Tesfaye Law Office

Directions

Tesfaye Law Office Your Legal partner

23/05/2026

የብቸኝነት ጥበብ፡ የደካማነት ሳይሆን የጥንካሬ ማሳያ! 🤔🛡️

በሕይወት መንገድ ላይ ብቸኝነት ብዙ ጊዜ እንደ ጉድለት፣ ባዶነት ወይም መገለል ይታያል። ነገር ግን እውነታው ከዚህ በተቃራኒ ነው፤ ብቸኝነት የሕይወት ውጣ ውረዶች የጠረቡት የጥበብ ጋሻ ነው።

አንድ ሰው ወደ ራሱ ዓለም ሲሸሽ ያንን የሚያደርገው በመንገዱ ላይ ካጋጠመው ክህደት የተገኘውን መራራ ትምህርት ለመቅሰም ነው። ያ ብቸኝነት የሚመስለው ስፍራ በእውነቱ ከውሸት የተጠበቀ፣ የነፍስን ሰላም የሚያስጠብቅ ብቸኛው አስተማማኝ ወደብ ነው።

ጠንካራ መሪዎችና የሕይወት ፈላስፋዎች ከውሸት ስብስብ ይልቅ ብቸኝነትን የሚመርጡባቸው 4 ዋና ምክንያቶች፡

የራስን ሰላም ማስከበር 🕊️
ከጭቅጭቅና ከማስመሰል ይልቅ ርቀትን መምረጥ መሸሽ አይደለም። ለራስ ክብር የሚሰጥና ውስጣዊ ሚዛንን የሚጠብቅ ስልታዊ ዝግጅት ነው እንጂ።

ከማስመሰል መራቅ 🎭
ብዙ ሰዎች በዙሪያቸው ባሉ ግለሰቦች ለመቀበል ሲሉ እውነተኛ ማንነታቸውን አሳልፈው ይሸጣሉ። ጠንካራ ሰው ግን በውሸት ስብስብ ውስጥ ከመበታተን ይልቅ በብቸኝነት ውስጥ ራሱን መገንባት ይመርጣል።

እውነተኛ ታማኝነትን መረዳት 💎
እውነተኛ ትስስሮች በኃይል የሚገዙ ሳይሆን በጊዜና በቅንነት የሚፈጠሩ መሆናቸውን በመገንዘብ፣ ጠንካራ ሰው የራሱን ሰላም አሳልፎ ለከንቱ ግንኙነት አይሰጥም።

የራስ አለቃ መሆን 👑
መሪዎች ከሰዎች ሲርቁ ሰዎችን ስለጠሉ አይደለም። በዙሪያቸው ያለው የውሸት መረብ የሕይወታቸውን ትርጉም እንዳይበታትን ለመከላከል ነው። በዚህ ጊዜ ሰው የራሱ አስተማሪና ሰላም ፈጣሪ ይሆናል።

ባጭሩ፡
ለብቻ የመጓዝ ጥበብ የሽንፈት ማሳያ ሳይሆን፣ ትርጉም አልባ ከሆኑ ግንኙነቶች በመላቀቅ የራስን ማንነት የመታደግ ከፍተኛ የአእምሮ ብስለት ነው። የዚህ ጉዞ ፍጻሜ ባዶነት ሳይሆን፣ ከማንም ጋር ሳይመሳሰሉ የራስን እውነት በድፍረት መኖር ነው!

✍️ዋናዉ ሀሳብ የተፃፈዉ በዛዲግ አብርሃ (የአፍሌክስ ፕሬዝደንት) ነዉ

#የሕይወትጥበብ #ብቸኝነት #ጥንካሬ #መሪነት

20/05/2026

⚖️ በፍርድ ቤት ውስጥ በፍጹም ሊያደርጓቸው የማይገቡ እና ዳኞችን በጣም የሚያናድዱ 12 ነገሮች!

ፍርድ ቤት የገበያ ቦታ አይደለም! በፍርድ ቤት ውስጥ የሚታይ አንድ የተሳሳተ ባህሪ ወይም ስነ-ምግባር ማጣት ብቻ በእርስዎ የክስ መዝገብ ላይ ትልቅ እና የማይመለስ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። በተለይ ዳኞችን በጣም የሚያናድዱ እና መደረግ የሌለባቸው ዋና ዋና ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፦

⏰ 1. ዘግይቶ መምጣት፦ ዘግይተው ደርሰው ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ብሎ መግባት።
📞 2. ስልክ ማንሳት፦ በፍርድ ቤት አዳራሽ ውስጥ ስልክ ማውራት ወይም ድምፅ መክፈት።
🗣️ 3. ከዳኛ ጋር መከራከር፦ ድምፅን ከፍ አድርጎ ከዳኛው ጋር መጮኽ ወይም አለማክበር።
👗 4. አለባበስ፦ ወደ ምሽት ክበብ የሚሄዱ ይመስል የማይመጥን ልብስ መልበስ።
🤥 5. መዋሸት፦ ግልጽ ማስረጃ እያለ ፊት ለፊት መዋሸት።
6. ጣልቃ መግባት፦ ዳኛው ወይም ጠበቃው እየተናገሩ ንግግራቸውን ማቋረጥ።
😂 7. መሳቅ፦ አሳሳቢ እና ከባድ የሕግ ጉዳይ እየታየ መሳቅ ወይም ማሾፍ።
🤬 8. መሳደብ፦ በፍርድ ቤት ውስጥ ተቃራኒ ወገንን ወይም ባለጉዳይን መስደብና ማንቋሸሽ።
👥 9. ሀሰተኛ ምስክር፦ ፍርድ ቤቱን ለማታለል ሀሰተኛ ምስክሮችን ይዞ መቅረብ።
🍬 10. ማስቲካ ማኘክ፦ በገዛ ሳሎንዎ ውስጥ እንዳሉ ዘና ብለው ማስቲካ ማኘክ።
🧍‍♂️ 11. አለመቆም፦ ዳኛው ወደ ችሎት ሲገቡ ለክብር አለመቆም።
📱 12. በሶሻል ሚዲያ መለጠፍ፦ የፍርድ ቤቱን ክርክር ወይም ህደት ጉዳዩ ገና ሳይጠናቀቅ ኦንላይን ላይ መለጠፍ።

💡 ማሳሰቢያ፦
ምንም እንኳ በጉዳዩ ቢናደዱም ወይም ቢበሳጩም ለፍርድ ቤቱ ሁልጊዜ ተገቢውን ክብር ይስጡ። የራሳችን ስህተት እና የባህሪ ጉድለት በጉዳያችን ላይ ተፅዕኖ እንዳያደርግ መጠንቀቅ አለብን!

#የሕግምክር #ፍርድቤት #ስነምግባር

✅
07/05/2026

✅

07/05/2026

ነፃ የህግ ምክርና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን የተላለፈ መልዕክት! ⚖️

በገጻችን በኩል ነፃ የህግ ምክር እንደምንሰጥ ካሳወቅንበት ጊዜ ጀምሮ እያሳያችሁ ላለው ከፍተኛ ፍላጎት እና እምነት እናመሰግናለን። ባለፉት 3 ቀናት ብቻ፦
✅ ለ3 ሰዎች በጉዳያቸው ላይ አቋም እንዲይዙ የሚያስችል ምክር ሰጥተናል፤
✅ ለአንድ ሰው ደግሞ የቅሬታ ማመልከቻ በነፃ እየተጻፈለታ ይገኛል።

በሂደቱ ብዙዎችን መርዳት መቻላችን ትልቅ ደስታ ይሰጠናል። ይሁንና አገልግሎቱ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የሚከተሉትን ነጥቦች ግምት ውስጥ እንድታስገቡ እንጠይቃለን፦

1️⃣ አቅም ለሌላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፦ አገልግሎቱን የምንሰጠው ከመደበኛ ስራችን ጎን ለጎን በመሆኑ፣ ሁሉንም ጥያቄዎች በአንዴ ለማስተናገድ አቅማችን ውስን ነው። ስለሆነም በእውነት አቅም የሌላቸውን በጥንቃቄ መርጠን እናስተናግዳለን። እናንተም ሰዎችን ስትጠቁሙ ይህንን ከግምት ውስጥ እንድታስገቡልን እንሻለን።

2️⃣ ሚስጥራዊነት የተጠበቀ ነው፦ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የባለጉዳዮችን ስምም ሆነ የጉዳይ ዝርዝር ማጋራት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ስለ ልዩ ጉዳዮች (Specific cases) የምንወያየው ሚስጥራዊነቱን ለመጠበቅ በውስጥ መስመር (Inbox) ወይም በስልክ ብቻ ይሆናል።

3️⃣ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው፦ ለህግ አገልግሎታችን ምንም ዓይነት ክፍያ አንጠይቅም። ነገር ግን እንደ ጉዳዩ ስፋት ለጸሐፊዎች የሚከፈል መጠነኛ ክፍያ ካለ እናሳውቃለን። ስለዚህ ሳትሸማቀቁ ደውሉ፣ መልዕክት አስቀምጡ። በስራ ብዛት ስልክ ባናነሳ እንኳ በትርፍ ሰዓታችን ተመልሰን እንደውላለን።

4️⃣ በትዕግስት ይጠብቁን፦ ጉዳዮችን እንደ አጣዳፊነታቸው ቅደም ተከተል እየሰጠን እንሰራለን። መልዕክት አስቀምጣችሁ ያልተመለሰላችሁ ሰዎች በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን፤ ለሁሉም ምላሽ ለመስጠት እንጥራለን።

ይህ መልዕክት ለሚገባቸው እንዲደርስ Like እና Share በማድረግ ተባበሩን። መርዳት የምንችላቸውን ሰዎች መጠቆማችሁን ቀጥሉ!

📞 ስልክ፦ +251933015535
📩 Facebook፦ በገጻችን የውስጥ መስመር መልዕክት ይላኩ።

ፍትህ ለሁሉም! ⚖️

06/05/2026

አስገራሚው የይቅርታ መግለጫ

የፌደራል ጠበቆች ማህበር በስሕተት የቀብር ሥነ ሥርዓት እንዲታደሙ የጠራቸውን ሠራተኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።

የፌደራል ጠበቆች ማህበር ጠበቃ አስቴር ዓርአያ የተባለች አንድ ሠራተኛው እንዳረፈች ገልፆ የሀዘን መግለጫ በማውጣት ሠራተኞቹ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን እንዲካፈሉ ጥሪ ያደርጋል።

በጥሪው መሠረት በዛሬው ዕለት ሰራተኛው ተደናግጦ በሥራ የባልደረባው የቀብር ሥርዓት ይፈፀምበታል በተባለው ስፍራ ቢገኝም በዕለቱ የነበረው ቀብር ግን ሕልፈታቸው የተገለፁው ጠበቃ አስቴር የተባሉት የማህበሩ ሰራተኛ ሳይሆኑ ወ/ሮ አስቴር አሻግሬ የተባሉ ሌላ ግለሰብ መሆናቸው ታውቋል።

የፌደራል ጠበቆች ማህበርም ሳይሞቱ ሞተዋል የተባሉትን ጠበቃ አስቴር ዓርአያን እና ቤተሰባቸውን ይቅርታ ጠይቋል። እንዲህ ዓይነት ስሕተት እንዳይደገመም "ውስጣዊ ሒደቴን" እገመግማለሁ ብሏል።

06/05/2026
06/05/2026

በዋስትና ከመፈታት አኳያ አዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ ያመጣቸው አዳዲስ ነገሮች መካከል:-
By Hailu Hasena (Legal Advocate)

1. "ያለ ዋስትና መለቀቅ (Release without bail/unconditional release)" የተሰኘ አዲስ ድንጋጌ አምጥቷል::

በዚህ ድንጋጌ መሠረት ተጠርጣሪው የተጠረጠበትን ወንጀል ስለመፈጸሙ ወይም የተባለው ወንጀል ስለመፈጸሙ አጠራጣሪ (doubtful) በሆነ ጊዜ የወንጀል ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ፍ/ቤትም ሆነ ቀዳሚ ምርመራ አድራጊ ፍ/ቤት ተጠርጣሪውን ያለ ዋስትና እንዲሁ እንዲለቁት ይገደዳሉ:: አንቀጽ 118(4)፣ 137(2)

*በቀድሞው የወ/መሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 59(1) እና 93 መሠረት የጊዜ ቀጠሮ እና የቀዳሚ ምርመራ ፍ/ቤቶች ተጠርጣሪው ወንጀል ስለመፈጸሙም ሆነ ወንጀሉ ራሱ ስለመፈጸሙ ቢጠራጠሩም ስንኳ ተጠርጣሪውን የግድ ዋስትና እንዲያስይዝ ወይም በማረፊያ ቤት እንዲቆይ እንዲያዙ ይገደዱ ነበር:: በአዲሱ መድብለ ሕግ ያ አሠራር ተሽሯል::

*ይህ ድንጋጌ በተለይ ለሚታፈሱ ወይም በመመሳጠር በፍ/ብሔር ወይም ወንጀል ባልሆነ ጉዳይ ለሚታሰሩ ሰዎች ይህ ትልቅ የሕግ ጥበቃ የሚያደርግ ነው::

*ስለዚህ የተያዙ ሰዎች የሚለቀቁባቸው መንገዶች እነዚህ ናቸው—ያለ ዋስትና መለቀቅ፣ ያለ ገደብ መለቀቅ፣ በራስ ዋስትና መለቀቅ፣ በንብረት ዋስትና መለቀቅ፣ በሰው ዋስትና፣ በገንዘብ ዋስትና መለቀቅ፣ በተጨማሪ ዋስትና መለቀቅ::

*ስለሆነም ከእንግዲህ የጠበቆች ሥራ የታሰረን ሰው በዋስትና ማስፈታት ብቻ ሳይሆን ያለ ዋስትና ማስፈታትንም ይጨምራል::👴🏽🧓🏾👩🏽‍⚖️🧑🏾‍⚖️👨🏾‍🦳

*Note: በፍ/ቤት መደበኛ ክስ (charge) የተከፈተ ከሆነ ያለ ዋስትና የመለቀቅ ጉዳይ አይነሣም::

2. በሕግ ዋስትና የሚያስከለክሉ ወንጀሎች (non-bailable crimes)
* በሞት የሚያስቀጡ ወንጀሎች፣ ወይም
* በ ≥15 ዓመት ጽኑ እሥራት የሚያስቀጡ ሰው የሞተባቸው ወንጀሎች ብቻ እንዲሆኑ የተደነገገ ስለሆነ በእንደዚህ ዓይነት ወንጀሎች ውጭ ያሉ ወንጀሎች በሙሉ በሕግ ዋስትና የማያስከለክሉ ወንጀሎች (bailable crimes) ሆነዋል:: አንቀጽ 138(2,3)

ስለሆነም:-
➡️ስለሆነም በሕግ ዋስትናን በማይከለከልባቸው ወንጀሎች በመሉ ተጠርጣሪዎች/ተከሳሾች በዋስትና የመለቀቅ መብት አለው::
➡️በዕድሜ ልክ ወይም የጽኑ እሥራት ጣሪያ በሆነው በ25 ጽኑ እሥራት የሚያስቀጣ ወንጀል ብቻውን ዋስትናን አያስከለክልም::

➡️በማንኛውም የሙስና ወንጀል የተጠረጠረ/የተከሰሰ ሰው በሕግ ዋስትናን አይከለከልም—all corruption crimes have become bailable.
ከዚህ ቀደም በዐዋጅ ቁ. 434/1997 (በዐዋጅ ቁ. 882/2007 እንደተሻሻለ) አንቀጽ 4(1) መሠረት "ከ10 ዓመት በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል የተጠረጠረ ወይም የተከሰሰ ሰው በዋስትና አይለቀቅም በማለት ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጡትን ለይቶ non-bailable corruption crimes ተደርጎ የነበረው ድንጋጌ ቀሪ (abolished) ተደርጎአል::

➡️በአደገኛ ቦዘኔነት ዐዋጅ ቁጥር 384/96 አንቀጽ 6(3) "በአደገኛ ቦዘኔነት ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው በዋስትና አይለቀቅም:" ተብሎ በወንጀል ዓይነት ዋስትና ይከለከል የነበረው (categorical bail denial) ዘፈቀዳዊ ነው ተብሎ በዚህ ዐዋጅ ተሽሮአል::

➡️በሕግ ዋስትና የማያስከለክሉ ወንጀሎችን (bailable crimes) አስመልክቶ ዋስትና መብት (right) ሲሆን ዋስትና ሊከለከልም ሊፈቀድም የሚችለው በዳኞች ፍቅድ ሥልጣን (judicial discretion) ነው::
ፍቅድ ሥልጣኑ የሚመራባቸው መርኆዎችም ደግሞ "ዳኛው ተጠርጣሪውን/ተከሳሹን በዋስትና ይለቃል የሚል ግምት (presumption of release on bail) ይወሰዳል:"፤ "ዋስትናን በሁኔታ የሚያስከለክሉ ሁኔታዎችም አይኖሩም: ተብሎ ይገመታል::"
"ዋስትናን ለመከልከል የሚያበቁ ልዩ ሁኔታዎች በጠባቡ እና ለተከሳሽ/ተጠርጣሪ በሚጠቅም መልኩ ይተረጎማሉ:" የሚሉ ናቸው—ከተመድ የሰብኣዊ መብቶች የዋስትና መብት ትርጉም አኳያ::

ለምሳሌ:- ተጠርጣሪው በዋስ ቢወጣ ሌላ ወንጀል ይፈጽማል ወይም ማስረጃ ያጠፋል ወይም በተፈለገ ጊዜ አይቀርብም ወይም ቋም አድራሻ የለውም ወይም መውጣቱ ለኅ/ሰቡ ደኅንነት ያሰጋል ወይም የዋስትና ግዴታውን አይወጣም ወዘተ. የሚል ግምት አይያዝም::
ስለሆነም መርማሪ ፖሊስ ወይም ዐቃቤ ሕግ እነዚህን መርኀዊ ግምቶች ለማስተባበልና ለመሠረታዊ መብቶች (የነጻነት መብት፣ ንጹሕ ሆኖ የመገመት መብት) የሥነ ሥርዓታዊ ጥበቃ የሆነውን የዋስትና መብት ለመቃወም ሕጋዊ፣ በቂ እና አሳማኝ ምክንያት ያለ መሆኑን በቂ ማስረጃ በማቅረብ ማስረዳት ይኖርበታል::

3. የድኅረ ጥፋተኝነት ፍርድ ዋስትና (Post-conviction bail) የተሰኘ አዲስ ድንጋጌ አምጥቷል::
አንቀጽ 301(2)

ይህ ድንጋጌ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ነህ ተብሎ ከተፈረደበት በኋላ የቅጣት ውሳኔ እስኪተላለፍበት ድረስ ባለው ጊዜ በዋስትና እንዲቆይ የሚያደርግ ነው::
ይሁንና ይህ ዋስትና የሚሠራው ወንጀሉ በመቀጮ ብቻ የሚያስቀጣ ሲሆን ነው::

እንደሚታወቀው በነባሩ የወ/ሕ/ሥ/ሥ መሠረት ዳኞች የፈረዱበትን ማንኛውንም ሰው ቅጣቱ እስኪወሰን ድረስ 'ታስሮ' እንዲቆይ ያዙ ነበር—በጣም ጥቂት ሰብኣዊነት ላይ የተመሠረተ ልዩነት ቢኖርም::

ለዚህ እንደ ምክንያት ይጠቀስ የነበረው የዋስትና መብት ንጹሕ ሆኖ ከመገመት መርኅ ጋር ብቻ የተቆራኘ ስለሆነ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሲባል መብቱም ዐብሮ ቀሪ ይሆናል፣ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ በዋስትና ቢወጣ ሊጣልበት የሚችለውን ቅጣት ፈርቶ ላይቀርብ ስለሚችል የሚጣለው ቅጣት አፈጻጸም ችግር እንዳይገጥመው የሚል ግምት በመያዝ ነበር::

ይሁንና ሁለቱም ምክንያቶች የተሳሳቱ እና የሕግ ፍልስና መሠረት የሌላቸው ስለሆኑ በሥሡ ለማረም ተሞክሯል::
*ለምሳሌ በፌስታል ዐዋጅ ቁ. 1383/2017 አንቀጽ 25(1/ሀ) ሥር ፌስታል በመጠቀም ወይም ለመጠቀም ይዞ በመገኘት ወንጀል ተከሶ የጥፋተኛነት ፍርድ የተሰጠበት ተከሳሽ የቅጣት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በማረፊያ/በማቆያ ቤት እንዲቆይ አዲሱ ሕግ አይፈቅድም::

*** *** ***
ስማችን ሳይጠቀስ በሌላ ገጽ ላይ ኮፒ-ፔስት ሲደረግ እኛውኑ ሌላ ሰው የጻፈውን ጽሑፍ ሰርቀን ያጋራን ሊያስመስል ስለሚችል ምቾት አይሰጠንም::

ተባረኩ!
Hailu Hasena (Legal Advocate)

contact us for your legal needs & servicesour door is now open for both probono services & services based on payment.☎️+...
06/05/2026

contact us for your legal needs & services
our door is now open for both probono services & services based on payment.☎️+251933015535

06/05/2026
04/05/2026

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tesfaye Law Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share