Ethiopian Law Group - የሕግ ቢሮ

Ethiopian Law Group - የሕግ ቢሮ «Jurisprudence ማለት ሕግ የተባለች ኮረዳ ፖለቲካ በሚባል ጎረምሳ በአይን ስትጠቀስ የምታሳየው የመሽኮርመም አፍታ ነች»

01/09/2015

#ችሎት - እውነተኛ ገጠመኞች

(1)
ልጁ በሸንኮራ አገዳ የመኪና የጎን መብራት በመስበር ይከሰስና ፍርድ ቤት ይቀርባል። ኋላ ላይ ዳኛዋ ሲጠይቁት «ኧረ እኔ ሸንኮራ የሚባል አልያዝኩም - ገና ሸንኮራ ልገዛ እየሄድኩ ነበር . . .» ሲል ይመልሳል።
ዳኛዋ ወደ ምስክሩ ዞረው «አንተ ያየኸው ምንድነው?» ሲሉ ይጠይቁታል።
ምስክሩም « የተከበሩ ዳኛ ሸንኮራ ይዞ ነበር። ከዚያ በሸንኮራው የመኪናውን የጎን መብራት ሰብሮ አለፈ። ፖሊስ ጣቢያ ከደረሰ በኋላ ነው እንደውም ሸንኮራውን የበላው» በማለት ይመልሳል።
ዳኛዋም ወደ ተከሳሹ ዞረው «ኤግዚቢቱን በላኸው ማለት ነው?»
- - - - - -

(2)
ለምስክርነት የቀረቡት ሴት እድሜያቸው የገፋ አሮጊት ናቸው። ምስኪንነታቸው ከፊታቸው የሚነበብና በጣም የሚያሳዝን ገጽታ ያላቸው ሴትዮ ነበሩ። ከምስክር ወንበር ላይ ተቀምጠው ሌሎች ሃተታዎች ከተነገራቸው በኋላ ጥያቄ ይጠየቁ ጀመር፦
ዳኛዋ ፦ እድሜዎት?
እሳቸው፦ 25
በችሎት የታደመው ሰው ሁሉ ሳቀ። ዳኛዋም የታፈነ ሳቃቸውን እንደምንም በፈገግታ ሸፍነው አሳለፉ ። እማማ ተሸማቀቁ። እኔን! አልኩ በልቤ። የሰዉን መሳቅ አይተው የተሸማቀቁት እማማ ያጠፉት አንድ ጥፋት እንዳለ ተሰምቷቸው እሷን ሊያስተካክሉ የተናገሯት ነገር ሌላ ሳቅ ፈጠረች። ከዚያ በኋላ ምን እንደተሰማኝ ማስታወስ አልቻልኩም። እማማ ያሉት እንዲህ ነበር ፥
«ካነሰ እጨምራለሁ»

Address

Liberia Street
Addis Ababa
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Law Group - የሕግ ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Law Group - የሕግ ቢሮ:

Share