ሕግ አገልግሎት / Legal Service

ሕግ አገልግሎት / Legal Service Top Rated Legal Service Provider in Addis Ababa, Ethiopia. SAMUEL GIRMA +251911190299. Your First Choice
(6)

ዘርፈ ብዙ የሕግ አገልግሎት የሚያገኙበት ደረጃውን የጠበቀ የሕግ ቢሮ ነው:: Legal Service provider in Addis Ababa, Ethiopia. 🇪🇹

16/06/2026

“የቤት ኪራይ ዋጋን የማስተካከል ሥልጣን ያለው መንግሥት ብቻ ነው”

📌የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በሕገ-ወጥ መንገድ ኪራይ በሚጨምሩ አከራዮች ላይ ጠንካራ
እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ

| የኪራይ ውል ምዝገባ የሕግ ገደብ ሰኔ 30 ቀን መቃረቡን ተከትሎ፣ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያለአግባብ የቤት ኪራይ ዋጋ በሚጨምሩ እና ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ተከራዮችን በሚያባርሩ አከራዮች ላይ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ቢሮው ይህንን ማሳሰቢያ የሰጠው፣ አከራዮች “ቤቱን ለራሴ ልጠቀምበት ነው” ወይም “ልሸጠው ስለፈለግኩ” የሚሉ ምክንያቶችን በመደርደር ተከራዮች እንዲለቁ እያስገደዱና ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እየጠየቁ ነው የሚሉ ሪፖርቶች ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ከደረሱ በኋላ ነው።

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ እንደገለጹት፣ መዲናዋ የቤት ኪራይ ገበያውን ለማረጋጋት በሚያስችል መልኩ የተደራጀ ሥርዓት ዘርግታለች። በዚህም መሠረት የቤቱን አቀማመጥ፣ ዝርዝር መገለጫዎች፣ የኪራይ መጠን እና የተከራዮችን ማንነት የሚያካትት መረጃ የያዘ ማዕከላዊ የመረጃ ቋት (ዳታቤዝ) ተዘጋጅቶ ወደ 500 ሺህ የሚጠጉ የኪራይ ቤቶች ተመዝግበዋል።

ኃላፊዋ አክለውም የቤት ኪራይ ውል በሕግ የተቀመጠው ቢያንስ ለሁለት ዓመታት እንዲያገለግል ተደርጎ መሆኑን ገልጸው፣ አከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ብቻ የኪራይ ዋጋን መለወጥ እንደማይችሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

“የቤት ኪራይ ዋጋን የማስተካከል ሥልጣን ያለው መንግሥት ብቻ ነው” ያሉት ወይዘሮ ቅድስት፣ ዓመታዊ የዋጋ ማሻሻያዎች የሚደረጉትም በይፋዊ የገበያ ጥናቶች እና በማክሮ-ኢኮኖሚ አመልካቾች ላይ ተመስርቶ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባለፈው ግምገማ መሠረት በበጀቱ ዓመት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ እንዳልተፈቀደ ያስታወሱት ኃላፊዋ፣ ለሚቀጥለው የኪራይ ዘመን ማስተካከያ ያስፈልግ እንደሆነ ለመወሰን አሁን ላይ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም መንግሥት ይፋዊ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ አከራዮች ተጨማሪ ክፍያ የመጠየቅ መብት የላቸውም።

ቢሮው ተከራዮች ሕጋዊ መብቶቻቸውን እንዲያስከብሩና ጥሰቶችን እንዲያሳውቁ ጥሪ አቅርቧል። ከቤት ኪራይ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችና አለመግባባቶች ሲፈጠሩም ከወረዳ ጽሕፈት ቤቶች ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ አስተዳደሮች፣ አልፎ ተርፎም እስከ ማዕከላዊው የቤቶች ቢሮ ድረስ ባለው ደረጃ በደረጃ በተዘረጋው የቅሬታ ማቅረቢያ ሥርዓት መሠረት ማቅረብ እንደሚቻል አስታውቋል።

12/06/2026

የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በሽያጭ ወይም በስጦታ ማስተላለፍን በተመለከተ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች

ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም

1) በስጦታ፣ በሽያጭ ወይም በሌላ መንገድ ተገልጋዮች ንብረት
ለማስተላለፍ ሲመጡ ካርታው ከጀርባው የተረጋገጠ መሆን አለበት፡፡ ካርታው ዲጂታል ከሆነ የጀርባ ማህተም አያስፈልገውም፡፡

2)በካርታው ከጀርባ ላይ ንብረቱ በውርስ የተገኘና የወራሾች ዝርዝር የተፃፈበት ከሆነ ተጨማሪ ማስረጃ ማየት ሳያስፈልግ መስተናገድ ይችላሉ፡፡ ሆኖም የንብረቱ መለያ ተጠቅሶ ወራሾች መሆናቸው በደብዳቤ ከተገለጸ አገልግሎቱን መስጠት ይቻላል፡፡

3)በውርስ ወይም በስጦታ የተገኘ ንብረትን ለማስተላለፍ ወይም ለማከራየት የጋብቻ ማስረጃ አይጠየቅም፡፡

4)ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ የተመዘገቡ የሚንቀሳቀሱም ሆነ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የማስተላለፍ ወይም የማከራየት አገልግሎት ማግኘት የሚቻለው ንብረቶቹ በሚገኙበት ክልል/ከተማ አስተዳደር ነው፡፡ ስለሆነም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተቋሙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሊስተናገዱ አይችሉም፡፡ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትም የሚያስተናግደው በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሚመለከተው መ/ቤት የተመዘገቡ ንብረቶችን ብቻ ይሆናል፡፡

5)ከጋብቻ በፊት በተቋሙ ቀርበው የንብረት ማግለል ውል ያደረጉ ወይም በፍ/ቤት ያጸደቁ ተጋቢዎች ንብረታቸውን ለማስተላለፍ ወይም ለማከራየት ሲመጡ የትዳር አጋራቸው ስምምነት አያስፈልግም፡፡ ሆኖም የንብረት ማግለሉ ስምምነት አሁን ጸንቶ ካለው ጋብቻ የትዳር አጋር ጋር የተደረገ ሊሆን ይገባል፡፡

6)አካለ መጠን ላልደረሱ ልጆች ንብረት ለመግዛት የሚቻል ሲሆን ሁለቱም ወላጆች ሊገኙ ይገባል ፡፡ ካልሆነ አባት ወይም እናት ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ከእናትና አባት ውጪ የሆነ ሞግዚት አካላመጠን ባልደረሰው ልጅ ስም ንብረት ለመግዛት በፍ/ቤት የተሰጠ ተጨማሪ ስልጣን ሊቀርብ ይገባል፡፡

7.)ለአካለ መጠን ባልደረሰው ልጅ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ ሞግዚቱ እናትና አባትም ቢሆኑም በፍ/ቤት የተሰጠ ተጨማሪ ስልጣን ሊቀርብ ይገባል፡፡

8.)ያላገባ ማስረጃ ላይ ቀደም ሲል ጋብቻ ስለመኖሩ የሚጠቁም የጊዜ መረጃ ሲኖር ንብረቱ በጋብቻ ወቅት የተፈራ ሊሆን ስለሚችል ንብረቱ የተፈራበትን ጊዜ የሚያመለክት ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ተጨማሪ ማስረጃ ሊቀርብ ይገባል፡፡

9.)ተነጻጻሪ ካርታ ማለት በአንድ የቦታ ስፋት ውስጥ የተለያዩ ቤቶችና ባለመብቶች ያሉበትና በተለያዩ ሰዎች ሊያዝ የሚችል ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ይዞታ ላይ የባለቤትነት መብት ያለው ሰው የራሱን ካርታ በመያዝ ድርሻውን ጠቅሶ መሸጥ ይችላል፡፡

10)ካርታ ላይ የሚጠቀሰው ቀን ካርታው የተሰጠበትን ቀን እንጂ ንብረቱ የተፈራበትን ቀን በቀጥታ ላያመለክት ይችላል፡፡ ስለሆነም ንብረቱ የተፈራበትን ቀን ለማወቅ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የንብረቱ ባለቤት ተጨማሪ ማስረጃ እንዲያቀርብ መደረግ አለበት፡፡ ለምሳሌ ከመሬት አስተዳደር ለገቢዎች እና ለካርታው ባለቤት የሚሰጡ ደብዳቤዎችን አያይዞ መስራት ይቻላል፡፡

11) የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭም ሆነ በስጦታ ለማስተላለፍ የፍቺ ውሳኔ ይዘው የሚቀርቡ ባለጉዳዮች ንብረቱ የጋራ ወይም የግል ስለመሆኑ በፍርድ ቤት የጸደቀ የንብረት ክፍፍል ስምምነት ወይም ውሳኔ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

12)ንብረት በስጦታ ለማስተላለፍ የተሠጠ የውክልና ሥልጣን ስጦታው ለማን እንደሚሰጥ እና ንብረቱ ምን አይነት እንደሆነ በውክልናው ላይ በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡ ነገር ግን በውክልና ስጦታ ለመቀበል ሲሆን ስጦታ ይቀበልልኝ የሚለው አገላለጽ በቂ ነው፡፡

13) የጋራ ንብረት በሽያጭ በሚተላለፍበት ጊዜ ገዢው ከንብረት ተጋሪው ውጪ የሆነ እንደሆነ የተጋሪው የቅድሚያ መግዛት መብት መጠበቁን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሆን ተጋሪውን ምስክር በማድረግ፣ የሚንቀሳቀስ ንብረት ሲሆን ተጋሪው ማረጋገጫ እንዲሰጥ ማድረግ ይቻላል፡፡

14) የማይንቀሳቀስ ንብረት ገዢው የውጭ ሃገር ዜጋ ከሆነ የታደሰ በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ወይም በኢንቨስትመንት አዋጁ መሠረት ቢያንስ አሥር ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ በሥራ ላይ ማዋሉን የሚገልጽ ማስረጃ እና የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሊቀርብ ይገባል፡፡

የማይንቀሳቀስ ንብረት ገዢው የውጭ ሃገር ዜጋ ሌላ የመኖሪያ ቤት በስሙ የሌለ ስለመሆኑ የሚገልጽ ከሚመለከተው የንብረት መዝጋቢ አካል ማስረጃ ማቅረቡን እንዲሁም ከተቋሙ የመረጃ ቋት ማጣራት ያስፈልጋል፡፡

Address

CMC, Addis Ababa
Addis Ababa
42088

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሕግ አገልግሎት / Legal Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share