና የማህበረሰቡ አስተሳሰቦች እኩል ክብርና አወንታዊ እይታ የላቸውም፡፡
ከዚህ የተነሳ በጋብቻ መሰል የትዳር ግንኙነት የሚመሰርት ቤተሰብ የሚፈጠረው የግልና የጋራ ግንኙነት እንዲሁም የሚፈራ ንብረት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዳይዳኙና በዚህ ግንኙነት ውስጥ የሚያልፉ የሰው ልጆች በተለይም ህፃናትና ሴቶች ተጎጂ እንዲሆኑ ሲያደርግ መቆቱን የተለያዩ በጉዳዩ ላይ የተዘጋጁ ጽሁፎች ያመላክታሉ፡፡
በሌላ በኩል በጋብቻ፣ በትዳርና ጋብቻ መሰል ጠባይ ባላቸው ግንኙነቶች (እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር) መካከል ያለው አንድነትና ልዩነት እንዲሁም በህግ ያለውን ውጤት አስመልክቶ ግልፅ ግንዛቤ ባለመኖሩ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች ሲከሰቱ ይስተዋላል፡፡ በዚህም የተነሳ የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማስረጽ ዳይሬክቶሬት በበጀት ዓመቱ የንቃተ ህግ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በአበይትነት ከያዛቸው ርዕስ ጉዳዮች አንዱ ጋብቻና እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር በህግ ያለው ውጤት የሚመለከት እንዲሆን ተደርጓል፡፡
በመሆኑም ከፍ ብሎ በተገለፀው ርዕስን መሰረት በማድረግ
1ኛ. ጋብቻና ትዳር ምንድን ነው?
2ኛ. እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር ማለት ምን ማለት ነው ? ለምን? በሀገራችን ያለው
ልማድና ማህበራዊ ትግበራ ምን ይመስላል?
3ኛ፣ ጋብቻና እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር በህግ የተሰጠው እውቅና ምንድን ነው? በህግ
ያለው ውጤት አንድነትና ልዩነት ምንድን ነው?
የሚሉ ነጥቦች በመዳሰስ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይህ አጭር ጽሁፍ ተዘጋጅቷል፡፡
1. የጋብቻና የትዳር ምንነት
የጋብቻ ትርጓሜ ከልዩ ልዩ ጽሁፎችና ከህግ አንጻር፡-
ሀ. ከልዩ ልዩ ፅሁፎች አንጻር
‹‹ጋብቻ›› የቤተሰብ መገኛ ተፈጥሯዊ ምንጭ መሆኑን በአብዛኛው የልዩ ልዩ ጽንሰ ሀሳብ ምሁራን የህግ ምሁራንን ጨምሮ የሚስማሙበት ቢሆንም በሁሉም ሃገራት ወጥነት ባለው አግባብ ጋብቻ አንድአይነት ትርጉም ሲሰጠው አይስተዋልም፡፡
ከዚህ ጋር በሚስማማ መንገድ Sherif Girgis, Rayn T Erson And Robert P Geroge የተባሉ የህግና የማህበራዊ ሳይነስ ምሁራን (Ecounter Book) በተባለው መፅፋቸው ጋብቻ ማለት “በስነ ልቦና፣ በስነ አምሮአዊ እና አካላዊ ጥምረት ቤተሰብ ለማስተዳደር ወይም ለመምራት አንድ ወንድ አንድ ሴት ባልና ሚስት ሆነው የሚጣመሩበትና ያዳበሩቸውን ማህበራዊ ዕሴቶች በህግ አግባብ የሚተገብሩበት ሂደት ነው፡፡” ሲሉ ይተረጉሙታል፤ (Marriage is a Comprehensive union of Mind and body ordered to family life, Unites a man and a woman as Husband and Wife, They document the social Values of applying this principle in laws.) የሚል የእንግሊዝኛ ማብራሪያ አስቀምጠውለታል፡፡
በተያያዘም Dictionary.Com የተባለው ድህረ ገጽ ጋብቻን በሁለት መንገድ ተርጉሞት እናገኘዋለን፡፡ በአንድ በኩል ጋብቻ “አንድ ወንድና አንድ ሴት ባልና ሚስት ሆነው ለመኖርና የህግ፣ ሃይማኖታዊና ማህበራዊ ሃላፊነትን ለመሰውድ ተስማምተው የሚመሰርቱት ግንኙነት ነው፡፡” የሚል ጠባብ ትርጉም ሲሰጠው በሌላ በኩል “ጋብቻ በተለያየ የስርዓት አይነት፣ ቤተሰባዊ ትስስር ለመፍጠር፣ የሚመሰረት በህግ እውቅና የተሰጠውና የጋራ ጥቅም፣ ኃላፊነትና ግዴታ የሚያስከትል እንዲሁም የዝምድና ትስስር የሚመሰረት ግንኙነት ነው፡፡” ሲል ይገልጸዋል፡፡
የእነዚህ ጽሁፎች ሃሳብ ጠቅለል ተደርጎ ሲወሰድ ‹‹ ጋብቻ ›› በአንድ ወንድ በአንዲት ሴት ቤተሰብ የመመስረት ወይም የመፍጠር ነጻ ፍላጎት ባልና ሚስት የመሆን ፍቃደኝነት ላይ የሚመሰረትና በሁለቱ መካከል የሚገኙ ሰዎችን በዝምድና የሚያስተሳስር በባልና ሚስቱ እንዲሁም በማህበረሰቡ መካከል ትስስር የሚፈጥር ህጋዊ፣ ማህበራዊ እና ሀይማኖታዊ ሃላፊነት እና ግዴታን የሚያስከትል ግንኙነት ነው የሚል ጠቅላላ ግንዛቤን (ትርጓሜን) ይሰጣል፡፡ ይሁንና እያንዳንዱ በዚህ ትርጉም ውስጥ የተካተቱ ሀሳቦች በህግ ይዘት የራሳቸው የተለየ ዝርዝር ትርጎሜ የሚኖራቸው በመሆኑ ከተለያዩ ሀገራት የህግ ማዕቀፎች አንፃር በአጭሩ የጋብቻን ትርጉም መዳሰስ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
ለ) የጋብቻ ትርጓሜ ከተለያዩ ሀገራት ህግ አንፃር
በእንግሊዝ ሃገር የህግ ሰርዓት ‹‹ የጋብቻ ›› የተሰጠውን ትርጉም ስንመለከት ‘’ Marriage is the voluntary Union for life of one man and one women to the exclusion of all others ’’ በአማርኛ ይህ አነጋገር በግድፍ ሲትርጉም ጋብቻ ማለት አንድ ወንድና አንድ ሴት በራሳቸው ፈቃድና ፍላጎት ለዘለቄታው ባልና ሚስት ሆነው ለመኖር የሚመሰረቱት ህብረት ወይም ግንኙነት ነው የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡ በተመሳሳይ የአውስትራሊያ 1961 የጋብቻ ህግ በአንቀጽ 46 ውስጥ ከፍ ብሎ የተመለከትነውን የእንግሊዝ ሀገር የህግ ስርዓት የጋብቻ ትርጉም ቃል በቃል ወስዶት እናገኘዋለን፡፡
በሌላ በኩል የኢንዶኔዥያ ህግ ለጋብቻ የሰጠው ትርጉም “በአንድ ወንድና አንድ ሴት መካከል መንፈሳዊይና ቁሳዊ ጥምርት በመፈጠር በፈጣሪ ፈቃድ ዘላቂና ደስተኛ ቤተሰብ ለመመስረት የሚፈጠር ግንኙነት ነው፡፡” የሚል ትርጉም ሰጥቶት እናገኛለን፡፡
ከላይ የሶስት ሀገራትን የህግ ማዕቀፎች ዋቢ በማድረግ ለማሳየት የተሞከሩት የጋብቻ ትርጉሞች ታዲያ ሶስት አብይ ነጥቦች መያዣቸውን ማጤን ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው ጋብቻ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚፈጠር ትስስር መሆኑ፣ ሁለተኛው ትስስር የሚመሰርተው በተጋቢዎች ፍፁም ፈቃድ ላይ ብቻ መሆኑን እና ሶስተኛው ትስስር ዘለቄታዊ መሆኑ ናቸው ፡፡
ስለሆነም ከፍ ብሎ በተገለፁት ፅሁፎችና የሶስቱ ሀገራት የህግ ትርጓሜዎች ከተገለጸው ሀሳብ መረዳት የሚቻለው ‹‹ ጋብቻ ›› ማለት በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት ፍፁም ፈቃደኝነት በመካከላቸው የሚመሰረትና በእያንዳንዳቸው ቤተሰቦች መካከል የዝምድና ትስስር የሚፈጥር ማህበራዊ፣ ህጋዊና ሐይማኖታዊ ተቀባይነት፣ ሃላፊነትና ግዴታ በተጋቢዎችና ቤተሰቦቻቸው ላይ የሚያስከትል ተፈጥሮአዊ ተቋም ነው፡፡
ሐ. የትዳር ምንነት
ስለ ጋብቻና እንደ ባልና ሚስት አብሮ ስለመኖር ምንነት በሚነሳበት ወቅት ተያያዥ ሆነ የሚነሳው ጉዳይ የትዳር (የባለትዳር) ምንነት ነው፡፡ የትዳርን ምንነት በተመለከተ ተያያዥ ሆኖ የሚነሳው ጉዳይ የትዳር (የባለትዳር) ምንነት ነው፡፡ የትዳርን ምንነት በተመለከተ የእንግሊዝኛው ተዛማጅ ቃል ‹‹Marriage’’ የሚለው ቃል በመሆኑና ይህ ቃል የተለያየ የሕግ ስርዓትና ከእኛ ሀገር ማህበራዊ ትስስር ባህልና እሴት የተለየ ልማድና ስርአት ባላቸው ሀገራት በአንድ አግባብ ለጋብቻ ትርጉም የሚጠቀሙበት ከመሆኑ አንጻር የቃሉን ቀጥተኛ የእግሊዝኛ ትርጉም ማግኘት ባይቻልም ከሀገራችን ማህበራዊ ኩነት አንጻር ‹‹ ትዳር ›› ከጋብቻና እንደ ባልና ሚስት አብሮ ከመኖር ጋር ቁርኝት ያለው ሀሳብ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
ከዚህ በመነሳት ከሳቴ ብርሃን ተሰማ ሀብተሚካኤል ግደው በ1951 ለመጀመሪያ ጊዜ ባሳተሙትና በ2002ዓ.ም በድጋሚ በታተመው የአማርኛ መዝገበ ቃላት ህትመት ውስጥ ‹‹ትዳር›› (ሀደረ) ወይም (አደረ) ከሚለው የግዕዝ ቃል ሆነ የሚሰጠውም የአማርኛ ትርጉም ‹‹ሰው ሁሉ ባለፀጋም ሆነ ድሃ ንብረቱን የሚያስተዳድርበት የቤት ስራ ነው›› የሚል ትርጉም ተሰጥቶት ስንመለከት የትዳር ትርጓሜ ከጋብቻ እና እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር ግንኙነት ምንነት ጋር ሲያይዝ ከተጋቢዎች ወይም እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግኝኙነት ካላቸው ሰዎች የግል ግንኙነት ባሻግር ሁለቱ ጉዳዮች ማለትም ጋብቻና እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር የንብረት አስተዳደርና አመራር የሚወስንበትን ሂደት የሚጨምርና የንብረት ውጤት ያላቸው በመሆኑ በተለይም ጋብቻ ማህበራዊና ህጋዊ ተቋም (social or legal institution) ነው ሲባል ‹‹ትዳር ወይም ባለ ትዳር ›› የሚለውን ጽንስ ሀሳብ ማካተቱን ያመለክታል፡፡
ይሁንና በተሻሻለው የፌዴራሉ የቤተሰብ ህግ በአንቀጽ 96 እና 98 ውስጥ ከጋብቻ ውጪ እንደ ባልና ሚስት አብሮ ከመኖርና ከትዳር ምንነት ውጪ ጋብቻን ትርጉም ሰጥቶት አይታይም፡፡ ይልቁንም በጋብቻ ተፈጥሮዊ ምንጭነት የሚመሰረተውን ቤተሰብ የህብረተሰብ ምንጭነት እውቅና በመስጠት ለዚህ ተቋም በህግ ጥበቃ ሊደረግት የሚገባበትን አስፈላጊነት ምክንያት ብቻ በመግቢያው ክፍል አስቀምጦ ይገኛል፡፡ በዚህ ረገድ በህግ ባለሙያዎች መካከል በአንድ በኩል ህጉ ጋብቻ ሊፈጸምበት የሚገባውን መንገድ ወይም የስርዓት አይነት በማስቀመጥ የጋብቻን ትርጉም አለማስቀመጡ የህጉን ክፍተት ያሳያል፡፡ ምክንያቱም ‹‹በጋብቻ›› እና ‹‹በቤተሰብ ምንነት መካከል የትርጉም መቀላቀል የህጉ የመግቢያ ክፍል ያሳያል የሚል መከራከሪያ ሲያነሱ፡፡ በሌላ በኩል ህጉ ሶስት አይነት የጋብቻ መፈጸሚያ ስርዓቶችን ወይም መንገዶች ያስቀመጠ በመሆኑ የጋብቻን ምንነት ትርጉም ቢያስቀምጥ አንደኛውን የጋብቻ ስርአት መንገድ የበላይ ሌላኛውን የጋብቻ ስርአት መንገድ የበታች የሚያደርግ የተዛባ ሀሳብ እንዳይያዝ ለመከላከል ህግ አውጪ አካል ሆን ብሎ ትቶታል፡፡ ይህም ትክክለኛ አካሄድ ነው የሚል መከራከሪያ ያነሳሉ፡፡ በተጨማሪም ህጉ የጋብቻን ምንነት ትርጉም ሳያስቀምጥ አልፎታል ማለት አይቻልም ምክንያቱም በቤተሰብ ህጉ ከአንቀጽ 1 - 4 በግልፅ ተደንግጎ እንደሚገኘው ጋብቻ ከሶስቱ በአንደኛው መንገድ ሊፈጸም እንደሚገባው ከተቀመጠ ( ከሶስቱ በአንደኛው መንገድ የተመሰረተ ግንኙት ጋብቻ ማለት ነው፡፡) የሚል ትርጉም ለጋብቻ እንደሰጠ ይቆጠራ የሚል መከራሪያ የተወሰኑ የህግ ባለሙያዎች ያነሳሉ፡፡
2. እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር ምንነት በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ውስጥ
በፌደራሉ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ‹‹ጋብቻ ሳይፈጸሙ ወይም ከጋብቻ ውጪ እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር›› ማለት አንድ ወንድ አንድ ሴት በህግ በሚፀና አኳኋን ጋብቻ ሳይፈጽሙ በትዳር መልክ አብሮ የሚኖሩ ሲሆን ነው፡፡ የሚል ትርጉም ተሰጥቶት ተሰጥቶት የሚገኝ ሲሆን፡-
ሀ. በህግ በሚፀና አኳኋን ጋብቻ አለመፈጸም ማለት ምንድን ነው?
ለ. በትዳር መክል አብሮ መኖር ማለት ምንድን ነው?
የሚሉ መጠይቃዊ ነጥቦች እንዲነሱ ያስገድዳል፡፡
በዚህ ረገድ እንደ ቤተሰብ ህግ ሀሳብ አንድ ወንድና አንዲት ሴት በህግ የሚፀና ጋብቻ ፈጽመዋል ለማለት አንድም በቤተሰብ ህጉ ከአንቀጽ 1 - 4 በተደነገገው መሰረት ከሶስቱ የጋብቻ ስርዓት አይነቶች ማለትም በማዘጋጃ ቤት በክብር መዝገብ ሹም ፊት በሚደረግ የጋብቻ ስምምነት፣ በሐይማኖት ተቋማት በሚደረግ የጋብቻ ስርዓት የሚፈጸም ጋብቻና በባህላዊ ስርዓት መሠረት በሚፈጸም የጋብቻ ስምምነት ጋብቻ ሳይፈጸሙ አልያም በህጉ ጋብቻ እንዳይከናወን ክልከላ የተቀመጠባቸው ምክንያቶች ሳያግዷቸው በህግ በተፈቀደው አግባብ ጋብቻ ሳይፈጸሙ በራሳቸው አነሳሽነት ከጋብቻ ስርዓት ውጪ የባልና ሚስት ግንኙነት የመሰለ ትስስር መፈጠርን የሚያመለክት ሲሆን ‹‹ በትዳር መልክ አብሮ መኖር ›› ማለት ደግሞ በቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 96 ውስጥ በግልፅ ሰፍሮ እንደሚገኘው አንድ ወንድና አንዲት ሴት ራሳቸውን እንደ ባልና ሚስት የሚቆጥሩና የሚኖር ከመሆናቸውም በላይ ቤተሰቦቻቸው ወይም ቤተዘመዶቻቸውና ማህበረሰቡ እንደ ባልና ሚስት የሚቀበላቸው አልያም የሚቆጥራቸው ሆኖ ሲገኝ ‹‹የትዳር መልክ›› ያለው ግንኙነት እንዳላቸው ወይም የትዳር ሁኔታ በመካከላቸው እንዳለ መረዳት እንደሚቻል ያስገነዝባል፡፡ ከዚህ በተያያዘ ሊሰመርበት የሚገባው ሃሳብ ትዳር የሚለው ሃሳብ የአብሮ መኖር ትስስርን የሚያመላክት ከመሆኑ ባሻግር በጋብቻ ውስጥ ለሚኖር ባልና ሚስትም ሆነ እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት ላላቸው ሰዎች ጭምር የሚሰራ መሆኑን የቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 96 እና አንቀጽ 98 ሀሳብ የሚያመለክት መሆኑን ነው፡፡
በሌላ በኩል እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር ወይም ጋብቻ ሳይፈፅሙ እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር የሚለው አነጋገር በአዲስ መልክ ተሻሽሎ ለምን ግንኙነቱ በህግ እውቅና እንዲሰጠው አስፈለገ? የሚለው ነጥብ ስንመለከት ቀደም ባለው የፍትሐብሔር ህግ ይሄው የትዳር መልክ ያለው ግንኙነት የራሱ እውቅና የነበረው ቢሆንም ተሰጥቶት የነበረው ስያሜ‹‹ ከጋብቻ ውጪ በግብረ ስጋ ግንኙነት መኖር›› የሚል መሆኑና አብሮ ከመኖር ትስስር ባሻግር በሌሎች ንብረት ነክና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ያለውን ውጤት የማያመላክት ይልቁንም ዋጋ ያሳጣ በመሆኑ የተነሳ ገላጭ በሆነ አነጋገር ወይም ሃረግ መተካት የሚስፈልግ በመሆኑ ቀደም ሲል በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 708 ተሰጥቶት የነበረው ስያሜ በመቀየር በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 98 ስር ‹‹ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደ ባልና ሚስት መኖር ›› የሚል ስያሜ መስጠትን መረዳት ይቻላል፡፡
በተያያዘም በቤተሰብ ህግ ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖርን ግንኙነት ትርጉም ከማስቀመጥ በተጨማሪ ለዚህ ግንኙነት እውቅና መስጠት ለምን አስፈለገ ? ይህ የግንኙነት ትስስር በኢተዮጵያ ምን ማህበራዊ ተጨባጭነትና ልማድ አለው ? የሚለውን ነጥብ መመልከት ያሻል፡፡
የቤተሰብ ህጉን ለማሻሻል አበይት ምክንያት የነበሩ ጉዳዮች በርካታ ሲሆኑ ከእነዚህ ምክንያቶች አንዱ የህፃናት ሁለተናዊ ተጠቃሚነት እና ሴቶች በትዳር ውስጥ የነበራቸውን ሚና ማሻሻል እና ሁለተናዊ ተጠቃሚነታቸው ማረጋገጥ ቀዳሚው ምክንያት ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የሴቶች እና ህፃናትን ሁለተናዊ ደህንነት አዳጋ ውስጥ ከሚጥሉ ጉዳዮች አንዱ ጋብቻ ሳይፈፅሙ እንደ ባል ና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት ሊያስከትል የሚችለውን ውጤት ጨምሮ አስቀድሞ በነበረው የፍትሐብሄር ህግ በተሸፈኑት ጋብቻ መሰል ግንኙነቶች ውስጥ በአግባብ እውቅና ያልተሰጠው መሆኑ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከኑሮ ልማድ እንደሚታየው እና ህጉ በተሻሻለበት ወቅት በጥናት እንደተረጋገጠው በአብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል ጋብቻ ሳይፈፅሙ በአንድ ጣሪያ ውስጥ እንደባልና ሚስት አብሮ በመኖር ቤተሰብ ማፍራት እየተተገበረ የነበረና ያለ ተግባር መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ምንም እንኳን ለዚህ ግንኙነት በህግ እውቅና መሰጠት አይገባም የሚል ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው የመቃወሚያ መከራከሪያ ነጥብ ጠንከር ባለ ሁኔታ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም የትስስሩ መፈጠር የማይቆምና ቀጣይነት ያለው መሆን ጉዳት የሚያስከትልባቸው የግንኙነቱ ተካፋይ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ሴቶችና ህፃናት ሊደርስባቸው ከሚችለው የሞራል፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳት መታደግ ግድ የሚል በመሆኑ ጋብቻ ሳይፈፅሙ እንደ ባልና ሚሰት አብሮ ለመኖር ትስስር አግባብነት ያለው እውቅና በህግ መሰጠት አስፈላጊ በመሆኑ በቤተሰብ ህግ ምእራፍ 7 ውሰጥ እንዲካተት ተደርጎል፡፡
በተጨማሪም ይህው ትስስር በህግ ውስጥ የተሰጠው የእውቅና ደረጃ ከተራ የአንድ ወንድና የአንዲት ሴት የተቃራኒ ፆታ ትስስር ከፍ ያለ መሆኑን በቤተሰብ ህጉ በአንቀፅ 99 (3) ተመልክቶ ከሚገኘው ‹‹አንድ ወንድና አንዲት ሴት በታወቀና በተደጋገመ ሁኔታ የሩካቤ ስጋ ግንኙነት መፈፀማቸው ብቻ በሁለቱ መካከል ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባልና ሚሰት ግንኙነት አላቸው ለማለት በቂ ምክንያት አይደለም››፡፡የሚለው ሃሳብ መገንዘብ ከመቻሉም በላይ ይሄው አነጋገር ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባል እና ሚስት መኖር ከፍ ያለ ሃላፊነትና ግዴታ የሚጠበቅበት ግንኙነት መሆኑን ጨምሮ ሚያስገነዝብ ነው፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊነሳ የሚገባው ጭብጥ ግንኙነቱ መፈጠሩን ወይም መመስረቱን ማረጋገጥ የሚቻለው እንዴት ነው? የሚለው ነጥብ ሲሆን አንድ ወንድና ሴት በህግ ተጋብተው እንደሚኖር ሰዎች አይነት ሁኔታ ማሳየታቸው ብቻውን ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባል ና ሚስት የመኖር ግንኙነት መመስረቱ የሚያስረዳ መሆኑን በቤተሰብ ህግ አንቀፅ99 (1) ‹‹ጋብቻ ሳይፈፅሙ እንደባል እና ሚስት አብረው ኖሩ ለማለት ውንድየው እና ሴትየዋ የሚያሳዩት ሁኔታ በህግ እንደ ተጋቡ ሰዎች አይነት መሆኑ አስፈላጊ እና በቂ ነው›› በሚል ከተገለፅው ሀሳብ መረዳት ይቻላል፡፡ ይሁንና ‹‹በህግ እንደ ተጋቡ ሰዎች አይነት መሆኑ አስፈላጊ እና በቂ ነው›› የሚለው አነጋገር ወንድየው ና ሴትየዋ የሚያሳዩት ሁኔታ ምንምን ጉዳዮችን ያካተተ ቢሆን ነው ‹‹በህግ የተጋቡ ሰዎችን አይነት›› ነው የሚባለው የሚለውን ጥያቄ የሚያስከትል ሆኖ ይስተዋላል፡፡
በዚህ ረገድ ከሶስቱ በአንዱ የጋብቻ ስርዓት ዓይነት ጋብቻቸውን በህግ መሰረት የፈፀሙ ባልና ሚሰት ምን አይነት ሁኔታ ያሳያሉ የሚለውን ስንመለከት በቤተሰብ ህጉ ከአንቀፅ 49 - 56 በተደነገገው መሰረት እርስ በርዕስ በመከባበር እና የጋራ ኑሮቸውን በጋራ በመምራት፣ ቤተሰብን የማሰተዳደር የጋራ ሃላፊነት በመውሰድና በመተማመን ላይ የተመሰረተ ኑሮ በመምራት በአንድ ላይ መኖርን ወዘተ የሚያጠቃልሉ ሁኔታዎችን የሚያሳዩ መሆን እንዳለባቸው ይጠበቃል፡፡
በመሆኑም ጋብቻ ሳይፈፀሙ እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መካከል አለ ለማለት ከፍ ብሎ የተገለፁት ኩነቶች በእነዚህ ሰዎች መካከል ለመኖር እንዳለባቸው ለመጠየቅ የቤተሰብ ህጉን አንቀጽ 99 (1) ሥር የተካተው አላባዊ ምክንያት መደንገጉን ማየት ይቻላል፡፡ ሆኖም ጋብቻ ሳይፈፅሙ እንደ ባልና ሚስት የመኖር ግንኙነት የፈጠሩ ሰዎች በጋብቻ ሥርዓት የትዳር ግኙነት እንደመሰረቱ ሰዎች የህግ ሰውነት የተሰጠው አካል ፊት ወይም በተፈጥሮ ሰው ፊት ግንኙነት መመስረታቸውን ቀርበው ማስረዳትም ሆነ ማስመስከር ወይም የተለየ ሥርዓት መፈፀም አይጠበቀባቸውም (አንቀፅ 99 (2) እና አንቀፅ 2 - 4 እንደተደነገገው)፡፡ ይህም ማለት በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 99 (1) እና አንቀፅ 98 እንዲሁም በአንቀፅ 49፣ 50 እና 53 በተደነገገው መሰረት በትዳር መልክ አብሮ መኖራቸው እና ማህበረሰቡ ይህንኑ ግምት በመውሰዱ እንደ ባል ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት ተመስርቷል በማለት ለማስረዳት እና ለማረጋገጥት እንደሚያስችል ያስገነዝባል፡፡
3. ጋብቻ እና እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት በህግ ያላቸው ውጤት አንድነት እና ልዩነት
ሀ) ልዩነት
• ጋብቻ በህግ ከተደነገጉት ሶስት የጋብቻ አፈፃፀም ስርዓቶች ቢያንስ በአንደኛው መንገድ መፈፀም እና ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ሰለስርዓቱ መከናወን ወይም ጋብቻ ስለመፈፀሙ ማረጋገጫ1 በሰነድ ማስረጃ አሳርነት የሚፈጸም መሆኑ (በአንቀፅ 1 - 4 እና ከ አንቀፅ 22 - 27 በቤተሰብ ህጉ እንደተነገገው)፡፡
• እንደባልና ሚስት መኖር በቤተሰብ ህጉ ለጋብቻ አፈፃፀም የተቀመጡ ስርአቶችን መፈፀምን ሳይጠብቅ በግለሰቦች ስምምነት ብቻ ያለተጨማሪ ስነስርአትና ማረጋገጫ ማስረጃ የሚመሰረት ግንኙነት መሆኑ (በአንቀፅ 98፣ በአንቀፅ 99(1)ና (2) በአንቀፅ 106 (1 - 3) በቤተሰብ ህጉ ውስጥ እንደተደነገገው)፡፡
• በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 9 መሰረት ‹‹ጋብቻ›› በታጋቢዎች ዘመዶች መካከል የጋብቻ ዝምድና የመፈጠር ውጤት ያለው ሲሆን እንደ ባልና ሚስት መኖር ግን የጋብቻ ዝምድና የሚያስከትል ውጤት የሌለው መሆኑ በአንቀፅ 100 (1) የቤተሰብ ህጉ ውስጥ እንደተደነገገው፡፡
• ጋብቻ የሚፈርሰው በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 75 እና 76 በግልፅ ተደንግገው በሚገኙት ጉዳዮች መነሻነት በፍርድ ቤት ውሳኔ ሲሆን እንደ ባልና ሚስት የመኖር ግንኙነት ግን ያለ ፍርድቤት ውሳኔ በሴትየዋ ወይም በስውዬው አነሳሽነት ቀሪ ሊሆን የሚችል መሆኑ (በአንቀፅ 105 (1) በቤተሰብ ህጉ ውስጥ እንደተደነገገው)፡፡
• ጋብቻ በተጋቢዎቹ ወይም በባልና ሚስቱ መካከል የግል ግንኙነትን አስመልክቶ ግዴታ የሚያስከትል ውጤት እንዳለው በቤተሰብ ህጉ ከአንቀፅ 49 - 56 በግልፅ ሲደነግግ ይህ አይነቱ አስገዳጅ የግል ግንኙነት መምሪያ ስርአት እንደ ባልና ሚሰት ለመኖር ግንኙነት በግልፅ በህጉ ያልተደነገገ መሆኑ፡፡
• የጋራ ሃብትን አስመልክቶ በጋብቻ ውስጥ ያሉ ሰዎች ወይም ባልና ሚስት ከተጋቡ በኃላ ያፈሯቸው ንብረቶች በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 62 መሰረት የጋራ ባለቤትነት መብት ሲኖራቸው እንደ ባልና ሚስት በመኖር ግንኙነት ውስጥ ላሉ ሰዎች የጋራ ባለቤትነት መብት መብት ቢያንስ የሶስት ዓመት የአብሮነት ቆይታን የሚጠይቅ መሆኑ (የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 102(1))፡፡
• እንደ ባልና ሚስት የመኖር ትስስር የጋበቻ ዝምድና በአንቀፅ 100(1) የማያስከትል በመሆኑ በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 198 (1) መሰረት ቀለብ የመቁረጥ ግዴታ የማያስክትል ሲሆን በተቃራኒው ጋብቻ በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 9 መሰረት የጋብቻ ዝምድና የሚያስከትል በመሆኑ ቀለብ የመቁረጥ ግዴታን የሚያስከትል መሆኑ፡፡
ለ) አንድነት ወይም ተመሳሳይነታቸው
• ባልና ሚስቶቹ ወይም ተጋቢዎቹ የግል ግንኙነታቸውንና ንብረታቸውን በሚመለከት ‹‹የጋብቻ ውል›› ሊዋዋሉ ሲችሉ ምንም እንኳን በመካከላቸው የተፈፀመ ጋብቻ ባለመኖሩ ‹‹የጋብቻ ውል›› የሚል ስያሜ ሊሰጠው እንደማይቻል ከህጉ መንፈስ መረዳት ቢቻልም እንደ ባልና ሚስት የመኖር ትስስር ውስጥ ያሉ ሰዎች ንብረታቸውን በሚመለከት የውል ስምምነት የሚያደርጉ ወይም ሊያደርጉ የሚችሉ መሆኑ በአንቀፅ 42 እና 102 (1) ውስጥ እንደ ተደነገገው፡፡
• ምንም እንኳን በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 73 እና አንቀፅ 101 የተሰጠው ስያሜ የተለያየ ቢሆንም በጋብቻ ውሰጥ ያሉ ባል ና ሚስትም ሆኖ እንደ ባልና ሚስት በትዳር መልክ የሚኖሩ ወንድና ሴት የጋራ ወጪያቸውን እያንዳንዳቸው አቅማቸውና ችሎታቸው በፈቀደ መጠን አስተዋጾ ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑ በአንቀፅ 73 እና አንቀፅ 101 እንደ ተደነገገው፡፡
• በጋብቻ ውስጥ የተፈራው የባልና ሚስት የጋራ ንብረት የሚተዳደርበት፣ የሶስተኛ ወገን እዳ የሚከፈልበት እና ንብረት የሚጣራበት እንዲሁም ጋብቻው ሲፈርስ የጋራ ንብረት ክፍፍል የሚከናወንበት ሁኔታ እንደ ባል ና ሚስት የመኖር ትስስር ውስጥ ለተፈራው የጋራ ንብረት አንድ አይነት ውጤት ወይም ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ (በአንቀፅ 103)፡፡
• ከጋብቻ ለሚወለዱ ልጆች እና እንደ ባልና ሚስት ከመኖር ግንኙነት ለሚወለዱ ልጆች የአባትነትና የእናትነትና የልጅነት እንዲሁም ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች አፈፃፃም በአንድ አይነት ስርዓት የሚመሩ መሆናቸው በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 104 እና አንቀፅ 124 እና ተከታዮቹ አንቀፆች ውስጥ በግልፅ ተደነግጓል፡፡
• ጋብቻ ሲፈርስ ሊከፈል የሚገባውን ካሳ አስመልክቶ በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 84 መሰረት ጥፋት የፈፀመ አካል መኖሩ ሲረጋገጥ ለተጋቢው ሌላኛው አካል ጥፋት ፈፃሚው ካሳ ሊከፍል እንደሚገባ የተደነገገ ሲሆን እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት ቀሪ በሆኑ ጊዜ ጥፋት የፈፀመ ወገን አለ ተብሎ ሲታመን ወይም ሲረጋገጥ አጥፊው ለሌላኛው ወገን ካሳ ሊከፍል እንደሚገባ በአንቀፅ 105 (2) ስር መደንገጉ በዚህ ረገድ ሁለቱ ግንኙነቶች ማለትም ጋብቻ እና እንደ ባልና ሚስት መኖር ተመሳሳይ ውጤት ያላቸው መሆኑን መረዳት ያስችል፡፡
• በሌላ በኩል ጋብቻን እና ጋብቻ ሳይፈፅሙ እንደ ባልና ሚስት መኖርን የተመለከቱ ክርክሮች ሲነሱ በተመሳሳይ ስርዓት የሚመሩ መሆናቸው ሁለቱን ግንኙነቶች የሚያመሳስል አንድ ውጤት መኖሩን በአንቀፅ 108 ተከታዮች የተቀመጠው ድንጋጌ ሲያስረዳ ጋብቻ ስለመፈፀሙ እንዲሁም ጋብቻ ሳይፈፀም እንደ ባልና ሚስት የመኖር ትስስር ስለመኖሩ አከራካሪ ጉዳይ ሲፈጠር የግንኙነቶቹን መኖር ወይም አለመኖር የመወሰን ስልጣን የፍርድ ቤት መሆኑ አንደኛው የሚያመሳስላቸው ውጤት መሆኑን በቤሰብ ህጉ አንቀፅ 115 እና 116 በመመልከት መረዳት ይቻላል፡፡
• በመጨረሻም ምንም እንኳን ጋብቻ ሳይፈፅሙ እንደ ባልና ሚስት መኖር የጋብቻ ዝምድና የማያስከትል ቢሆንም በቤተሰብ ህጉ ጋብቻ እንዳይፈፀም በአንቀፅ 9 መሰረት ክልከላ የተደረገበት የጋብቻ ዝምድና ውጤት እንደ ባልና ሚስት አብሮ ለመኖር ግንኙነትም የሚሰራ መሆኑን በአንቀፅ 100 (2) ሥር መደንገጉ ሁለቱ ግንኙነቶች ማለትም ጋብቻ እና እንደ ባልና ሚስት መኖር ተፈጥሮአዊ የቤተሰብና የህብረተሰብ መገኛ ምንጮች መሆናቸውን የማስጠበቅ እውቅና እና ውጤት ያላቸው መሆኑ እንደሚያስገነዝብ መረዳት ይቻላል፡፡

21/09/2017

የጠበቃ ቀልዶች

ወይኔ አባዬ

አንድ ጠበቃ በአንዲት ትንሽ የገጠር ከተማ የገጠሩን ውበት እያደነቀ ይንሸራሸር ነበር፡፡ ትንሽ መንገድ ከሄደ በኋላ ከመንገዱ ጠርዝ ላይ አደጋ የደረሰ በሚመስል መልኩ ሰዎች ተሰብስበው ግርግር ሲፈጥሩ ይመለከታል፡፡ ወዲያውኑ በዛ ቦታ ላይ የመኪና አደጋ እንደደረሰ የጠበቃ ቀልቡ ከነገረው ነገር ተነስቶ ድምዳሜ ላይ ደረሰ፡፡ በአደጋው ቦታ ዙሪያ ወደተሰበሰቡት ሰዎች በመጠጋት የአደጋውን ዓይነትና ሁኔታ ለማጣራት ቢንጠራራም መግቢያ ቀዳዳ አላገኘም፡፡ በዚህ ጊዜ ፈጣን የጠበቃ ብልጠቱን በመጠቀም ዘዴ ቀየሰና “ወይኔ አባዬ! አሳልፉኝ! ወይኔ አባዬ! አባዬ!” እያለ ሲጮህ ወለል ብሎ ተከፈተለት፡፡ በግጭቱ ክፉኛ የተጎዳው አህያ አስፓልቱ ዳር ተዘርሮ እያቃሰተ ነበር፡፡

የኪስ ምስጋና

አንዲት ሴት በጣም ያስቸገራትን የፍርድ ቤት ሙግት ወደ አሸነፈላት ጠበቃ ዘንድ ትሔድና በደስታ ተውጣ “እንዴት አድርጌ እንደማመሰግንህ አላውቅም!” ትለዋለች፡፡ ጠበቃውም “ግብጾች ገንዘብን ከፈጠሩበት ጊዜ አንስቶ ለጥያቄሽ አንድና አንድ መልስ ብቻ ነው ያለው!” ሲል እቅጩን ነግሯታል፡፡

የችሎት ቀልዶች

ፍትሐዊ ጉቦ

የተከበሩት ዳኛ በጥቁሩ ካባቸው ደምቀው በችሎት አስከባሪ ፖሊስ ታጅበው ወደ ችሎት ሲገቡ ፖሊሱ ገና “አንዴ ተነሱ!” ብሎ ተናግሮ ሳይጨርስ በአዳራሽ የነበረው ሁሉ ብድግ ብሎ አከበራቸው፡፡ “ተቀመጡ!” አሉና የመጀመሪያውን መዝገብ ገልጠው ከሳሽና ተከሳሽን ተጣሩ፡፡ በመቀጠል የግራ ቀኙ ጠበቆች ብድግ ብለው በየተራ ስማቸውን አስመዘገቡ፡፡

ዳኛው በችሎት አዳራሽ የተሰበሰበውን ባለጉዳይ አንዴ አየት አደረጉና ወደ ጠበቆቹ ዞረው በትኩረት እየተመለከቱ “በዚህ ጉዳይ የከሳሽና የተከሳሽ ጠበቆች የሰጣችሁን ጉቦ ደርሶኛል” በማለት ተናገሩ፡፡ ይሄኔ ጠበቆቹ በሐፍረት እርስ በእርስ መተያየት ጀመሩ፡፡

“የከሳሽ ጠበቃ የሰጠኝ 15 ሺ ብር ሲሆን የተከሳሽ ጠበቃ ደግሞ 10 ሺ ብር ሰጥቶኛል፡፡” ዳኛው ይህን ከተናገሩ በኋላ ከኪሳቸው ቼክ አውጥተው ለከሳሽ ጠበቃ የሚከፈል 5 ሺ ብር ከጻፉ በኋላ “የከሳሽ ጠበቃ 5 ሺ ብር እላፊ ሰጥተኸኛል፡፡ እንካ ቼኩን ተቀበል፡፡” ብለው ቼኩን ሰጡት፡፡ ጠበቃው እያላበው ቼኩን ተቀበለ፡፡

በመጨረሻም ዳኛው ፊታቸው ላይ እፎይታና እርጋታ እየተነበበ እንዲህ አሉ፡፡

“አሁን ችሎቱ የእናንተን ጉዳይ ያለ አድልዎ ገለልተኛ ሆኖ ማየቱን ይቀጥላል፡፡”

የቀበጡ ዕለት

ምስክር ሆኖ የቀረበው ግለሰብ የዳኛው የችሎት አመራር ብዙም አልተመቸውም፡፡ እናም ለሚቀርብለት ጥያቄ ጠማማ መልስ እየሰጠ ዳኛውን ትንሽ ‘ሊያስነቅላቸው’ ዳዳው፡፡

ዳኛ——“ስምህ ማነው?”

ምስክር——“ማሙሽም ማሙሸትም ብለው ይጠሩኛል”

ዳኛ——“ዕድሜህ ስንት ነው?”

ምስክር——“አርባም ሃምሳም ይሆነኛል”

ዳኛ——“የት ነው የምትኖረው?”

ምስክር——“እዚህም እዚያም”

ዳኛ——“ምንድነው የምትሰራው?”

ምስክር——“ይሄንንም ያንንም”

የተከበሩት ዳኛ የምር ትዕግስታቸው አለቀ፡፡ “አስገቡት!” አሉና ከረር ያለ ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ በገዛ ምላሱ ዘብጥያ መውረዱ እንደማይቀርለት የተረዳው ምስክር ድንጋጤ እየተሰማው “ቆይ! መቼ ነው የምወጣው?” ሲል መልሶ ጠየቀ፡፡

ዳኛ——“በቅርቡ ወይም አንድ ቀን!”

የችሎት ገጠመኞች

ሳቅ በሳቅ

“እኔ ላንቺ አንቺ ለእኔ!” ተባብለው የተጋቡ ባልና ሚስት ነፋስ መሃላቸው ገባና “አይንሺን ላፈር አይንህን ላፈር!” ተባብለው በፍቺ ተለያዩ፡፡ ቀጥሎ በጋራ ያፈሩትን መኖሪያ ቤት እኩል በዓይነት ተካፈሉ፡፡ ሚስት ቤቱን አድሳ ወደ ሆቴል ቀየረችው፡፡ የሆቴሉንም ስም “ሳቅ በሳቅ ሆቴል” አለችው፡፡ ትንሽ ቆይቶ ባልም በተራው ቤቱን አድሶ ሆቴል ከፈተ፡፡ ለሆቴሉ ያወጣለት ስም “ደም ሳቂ ሆቴል” የሚል ነበር፡፡

ችሎቱ ወዶሻል

እውነተኛነቱ ያልተረጋገጠ አንድ የችሎት ገጠመኝ እንዲህ ይነበባል፡፡ ተከሳሽ ሆና የቀረበችው ሴት መልኳ የሚማርክ ሰውነቷ የሚያማልል ዓይነት ነበረች፡፡ በዛ ላይ የለበሰችው ጉርድ ቀሚስ ተደማምሮ የዳኛውን ቀልብ ሳትስብ አልቀረችም፡፡ በችሎት የሚከናወነው አጭር የቃል ክርክር እንዳበቃ ከሳሽና ተከሳሽ ከችሎት (ጉዳዩ የሚታው በዳኛው ቢሮ ውስጥ ነበር፡፡) ሊወጡ ሲያመሩ ዳኛው ተከሳሽ ወደኋላ እንድትቀር ምልክት ይሰጧታል፡፡ ድንጋጤ የተሰማት ተከሳሽ የዳኛውን ትዕዛዝ ሳታቅማማ በመቀበል አቋቋሟን አሳምራ ተገትራ ቀረች፡፡ በዚህ ጊዜ ውበቷን ለማድነቅ ዕድል አጥተው የነበሩት ዳኛ “ችሎቱ ወዶሻል!’ በማለት አድናቆታቸውን በጨዋ ደንብ ገልፀዋል፡፡

መማር ደጉ

ምስክሩ ለችሎቱ የመግቢያ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠ ነው፡፡ ስሙን፤ ዕድሜውን፤ መኖሪያ አድራሻውን ከተናገረ በኋላ ዳኛው “የትምህርት ደረጃ?” ሲሉ ጠየቁት

ምሰክር——“አቋርጫለው”

ዳኛ——“ከስንት?”

ምስክር——“ከ1ኛ ክፍል”

Source Hig keld ena kumneger By Abreham Yohannes

This page is about a local business founded in Ethiopia in April 1, 2015.

30/08/2017

Found on Google from izquotes.com

Address

Helen Bldg, 3rd Floor
Addis Ababa

Telephone

251939803233

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tesfaalem Melaku Law office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tesfaalem Melaku Law office:

Share