የህግ አምድ-legal column

የህግ አምድ-legal column በማናቸዉም የፌደራል ፍ/ቤቶች ጠበቃ እና የህግ አማካሪ

ለዋስትና የተሰጠ ቼክ በቂ ስንቅ የሌለዉ መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ሰጪዉን በወንጀል የማያስጠይቅ ስለመሆኑ
10/06/2026

ለዋስትና የተሰጠ ቼክ በቂ ስንቅ የሌለዉ መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ሰጪዉን በወንጀል የማያስጠይቅ ስለመሆኑ

የተቋረጠ ጥቅም vs መድን
10/06/2026

የተቋረጠ ጥቅም vs መድን

ክፉ ልቦናን መከላከያ ዉሳኔ 358
10/06/2026

ክፉ ልቦናን መከላከያ ዉሳኔ 358

ውርስን በተመለከተ በ7 ዳኛ
10/06/2026

ውርስን በተመለከተ በ7 ዳኛ

10/06/2026
ሰ/መ/ቁጥር 253783       የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ/ምየማይንቀሳቀሰረ ንብረት ሽያጭ ዉል ስልጣን ባለው አካል ዘንድ ቀርቦ ባለመመዝገቡ ምክንያት ውሉ ህጋዊ ውጤት እንዳይኖረው የሚደረ...
09/06/2026

ሰ/መ/ቁጥር 253783
የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ/ም
የማይንቀሳቀሰረ ንብረት ሽያጭ ዉል ስልጣን ባለው አካል ዘንድ ቀርቦ ባለመመዝገቡ ምክንያት ውሉ ህጋዊ ውጤት እንዳይኖረው የሚደረገው ውሉ ስለመደረጉ ተዋዋዮች ክደው ከተከራከሩ ብቻ ነው።

የሰ/መ/ቁ 205075  የገጠር እርሻ መሬት በሽያጭ ውል ተላልፎ ገዢው ይዞታው በእጁ በነበረበት ወቅት ቋሚ ንብረት ቤትና አትክልቶች ቢያለማበት የመሬት ሽያጭ ውሉ ውጤት አልባ ሆኖ ወደ ነበሩ...
09/06/2026

የሰ/መ/ቁ 205075
የገጠር እርሻ መሬት በሽያጭ ውል ተላልፎ ገዢው ይዞታው በእጁ በነበረበት ወቅት ቋሚ ንብረት ቤትና አትክልቶች ቢያለማበት የመሬት ሽያጭ ውሉ ውጤት አልባ ሆኖ ወደ ነበሩበት ቦታ ይመለሱ በመባሉ ይዞታውን የተረከበ ሻጭ ገዢ በይዞታው ላይ የገነባውን ቤት አፍርሶ የመሄድድ እንጂ ግምት የመጠየቅ መብት እንደሌለው፤ ቋሚ አትክልቶችን በተመለከተ ደግሞ እነዚህን አትክልቶች ለመንከባከብ ከችግኝ ጀምሮ እስከ ምርት እንዲሰጥ ለማድረስ ያወጣውን መጪ የመጠየቅ መብት አለው በማለት አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል
case comment for lawyers

09/06/2026

ዲክላራሲዮን አቅራቢው/importer ለቀረጥና ታክሱ
አለመከፈል ምክንያት ካልሆነ ቅጣትና ወለድ ለመክፈል
****ይገደዳል ?
• የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006
• የሰ/መ/ቁ 244742
• የሰ/መ/ቁ 219003

1. በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀጽ 122 (1)(2) ድንጋጌ ቀረጥና ታክስ በማናቸውም ምክንያት ያልተከፈለ ወይም የተከፈለ መሆኑ በድህረ እቃ አወጣጥ ኦዲት የተደረሰበት እንደሆነ ባለስልጣኑ ዲክላራሲዮን አቅራቢውን ያልተከፈለውን ወይም በልዩነት ሊከፈል የሚገባውን ቀረጥ እና ታክስ ሊከፈል ከሚገባበበት ቀን ጀምሮ በ5 አመት ውስጥ ሊያስከፍል ይችላል፡፡

2. በሌላ በኩል ላልተከፈለው ወይም በልዩነት ላልተከፈለው ቀረጥና ታክስ አለመከፈል ተጠያቂው ዲክላራሲዩን አቅራቢው ከሆነ ሳይከፈል በቀረው ቀረጥና ታክስ ላይ 10 በመቶ የባንክ ወለድና ቅጣት ጨምሮ ለመክፈል ይገደዳል፡፡

3. አንቀጽ 122 (4) ባለስልጣኑ ኦዲት ሊያደርግ መሆኑን ካሳወቀ በኋላ ዲክላራሲዩን አቅራቢው ያልተከፈለ ቀረጥና ታክስ መኖሩን ከገለጸ እና ለመክፈል ፍቃደኛ ከሆነ ከቀረጥና ወለድ ውጪ ቅጣት እንዲከፍል አይገደድም፡፡

4. ስለሆነም በድህረ እቃ አወጣጥ ኦዲት የተደረሰበት ሊከፈል የሚገባው ወይም ሳይከፈል የቀረ ቀረጥና ታክስ መኖሩ ከተረጋገጠ ታክሱ ሳይከፈል ከቀረበት ቀን ጀምሮ በ5 አመት ውስጥ ማስከፈል እንደሚችል ዲክላራሲዩን አቅራቢ ለቀረጥና ታክስ አለመከፈል ምክንያት ካልሆነ ከዋናው ቀረጥና ታክስ እንዲሁም በዚሁ ላይ ከሚታሰብ የባንክ ወለድ ጋር እንዲከፍል የጉምሩክ ባልስልጣን ሊወስን እንደሚችል ከዚህ አንጻር ቅጣት ላይጣልበት ስለመቻሉ መረዳት ይገባል ፡፤

5. ጉምሩክ በራሱ አሰራር ምክንያት በተለይም በአየር ወደ ሀገር የገቡ እቃዎችን የቀረጥና ታክስ ስሌት አስመልክቶ አዲስ በጀመረው አሰራር በተፈጠረ ችግር ተገቢውን ቀረጥና ታክስ ያልከፈለ ዲክላራሲዩን አቅራቢ ወለድና ቅጣት ለመክፈል መገደድ የለብኝም በሚል በጀመረው ይግባኝ ይህን ተከትሎ እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት በተካሄደ ክርክር ዲክላራሲዩን አቅራቢው ለቀረጥና ታክሱ አለመከፈል ምክንያት ሆኖም ባይሆን ወለድ ሳይከፈል ለቆየ ገንዘብ በተጨማሪነት የሚከፈል በመሆኑ አቅራቢው ጥፋት ባይኖርበትም ቀረጥና ታክሱ ዘግይቶ ለጉምሩክ በመከፈሉ ወለድ ለመክፈል እንደሚገደድ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አስገዳጅ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡

6. በመሆኑም ቀረጥና ታክስ ላለመከፈሉ ተጠያቂ ያልሆነ ዲክላራሲዩን ነጻ የሚሆነው ከቅጣት እንጂ ከወለድ አደለም፡፡ ጉምሩክ ቀረጥና ታክስ በወቅቱ ላለመሰብሰቡ ጥፋቱ የራሱ ቢሆንም ዲክላራሲዩን አቅራቢው ዘግይቶ ለተከፈለ ቀረጥና ታክስ ወለድ ለመክፈል ይገደዳል፡፡ ቅጣት ግን ሊጣልበት አይገባም፡፡

09/06/2026

የሰ/መ/ቁ 206699
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 231(1) መሠረት በክስ አቤቱታው የተገለጸው የማያስከስስ መሆን መሆን አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ የመመርመር ኃላፊነት አለበት፡፡
የክስ ምክንያት ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ግዴታ መኖሩን፣ የተጠየቀው ዳኝነት በፍርድ ቤት የሚዳኝ መሆን አለመሆኑን እና በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተመለከቱት ጉዳዮች ቢረጋገጡ የተጠየቀውን ዳኝነት ለከሳሽ ለመወሰን ህግ የሚፈቅድ መሆን አለመሆኑን መመርመርን የሚጠይቅ ነው፡፡
👉ይህም የክስ ምክንያት የሌለው ጉዳይ የሚለው በዋነኛነት ዳኝነቱን ለመጠየቅ ከህግ የመነጨ ግንኙነት
እያለው ግን በፍርድ ቤት ሊዳኙ የማይችሉ ጉዳችን (non-justiciable matters) ፍርድ ቤት አከራክሮ ሊፈጸም የሚችል ውሳኔ ሊሰጥባቸው የማይችሉ በመሆናቸውና ከሳሽ ወገን ክሱን ሲያቀርብ የጠቀሰው ወይም
የገለጸው የክሱ መሰረት የሆነው ምክንያት በህግ የክስ መሰረት ሊሆን የማይችል ከሆነ የማያስከስስ ነው
ተብሎ ክሱ ውደቅ የሚደረግበት ሥርዓት ነዉ

06/06/2026

ተደራሽነታችንን ለማስፋት 20k መግባት አለብን follow.

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የህግ አምድ-legal column posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share