Abnet Law Office

Abnet Law Office AbnetLaw provides a customized and personalized legal services in Addis Ababa, Ethiopia.

15/11/2023
11/09/2023
         #የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 130 እና 131‘’በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 130 ንዑስ አንቀጽ 2 የተዘረዘሩት የወንጀል ክስ መቃወሚያዎች አመላካች (indicative ...
02/04/2023





#የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 130 እና 131

‘’በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 130 ንዑስ አንቀጽ 2 የተዘረዘሩት የወንጀል ክስ መቃወሚያዎች አመላካች (indicative provision) እንጅ ሁሉንም በመቃወሚያነት ሊቀርቡ የሚችሉ ጉዳዮችን በሙሉ የሚዘረዝር (exhaustive provision) ድንጋጌ አይደለም፡፡’’

አንድ የወንጀል ክስ የቀረበበት ተከሳሽ ከሱ ደርሶት ከተነበበለት በዃላ መጀመሪያ የሚጠየቀው ክሱን ይቃወም እንደሆነ ነዉ። ክሱን እቃወማለዉ ለሚል ተከሳሽ ምክንያት የሚሆኑ ጉደሸዮች በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 130 ሰር ተዘርዝረዋል።

ይህም ሆኖ ግን አንድ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ወይም የክስ ማመልከቻውን ለመቃወም የሚችለው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 130 ሰር በተመለከቱት ጉዳዮች ብቻ ነው ተበሎ ሊገደብ አይገባም ሲል ይህ የሰበር ችሎት ወሳኔ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።

የሰበር ችሎቱ ሙሉ ወሳኔ ኮፒን ከሊንኩ ላይ ማዉረድ ይቻላል።

#የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 130 እና 131 ‘’በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 130 ንዑስ አንቀጽ 2 የተዘረዘሩት የወንጀል ክስ መቃወሚያዎች አመላካ.....

       #244   #33(1 እና 2)  #231(1/ሀ)ተከሳሽ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33(2) እና 231(1) መሰረት ያደረገ የመ/ያ ደረጃ መቃወሚያ ሲያቀርብ ብዙ ግዜ ከሳሽ የሆነዉ ወገን “...
02/04/2023




#244 #33(1 እና 2) #231(1/ሀ)

ተከሳሽ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33(2) እና 231(1) መሰረት ያደረገ የመ/ያ ደረጃ መቃወሚያ ሲያቀርብ ብዙ ግዜ ከሳሽ የሆነዉ ወገን “መቃወሚያዉ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 244 መሰረት የሚቀርብና በቁ. 245 መሰረት ተመርምሮ ወሳኔ የሚሰጥበት አይደለም::” የሚል ክርክር ሲያቀርብ ይስተዋላል።

ለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 244 ስር ከተዘረዘሩት ወጪ ያሉ የሕግና የፍሬ ነገር ክርክሮች ላይ በመመስረት የሚቀርብ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እንዴት ሊስተናገድ ይገባል?

ለዚህ ጥያቄ በከፊል መልስ የሚሰጠን #በሰ/መ/ቁ_204199 (የታተመ ቅፅ 25)ነዉ። በዚህ መዝገብ የሰበር ችሎቱ በሰጠው ወሳኔ ላይ

“አንድ ሰዉ በሌላ ሰዉ ሊይ ክስ በማቅረብ በዳኝነት አካል ማስወሰን የሚችለው ክሱ በቀረበበት ሰዉ የተጣሰበት/ የተነካበት በሕግ ወይም በዉል እዉቅና እና/ወይም ጥበቃ ያገኘ መብት ወይም ጥቅም ሊኖረዉ ይገበሸል።(የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33(2 እና 3) ይመለከቷል፡፡) ይሕንንም ከሳሽ በፍሬ ነገር ደረጃ በክስ አቤቱታዉ ሊይ ማሳየት(ማረጋገጥ) ይጠበቅበታል።

በፍሬ ነገር ደረጃ በክሱ ላይ የተገለፀውን በተመለከተ ሌላኛዉ ወገን ክስ በተመሰረተበት ነገር ሊይ ከሳሹ በሕግ እና/ወይም በዉል እዉቅና እና ጥበቃ ያገኘ መብት ወይም ጥቅም የለዉም እንዱሁም የሚያስከስሰኝን ተግባር አልፈጸምኩም ወይም በክሱ የተገለፀው ድርጊት የሚያስከስስ አይደለም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማቅረብ መቃወሚያ አቅርቦ እንዲቃወም ሳይጠብቅ ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት በእራሱ ጊዜ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33(2 እና 3) እና 231(1/ሀ) መሰረት የክስ አቤቱታዉን መርምሮ ተገቢዉን የመወሰን ኃላፊነት አለበት።

እንዱሁም ተከሳሹ ይህንን መከራከሪያ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 244/2 መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ሲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ሥረ ነገሩን የሚመለከት ጭብጥ ከመመስረቱና በጭብጡ ላይ ማስረጃ ከመስማቱ እና ከመመርመሩ በፊት እነደነገሩ ሁኔታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 245/1 መሰረት እንደ አስፈሊጊነቱ ዉሳኔ ለመስጠት ተገቢ ነዉ ያለዉን ማስረጃ አስቀርቦና መርመሮ ዉሳኔ መስጠት ይኖርበታል።”

ብሏል።

ሙሉ ወሳኔው በሚከተለዉ ሊንክ ላይ ይገኛል።

#244 #33(1 እና 2) #231(1/ሀ) ተከሳሽ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33(2) እና 231(1) መሰረት ያደረገ የመ/ያ ደረጃ መቃወሚያ ሲያቀርብ ብዙ ግዜ ከሳሽ የሆነዉ ወገን “መቃ...

ቅፅ 25 የሰበር ችሎት ወሳኔ (የታተመ)
19/01/2023

ቅፅ 25 የሰበር ችሎት ወሳኔ (የታተመ)

It has been a long time since we have posted an update ... we are  back now and will start to update our page regularly ...
20/10/2021

It has been a long time since we have posted an update ... we are back now and will start to update our page regularly soon ... with a new brand and for our third year anniversary.

እውነት ነው ጠፍተን ነበር! .. አሁን ግን ተመልሰናል! በአዲሰ ብራንድና አቀራረብ ከሦስተኛው ዓመት ክብረ በዓላችን ጋር አያይዘን በቅርቡ በመደበኛነት እንመለሳለን።

Q&A: Conflict in Ethiopia and International Law
28/11/2020

Q&A: Conflict in Ethiopia and International Law

The following question-and-answer document focuses on existing and emerging international law issues in the Ethiopia conflict. In accordance with Human Rights Watch’s institutional mandate, the organization maintains a position of neutrality on issues concerning the legitimacy of resorting to arme...

17/07/2020

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከሀምሌ 13/2012 ዓ.ም ጀምሮ ስለሚሰጡ ተጨማሪ የዳኝነት አገልግሎቶች የተሰጠ መግለጫ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የኮሮና ቫይረስ (Covid-19) ወረርሽኝ በሀገራችን መኖሩ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል ዝግ በመሆን እና የከፊል ዝግ ውሳኔውን በማራዘም እስከ ሐምሌ 10/2012 ዓ.ም ድረስ በፍ/ቤቱ አመራር በተለዩ ጉዳዮች ላይ ብቻ አገልግሎት እየሰጡ ቆይተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባህሪና ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ወረርሽኙ በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ውስጥ ልናስገባውና ስርጭቱን ሙሉ በሙሉ ልንገታው የማንችል መሆኑን እንዲሁም አብሮን በተግዳሮትነት የሚቀጥል እንደሆነ ማስረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቶችን በከፊል በመዝጋት የዜጎች ፍትህ የማግኘት መብትን በውል ላልታወቀና ለተራዘመ ጊዜ ማቆየት የማይቻል መሆኑን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ከኮቪድ በኋላ ፍርድ ቤቶች መደበኛ ስራቸውን ይጀምሩ በሚባልበት ጊዜ ወደ ፍ/ቤት ሊመጣ የሚችለው ከፍተኛ የመዛግብት ፍሰት ፍርድ ቤቶች ስራቸውን መስራት የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሊያስገባቸው እንደሚችል በፍርድ ቤቱ የተከናወነው የመላምት ትንታኔ ያሳያል፡፡ ለእነዚህ ሁለት አበይት ችግሮች መፍትሄ መስጠት ያስችል ዘንድ ወረርሽኙን በከፍተኛ የመካላከልና የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ የተቋረጡትን አገልግሎቶች ደረጃ በደረጃ ማስጀመር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ስለሆነም ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩ ከተደረጉበት ከሃምሌ 13 ቀን 2012 ዓ.ም በኋላ ደረጃ በደረጃ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ስለሚጀምሩበት ሁኔታ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 16 (1) እና በዚሁ አዋጅ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 4 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መመሪያ አውጥቷል፡፡

በመመሪያው መሰረት በየደረጃው ባሉ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከሃምሌ 13 2012 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጡ አገልግሎቶች እና የሚወሰዱ አስገዳጅ እርምጃዎች የሚከተሉት ይሆናሉ፡፡

1. ከሐምሌ 13 - 30 /2012 ዓ.ም የሚሰጡ አገልግሎቶች
 በሁሉም ደረጃ ባሉት ፍ/ቤቶች መልስ፣የመልስ መልስ፣ አስተያየቶች ፣የትዕዛዝ ውጤቶች ለመቀበል የተቀጠሩ፣ እልባት ለመስጠት ጥቂት ሂደት ብቻ የሚቀራቸው ጉዳዮች እንዲሁም እስረኛ ያላቸው መዛግብት በየቀጠሮ ቀናቸው የማስተናገድ፤
 ማስረጃ ለመስማት' ክስ ለመስማት የተቀጠሩ መዝገቦች በጣም አስቸኳይነታቸዉ በዳኛው፣ በየፍርድ ቤቱ በየደረጃው በሚገኝ አመራር እስካልታመነ ድረስ ለቀጣይ የ2013 በጀት ዓመት የሚቀጠር ይሆናል ሆኖም ግን ከዚህ በፊት በተሰጡት መመሪያዎች መሰረት ሲከናወኑ የነበሩ ተረኛ ችሎቶችን በማደራጀት በአመራሩ የተለዩ ወሳኝ እና አንገብጋቢ ጉዳዮች በተለይም ከዜጐች የሰብዓዊ መብት ጋር የተቆራኙ ጉዳዮችን፣ ከቤት ውስጥ ጥቃት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን፣ እግድ፣ በስምምነት ፍች፣ ጥፋት ውስጥ ገብተው የተገኙ ወጣቶች (ወጣት ጥፋተኞች)፣ የልጆች አስተዳደግ እና ቀለብን የመሠሉ የቤተሰብ ጉዳዮች፣ አፋጣኝ የወንጀል ጉዳዮች (RTD) ከአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አፈፃፀም ጋር የተያያዘ የወንጀል ጉዳዮችን፣ በስምምነት ክስን ማቋረጥ፣ ከትላልቅ ሜጋ ኘሮጀክቶች ጋር የተያያዙ የንግድ ኢንቨስትመንት ጉዳዮች፣ ከሀገር ፀጥታ እና ሠላም ጋር የተያያዙ የወንጀል ጉዳዮች እንዲሁም ብዙ ተካራካሪ የሌላቸው መዛግብትን የሚስተናገዱ ሲሆን በመደበኛ ችሎት ሲስተናገዱ የነበሩ የስራ ክርክር፣ የሴቶች እና ህፃናት ችሎቶች፣ የሁከት እና ሌሎች የአስተዳደር ጉዳዮች በመደበኛ ችሎት ዳኞች በየቀጠሯቸው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
 በየደረጃው ያሉ የፍርድ አፈጻጸም ችሎቶች በአጭርና በቀላሉ የሚፈፀሙ የአፈፃፀም ጉዳዮችን ማስተናገድ የሚጀምሩ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተያያዘም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ከሐምሌ 13/2012ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ስራውን የሚጀምር ሲሆን በፍርድ አፈፃፀም ምክንያት ከመኖሪያ ቤት ማስለቀቅ፣ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ማጫረት ማካሄድ ውስብስብነት ያላቸውና የሰዎች መሰባሰብ የሚጠይቁ የአፈፃፀም ጉዳዮች ተለዋጭ የስራ አቅጣጫ እስከሚሰጥ ድረስ ባሉበት ደረጃ እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡
 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአዲስ አበባ ከሚገኙ ባለጉዳዮች የሚቀርቡ የሰበር አቤቱታዎችን የሚያሥተናግድ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከአዲስ አበባ ውጪ የሚገኙ ባለጉዳዮችን በዚህ ወቅት ማስተናገድ ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ያላቸውን ተጋላጭነት የሚጨምር መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የወረርሽኙ ስርጭት አስጊነት በቀነሰና ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ የስራ አቅጣጫ በሚሰጥበት ጊዜ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
 በሁሉም ፍርድ ቤቶች የምርመራ መዛግብት የማጥራት ተግባር በተጨማሪነት የሚከናወን ይሆናል፡፡

2. በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም የሚሰጡ አገልግሎቶች
 በሁሉም ደረጃ ባሉት ፍ/ቤቶች አዲስ መዝገቦችን ማለትም ቀጥታ ክስ፣ ይግባኝ እና አፈፃፀም መዝገቦችን የመክፈት አገልግሎት ይጀመራል፡፡
 ዳኞች በየዓመቱ በነሐሴ ወር እረፍት የሚወስዱ የነበረ ቢሆንም ወደፊት በዳኝነት ስራ ላይ የሚፈጠረውን የስራ ጫና ለማቃለል እንዲረዳ ዳኞች በስራ ገበታቸው በመገኘት አዲስ የሚከፈቱ መዝገቦችን በመመርመር በጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መርህ መሰረት ቀጠሮ ወይም ተገቢውን ትእዛዝ የሚሰጡ ይሆናል፡፡
 አስቸኳይነት ያላቸው ጉዳዮች ማለትም ቀደም ሲል በተረኛ ችሎት ሲስተናገዱ የነበሩ ጉዳዮች በተረኛ ችሎት መስተናገዳቸውን ይቀጥላሉ፡፡
 የምርመራ መዛግብት የማጥራት ስራ በተጨማሪነት የሚከናወን ይሆናል፡፡
3. በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም የሚሰጡ አገልግሎቶች
 የመስከረም ወር 2013ዓ.ም የዳኞች የእረፍት ጊዜ ይሆናል፡፡
 አስቸኳይ ጉዳዮች ማለትም በተረኛ ችሎት ሲስተናገዱ የነበሩ ጉዳዮች እስከ መስከረም 30/2013ዓ.ም በተረኛ ችሎት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

ፍርድ ቤቶች አብዛኛውን አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ተከትሎ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሁሉም ፍርድ ቤቶች በአስገዳጅነት ሊተገበሩ የሚገባቸዉ የጥንቃቄ እርምጃዎች
1. በቀጣይ የሚሰጡ አገልግሎቶች ቢያንስ ሁለት ሜትር ርቀትን በጠበቀ ሁኔታ እንዲከናወን ማድረግ፤
2. ሰራተኞችም ይሁኑ ተገልጋዮች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ እንዲጠቀሙ ማድረግ፤
3. ለፍ/ቤቱ ማህበረሰብና ለተገልጋይ የሚያገለግሉ የንፅህና መጠበቂያ ግብአቶችን እንደ የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ውሃ፣ ሳሙና፣ አልኮል እና ሳኒታይዘር የመሳሰሉትን ማሟላትና እንዲጠቀም ማድረግ፡፡
4. ተገልጋይም ሆነ የፍ/ቤቱ ማህበረሰብ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊት የሙቀት መጠን እንዲለካ ማድረግና የሙቀት መጠኑ ከ38 ዲግሪ በላይ ከሆነ ተለይቶ ማቆየት እና በአቅራቢያው ለሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ማሳወቅ፡፡
5. በየእለቱ ቀጠሮ ካላቸዉ ተከራካሪ ወገኖች እና የፍ/ቤቱን ሌሎች አገልግሎት ፈልገው የሚመጡ ባለጉዳዮች ብቻ ወደ ፍ/ቤቱ ግቢ እንዲገቡ ማድረግ፡፡
6. በየደረጃው ባሉ ፍ/ቤቶች በሚወሰን ግዜ በመደበኛነት የኮቪድ 19 ተጋላጭነት ለመከላከል የፀረ-ተሀዋሲያን ርጭት ማከናወን፡፡
7. የፍ/ቤቱ አመራር የሚያወጣቸውን ተጨማሪ የጥንቃቄ እርምጃዎች በጥብቅ መተግበር ይሆናል፡፡
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል በጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክሮችን በጥብቅ በመተግበር ከወረርሽኙ ራሳችንን፤ ቤተሰቦቻችንንና ሃገራችን ከችግር እንታደግ!!
----------------------- // ----------------------------

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Address

Liberia Street, Lideta Merkato Mall, 3rd Floor, Office No. 364
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 18:00
Tuesday 09:00 - 18:00
Wednesday 09:00 - 18:00
Thursday 09:00 - 18:00
Friday 09:00 - 18:00
Saturday 09:00 - 13:00

Telephone

+251953946040

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abnet Law Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abnet Law Office:

Share