Legality and morality

Legality and morality Working For strong social morality and functional legal system
(4)

07/06/2026
05/06/2026

በምዕራብ ሸዋ ዞን ወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት በዳኛ ክብርት ወ/ሮ ወርቄ ፈከንሳ ላይ በደረሰ ጥቃት ህይወታቸዉ ማለፉን አስመልክቶ ከኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠ መግለጫ
-------------------------------
(ግንቦት 27,2018 ኦ/ጠ/ፍ/ቤት)-በዛሬዉ ዕለት በምዕራብ ሸዋ ዞን ወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት የባልና ሚስት ክርክር ተከራካሪ የሆነ ባለጉዳይ የፍርድ ቤቱ ዳኛ የሆኑትን ክብርት ወ/ሮ ወርቄ ፈከንሳ እና በባልና ሚስት ክርክሩ ላይ ተከራካሪ በነበሩ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን (የጥቃት አድራሹ ቀድሞ ባለቤት) ላይ ሽጉጥ በመተኮስ ህይወታቸዉ እንድያልፍ ካደረገ በኋላ በራሱም ላይ በተደጋጋሚ በመተኮስ ቆስሎ ሆስፒታል እንደሚገኝ ማረጋገጥ ተችሏል።ግለሰቡ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ፍርድ ቤቱ አዲስ ባስገነባው ህንፃ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ለመስጠት እንቅስቃሴ እያደረገ ባለበትና በከፊል አገልግሎት በጀመረበት ሁኔታ ውስጥ ልያጋጥም የሚችልን የደህንነት ክፍተት ተጠቅሞ መሆኑ ግምት ተወስዷል።በዛሬዉ ዕለት ከተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ጋር ተያይዞ ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ የተጀመረባቸው ሲሆን በክብርት ዳኛ ወርቄ ፈከንሳ ላይ የደረሰዉ አሳዛኝ ጥቃት በየትኛዉ መመዘኛ ተቀባይነት የሌለዉና የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች ማህበረሰብንና መላዉን ህብረተሰብ ያስደነገጠና ልብ የሰበረ ድርጊት ሆኗል።በተጨማሪም የቀድሞ የትዳር አጋሩን በእንደዚህ አይነት መልኩ ህይወቷ እንድያልፍ ማድረጉ በጣም የሚያሳዝን ድርጊት ሲሆን የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክብርት ዳኛ ወርቄ ፈከንሳ ላይ በደረሰ አሳዛኝ አደጋ የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል።ከወንጀል ድርጊቱ ጋር በተያያዘ የተጀመሩ ምርመራዎችንና ወደፊትም ሊጀመሩ የሚችሉ ምርመራዎችን ተከታትሎ ለህዝቡ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ይገልፃል።

05/06/2026

Ajjeefamuu Abbaa Seeraa Mana Murtii Aanaa Walmaraa,Aadde Warqee Fakkansaa, Ilaachisee Ibsa Mana Murtii Waliigalaa Oromiyaa Irraa Kenname
-------------------------------------------
(Caamsaa 27,2018 MMWO, Caffee Araaraa, Finfinnee)-Guyyaa har'aa Godina Shawaa Lixaa, Mana Murtii Aanaa Walmaraatti abbaan dhimmaa falmii abbaa manaa fi haadha manaa mana murtichaa irraa qabu Abbaa Seeraa Mana Murtii Aanaa Walmaraa kan ta'an Aadde Warqee Fakkansaa akkasumas haadha manaa isaa kan turanii fi falmii qoodinsa qabeenyaa isa waliin gaggeessaa jiran Aadde Almaaz Makonninitti shugguxii dhukaasuun lubbuun isaanii akka darbu kan taasise yammuu ta'u, ofii isaattis irra deddeebiin dhukaasuun yeroo ammaa kana hospitaalatti kan argamu ta'uun mirkanaa'ee jira. Gochaan kun kan raawwatame yeroo manni murtichaa gamoo haaraa eebbisiisee gamiisaan hojii itti eegalaa jirutti yammuu ta'u, yeroo ammaa kana yakka raawwatameen wal qabatee namoonni dabalataa shakkaman to'atamanii qorannoon gaggeeffamuu eegalee jira. Gochaan suukanneessaan Abbaa Seeraa Aadde Warqee Fakkaansaa irratti raawwatame haala kamiinuu fudhatama kan hin qabnee fi hawaasa manneen murtii fi hawaasa magaalichaa laphee kan cabsedha.Dabalataanis haadha warraa isaa waggoota dheeraaf waliin jiraatanii fi wal himatanii addaan bahan dubartii ulfoo akkaataa kanaan lubbuu dabarsuun heddu kan nama gaddisiisudha. Manni Murtii Waliigalaa Oromiyaa gochaa suukanneessaa abbaa seeraa Aadde Warqee Fakkansaa irra qaqqabeen gadda itti dhagayame ibsaa, maatii fi firoottan isaaniif jajjabina hawwa.Gochaa yakka raawwatameen wal qaabatee qorannoowwan gaggeeffamuu eegalanii fi gara fuula duraati gaggeeffamanii seeraan ilaalaman adeemsaan kan ifoomsu ta'uus beeksiseera.

04/06/2026

የሀዘን መግለጫ
››››››››››››››››››››››››››
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩት ክቡር አቶ ሺመክት አሰፋ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ግንቦትት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል::
ክቡር አቶ ሺመክት አሰፋ ከመጋቢት 15 2003 ዓ.ም ጀምሮ በሞት እስከተለዩበት እለት ድረስ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት ተሹመው ሲያገለግሉ ቆይተዋል::
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ለመላው ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

26/05/2026
24/05/2026
19/05/2026

ቋሚ የመንግሥት ሠራተኛ ሆኖ ለመቀጠር ምን ያስፈልጋል?

1. በቋሚ መንግሥት ሠራተኛነት ለመቀጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች

የሚከተሉት በቋሚ መንግሥት ሠራተኛነት ለመቀጠር የሚያስችሉ ምክንያቶች ናቸው፡
ሀ. ዕድሜ 18 ዓመት እና በላይ፣ 60 አመት በታች የሆነ ሰው፣

ለ. የሙስና፣ የእምነት ማጉደል፣ የስርቆት፣ የማጭበርበር ወይም አስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተፈረደበትን ቅጣት ካጠናቀቀ በኋላ አምስት ዓመት ያለፈው እና በፍርድ ቤት የተሰየመ ማንኛውም ሰው፣

ሐ. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 (ለ) የተመለከተውን የፍርድ ቅጣት በይርጋ ከታገደ ወይም በይቅርታ ከተሠረዘ በኋላ አምስት ዓመት ያለፈው ማንኛውም ሰው፣
መ. የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ያለው ወይም በመስተዳድር ምክር ቤት ደንብ በሚወሰነው ጊዜ ገደብ ማስረጃው የታደሰ ሰው፣
ሠ. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 31 መሠረት ቃለ መሀላ ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ ሰው፡፡

2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) (ለ) እንደተጠበቀ ሆኖ ከማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፩፻፵ መሠረት በዲስፕሊን ጉድለት ምክንያት ከሥራ የተሰናበተ ሰው የባህሪው መሻሻል ተረጋግጦ ከሥራ ከተሰናበተበት ጊዜ ጀምሮ አምስት ዓመት ከሞላበት ቀን ጀምሮ በመንግሥት ሠራተኛነት መቅጠር ይቻላል፡፡

3. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) (ሐ) እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም አመልካች በመንግሥት ሥራ ተቀጥሮ ለማገልገል ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምርመራ በስተቀር የጤንነት ማረጋገጫ የሕክምና ምርመራ ከጤና ተቋም እና በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (1)(ለ) ከተጠቀሱት ወንጀሎች ነጻ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከፖሊስ የተሰጠ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

Address

Debrezeyt Road
Addis Ababa
AKAKIKALITY

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Legality and morality posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Legality and morality:

Share