Justice 4 ALL

Justice 4 ALL Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Justice 4 ALL, Lawyer & Law Firm, Addis ababa, Addis Ababa.

02/08/2024

የውጭ ምንዛሬን ማን፤ መቼ፤ እንዴት፤ ለምን... መያዝ፤ መሸጥ እንዲሁም መግዛት ይችላል?

- ከኢትዮጵያ ወደ ሌላ ሀገር የሚጓዝ ወይም ከሌላ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ሰው ከ3,000 የኢትዮጵያ ብር በላይ በጥሬው መያዝ አይችልም።

- ወደ ጅቡቲ ወይም ወደሌላ የጎረቤት ሀገር ወደብ ከተሞች የሚጓዝ ሰው እስከ 10,000 የኢትዮጵያ ብር መያዝ ይችላል።

- በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው ወደ ግዛት ክልሏ ሲገባ በጉዞ ሰነዱ ላይ በስደተኞችና በዜግነት አገልግሎት ማህተም ተረጋግጦ የገባበት ቀን ተብሎ ከሚጠቀሰው ቀን አንስቶ በ30 ቀናት ውስጥ የያዘውን የውጭ ሀገር ገንዘብ ፍቃድ ባላቸው የምንዛሪ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት የመመንዘር ወይም በባንክ በስሙ በተከፈተ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት።

- ሆኖም ግለሰቡ የያዘው ሊመነዘር የሚችል የውጭ ሀገር ገንዘብ ከ10,000 የአሜሪካን ዶላር እኩል ወይም በላይ ከሆነ የውጭ ሀገር ገንዘቡ በውጭ ሀገር ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማድረግ አለበት። ገቢ ሲያደርግም የጉምሩክ ዲክላሬሽን ወይም ወደ ሀገር የገባ የውጭ ሀገር ገንዘብ ማሳወቂያ መግለጫ ሰነድ ማቅረብ አለበት።

- ግለሰቡ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ዜጋ ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ ማይኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከሆነና ከዘጠና ቀናት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የመቆየት ሀሳብ ካለው፤ የያዘውን የውጭ ሀገር ገንዘብ በሙሉ በጉዞ ሰነዱ ላይ ከሚጠቀሰው ወደ ሀገር የገባበት ቀን ጀምሮ በዘጠና ቀናት ውስጥ በውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳቡ ገቢ ማድረግ አለበት።

- ከ10,000 ዶላር በላይ የውጭ ሀገር ገንዘብ ይዞ ከሆነም ገንዘቡን በውጭ ምንዛሪ ሂሳቡ ገቢ ሲያደርግ ወይም በሕጋዊ መልኩ ሲመነዝር የጉምሩክ የውጭ ምንዛሪ ማሳወቂያ ሰነድ ማቅረብ አለበት።

- ወደ ውጭ ሀገር የሚጓዝ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ሰው ከተፈቀደላቸው የምንዛሪ አገልግሎት ሰጪዎች የገዛው የውጭ ሀገር ገንዘብ ካለ የገዛበት ደረሰኝ ላይ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ይዞ ማቆየት ይችላል።

- ከኢትዮጵያ ጋር ድንበር ከሚጋሩ የጎረቤት ሀገራት በየብስ መጓጓዣ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ማንኛውም ሰው በድንበር ላይ ላለ የጉምሩክ ቅርንጫፍ ወይም ጣቢያ ከ500 የአሜሪካ ዶላር ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ወይም ከዛ በላይ ሌላ የውጭ ሀገር ገንዘብ ከያዘ የያዘውን የገንዘብ መጠን የጉምሩክ የውጭ ምንዛሪ ማሳወቂያ መግለጫ ላይ በመሙላት ማሳወቅ ያለበት ሲሆን፤ ይህንኑ ያሳወቀውን የውጭ ሀገር ገንዘብ መጠንም ጉዳዩን ጨርሶ ሲመለስ ይዞ መውጣት ይችላል።

- በብሔራዊ ባንክ ወይም አግባብ ባለው ሕግ ካልተፈቀደለት በስተቀር ማንኛውም ሰው የውጭ ሀገር ገንዘብ በጥሬው በስጦታም ሆነ በእርዳታ ወይም ለግብይት ክፍያ ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ ወይም መክፈል አይችልም።

- በብሔራዊ ባንክ ፍቃድ በዚህ መመሪያ ወይም በሌላ ሕግ በተፈቀደው መሰረት ካልሆነ በቀር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የውጭ ምንዛሪ መያዝ አይፈቀድም።
የመረጃው ምንጭ
www.ethiopianlegalinsight.com
https://t.me/Ethiopianlegalinsight

ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሜዳሊሊያዋን አሳካችበፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሜዳሊሊያዋን በወንዶች 10 ሺህ ሜትር አሳካች።አትሌት በሪሁ አረጋዊ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኝቷል።በርቀቱ ...
02/08/2024

ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሜዳሊሊያዋን አሳካች

በፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሜዳሊሊያዋን በወንዶች 10 ሺህ ሜትር አሳካች።

አትሌት በሪሁ አረጋዊ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኝቷል።

በርቀቱ የዓለም ሻምፒዮኑ ዩጋንዳዊው ጆሽዋ ቼፕቴጌ የኦሎምፒክ ክብረ ወሰንን በማሻሻል ጭምር ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ አሰገኝቷል።

አሜሪካዊው ግርሀም ፊሸር ሶስተኛ በመውጣት ለሀገሩ ነሐስ አስገኝቷል።

የወቅቱ ሻምፒዮን ሰለሞን ባረጋ ሰባተኛ እንዲሁም ዮሚፍ ቀጀልቻ ደግሞ ስድስተኛ ሆነው ጨርሰዋል።
ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንኳን ደስ አላችሁ።

02/08/2024

ትዕዛዝ አላከበሩም የተባሉ የፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል እና የእስረኞች አሥተዳደር ኃላፊዎች ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍርድ ቤት ትዕዛዝን አላከበሩም የተባሉ የፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል እና የእስረኞች አሥተዳደር ኃላፊዎች ተቀጡ፡፡

የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ነው።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ፍስሀ ጀንበሩ በወንጀል ተጠርጥረው በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ፍርድ ቤት ቀርበው በተሰጣቸው የዋስትና መብት ከእስር እንዲፈቱ የታዘዘላቸው ተጠርጣሪዎችን ባለመፍታት እና የፍርድ ቤት ትዕዛዝን ባለማክበር ምክንያት ተከሳሾቹን ለምን ከእስር እንዳልፈታ ችሎት ቀርቦ እንዲያስረዳ ሲታዘዝ ባለመቅረቡና ተገቢውን መልስ ባለመስጠቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስላላከበረ በአንድ ወር እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል።

እንዲሁም በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእስረኞች አሥተዳደር ኃላፊ ሳጅን ኢብራሂም አብዲሚኖኒ በጊዜያዊ የእስረኞች ማቆያ የነበሩ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በሕገ-መንግስቱ የተሰጣቸውን ከቤተሰብ ጋር የመገናኘት መብታቸው እንዲከበርና እንዲገናኙ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትዕዛዝ ባለማክበር በአንድ ወር ደሞዝ እንዲቀጣ ተወስኗል።
የመረጃው ምንጭ
ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Email- nurotekore@gmail. Com

21/07/2024

በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ11 ዓመቷን ታዳጊ ልጁን የደፈረ አባት በፅኑ እስራት መቀጣቱ ተነገረ

ሐምሌ 13 ቀን 2016 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ11 ዓመት ታዳጊ ልጁን የደፈረው አባት በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡

በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሰፋቶ ቀርሳ ቀበሌ ልዩ ስሙ ከዊሶ ተብሎ በሚጠራው መንደር ነዋሪ የሆነዉ ተከሳሽ ሙሂዲን ወራቄ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም ቀንና ሰዓቱ በውል ባልታወቀባቸዉ የተለያዩ ጊዜያት የግል ተበዳይ የሆነችውን የ11 ዓመት ህፃን ልጁን ተደጋጋሚ የሆነ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል እንደፈፀመባት የተከሳሹ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

ተከሳሽ ጋብቻ እየመሰረተ ሲፈታ ከሶስት ጊዜ በላይ ትዳር መስርቶ ፍቺ የፈፀመ ሲሆን የደረሱ ልጆቹንም ድሮ የልጅ ልጅ ለማየት በቅቷል ነዉ የተባለዉ።
የግል ተበዳይዋ በወላጆችዋ መለያነት ምክንያት ወደ ሌላ አካባቢ ሄዳ በሰራተኝነት ከተቀጠረችበት አዲስ አበባ ወደ ከዊሶ የተመለሰችዉ በብቸኝነት የሚኖረዉን አባቷን ለመደገፍ እሳቤ ስለነበራት ነዉ ተብሏል።

አባቴን ትቼ የትም አልሄድም ስትል ከወላጅ አባቷ መኖር የጀመረችዉ ታዳጊ በወላጅ አባቷ ጭካኔና የነዉረኝነት ባህሪ የደረሰባትን በደል ለመንገር ወደ ወላጅ እናቷ አቀናች።አቅንታም አባቴ የነገዉን ህይወቴ አጨልሞታል ስትል ተደጋጋሚ የሆነ የአስገድዶ መደፈር የፈፀመባት መሆኑ ለወላጅ እናቷ አረዳቻት።

ከልጇ በሰማችዉ ነገር አንጀቷ የበገነዉ ወላጅ እናት ፈጥና ወደ ወረዳዉ ሴቶች ጉዳይ ጽህፈት ቤት አቅንታ ሰዉየዉ ለፍርድ ይቀርብ ዘንድ እገዛ እንዲደረግልኝ ስትል አቤቱታ አሰማች።

መረጃ የደረሰዉ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ የተፈፀመዉን ወንጀል በሰዉና በሰነድ ማስረጃ አስደግፎ በማጣራት መዝገቡን ለዐቃቤ ህግ ይልካል።

ዐቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ በወንጀል ህግ አንቀጽ 627(1) በመጥቀስ በህፃናት ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል ክስ እና በወንጀል ህግ 654 በዘመዳሞች መሀከል የሚፈጸም የግብረ ስጋ ግንኙት ክስ መስርቶበታል፡፡

ዐቃቤ ህግ የመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ ክስ በቀረበበት ድንጋጌ ይከላከል በማለት ብይን የሰጠ ቢሆንም ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ነው ሲል ብይን ሰጥቷል።ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ተከሳሽ ሙሂዲን ወራቄን በ16 ዓመት ከ 6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

አልፎ አልፎ በልጆቻቸዉ ላይ እንዲህ ያለዉን የነዉረኝነት ተግባር የፈፅሙ አባቶች ስለ መኖራቸዉ የፖሊስ የመረጃ መዛግብቶች ያመላክታሉ።በፍቅርና በዕንክብካቤ ያሳደጓትን ህፃን ጨክኖ ለመድፈር አይደለም እቤት ዉስጥ ያሳደጉትን ጠቦት ለማረድ የሚራሩ የሀገሬ ሰዎች እልፍ አእላፍ ናቸዉ። በማለት የዘገበው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

21/07/2024

የዚህ ገፆ አለማው የተለያዩ ህጎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን በመልቀቅ ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ እና ህጋዊ ጥየቄዎችን በሚነሱበት ወቅት ውይይት በማድረግ የህዝብን የህግ ግንዛቤን ከፍ ማድረግ ነው።

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Justice 4 ALL posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share