Mesfin Abebe Legal clinic/Law Office

Mesfin Abebe Legal clinic/Law Office Consultancy &
Advocacy service !

04/09/2025

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 በአከራይ እና በተከራይ መካከል የኪራይ ውሎች የሚፈጸሙት በተቆጣጣሪ አካል በተያዘው ጉዳይ በቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ፊት መሆኑን፤አለመግባባቶች መነሻ ያደረገ አቤቱታ በአከራይም ሆነ በተከራይ በመጀመሪያ ደረጃ ለተቆጣጣሪ አካል እንደሚቀርብ፣በ2ኛ ደረጃ ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እንዲሁም በመጨረሻም በይግባኝ ደረጃ ለፍ/ቤት መሆኑን የአዋጁ ደንጋጌዎች ያስረዳሉ፡፡ሆኖም ውሳኔው በምን አግባብ ሊፈጸም እንደሚችል በአዋጁም ሆነ በመመሪያው ላይ ተገቢ ድንጋጌ የለም፡፡

ይህ ደግሞ በአከራይ እና ተከራይ መካከል የሚነሱ አለመግባባቶች ከዚህ ቀደም ዜጎች ለፍ/ቤት የሚያቀርቡትን አቤቱታ ያስቀረ ነው፡፡

በዚህ ረገድ የቤት ኪራይ ውሎች በተቆጣጣሪ አካል ዘንድ እየተደረጉ መሆኑ አገልግሎት በወቅቱ እስከተሰጠ ጊዜ ድረስ እና አከራይ እና ተከራይ ላይ መጉላላት እስካላስከተለ ድረስ ችግር ያለው አይደለም፡፡በተግባር ግን በአከራይ እና በተከራይ በዚህ ረገድ መጉላላት እየደረሰ መሆኑ በየቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤቶች ያለው ሰልፍ ገላጭ ነው፡፡በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወረዳ ደረጃ ያለው ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ቀሪ በመደረጉ ይህ አገልግሎት እየተሰጠ ያለው በክ/ከተማ ደረጃ በመሆኑ በክ/ከተማ ደረጃ ያለው የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ከዚህ ቀደም በስሩ ባሉ ከ10 ያላነሱ ወረዳዎች ሲሰጥ የነበረው አገልግሎት በክ/ከተማ መወሰኑ አከራይም ሆነ ተከራይ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚኖርበትን ውጣ ውረድ መገመት አያዳግትም፡፡

እንዲሁም ውሉ በተቆጣጣሪ አካል ብቻ ተዘጋጅቶ መቅረቡ መካተት ያለባቸውን የአከራይን እና የተከራይን ሀሣብ እንዳይኖረው የሚያደርግ በመሆኑ በፍ/ብ/ህጉ በጠቅላላ የውል ህግ የተቀመጠውን የተዋዋይ ወገኖች የመዋዋል ነፃነት ላይ ገደብ የጣለ ነው።

ሌላው ከዚህን ቀደም በአከራይ እና በተከራይ መካከል የሚኖር አለመግባት ለፍ/ቤቶች እየቀረቡ ሲታዩ የመጨረሻ ውሳኔ ለመሰጠት ጊዜ የሚፈጅ መሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡ሆኖም ግን ዜጎች ፍትህ አገኛለው ብሎ ከማመን አንጻር ከአስተዳደር አካላት ይልቅ ፍ/ቤትን የሚመርጡበት ሁኔታ መኖሩን ለማወቅ አደጋች አይደለም፡፡ፍ/ቤቶች ለሚሰጡት ዳኝነት የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከህግ አንጻር ለመመዘን የሚያስችል ተቋማዊ አሰራር፣የህግ ስነ ስርዓት፣እንዲሁም ህግን ለመተርጎም የሚያስችል ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ልምድ እና የትምህርት ደረጃ የሚያሟላ ባለሙያ አላቸው፡፡በአስተዳደር አካል የሚሰጥ ዳኝነት ከሚኖረው ፍጥነት ውጪ አንድ ፍትኃዊ ውሳኔ ለመስጠት በፍ/ቤቶች ተሟልቶ የሚገኘውን ሂደት ያሟላ ነው ተብሎ አይገመትም፡፡ከዚህ አንጻር በዚህ አዋጅ አለመግባባት የሚፈታበት መንገድ በቅድሚያ ለአስተዳደር አካላት እና በእነሱ ስር ለተቋቋመ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ መሰጠቱ እንዲሁም የተሠጠውን ውሳኔ ማነው የሚያስፈፅመው የሚለው ጉዳይ በአዋጁ አለመካተቱ በአከራይም ሆነ በተከራይ ላይ እያስከተለ ያለው ችግር መፈተሸ አለበት።

27/09/2024

Enjoy exclusive community benefits!

27/09/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Dawit Woldeamanuel, Mulu Hadush, Bewin Moliso, Etalem Minda, Esam T**i, Tesfaye Tadese, Tilahun Woldetinsae, Tadele Agza, Selamu Selamu, Menegesh Molla, Sh*tahun Asrat, Ahmed Endris, Whaite Gosete, Kebron Daniel, Fikadu Moges

26/09/2024

Check out Mesfin Abebe(Lawyer)’s video.

ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ እቃዎች ላይ ከተጣለው የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመደንገግ በገንዘብ ሚ/ር የወጣ መመሪያ
23/09/2024

ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ እቃዎች ላይ ከተጣለው የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመደንገግ በገንዘብ ሚ/ር የወጣ መመሪያ

22/09/2024
21/09/2024
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሠሚ ችሎት ቀደም ሲል በ5 ዳኞች ተሰጥተው የነበሩ የህግ ትርጉሞች ሆነው በ7 ዳኞች ተለውጠው እንዲሁም ሳይለወጡ  የህግ ትርጉም የተሠጠባቸው  ጉዳዮች
18/09/2024

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሠሚ ችሎት ቀደም ሲል በ5 ዳኞች ተሰጥተው የነበሩ የህግ ትርጉሞች ሆነው በ7 ዳኞች ተለውጠው እንዲሁም ሳይለወጡ የህግ ትርጉም የተሠጠባቸው ጉዳዮች

Federal Supreme Court Cassation Procedure Directive Number 17/2015
24/05/2024

Federal Supreme Court Cassation Procedure Directive Number 17/2015

Address

Ethiopia/Addis Ababa
Addis Ababa
ZIPCODE

Telephone

+251921333788

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mesfin Abebe Legal clinic/Law Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mesfin Abebe Legal clinic/Law Office:

Share